ከጠ/ሚንስትሩ የደቡብ ኮርያ ጉብኝት ዜና ሳንወጣ፤
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው የኮርያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋምን ጎብኝተው የኮርያን ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተጫወተው ሚና ዙሪያ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል:: ምንም እንኳን ተቋሙ በአሁን ወቅት ያለው የሥራ ግንኙነት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትና ከአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር ቢሆንም ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ይህንኑ መሳይ ተቋም በኢትዮጵያ ለማቋቋም በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል::
@YeneTube @FikerAssefa

የአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ሥራቸውን ለመጀመር ዝግጅቶቻቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።
መንግሥት በወሰነው መሰረት በተመረጡ ሁለት ትምህርት ቤቶች ለሚጀመረው አዳሪ ትምህርት ተማሪዎችን ለመቀበልና ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገለፀ።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን፣ የትምህርት አመራር ባለሙያዎች ልማት ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ሻንቆ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፣ ለአዳሪ ትምህርት ቤትነት ከተመረጡት ነባር ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነውን የካቲት 12 መሰናዶ ትምህርት ቤት (የቀድሞው “መነን”) እና በሰበታ የሚገኘውን አዳሪ ትምህርት ቤት አደረጃጀት የማስተካከልና ለሚፈለገው ተግባር ምቹ የማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁት እነዚህ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በመንግሥት፤ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸው በመሰራት ላይ ሲሆኑ፤ ሥራውም በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ምንጭ:EPA

“አፋልጉኝ"
ተማሪ ፅዮን አበበ ነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 3 ሰአት አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዮን አበበ መጨረሻ የታየችው አዲስ አበባ ቀበና መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን የለበሰችው ልብስ ሰማያዊ ሱሪ እና ከላይ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነበር። በእለቱ እናቷ ስለሞተችባት በመሪር ሃዘን እራሷን ማረጋጋት ስላቃታት እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዩን ምንም አይነት የአዕምሮ ችግር የሌለባት ሲሆን ያለችበትን የሚያውቅ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወሮታውን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን።
ቤተሰቦቿ
09 11 81 5050
09 20 85 6595

ሱዳን ውስጥ ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ 62 ሰዎች ሲሞቱ በ15 ግዛቶች ከ200 ሺህ ያላነሱ ሰዎች መጎዳታቸው ተነግሯል።
በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የምትገኘው የዋይት ናይል ግዛት አስከፊ ጉዳት አስተናግዳለች።የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው በጎርፍ አደጋው ከ37 ሺህ በላይ ቤቶች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።አዳዲስ የጎርፍ አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ የተነገረ ሲሆን፥ የዝናባማ ወቅቱ እስከ መጪው ጥቅምት ወር ድረስ እንደሚቀጥልም መነገሩን ቢቢሲ/OBN ዘግቧል፡፡

ኢሠማኮ ከስደት ለተመለሱት የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ዕውቅና ሰጠ።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በኮንፌዴሬሽኑ ምሥረታና ሠራተኞችን ለመብታቸው በማታገል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ለሚነገርላቸው የቀድሞ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት ዕውቅና ሰጠ፡፡በተለያዩ ተፅዕኖዎች ከአገር እንዲሰደዱና ኑሯቸውን በውጭ አድርገው የቆዩት አቶ ዳዊ ኢብራሂም፣ በኢትዮጵያ የሠራተኞች ትግል ታሪክ ውስጥ የነበራቸውን አስተዋጽኦ በመዘከር ዕውቅናው እንዲቸራቸው የተደረገው፣ ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ስለሳቸው በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
ኢሠማኮ ከመንግሥት ተፅዕኖ ውጪ ሆኖ በነፃነት እንዲመሠረትና እንዲንቀሳቀስ ከንጥስሱ ጀምረው በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት አቶ ዳዊ፣ ከሃያ ዓመታት በላይ በስደት ቆይተው በቅርቡ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል፡፡ ኢሠማኮም የአቶ ዳዊን አስተዋጽኦ በመዘከር ዕውቅና እንደሰጣቸው ከኮንፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ይገልጻል፡፡አቶ ዳዊ ለማስታወሻነት የአንገት ሀብል ከኢሠማኮ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከዕውቅናና ማበረታቻ በተጨማሪ ከኢሠማኮ ጋር መሥራት የሚችሉበት ዕድል ተሰጧቸዋል፡፡ አቶ ዳዊ ስለተሰጣቸው ዕውቅናና ማስታወሻም ኢሠማኮን አመሥግነዋል፡፡ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎም፣ አቶ ዳዊ ስለሠራተኛው መብት መከበር የነበራቸውን አበርክቶ አውስተዋል፡፡
Via Reporter

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያዩ:: ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ ሲደረጉ በነበሩና በአዳዲስ ድጋፎች ዙሪያ መክረዋል:: በአሁኑ ወቅት በኤግዚም ባንክ ድጋፍ ከ600 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 300 ሚሊዮን ዶላሩ በ2011-2012 በኮርያ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ ማእቀፍ ስር የተፈረመ ነው::
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ባሳለፍነው 2011 በጀት ዓመት በተደረገ የስፖርታዊ አደን 26 አዳኝ ቱሪስቶችን እና አብሮ ተገዦችን በማስተናገድ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።የውጭ ቱሪስቶች ለስፖርታዊ አደን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የማስተዋወቅ ስራዎች በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች አሃጉሮች መከናወኑንም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ኝኙነት ባለሙያ ናቃቸው ብርሌው ገልጸዋል።
Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ እንዳሉ ከሚገመቱ ስልሣ ሚሊየን ዶሮዎች የተሻሻሉ የውጭ ዝርያዎች ድርሻ ከአምስት በመቶ እንደማይበልጥ ተነገረ፡፡በዚህም ምክንያት ከዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ጥቅም ማግኘት አልተቻለም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻውን በየቀኑ ሁለት ሺህ ኪሎ ግራም የዶሮ ስጋ ከውጪ እንደሚያስገባም ሰምቻለው ብሏል ሸገር ራዲዮ በዘገባው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት‼️
በ2020ው የቶክዮ ኦሎምፒክ ማጣርያ 2ኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲዎቹ ዛሬ 10፡00 ከካሜሮን አቻቸው ጋር በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ይጫወታሉ፡፡ጨዋታውን ኬኒያዊያን ዳኞች ሲዳኙት ኮሚሽነሩ ደግሞ ከሱዳን እንደመጡ ተሰምቷል፡የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ሕዝብ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስታዲዬም ተገኝቶ ጨዋታውን እንዲመለከት እና ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያበረታታ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Via SRTA

ከ2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።
በኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች ከተፈናቀሉ ዜጎች ከ2 ሚሊዮን በላዩ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በግጭትና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ከተፈናቀሉ 2.3 ሚሊዮን ዜጎች 2.1 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
በግጭትና በፀጥታ ስጋት ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ የነበሩ ዜጎች በተሰራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ ወደነበሩበት ህይወት ተመልሰዋልም ብለዋል ኃላፊው፡፡
ዜጎችን ለመመለስም በየአካባቢው ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቀናነትና ቀደም ሲል የነበረው መተሳሰብና ማህበራዊ መስተጋብር ወሳኝነት ነበረው ተብሏል።
"ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በኋላ ከ6 - እስከ 8 ወራት ይረዳሉ፤ በእርዳታው ጥገኛ ሆነው መቆየት ስለሌለባቸውም ቶሎ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት ሊጠቀሙ የሚችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው" ብለዋል አቶ ደበበ፡፡
ተፈናቃዮችን የመልሶ ማገገምና የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ኃላፊው የዜጎችን የመቋቋም ሁኔታ በደንብ ጤናማ በማድረግ ዘላቂ የሆነ ህይወታቸውን እየመሩ መሆኑ ሲረጋገጥ ከክልሎች ጋር በመነጋገር እርዳታው ይቆማል ብለዋል፡፡
Via:- AMMA

እስካሁን ድረስ በጎርፍ አደጋ ከ23 ሺሕ በላይ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ 1,336,355 ወገኖች ከዚህ በኋላ በጎርፍ ሊጠቁ እንደሚችሉ፣ ከእነዚህም ውስጥ 335,814 ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደመና ዳሮታ ገልጸዋል፡፡
-Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
-Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይዛ የመጣችውን አዲስ ሃሳብ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡
ግበፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችን ይዛ ብቅ ማለቷን ተከትሎ፣ የኢትዮጲያ መንግስት ቀደም ሲል ከተቀመጠዉ መርህና አሰራር ውጪ በግብፅ የሚነሱ ሃሳቦች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል፡፡ግብፅ ከ ሰሞኑ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት በሰባት አመታት ውስጥ ይሁንልኝ ብላለች፡፡የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ኢትዮጲያ ያላት አቋም በ2012 የዉሃ ሙሌቱ ይጠናቀቃል የሚል ነዉ፡፡
ከምንከተለዉ መመሪያና የተፋሰስ ሃገራቱ ካስቀመጧቸው የመደራደሪያ ነጥቦች ውጪ በግብጽ የሚነዳዉ ሃሳብ ተቀባይነት እንደሌለዉም አስታውቀዋል፡፡ ሱዳንን ጨምሮ ሶስቱ ሃገራት በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያካሂዱትን የሶስትዮሽ ድርድር በሱዳን የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት መስተጓጎሉን ጠቅሰዉ፣ በቀጣይም ድርድሩ የሶስቱንም ሃገራት የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ከዚህ ውጪ ከሱዳንም ሆነ ከግብፅ የሚነሱ ምክንያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ መግለጫዎች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደማይኖራቸዉ አቶ ነብያት ተናግረዋል፡፡
Via Ethio FM

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግል ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ ማዘጋጀቱን ገልጿል። የከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ምክር ቤት ሁለተኛው ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩም በጉባኤው ላይ ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግለውን እና ያዘጋጀውን ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ አስተዋውቋል።
በቀረበው ረቂቅ እቅድ ላይም በጉባኤው ባለድርሻ አካላት እየመከሩበት ይገኛል። እቅዱ የከፍተኛ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተቶች ለማስተካከል የሚያግዝ ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈም አዳዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋት እንደሚያግዝም ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
ረቂቅ እቅዱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በቅንጅት መስራት ላይ ያሉባቸውን ችግሮች በምን መልኩ መፍታት ይገባል የሚለውን ተመልክቷልም ነው የተባለው፡፡ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ዙሪያ የሚታየውን የጥራትና ፍትሃዊነት ጥያቄዎችን ለማሻሻል እንደሚረዳም ታምኖበታል።
Via FBC

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሳምሰንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ እንዲሰማራ ጠየቁ።
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በደቡብ ኮሪያ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአገሪቱ ፕሬዘዳንት ሙንጃኒን ጋር በአራት ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት በአካባቢ ጥበቃ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጅ፣ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም እና በቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳምሰንግ ምክትል ፕሬዚዳንት ዎን ኪዮንግ ጋርም ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱም ኩባንያቸው ኢትዮጵያን አንደኛው መዳረሻው ባደረገ መልኩ ለመስራት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ወደ ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያን ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ ደቡብ ኮሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ ቪዛ ሳይጠየቁ መግባት እንዲችሉ አገራቱ ተስማምተዋል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲን የአቅም ግንባታ ስራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ፈጽመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአስካሁኑ የደቡብ ኮሪያ ቆይታቸውም በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር የተወያዩ ሲሆን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ለተሰው መታሰቢያ በሆነው መቃብር ስፍራ ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
Via:- #የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ነው

የሊድ ባትሪን በጥንቃቄ አስወግዱ ተባለ!!
በኢትዮጵያ ከአደገኛ ቆሻሻዎች መካከል የሚመደበው፣ በተሽከርካሪ ባትሪ ውስጥ የሚገኘውና ባለ-ሊድ አሲዳማ ባትሪ አወጋገድ ጥንቃቄ የተሞላበት ካልሆነ ከፍተኛ ችግር ያመጣል ሲል ያስጠነቀቀው የኢትዮጵያ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ነው። በሁሉም ተሽከርካሪዎችና በፀሃይ ሃይል በሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ጥቅም ላይ የዋለውን የሊድ-አሲድ ባትሪ በማሰባሰብ እንደገና መጠቀም የሚቻልበትን መንገድ ለመዘየድ ወይም ለማስወገድ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ደካማ መሆኑን ነው የኢትዮጵያ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የገለፀው።
-Addis Maleda

በአዲስ አበባ የፍጥነት ገደብ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጅ (ራዳር) በመተግበሩ ከፍተኛ ፍጥነትን በ10 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ።
https://telegra.ph/Speed-limit-08-26
https://telegra.ph/Speed-limit-08-26
ሱዳን በቀይ ባህር ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ደነገገች
በሱዳን ቀይ ባህር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉት ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መደንገጓ ተገለጸ፡፡በቀይ ባህር ግዛት በበኒ አመር እና በኑባ ጎሳዎች መካከል ለቀናት የዘለቀው ግጭት ሀገሪቱን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እንድትደነግግ አስገድዷታል፡፡
በዚህም አዲሱ የሱዳን መንግስት የምሥራቃዊውን ግዛት አስተዳዳሪ እና የክልሉን የፀጥታ ኃላፊ ከስልጣናቸው አንስቷል፡፡በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት መንስኤው ምን እንደሆነ ባይገለፅም ለግጭቱ መባባስ ግን የተለያዩ የውስጥና የውጭ አካላት እጅ እንዳለበት መንግስት ጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

በባሌ ዞን 340 ኩንታል ስኳር ተያዘ
በባሌ ዞን መዳ ወላቡ ወረዳ በሕገ ወጥ መልኩ ሲንቀሳቀስ የነበረ 340 ኩንታል ስኳር መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ስኳሩ በኅብረተሰቡ ጥቆማና በጸጥታ ኃይሎች ክትትል የተያዘው ከወረዳው ወደ ጉጂ ዞን ሲጓጓዝ መሆኑን በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ዲቪዥን ባለሙያ ኮማንደር ናስር ኡመር ገልጸዋል።
ኮድ 3 የሠሌዳ ቁጥር 79665 አዲስ አበባና ኮድ 3 የሠሌዳ ቁጥር 24685 ኢትዮጵያ በሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ስኳሩን ሲያጓጉዙ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ተናግረዋል።
አሽከርካሪዎቹ ለጊዜው መሰወራቸውንና የተያዘው ከ800ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ስኳር ለመንግሥት ገቢ መሆኑን ባለሙያው አመልክተዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሕገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት እንዲያጠናክር መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡