YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነሐሴ 24 ጀምሮ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ በቆይታዉ የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።በጉባኤው ምክር ቤቱ የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ማሳሰቢያ❗️

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፊታችን አርብና ቅዳሜ በአራት ከፍለ ከተሞች ውሃ እንደማይኖር አስታወቀ።

ባለስልጣኑ የራስ ኃይሉ ግፊት መስጫ እና ማጠራቀሚያ ጣቢያ አርብ ነሐሴ 24 እና ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ዓመታዊ የጥገና ሥራ አከናውናለሁ ብሏል፡፡

በዚህ ጥገና ሳቢያም

📌በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12፣ 13 እና 15፣

📌በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣ 3፣ 4 እና 5፣

📌በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ 6፣ 9 እና 10፣

📌ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እና 10፣

አካባቢዎች በከፊል የውሃ ስርጭት ስለሚቋረጥ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል፡፡

ምንጭ:Walta
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
🔶️Samsung _M30 (64 GB )
Camera: 13Mp + 8Mp+ 5Mp
4 GB Ram
5000 mAh Battery
📌 the Best Battery in the market
•Price: 9,499


Contact us
0953964175
0925927457
0956111111
@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከኢትዩጵያ ጋር የ86 ሚሊየን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የኮሪያው ወጪና ገቢ ለኢኮኖሚ ልማት ትብብር የሚውል የ86 ሚሊየን ዶላር ፈንድ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

ገንዘቡ በዩኒቨርስቲዎች ለሚታቀዱ ፕሬጀክቶችም የሚውል ስለመሆኑ የኮሪያው ሂራልድ ዘግቧል፡፡

የስምምነት ሰነዱን የባንኩ ዋና ስራ አስፈጸሚ ኡን ሰንግ ሱ እና የኢትዩጲያው የፋይናስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አድማሱ ነበበ ተፈራርመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኮሪያ ሲያርጉት የነበረውን ጎብኝት አጠናቀው ወደ ጃፓን ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡

የብድር ስምምነቱ በረጅም ጊዜ እና በአነስተተኛ ወለድ የሚታሰብ ይሆናል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ምሽት ኢሳት በዜና ፕሮግራሙ በወልዲያ ኬላ ንብረትነቱ የኦነግ እንደሆነ የተገመተ ወታደራዊ ዩኒፎርም ተያዘ ብሎ ዘግቦ ነበር። የዩኒፎርሙ ባለቤት እኛ ነን ብሎ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን ኮሚኒኬሽን ሀላፊ ነግሮኛል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የፓስፖርት አሰጣጥ እና ቅሬታዎቹን
በተመለከተ ከአቶ ደሳለኝ ተሬሳ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የተደረገ ቆይታ

Via Ethio FM

@YeneTube @FikerAssefa
ማሳሰቢያ‼️ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ የሚሰጠው ስልጠና ዕውቅና የለውም ተባለ።

ዩኒቨርስቲው ከየካቲት 2007 እስከ ጥር 2010 ድረስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን በመመዝገብ እንዲያስተምር ዕውቅና ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ከትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ውጪ አሁንም ድረስ እያስተማረ በመገኘቱ ከዕውቅና ውጪ መሆኑ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል።ከትምህርት ሚኒስቴር በወጣ መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ጳጉሜ 4/2007 ዩኒቨርስቲው እንዲያስተምር የተሰጠውን ዕውቅና እንደተሻረና የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች እንዲያስጨርስ ደብዳቤ ተፅፎለት ነበር። ይሁን አንጂ ዩኒቨርስቲው አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መገኘቱ በኤጀንሲው በተጨባጭ ታይቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ሰኔ 27/2011 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኹሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። ነገር ግን ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ መርሃግብር እያካሔደ እንደሚገኝ ታውቋል። ይህም ከኤጀንሲው ዕውቅና ያልተሰጠው ስለሆነ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅና ከሚኒስቴሩ ጋር በመመካከር አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድበትም ተገልጿል።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጃፓን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር በዛሬው እለት ተገናኝተው ተወያዩ።
@YeneTube @FikerAssefa
የተለመደው ሽልማት ዛሬ 3:00 ላይ አለ!!

የኔቲዩብን ያስተዋውቁ ካርዶች ያሸንፉ!!

ከአሁኑ ጋደኛዎን ይጋብዙ ወደ እናንተው ቻናል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል መንግስት በድሬዳዋ የተከሰተውን የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ለከተማ አስተዳደሩ የጤና ቢሮ ድጋፍ ሊያደረግ ነው። በወረርሽኙ የተነሳ እስካሁን አራት ግለሰቦች ህይወታቸው አልፏል።

Via ፋና ብሮድካስቲንግ
@YeneTube @FikerAssefa
መግለጫ‼️ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው የፌደራል ስርአቱን አይንድም ብሏል የትምህርት ሚኒስቴር።

አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው የፌደራል ስርአቱን የማይንድ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ተሰጥቷል፡፡አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት አለው በሚል ከህብረተሰቡ ሰፊ አስተያየት መሰጠቱን መግለጫው ተመልክቷል፡፡ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በሰጡት ማብራሪያ በሁሉም ት/ቤቶች ቢያንስ ለ1 አመት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሰጥ አስገዳጅ መሆኑ ፍኖተ ካርታውን ከዚህ ቀደሙ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አዲሱ ፍኖተ ካርታ የተሟላ የትምህርት ስርአትን ይከተላል ያሉት ሚንስትሩ እንደ ጆኦግራፊ እና ታሪክ ያሉ የትምህርት አይነቶች በአገር በቀል እውቀት እንዲቃኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ የሚፈቅድ ሲሆን የፌደራል የስራ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ በፍኖተ ካርታው ምክረ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ይህ በክልሎች ስልጣን የሚወሰን መሆኑን የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ገረመው ሁሉቃ ገልፀዋል፡፡ፍኖተ ካርታው 36 የተለያዩ ነጥቦች ያሉት ሲሆን ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል፡፡

ምንጭ:EBC
@YeneTube @FikerAssefa
@kiru04
+251 931607806
➡️የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ። 👇

@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy
@onlinesaleandbuy

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFBAc0Ri5bEWs7J4TQ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታወቀ።

ከተቋቋመ 20 አመታትን ያስቆጠረው የአዲስ ብደርና ቁጠባ ተቋም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለተጠቃሚዎች መማበደሩን ገልጿል።

የተቋሙ የገበያ ጥናትና ቢዝነስ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን ፊጡማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ለስራ አጥ እና መስራታ እየቻሉ ስራ አጥ ለሆኑ ከ 450 ሺ በላይ ዜጎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ ከተቋቋመ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ድረስ ከ250 ሺህ በላይ ቋሚ የብድር ደንበኞች እንዳሉትም አቶ መስፍን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ተቋሙ ከ180 ሺህ የቁጠባ ደንበኞቹ ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

ከ 2.8 ቢለዮን ብር በላይ ገንዘብ በደንበኞች እጅ እንዳለውም አቶ መስፍን ለጣቢያችን ነግረውናል፡፡

በ230 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል የተቋቋማው የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ጠቅላላ የካፒታል መጠኑ 870 ሚሊዩን ብር የደረሰ ሲሆን 3 ቢሊዮን የሚጠጋ ብር በደንበኞቹ እጅ ላይ እንደሚገኝም አቶ መስፍን ተናግረዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
የተለመደው ሽልማት ዛሬ 3:00 ላይ አለ!!

የኔቲዩብን ያስተዋውቁ ካርዶች ያሸንፉ!!

@YeneTube @FikerAssefa
ከሊቢያ አቅራቢያ በሜድትራኒያን ባሕር ላይ በሰጠመ ጀልባ በርካታ ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) አስታወቀ። የሊቢያ የባሕር ክልል ጠባቂ ኃይል በዛሬው ዕለት አምስት አስክሬኖች እና በሕይወት የተረፉ 65 ስደተኞች ማግኘቱን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የሱዳን መንግሥት ትናንት በሰሜናዊቷ ፖርት ሱዳን ከተማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡ አዋጁ የታወጀው በቤኒ አሚር እና ኑባ ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ፣ 16 ሰዎች ከሞቱ በኋላ መሆኑን የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡ በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው የወደብ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ነዳጅ ከሱዳን ገዝታ ታስገባባታለች፡፡ ደቡብ ሱዳንም ነዳጅ ምርቷን ለውጭ ገበያ የምታቀርብበው በዚችው ወደብ በኩል ነው፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመሩት የሲአን አንጃ እንደሚለዉ ባለፈዉ ኃምሌ 11 በተከሰተዉ ግጭት ሰበብ በርካታ ሰዎች ተይዘዉ ታስረዋል።

አንጃዉ እንደሚለዉ አፈሳና እስራቱ አሁንም በተለያዩ ወረዳዎች እንደቀጠለ ነዉ። #የሲዳማ_አርነት_ንቅናቄ (ሲአን) አንደኛዉ አንጃ የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች በጅምላ ታፍሰዉ እየታሰሩ ነዉ በማለት እርምጃዉን አቀወገዘ።አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመሩት የሲአን አንጃ እንደሚለዉ ባለፈዉ ኃምሌ 11 በተከሰተዉ ግጭት ሰበብ በርካታ ሰዎች ተይዘዉ ታስረዋል።አንጃዉ እንደሚለዉ አፈሳና እስራቱ አሁንም በተለያዩ ወረዳዎች እንደቀጠለ ነዉ።አንጃዉ በጅምላ ታሰሩ ያላቸዉን ሰዎች ቁጥር፣ የታሰሩበትን ትክክለኛ ቀንና ሥፍራና ግን አልገለፀም።ዶይቼ ወሌ ሥለዉግዘቱ፣ የሲዳማ ዞንና የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካለትም።

ምንጭ: ዶይቸ ወሌ
@YeneTube @FikerAssefa
ተጀመረ!!

የኔቲዩብን ያስተዋውቁ ካርዶች ያሸንፉ!!

ጫወታው እንዲህ ነው
ይህንን ፓስት ለ10 ጓደኛዎ ሼር በማድረግ ካርዶችን ያሸንፉ ። ሼር እንዳደረጉ Screenshot አድርጎ ወደዚህ አካውንት መላክ ነው።

@Eyuel73
@Eyuel73

👆ላይ ይላኩልን👆
__________________________
ቻናላችንን ያልተቀላቀላችሁ አሁን ተቀላቀሉ ሊንኩን ይንኩ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@yenetube @yenetube
@yenetube @yenetube
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
__________________________