#Update
የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑመር ሐሠን አል በሽር ከሥልጣን ተወግደው #በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገሪቱ #መከላከያ ምኒስትር አሳወቁ።
መከላከያ ምኒስትር እና ምክትል ፕሬዝዳንት #አዋድ_ኢብን አውፍ በአገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ በሱዳን የሶስት ወራት #የአስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ መደንገጉን አስታውቀዋል።
ሉቴናንት ጄነራል አዋድ ኢብን አውፍ የአገሪቱ ሕገ-መንግሥት መታገዱን፤ የሱዳን ድንበሮች መዘጋታቸውን ገልጸዋል። የሱዳን የአየር ክልል ለ24 ሰዓታት ተዘግቷል። ሱዳንን ለረዥም አመታት የመሩት ዑመር ሐሠን አል በሽር ደኅነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዲሆኑ መደረጋቸውን መከላከያ ምኒስትሩ ገልጸዋል።
በሁለት አመታት ውስጥ ምርጫ ተካሒዶ የስልጣን ዝውውር ሽግግር ይደረጋል ተብሏል።
Via - DW
@YeneTube @FikerAssefa