YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ኢብራሒም ሲራጅ ከ 28 አመታት ቡኃላ ወደ ውዲቷ ሀገራቸው በሰላም ገብተዋል።

ፎቶ በአዛን አንቲ-አህባ
@YeneTube @FikerAssefa
አመታዊው የአምባሳደሮች ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

ስብሰባው ተቋማዊ ለውጥ ለላቀ ዲፕሎማሲ በሚል ርዕስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።በዓመቱ የተሰሩ አፈጻጸሞች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ ባላፈም በመሻሻል ላይ ባለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይም ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው።በስብሰባው ላይ በውጭ ሀገራት ኢትዮጵያን የወከሉ አምባሳደሮች እና የቆንስላ ጄነራሎች እየተሳተፉ ይገኛል።ስብሰባው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ይሆናል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በዋጋ ንረት ላይ ያተኮረ ውይይት ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር እየተካሄደ ነው።

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዋጋ ንረት ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር እየተወያየ ነው።ውይይቱ በዋናነት በአገልግሎት እና በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ በሚታየው የዋጋ ንረት ላይ ነው እየመከረ ያለው። በመድረኩ የዋጋ ንረትን እና ህገ ወጥነትን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት አግባብ ዙሪያም ምክክር እየተደረገ ነው።

-ፋና
 @YeneTube @FikerAssefa
በኬንያ ሄልስ ጌት ብሄራዊ ፓርክ በጉብኝት ላይ የነበሩ ሰዎች በደራሽ ጎርፍ ተወሰዱ።

በጎርፍ ከተወሰዱት ጎብኚዎች መካከል ሁለቱ ሕይወታቸው ሲያልፍ አምስት ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተነግሯል።

የሁለቱ ጎብኚዎች አስከሬን በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍለጋ የተገኘ ሲሆን፥ ሌሎች የጠፉ ጎብኚዎችን የማፈላለግ ስራ በሂሊኮፕተር የታገዘ ፍለጋ ተጠናክሮ ቀጥሏል
@Yenetube @FikerAssefa
በሀዋሳ ከተማ አተት ሊከሰት ይችላል የሚሉ ስጋቶች ስላሉ የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

እስከአሁን ባለው በሀዋሳ ከተማ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ ያልተከሰተ ቢሆንም ነገር ግን ስጋቶች ያሉ በመሆናቸው የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡የመምሪያው ኃላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንደገለጹት ከሀዋሳ ውጪ ቶጋ አካባቢ የአተት ምልክቶች ያሉ በመሆናቸው ጤና መምሪያው የጥንቃቄ ርምጃዎች እየወሰደ ነው ብለዋል፡፡በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ በተቋቋመ ማዕከል በበሽታው የተጠረጠሩ ህሙማን ክትትል እየተደረገላቸው ነው፡፡ከሁሉም የጤና ተቋማት ለተውጣጡ የጤና ሙያተኞች በሽታውን በተመለከተ ስልጠና በመስጠት ዝግጁ ተደርገዋል፡፡በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሀኒባል አበራ የበሽታው ዋነኛ የመከላከያ መንገድ የግልና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ ነው ብለዋል፡፡

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት የኦሮሞን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንመሰርታለን የሚሉ ቡድኖች መግለጫ ሰጥተዋል።

ይህ ቪዲዮ አነጋጋሪ ሆኗል ይመልከቱት
@YeneTube @FikerAssefa
በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የስፖርት ልኡካን ቡድን አቀባበል እየተደረገለት ነው፡፡

በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት ዓይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል፡፡
በአቀባበል ስነ-ስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን የተውጣጡ አካላት ተሳታፊ ናቸው፡፡የስፖርት ልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባበት ሰዓት ለአቀባበል ምቹ ስላልነበረ የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለዛሬ መተላለፉ ተገልጿል፡፡250 አባላትን የያዘው የስፖርት ልኡካን ቡድኑ በሞሮው መድረክ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 12 የነሃስ ሜዳሊያዎች በማስመዝብ ከአፍሪካ 9ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ሃገራት ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።በደቡብ ኮሪያ ቆይታቸው ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ በኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈርመዋል። በጃፓን ቆይታቸውም ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ተወያይተው፥ በሃገራቱ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።የደቡብ ኮሪያ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላም ወደ እስራኤል በማቅናት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል።በቆይታቸውም ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቨን ሬቭሊን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በዚህ ወቅትም ሃገራቱ በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሃገራት ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የኦሮሚያ ቴክኖክና ሙያ ትምህርት ስልጠናን የ2011 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም በመገምገም በ2012 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ በአደማ እየመከረ ነው፡፡በውይይት መድረኩ የዞንና የከተማ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ሀላፊ፣ የኮሌጆች ዲንና ባለድራሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡ መድረኩ ለ3 ቀናት እንደሚቆይ ከወጣው መርሀ ግብር መረዳት ተችሏል፡፡

Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንጀራና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ የኢትዮጵያ የባልትና ውጤቶች ከባዕድ ነገሮች ጋር እየተቀላቀሉ መሸጣቸው ይነገራል፡፡
ታዲያ ይህ ጉዳይ ሁሉንም ምርቶች በጅምላ በመጨፍለቁ እንጀራን ለውጪ ገበያ የማቅረብ ስራችንን ጎድቶብናል ገበያም አሳጥቶናል ሲሉ አምራቾች ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

via:- Shager FM
@YeneTube @FikerAssefa
80 በአደንዛዥ እፅ ዝውውር የተሳተፉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻሉ የኦፐሬሽኑ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስተአብ በየነ ለኢዜአ ተናግረዋል ። በዚሁም ዘመቻ 186 ኪግ ኮኬይን ፣ 9 ኪግ ሄሮይን፣ እንዲሁም 1.104 ቶን ካናቢስ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ተይዘዋል። እነዚህ ዕፆች በናይጄሪያ፣ ብራዚል፣ ቬንዙዌላ እና ደቡብ አፍሪካ ዜጎች ሊተላለፉ የነበሩ ናቸው ተብሏል። ከነዚህ መካከል 57 ወንድ ሲሆኑ 23 ሴቶች ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት በ2011 በጀት አመት ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ገቢው የተሰበሰበው በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ከተሸከርካሪ ታሪፍና ቅባት፣ ከመንገድ ጠቀሜታ ክፍያ፣ከግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ወለድና በክብደት ላይ የተመሰረተ ዓመታዊ የተሸከርካሪ ፍቃድ ማደሻ መሆኑን ጽ/ቤቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ የተሰበሰበው የገቢ መጠን 2.7 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡

በበጀት አመቱ 2.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉን ነው ያስታወቀው፡፡በአንጻሩ ለመንገድ ጥገናና ደህንነት እርምጃዎች 2.3 ቢሊዮን ብር ቢመድብም ክፍያ መፈጸም የተቻለው ግን 1.7 ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ክፍያው የሚፈጸመው ጥገና መካሄዱ በቴክኒካዊ ኦዲትና በአማካሪዎች ሲረጋገጥ እንዲሁም የክፍያ ሰርተፊኬት ሲቀርብና ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ነው ያለው መግለጫው የክፍያ ሰርተፊኬቶች እየተረጋገጡ አለመቅረባቸውን ለአፈጻጸም ጉድለቱ በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡

ፈንዱ ለታለመለት አላማ መዋሉን ለማረጋገጥም የቴክኒካልና ፋይናንሺያል ኦዲት ስራዎች መከናወናቸውን ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት በዋናነት ለመንገድ ጥገና የሚሆን ፈንድ ማሰባሰብን አላማ አድርጎ በ1989 ዓ/ም የተቋቋመ ሲሆን ፈንድ በማሰባሰብ ለመንገድ ኤጀንሲዎች የማከፋፈልና ፈንዱ ለታለመለት አላማ መዋሉን የማረጋገጥ ስልጣን በአዋጅ ተሰጥቶታል፡፡

Via :- Ethio FM
@YeneTube @FIkerAssefa
ቱርክ ለዓለም ገበያ ምታቀርባቸውን ምርቶች በተመረጡ 17 አገራት ላይ በአምስት ዘርፍ የምትልካቸውን ምርቶች እጥፍ ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋለች። ከተመረጡት አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካን እና ኬንያን ጨምሮ ሦስት አገራት መሆናቸው ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም አሰቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል::
@YeneTube @FIkerAssefa
በደብረ ብርሀን ከተማ 13 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ሊገነቡ ነው፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ 13 ዘመናዊ ሆቴሎች ሊገነቡ እንደሆነ ተገልጻል፡፡

ሆቴሎቹ የዞኑን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወንድማገኝ ተፈራ እንደተናገሩት ሰሜን ሸዋ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ያላት ቢሆንም መጠቀም አልቻለችም ብለዋል፡፡

ለዚህም ዋና ምክንያቱ በቦታው ዘመናዊ ሆቴል አለመኖሩ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

በመሆኑም ዞኑ በቱሪዝሙ ተጠቃሚ ለማድረግ ከባለ ሀብቶች ጋር በመመካከር በሚቀጥሉት አመታት ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎች ይገነባሉ ብለዋል፡፡

ባለሀብቶቹም ሙሉ የግንባታ ፍቃድ ወስደው ወደ ግንባታ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
Via;- Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa
የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) ሰላም ባለባቸው የወላይታ አካባቢዎች የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ ሲል ዛሬ መጠየቁ ተሰማ።

የወህዴግ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ኢዮኤል ለሸገር እንደተናገሩት በደቡብ ክልል ችግር ባለባቸው ቦታዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጣሉን እንደግፋለን ይሁንና ሰላማዊውነረ የወላይታ አካባቢ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማካተቱ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወላይታን የክልልነት ጥያቄ ጉዳይ ህገ መንግስቱ በሚያዘው መልኩ መቀበልና ማስተናገድ ይገባዋል ሲል ፓርቲው አቋም መያዙንም ከአቶ ፍቃዱ ሰምተናል፡፡

ወህዴግ የህዝብን ፍላጎት በመያዝ ነው የክልልነት ጥያቄን ያነሳው ያሉት አቶ ፍቃዱ ክልሉን የሚመራው ፓርቲ ለህዝቡ የክልልነት ጥያቄ ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥናት አስደርጋለሁ በሚሉና በሌሎች ምክንያቶች ጥያቄውን ወደኋላ ለማስቀረት መሞከር ተገቢ አይደለም ሲሉም አቶ ፍቃዱ ነግረውናል፡፡ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) በተለያዩ ነጥቦች ዙሪያም ዛሬ መግለጫ መስጠቱ ተነግሯል፡፡

ምንጭ:Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ቱሪዝምን የማነቃቃት አቅም እንዳለው የተነገረለት የጉዞ መርሃ ግብር በይፋ መጀመሩ ተነገረ፡፡

መርሃ ግብሩ “ወርቃማው ጉዞ” የሚል መሪ ቃል ይኖረዋልም ተብሏል፡፡በናብሊስ ኮሚዩኒኬሽንና በተጉለት ሚዲያና ፕሮሞሽን መሰናዳቱንም ሰምተናል፡፡አዘጋጆቹ ዛሬ በእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰማነው ኢትዮጵያውያን የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ በማድረግ በባህል፣ በመልእአ ምድር፣ በታሪክ፣ በተፈጥሮ ሀብትና በሰው ሰራሽ መስህቦች የተሳሰሩ እና ተመጋጋቢ እንዲሆኑ ማገዝ የጉዞው ዓላማ ነው፡፡

ህብረተሰቡ አንድነቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያሉት እሴቶች አንደኛው ከአንዱ ጋር የተሳሰረ መሆኑን ማስተዋወቅም የጉዞው ሌላው ተግባር እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ፕሮጀክቱ በ2012 12 የጉዞ መሰናዶዎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡በታሪክ፣ በቋንቋና ባህል እንዲሁም በቱሪዝሙ ስራ ላይ የተሰማሩ የታሪክ ተመራማሪዎችና የኢንዱስትሪው አካላት ታግዞ ይካሄዳልም ተብሏል፡፡የጉዞው መርሃ ግብር የመጀመሪው ወደ አንጎለላ እንደተካሄደ ሰምተናል፡፡

-ሸገር ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በዴንማርክ ኮፐንሀገን በሚደረገው የሲ-40 አለምአቀፉ ከንቲባዎች ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ ተጋበዙ፡፡

ኢ/ር ታከለ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካሪን ፖልሰን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡አምባሳደሯ የግብዣ ጥሪውን ለኢ/ር ታከለ ኡማ አቅርበዋል፡፡ ከጥቅምት 17 እስከ 20/2012 ዓ/ም የሚደረገው ጉባኤ ዋነኛ ትኩረቱ የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ ይሆናል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በጉባኤው ላይ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን በአዲስ አበባ እየተሰሩ ባሉ የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ትኩረት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡በተለይ የአዲስ አበባ ወንዞች የሚለሙበት ግዙፉ ሸገርን የማልማት ፕሮጀክት በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የሚጠቀስ ይሆናል፡፡በጉባኤው የተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ከተማ ከንቲባዎች ይገኛሉ፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በዴንማርክ ቆይታቸውም በክርስቲያንስበርግ ቤተመንግስት ከዴንማርክ የንጉሳውያን ቤተሰቦች ጋር ቆይታ የሚኖራቸው ይሆናል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
አሳዛኝ ዜና ❗️

ለሁለት አስርት ዓመታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ሀኪም እና ፊዚዮቴራፒስት የነበረው ዘላለም አዱኛ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ዘላለም ቀደም ብሎ ባጋጠመው የጤና መታወክና ሆዱ ውስጥ በተገኘ ዕጢ ምክንያት ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ከሁለት ወራት በኋላ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሶ የነበረ ቢሆንም ህመሙ አገርሽቶበት ለህልፈት እንደበቃው ታውቋል።

የኔቲዩብ ለዘላለም ቤተሰቦች፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችና ለስፖርት ቤተሰቡ ሁሉ መፅናናትን ትመኛለች!

መረጃውን ያገኘነው ከ ሀትሪክ ነው
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ‘አፈና እየተፈፀመ’ ነው፣ አመራሮቻችንና አባላቶቻችን ላይ የግድያ ሙከራን ጨምሮ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ነው ሲሉ ዓረና ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ (አረና) እና የትግራይ ዴሞክራስያዊ ትብብር (ትዴት) ፓርቲዎች ሃሙስ 23/2011 በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ፡፡ሕገ መንግሥት ይከበር በሚባልበት ወቅት ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ነው ያሉት የአረና ሊቀ መንበር አብርሃ ደስታ፣ ሕገ መንግሥቱ የሰጠንን የመንቀሳቀስ መብት ተነፍገን እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa