YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተጎዱ ዜጎችን መልሶ #ለማቋቋም የሀብት ማሰባሰብ ስራ ጀመረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተከስቶ በነበረዉ ሁከትና ብጥብጥ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም የሀብት ማሰባሰብ ስራ መጀመሩን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት የብት ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥርም ይፋ አደርጓል፡፡

የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ #ዘላለም ጃለታ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ባሳለፍነዉ የመስከረም ወር ተከስቶ በነበረዉ ሁከትና ብጥብጥ ቁጥራቸው ከ57 ሽህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በከፋ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍም የክልሉ መንግስት #ከ5 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሰራ በክልሉ ካቢኔ መመሪያ ወጥቶ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሀብት የማሰባሰብ ስራ መጀመሩንም አቶ ዘላለም ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ አመራሮችና ሰራተኞች በችግሩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከጥቅምት ወር ደመወዛቸው የሚቆረጥ የደመወዛቸውን 10 በመቶ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተመሳሳይም የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ሰራኞችም ከጥቅምት ወር ደመወዛቸዉ 4 በመቶ ድጋፍ አድርገዋል።

ይሁን እንጂ እየተደረገ ያለዉ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ መላዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ለጋሽ አካላት የቻሉትን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ የሀብት ማሰባሰቢያ #የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000261313301 መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታዉቋል፡፡
ምንጭ ፦EBC
@yenetube @mycase27
⬆️በሰሜን #ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው ሰደድ እሳት በአካባቢው በጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እገዛ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታወቀ። ቃጠሎውን ለመቆጣጠር #ከ5 ሺ ህዝብ በላይ ርብርብ ማድረጉን የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

በቃጠሎው በግምት 300ሄክታር መሬት ላይ የበቀለ የአስታ ዛፍ(Alpine) እና የጓሳ ሳር መውደሙን ባለስልጣኑ አስታውቋል። አደጋ ሲከሰት የድረሱልን ጥሪ ተላቀን፣ በዘመናዊ መንገድ የምንሰራበትን አቅም መንግስት መገንባት አለበት ሲል ባለስልጣን አሳስቧል
@YeneTube @FikerAssefa