YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የ4 ቢሊየን የችግን መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል – ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ

የ4 ቢሊየን የችግኝ መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ መሳካቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ መርሃ ግብሩ አስተባባሪ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የችግኝ ተከላ ማሳረጊያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡

በዚህ ወቅት የ4 ቢሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተተከሉ የችግኝ አይነቶች እና ብዛት የማጣራት ስራ እንደሚካሄድ ነው የተነገረው፡፡

በክረምቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ 60 በመቶ የሚሆኑት ለጥምር ግብርና የሚያገለግሉ ሲሆን 40 በመቶዎቹ ደግሞ ለደን የሚሆኑ ችግኞች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይነትም ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በተቀናጀ ሁኔታ እንደሚከናወን ነው የተገለፀው፡፡
Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያን ሳተላይት ለመገንባት የኅዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩትና ቤጂንግ ስማርት ሳተላይት ቴክኖሎጂ የተባለ ኩባንያ ስምምነት ፈርመዋል። የኢንስቲቲዩቱ ምክትል ኃላፊ አብዲሳ ይልማ፤ አምባሳደር ተሾመ ቶጋና የቻይና ሹማምንት ተገኝተዋል።


ሙሉ ግንባታው ምን ያክል ገንዘብ እንደሚፈጅ አልተገለጸም። በETHSAT6U ሳተላይት ግንባታ ቻይና ዕገዛ ታደርጋለች ተብሏል፤ በቻይና ተገጣጥማና ተሞክራ ከዚያው ወደ ምድር ምሕዋር ትላካለች፤ ሳተላይቷ ለቻይናና የአፍሪካ አገሮች ትሰራለች ተብሏል

Via:- እሸት በቀለ
@YeneTube @FikerAssefa
ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በአስቸኳይ ስብሰባ ከ50 በላይ ፓርቲዎች የተቃወሙትን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ኢሕአዴግ ፅፏል። መኢአድና ኢሕአፓን ጨምሮ 57 ፓርቲዎች ዛሬ ረቂቅ አዋጁ ሊጸድቅ አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል።

Via:- እሸት በቀለ
@YeneTube @FikerAssefa
ፌስቡክ❗️

በርካታ በማይናማር የሚገኙ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ።

ፌስቡክ በትክክለኛ ማንነት አልተከፈቱም ያላቸውን 216 የሚሆኑ በማይናማር የሚገኙ የፌስቡክ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ፡፡

89 የሚሆኑ የግል አካውቶች፣ 107 ገፆች፣ 15 የፌስቡክ ቡድኖችና 5 የኢንስታግራም አካውንቶችን መዝጋቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው፡፡

የተዘጉት አንዳንድ የፌስቡክ ገጾች ከወታደራዊ አካላት ጋር የተያያዙና ህዝባዊ ውይይትን የሚያዛቡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ከጥላቻ ንግግር በተለይም ሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ የማይናማር ወታደራዊ ሓላፊ አካውንትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አካውንቶችን መዘጋታቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 1 ሚሊየን ደብተር ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ነው፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ፓትሪያርኩ የከተማ አስተዳደሩ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት ቤተ ክርስቲያኗ እንደምታደንቅ እና በቀጣይነትም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረገችው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ የውጭ ሃይሎችን እታገላለሁ እከላከለዋለሁ- ብሏል ኦብነግ፡፡ ሸገር የኦብነግ ሊቀመናብርት ትናንት የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ከሱማሊያ እየተነሳ ኢትዮጵያ ላይ ሽብር ጥቃት መፈጸም የሚያስበው ጽንፈኛው እስላማዊ መንግሥት (አይኤስ) በሱማሌ ክልል በኩል ሰርጎ እንዳይገባ ኦብነግ ጠንክሮ ይመክታል፤ ከክልሉ እና ፌደራል መንግሥትም ጋር በቅርበት ተባብሮ ይሠራል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የችኩንጉኒያ ወረርሽ በድሬዳዋ

ከሁለት ሳምንት በፊት ነዋሪዎችን መልከፍ እንደጀመረ የሚታመነዉ ወባ መሠል በሽታ በአጭር ጊዜ፣ በመላዉ ከተማይቱ ተሰራጭቷል። የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ እንደታዘበዉ ችኩንጉኒያ ድሬዳዋ ዉስጥ ያላንኳኳዉ ቤት፣ ያላተኮሰዉ ሰዉ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ። የከተማይቱ ጤና ቢሮ እንደሚለዉ እስከትናንት ድረስ በትንሽ ግምት ከ7ሺሕ በላይ ሰዉ በበሽታዉ ተለክፏል። የሞተ ስለሞኖር አለመኖሩ ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
የFana Broadcasting Corporate የዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ በቀለ ሙለታን ዋና ሃላፊ አድርጎ ሾሟል። አቶ በቀለ ለረጅም ጊዜ በቦታው የነበሩትን አቶ ወንዱ ይምሰልን በመተካት ነው ወደ ሃላፊነት የወጡት።

Via Fortune
@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የደም አለመርጋትና የመድማት ችግር (የሂሞፊሊያ) ሕሙማን የሕህምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮግራሙ እየተላለፈ ነው!!

በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በውስጥ ጽዳት ምንነት አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት ይከታተሉ::

@YeneTube @FikerAssefa
የፊዮዶር ዶስቶቭስኪን Crime & Punishment ወንጀልና ቅጣት በሚል ርዕስ በትብብር የተረጎሙት አምባሳደር ካሳ ገብረ ሕይወት (ዶ/ር) በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ለ10 አመታት በሩሲያ አምባሳደር ነበሩ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ማዕከል የሆነችውን የወሎን አማራነት ዘንግተው የራሳቸውን ማንነት ለመጫን ለሚፈልጉ ህልመኞችና ወፍ ዘራሽ ፈላስፎች ጆሮ ሳንሰጥ የአማራንም የኢትዮጵያንም አንድነት አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳሰቡ።

@yenetube @fikerassefa
Audio
በድሬዳዋ የመሬት ወረራ አሁንም በቁጥጥር ሥር ሊውል አልቻለም ተባለ።

በድሬዳዋ “የመሬት ወረራ አሁንም በቁጥጥር ሥር ሊውል አልቻለም” ሲል የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮው አስታወቀ።የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያም “የህገወጥ የመሬት ወረራ ሰለባ ከሆኑት መካከል ነው” ተብሏል።

ምንጭ:VOA
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
መተማ ተይዘው የነበሩት መኪኖች ህጋዊ ናቸው ተባለ!

የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ሰላምና ደህነንት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፤ ጭነቶቹን ከፀጥታ አካላትና ከሕዝብ ከተወከሉ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ሕጋዊና የአገራችን መንግሥት ንብረቶች መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄዳል ። ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Just A Remainder:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘመናዊ የሲስተም ማሻሻያ ለማድረግ ዛሬ ቅዳሜ ነሃሴ 18 ቀን 2011 አገልግሎት አይሰጥም፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ውስጥ በመጪዎቹ ስድስት ዓመታት የግንባታ ዕቃዎች በ6 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ ያሳያሉ ተባለ።

@YeneTube @FikerAssefa
ከአምደ ወርቅ ተከዜ የተገነባው የ48 ኪ/ሜ መንገድ በርእሰመስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተመርቀ።

መንገዱ ከ2006 ጀምሮ በ 146 ሚሊየንብር የተሠራ ሲሆን በአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የጎላ ሚና እንደሚኖረው በአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ የተመረቀው መንገድ ታምኖበታል።
መንገዱ ዋግኽምራ እና የደጎንደርን ዞኖች የሚያስተሳስር ነው።የዋግ አካባቢ የእንስሳት እና የማር ምርትን፣ ከደቡብ ጎንደር ደግሞ የሠብል ምርትን በማገበያየት ህብረተሰቡን በንግድ የሚያስተሳስር ነው።መንገዱ ከእብናት አምደወርቅ ከተያዘው የመንገድ ፕሮጀክት 90ኪሜ አካል ሲሆን በአጠቃላይ ግንባታው የፈጀው ገንዘብ መጠን 276 ሚሊየን ብር ነው። ግንባታው አራት አመታትን የፈጀው ከእብናት ተከዜ የተገነባው መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆኖ የቆየ ነው።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ከ50 ሀገራት ተበድራለች!

የብድር መጠኑ ከአጠቃላይ የሀገሪቷ ሀብት ውስጥ 49 በመቶ ደርሷል:: ኢትዮጵያ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ባሻገር ከ50 አገራት ብድር መውሰዷን እና መንግሥትም 830 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።በ2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ ካለባት ብድር መካከል መንግሥት 22 ቢሊዮን ብር የከፈለ ሲሆን፤ በ2012 ዓ.ም ደግሞ 25 ቢሊዮን ብር ብድር ለመክፈል አቅዷል። የገንዘብ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክ ተር አቶ ሃጂ ኢብሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያም ከፋይናንስ ተቋ ማት በተጨማሪ ከተለያዩ 50 ሀገራትም ብድር አለባት። ከአጠቃላዩ የመንግሥት ብድር 80 በመቶው በረጅም ጊዜ የሚከፈል እና አነስተኛ ወለድ የያዘ ነው።

በ2011 ዓ.ም አነስተኛ ወለድ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ያለው ብድር መንግሥት መውሰዱን የገለጹት አቶ ሃጂ፤ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለረጅም ዓመታት ከማዕከላዊ ባንክ እና ከውጭ አገራት የወሰደው ብድር 830 ቢሊዮን 641 ሚሊዮን ብር መድረሱን አስረድተዋል። የተለያዩ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በበኩ ላቸው 729 ቢሊዮን 907 ሚሊዮን ብር ብድር እንዳለባቸው ተናግረዋል።
እንደ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ከሆነ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የብድር መጠኑን ከአጠቃላይ የአገሪቷ ሀብት ውስጥ 49 በመቶ እንደሚደርስ እና በዓለም አቀፍ ምዘና እንደ ኢትዮጵያ ላለ ሀገር እስከ 55 በመቶ የሚደርስ ብድር ሊፈቀድ ይችላል። ኢትዮጵያም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ባትገኝም የብድር ጫናዋን ለመቀነስ የሚያስችል አካሄድ ላይ ትገኛለች።በዚህም መሰረት በ2010 እና 2011 ዓ.ም ብቻ 39 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለብድር ተከፍሏል።

Via Addis Zemen
@YeneTube @FikerAssefa
በተሽከርካሪዎች ላይ የሚለጠፈው የ3ተኛ ወገን መድህን ዋስትና ማረጋገጫ ሊቀየር ነው።

በሚ.ዴ ማዕረግ የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ እንደገለፁት፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ያለው የሶስተኛ ወገን መድን ማረጋገጫ ምልክት ለመቀየር ታቅዷል።በአሁኑ ወቅት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚለጠፈው ምልክት ቅርጹ ክብ ሲሆን ከሌሎች ምልክቶች ጋር ስለሚቀራረብ ወደ ሦስት ጎን ቅርጽ ይቀየራል።

በተጨማሪም ቀለሙና ዲዛይኑ በሌላ የሚተካ ይሆናል። ከዚህም ባሻገር ምስጢራዊ ህትመቱ በእጅጉ በረቀቀ መንገድ የሚከናወንና ከሀሰተኛ መረጃዎች ለመለየት ደግሞ በአመቺ ሁኔታ የሚታተም ነው።ምልክቱ ሐሰተኛ ቢሆን እንኳን በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል የሚሰሩ የትራፊክ ፖሊሶች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ በሚገጠም አፕሊኬሽን መለየት ያስችላቸዋል።ቀደም ሲል የነበረው የሶስተኛ ወገን መድን ማረጋገጫ ምልክት ሐሰተኛ ወይንም እውነተኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚችለው ምስጢራዊ ህትመቱን ያከናወነው ማተሚያ ቤት ብቻ እንደነበር አስታውሰው፤ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ ሲሆን ችግሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ማቃለል እንደ ሚችል ዳይሬክተሯ አብራርተዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa