#በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላን ጠራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 12 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው የመንገድ ትራፊክ ጥናትና ትምህርት ስልጠና ባለሙያ ኮማንደር መካሻ ተስፋዬ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደገለፁት ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
በትራፊክ አደጋው የ12 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡ ሌሎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡
እንደ ኮማንደሩ ገለፃ በአምስት ወራት በወረዳው በተከሰተ ሶስት የትራፊክ አደጋ 43 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ምንጭ ፦አብመድ
@yenetube @mycase27

#በሰሜን ሸዋ ዞን የሸኖ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ #ተሾመ ሙሉጌታን ጨምሮ 26 ተከሳሾች እስከ 8 ዓመት የሚደርስ እስራትና በገንዘብ #ተቀጡ።
ተከሳሾቹ ያለአግባብ 60 ሺህ 556 ካሬ ሜትር መሬት በመሸንሸን ከ12 በላይ ለሚሆኑ ባለሀብቶች በመስጠት እና በመቀበል ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሙስና ወንጀል ነው የተከሰሱት።
የቅጣት ውሳኔውን #የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው የበየነው።
አንደኛ ተከሳሽ የሸኖ ከተማዋ ከንቲባ የነበሩት #ተሾመ ሙሉጌታን ሲሆኑ ከአንደኛ እስከ 11 ያሉት ተከሳሾች ደግሞ በከተማው መሬት አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ ሙያ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ናቻ፡፡
ከ11ኛ እስከ 26 ያሉ ተከሳሾች በኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ተከሳሾች #ናቸው።
ምንጭ ፦ OBN