YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ አመት የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሠባ በኢትዮጵያ ምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻል እየመረመረ ነው።

የምክር ቤቱ የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን አቅርቧል።የአዋጁ ሥያሜም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ በሚል ተስተካክሏል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ማስጠንቀቂያ‼️

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተማሪዎችና ወላጆች በአንዳንድ የግል ኮሌጆች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
1
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 73ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ ችግሮቻችን ፈቺ አጥተው በተቆለሉበት ወቅት "አዲስ የትምህርት ፖሊሲ" (መጥፎም ይሁን ቆንጆ) ማዘጋጀት የፖለቲካ ስህተት ነው ሲል አብርሃ ደስታ ሀሳቡን በቲውተር ገፁ አስፍሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ተቀማጭ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬዋ እየተሻሻለ ነው ተባለ፡፡ ሐገሪቱ በተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ ጉዳይ የሚያሳስባት ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ነግረዋል፡፡የኢትዮጵያ ተቀማጭ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ለአንድ ወር ከ15 ቀን ብቻ የሚበቃ ነው፤ ይህም ለመድሃኒትና ለነዳጅ ካልሆነ በስተቀር ለሌሎች ግዢዎች ለማዋል እንደማይቻል በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡በዚህም የተነሳ የጥቁር ገበያው ከመደበኛው የባንክ ምንዛሬ ከፍተኛ ልዩነት ሲያሳይ ቆይቷል፡፡አሁን የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ እየተሻሻለ መምጣቱን የብሔራዊ ባንኩ ዋና ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

Via ሸገር ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅን አጽድቋል። የህግ ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ 47 አንቀፆች መሻሻላቸውን ገልጿል። ምንጮቼ ዛሬ ቀርቦ የፀደቀውን የውሳኔ ሃሳብ አጋርተውኛል ብሏል Finfinne Intercept። ከዚህ በላይ ተያይዟል።⬆️

@YeneTube @FikerAssefa
ዜና ዕረፍት!!

የቀድሞ ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ዳኛ አቶ ተስፋዬ ገ/እየሱስ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡አቶ ተስፋዬ ገ/እየሱስ በእግር ኳስ በዳኝነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡የአቶ ተስፋዬ ገ/እየሱስ የቀብር ስነስርዓት በነገው ዕለት በአስመራ ከተማ የሚፈፀም መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!!

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመማጣሪያ የመልስ ጨዋታ
የመጀመሪያ 45 ተጠናቌል!

HT፡- Azam FC 2-1 Fasil Kenema

ለአዛም ሁለቱንም ጎሎች ያስቆጠረው Djodi ደስታዉን ሲገልፅ፡ለፋሲል ከነማ ሙጂብ ቃሲም ጎሏን አስቆጥሯል

Via Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
የ56 ዓመቱ የቱኒዚያ ዕጩ የፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ ናቢል ካሮይ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ክስ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

-Fana
@YeneTube @FikerAssefa
⚽️ጨዋታው 3 ለ1 ተጠናቀቀ
አዛም ፋሲል ከነማን 3 ለ1 አሸንፏል።⚽️

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የታንዛንያው አዛምን ከሜዳው ውጭ የገጠመው የኢትዮጵያው ፋሲል ከነማ 3 ለ1 ተሸንፏል።በድምር ውጤትም 3-2 በመሸነፉ ፋሲል ከነማ ወደ ተከታዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት የታንዛንያ አየር መንገድ በሊዝ የተከራየውን ኤርባስ አውሮፕላን መያዛቸውን የታንዛንያ መንግስት አስታወቀ። አውሮፕላኑ ከደቡብ አፍሪካዊቷ ጆሃንስበርግ ከተማ ወደ ታንዛንያ መዲና ዳሬሰላም ትላንት አርብ በረራ ነበረው።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ አባላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሄደ!!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማሻሻያ የማድረግና አዳዲስ ሕጎችን የማርቀቅ ስራ ላይ ጥናት በማድረግና ምክረ ሀሳብ በማቅረብ በርካታ ሕጎች ነባር እንዲሻሻሉና አዳዲስ ረቂቆችም እንዲዘጋጁ አድርጓል፡፡ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመው ይህ አማካሪ ጉባኤ ለሰራቸው ስራዎች በጠቅላይ አቃቤ ሕግ አማካይነት የእውቅና ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በዚህ የእውቅና መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ አባላቱ ያለምንም ክፍያ ለአገራቸው ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮርያ ገቡ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሴዑል ሲደርሱ በሀገሪቱ ከፍተኛባለስልጣናት እና በኮርያ የሚኖሩ የኢትዮዽያ ኮሚኒቲ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከደቡብ ኮርያው ፕሬዘዳንት ሙንጃይኢን ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዬች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል::

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የልጃገረዶች ጨዋታ ዛሬ በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ ይከበራል።አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒዬም አዳራሽ ነው የሚከበረው። በዓሉ በዋግ ኽምራ፣ በላልይበላ እና በቆቦ ከነሐሴ 16/2011 ጀምሮ እየተከበረ ነው። አከባበሩ እስከ ነሐሴ 21 ድረስ እንደሚቆይም ይታወቃል።ዛሬ ደግሞ በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ ይከበራል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዩኤስ ኤድ ፍትህ (Justice) አክቲቪቲስ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ወጥና ከዳኝነት መርሆዎች ጋር የተጣጣመ የፌዴራል ዳኞች የስራ አፈጻጸም መመዘኛ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ነሓሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ለተጨማሪ ግብአት ለውይይተ አቅቧል፡፡በረቂቅ የፌዴራል ዳኞች የስራ አፈጻጸም መመዘኛ መመሪያ ላይ ተጨማሪ ግብአት ለማሰባሰብ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕዝደንቶች፤ ምክትል ፕዝደንቶች፤ የምድብ ችሎት አስተባባሪዎችና ከሶስቱም ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች ተሳትፈውበታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የዪንቨርስቲ ተመራቂዎች ለመንግስት የሚከፍሉት የወጪ መጋራት ብር መጠን በእጥፍ ሊያድግ ነው።

Via:- ካፒታል ጋዜጣ
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ውስጥ በጎዳና ተዳዳሪ ከተሰማሩ ሰዎች 92% ከክልል የመጡ ሲሆን ከዚህምአብላጫውን የሚይዙት ደቡብ፣ኦሮሚያ፣አማራ ክልል መሆናቸው ጥናት አመለከተ።

Via:- ካፒታል ጋዜጣ
@YeneTube @FikerAssefa
300 ሚልዮን ብር ከተለያዩ ባንኮች ተሰረቀ

ከንግድ ባንክ፣ከዳሽን፣ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል የደንበኞች የባንክ አካውንት 300 ሚልየን ብር በላይ በተጭበረበረ ቼክ ተሰረቀ።23 ተጠርጣሪዎችን ፓሊስ አስሯል። አቀነባባሪው ከሀገር ወጥቷል።

Via:- ካፒታል ጋዜጣ
@YeneTube @Fikerassefa
የአሸንዳ በዓል በክልል ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ ነው በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ የሚገኘው።

@YeneTube @FikerAssefa
ሞሮኮ ራባት በመካሄድ ላይ በሚገኘው የመላው አፍሪቃ ጨዋታ በሴቶች የቡድን ታይም ትሪያል ኢትዮጵያ የነሀስ መዳሊያ ስታገኝ ደ/አፍሪካ እና ኤርትራ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝተዋል።

Via Ariyat Raya
@YeneTube @FikerAssefa