YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት #ግርማ ወልደጊዮርጊስ ስም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት በቡታ ጅራ ከተማ ሊገነባ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች #ገልጸዋል

95 በመቶ የሚሆኑትን ተማሪዎች በነፃ ተቀብሎ ያስተምራል።

ትናንት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ስም ሊገነባ መሆኑን ይፋ ካደረጉት አስተባባሪዎች መካከል የገቢ ማሰባሰብ ስራውን የሚመራው አቶ ብሩክ ዳንኤል እንደገለፀው፤ ግንባታው በጎ ፍቃደኛ በሆኑት ባለሀብት አቶ አህመድ ሁሴን ሃሳብ ጠንሳሽነት የሚጀመር ነው።

ትምህርት ቤቱን ለመገንባት 10 ሚሊዮን ብር የመነሻ ካፒታል በባለሀብቱ የተመደበ ሲሆን ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ 120 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል።

የፕሮጀክቱ ጠንሳሽ እና ባለቤት የሆኑት አቶ አህመድ ሁሴን ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ እውቀትን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ከማስጨበጡ ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ አኩሪ ባህል፣ ሰላም እና አንድነት ሁሉንም ዜጎች ያለምንም ልዩነት ያስተምራል። የትምህርት ቤቱ ዋና ዓላማም ኢትዮጵያዊነትን በአዲሱ ትውልድ ማስረፅ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቀደሰ ዓላማ ባለው ፕሮጀክት ላይ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች በቀናነት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን ያቀረቡት አቶ አህመድ፤ ትምህርት ቤቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ወጪ ለማሟላት በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቱ በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን መማሪያ ክፍሎች፣ ዲጂታል ቤተመፃህፍት፣ በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የጥናት ማዕከል ይኖረዋል።

📌በተጨማሪ አረጋዊያንን የሚረዳ ማዕከል እንደሚካተትበት ለመረዳት ችለናል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ፕሬሥ ድርጅት
@yenetube @mycase27
#ከስልጣን በፊትም ከስልጣን በሁዋላም #በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ህይወት እንዲህ #ይቀጥላል

☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ነጋሶ ጊዳዳ
☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት #ግርማ ወልደጊዮጊስ
☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ ተሾመ
☑️የአሁኗ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ሳህለወርቅ ዘውዴ
@yenetube @mycase27