በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ደሪቶ ቀበሌ #በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ20 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ማጋጠሙ #ተገለፀ።
በትናትናው ዕለት ከቡሌ ሆራ ወደ ሞያሌ ሰውና ቤንዚን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መኪና ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተገልብጦ ጉዳቱ እንዳጋጠመ ታውቋል።
አደጋ የደረሰበትን ምክንያት ለማወቅ የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተነግሯል።
መኪናው የያዘው ቤንዚን የጉዳቱን መጠን ከፍ እንዳደረገውና እንዳባባሰው ተነግሯል።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27

#update ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና #በጫካ ውስጥ ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው #ተገለፀ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ግለሰቦችን በመመልመል በጫካ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች መያዛቸውን ፖሊስ ገለጸ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ እንደገለፁት፥ በሕገ ወጥ መንገድ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩት አሠልጣኞች ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር የዋሉትም ከኅብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሆኑ ነው የተገለፀው ፡፡
ግለሰቦቹ የሚያሰለጥኗቸውን አካላት ከአሶሳ ዞን መንጌ፣ አሶሳና ኦዳቢልድግሉ ወረዳዎች በመመልመል ሲያሰለጥኑ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ የተጀመረው የምርመራው ውጤት በፍጥነት አጠናቆ ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፁት ኮማንደሩ የምርመራ ውጤቱንም በየጊዜው ለሕዝቡ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡
ኅብረተሰቡ በሕገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩትን ግለሰቦች ጉዳይ በማሳወቅ ትብብሩን #እንዲቀጥል ምክትል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።
በክልሉ ህዝብ ላይ ጥፋት ለመፈጸም በአሶሳ ወረዳ ገንገን ቀበሌ በጫካ ውስጥ ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው #ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ኢዜአ