YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን #ፈቀደ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት፥ በተጠረጠሩበት የማፈናቀል፣ የአካል ጉዳትና ህይዎት ማለፍ ወንጀል ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን #ፈቅዷል

መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ የ10 ቀን የጠየቀ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎቹ ተቃውሞ አቅርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጊዜ ለተመሳሳይ ምርመራ በየጊዜው ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን በመፍቀድ ለጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27
#update አብዲ መሐመድ

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ #አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የ14 ቀን  ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ #ፈቀደ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ መሐመድ ላይ የ10 ቀን ምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል ።

በዚህም መሰረት መርማሪ ፖሊስ ከሃምሌ 26 ቀን እስከ 30 /2010 ዓ/ም በሱማሌ ክልልና በአካባቢው #በተፈጸመው ወንጀል ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ምስክሮች ቃል መቀበሉን፣30 ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና ማስረጃ ማሰባሰቡን፣የ62 ሰዎች የጉዳት መጠንን ማስረጃ #በአማረኛ ማስተርጎሙን  ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

በተጨማሪም #ለኤጎ ቡድን ለወንጀሉ መፈጸሚያ የዋለውን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣ የገንዘብ መጠን እና የገንዘቡ 16 ገጽ የኦዲት ማስረጃ ማምጣቱን እና በንግድ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚገልጽ 35 ገጽ ማስረጃ  ማቅረቡን ለችሎቱ #አስረድቷል

በሌላ በኩል ፖሊስ #በኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ጠረፍ አካባቢ 200 ግለሰቦች መገደላቸውን ፥በቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ መሃመድን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ በሚደረግ ምርመራ #ማግኘቱን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

በመቀጠልም ፖሊስ ቀረኝ ያለውን በጅምላ የተቀበሩ 200 በላይ ግለሰቦች አስከሬን መለየትና የዚህን ድርጊት መፈጸም የሚያረጋገጡ #ምስክሮች ቃል ለመቀበል፥እንዲሁም በተለያዩ ዞኖች ጉዳት የደረሰባቸው 37 ግለሰቦች ማስረጃ ተርጉሞ ለማምጣት እና ለወንጀሉ ተግባረ የዋለ ገንዘብና መሳሪያን ለመያዝና ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጊዜ  ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ ስራ ተመሳሳይ በመሆኑና፥የሚያቀርበው ምክንያትንም አግባበነት የሌለውና የተጠርጣሪዎችን አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚጎዳ ነው #ብለዋል

ሰለሆነም ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው አደረሱት የተባለው ጉዳት መጠን በተናጠልና #በዝርዝር ሊቀርብ  ይገባል በማለት ተከራክረዋል።

በተጨማሪም #በኦሮሚያና ሱማሌ ጠረፍ 200 ሰው ተገደለ የተባለው አዲስ ምርመራ በመሆኑ ፥ለብቻው ተነጥሎ ሊታይ ይገባል ሲሉ የፖሊስን ምርመራ በምክንያት #ተቃውመዋል

ፖሊስ በበኩሉ 200 አዲስ ሰዎች ተገደሉ የተባለው በዚሁ ምርመራ ሲከናወን የተገኘ በመሆኑ አንድ ላይ ሊካተት ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል

ሰለሆነም ከወንጀሉ ከባደና ውስብስበነት አንጻር ተጨማሪ 14 ቀን መጠየቄ አግባበ ነው ሲል ምላሽ #ሰጥቷል

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ምርመራው #በአጭር ጊዜ ሊከናወን የማይችል በመሆኑ እና ከወንጀሉ ከባድና ውስብስብነት አንጻር ፖሊስ የ 14 ቀን ጊዜ መጠየቁ ትክክል ነው ብሏል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የምርመራ ስራውን  አጠናቆ እንዲቀርብ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 13 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ #ሰጥቷል
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ ድንበር አቅራቢያ ለማስገንባት ላቀዱት የግንብ አጥር 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንዲጠቀሙ #ፈቀደ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከሜክሲኮ በምትዋሰነው ድንበር የስደተኞችን ፍልሰት ለመቆጣጠር በሚል መከላከያ ግንብ የመገንባት እቅድ አላቸው።

ለዚህ ይረዳ ዘንድም 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
ይህ ፍላጎታቸው ግን ከኮንግረሱ ተቃውሞ ማስተናገዱን ተከትሎ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም የትራምፕ አስተዳደር ያስፈልገኛል ካለው ገንዘብ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላሩን ይጠቀም ዘንድ ይሁንታን ሰጥቷል።

ፈቃዱን ተከትሎም ትራምፕ በካሊፎርኒያ፣ አሪዞና እና ኒው ሜክሲኮ ግዛቶች ለሚገነባው መከላከያ ግንብ ገንዘቡን መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፈቃድ ግን ከዴሞክራቶች እና ከበርካታ ግዛቶች ተቃውሞ ገጥሞታል።
በርካቶችም ውሳኔው በአሜሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍና በአካባቢ ስነ ምህዳር ላይ ጉዳት ያመጣል ባይ ናቸው።

ከ20 በላይ ግዛቶችም ውሳኔውን ለማስቀልበስ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመሩ ገልጸዋል።
 
ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ሬውተርስ
@YeneTube @FikerAssefa