11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ያለምንም የጸጥታ ችግር #ተጠናቋል-ፖሊስ
11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ ጀማል በሰጡት መግለጫ ለጉባዔው በስኬት መጠናቀቅ የሀዋሳ ህዝብ፣ የፌደራልና የክልል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ወጣቶችንም ላደረጉት ትብብር ምስጋና #አቅርበዋል፡፡
በደቡብ ክልል #በሸካ ዞንና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ካሚሺ ዞን ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር መከላከያና ፖሊስ ወደ ቦታው ገብቶ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ኮሚሽነር ዘይኑ #ገልጸዋል፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27

ከአዋሽ ኮምቦልቻ -ወልዲያ ሀራ- ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት የመጨረሻ የዋሻ ቁፋሮ ስራ ተጠናቀቀ፡፡
📌ፕሮጀክቱ 85 በመቶ #ተጠናቋል፡፡ በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል፡፡
ከአዋሽ ኮምቦልቻ የመጀመርያው ምዕራፍ 270 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራም ያለቀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ከአዋሽ ኮምቦልቻ -ወልድያ ሀራ -ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት 393 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ፕሮጀክቱ #በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ይገኛል፡፡የመጀመርያው ምዕራፍ
ከአዋሽ ኮምቦልቻ 270 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከኮምቦልቻ -ወልዲያ ሀራ -ገቢያ 122 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው፡፡በፕሮጀክቱ ከሚገነቡ 12 የዋሻ ቁፋሮዎች መካከልም የመጨረሻ የሆነው 1 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ቁፋሮ ስራ መጠናቀቁንም የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱል ከሪም ሙሀመድ ለአብመድ አስረድተዋል፡፡
የሁለተኛው ፕሮጀክት ምዕራፍ ዋና ዋና ስራዎች መከናወኑን የገለጹት ኢንጅነሩ አፈጻጸሙም 65 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር
#ስንታየሁ ወልደሚካኤል የባቡር ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እየተገነባ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ይህም በሀገሪቱ
ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ከአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ- ሀራ- ገበያ የባቡር መንገድ ስራ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻጸሙ 85 በመቶ ደርሷል፡፡ ፕሮጀክቱን በመገንባት ላይ ያለው የቱርኩ ያፒ መርከዚ ነው፡፡ በቀጣይ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa