YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 13 መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው #ዕለት ይጀምራል።

የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በ12ኛ መደበኛ ጉባዔ የነበረውን ቃለ ጉባዔ ያፅድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የክልሉን የፈፃሚ እቅድ እንደሚመለከት ነው የተገለፀው።
እንዲሁም ምክር ቤቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲተር አመታዊ እቅድ በአጀንዳነት መያዙ ተጠቁሟል።

በዚህ ጉባዔ የቀበሌ ገጠር መሬት ዳኝነት፣ስልጣንና ተግባር እና የጠበቃ ምዝገባ፣ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር እንዲሁም ሌሎች አዋጆችና ደንቦችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሏል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27
#update አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ119ቱም ወረዳዎች የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት #ማቆሙን አስታወቀ።

አገልግሎቱ እንዲቋረጥ የተወሰነው የታዩ ክፍተቶችን ለመፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን በተመለከተ በነገው #ዕለት መግለጫ ይሰጣል።
@yenetube @mycase27