በአዲስ አበባ በአልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ!
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ “በተደረገ ፍተሻ”፣ “አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች” ጋር መያዙን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤ “ኦፕሬሽኑ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት አካል ነው” ያሉ ሲሆን፣ “የመዲናዋን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ እና የተጠና ፍተሻና አሰሳ እንደሚደረግ” ገልጸዋል።
የጦር መሳሪያዎቹ “መኝታ ቤቶችን በሚያከራዩ ቤቶች ውስጥ የተያዙ” ሲሆን፣ እነዚህ ቤቶች “ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ያለባቸው እና ውስን ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሆናቸውን” የከተማዋ ፖሊስ አመልክቷል።
ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ነበሩ ያላቸው ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ተገቢው ምርመራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባብ ለማስጠየቅ እንደሚሰራ ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa

❤32😁10👎8👍3
የአማራ ክልል ምክር ቤት ከ225 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ!
የአማራ ክልል ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት ጥቅል በጀት ከ225 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ አጽድቋል፡፡የ2018 በጀት ዓመት የድህነት ተኮር ሴክተሮች የበጀት ድርሻ ታሳቢ በማድረግ 225 ቢሊዮን 453 ሚሊዮን 779 ሺህ 237 ብር በጀት ጸድቋል። የሕዝብ አንገብጋቢ ችግሮችን ታሳቢ ያደረገ የካፒታል በጀት ድልድል ተደርጓል፡፡የበጀት ድልድሉ በተለያዩ አስተዳደር እርከኖች መካከል ፍትሃዊነትን የተደለደለ መሆኑንም በምክርቤቱ ተገልጿል።

❤13😁4🔥1
በደቡባዊ ትግራይ የተካሄደው ተቃውሞ እና ውጥረት
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጄነራል ታደሰ በክልሉ ደቡባዊ ዞን የአስተዳዳሪዎች ሹም ሽር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነባሩ አመራር ለምን ከሥልጣን ተነሳ እንዲሁም የወረዱበትን ሂደት በመቃወም እየተደረጉ ያሉ የአደባባይ ሰልፎች ቀጥለዋል።
ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ እሁድ በመኾኒ ከተማ እንዲሁም በትናንትናው ዕለት ሰኞ፣ ሐምሌ 21/ 2017 ዓ.ም. በአምባላጌ የአደባባይ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
እነዚህ የአደባባይ ተቃውሞዎች ወደ ደቡባዊ ምሥራቅ ዞኖች ተስፋፍቶ እሁድ ዕለት በወጅራት ኢስራ ዓዲ ውረዳ እንዲሁም ዓዲጉደም የተቀሰቀሱ ሲሆን፣ በዚህም ሞት መከሰቱን እንዲሁም እስሮችም መፈጸማቸው ተዘግቧል።
በመኾኒ ከተማ ወደ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች በትጥቅ የታገዘ ነው ያሉት ነባር አመራሮች መቀየርን በማውገዝ "በህወሓት አንመራም"፣ "በጠመንጃ አፈሙዝ አንገዛም"፣ "ጭቆና ይቁም" የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ነባሩ የደቡባዊ ዞን አስተዳደር ከሥልጣን ወርዶ በአዳዲስ ተሿሚዎች እንደሚተካ ውሳኔያቸውን ሐምሌ 15/ 2017 ዓ.ም. ባስታወቁበት ወቅት "በቀጣይ ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎችን ለማስቀረት" ያለመ እንደሆነ በወቅቱ ገልጸው ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c1leg45ld1po

❤23😭6😁3👍2👀2
የቤላሩስ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ከደገፉ በኋላ ከአዲስ አበባ ጋር ያላቸው የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከሩን አመላከቱ!
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ።በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት ጠንካራ “ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት” እንዳላቸውም ገልጸዋል።
“ኢትዮጵያ ለእኛ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት በጣም አስፈላጊ አገሮች መካከል አንዷ ናት” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ቤላሩስ የቴክኖሎጂ፣ የግብርና እና የምህንድስና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቤላሩስ ለኢትዮጵያ የግብር ማሽነሪዎችን ድጋፍ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል።
በጥቅምት ወር የቤላሩሱ መሪ ኢትዮጵያ የባህር መዳረሻ ለማግኘት ያላትን ፍላጎት በብርቱ ደግፈዋል። የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው፤ ሉካሼንኮ የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎትን የሚቃወሙ “ፍጹም ሞኞች" ናቸው ብለዋል። አክለውም "በጦርነት ወይም በድርድር ኢትዮጵያ ወደ ባህር በር ትደርሳለች። በእርግጥም በሰላማዊ መንገድ ቢሆን የተሻለ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

❤55😁21👍10🔥3
ሂውማን ራይትስ ዎች የሲቪል ማኅበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እንዲሻር ጥሪ አቀረበ!
ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ የሕግ አውጪዎች ለመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ሰፊ የሥራ ገደብ የሚጥለውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ። ድርጅቱ ይህ ረቂቅ ሕግ ከጸደቀ የሲቪል ማኅበራት ሥራን በእጅጉ እንደሚገድብ አስጠንቅቋል።
የሲቪል ማኅበራት ሕግ ረቂቅ ማሻሻያ ገና ለፓርላማ አልቀረበም ተብሏል። ሂውማን ራይትስ ዎች እንዳለው ከሆነ፣ እነዚህ ማሻሻያዎች ከፀደቁ መንግሥት በሲቪል ማኅበራት ላይ ያለውን ቁጥጥር በማጠናከር፣ የገንዘብ ድጋፍን በመገደብ እና ያለፍትህ አካል ጣልቃ ገብነት ድርጅቶችን የማገድ ወይም የመበተን ሥልጣን ይኖረዋል።
ይህ ረቂቅ ሕግ በተለይ በሀገሪቱ የዲሞክራሲ ሂደት እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ስጋት እየተገለጸ ነው።ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ለኢትዮጵያ አጋሮችም ጭምር መልዕክት አስተላልፏል፤ ይህም ማሻሻያዎቹ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ደረጃዎችን ማክበር እንዳለባቸው በግልጽ እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።
Via Capital

❤21👍7
Forwarded from YeneTube
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
-እንዲሁም በ ግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ደንበኞች ዳጎስ ያለ ቅናሽ አዘጋጅተን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#WhatsApp

❤4
Forwarded from YeneTube
የ5 ሚሊየን ቅናሽ ተደረገ 😳😳
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
❤4
በሩሲያ 8.8 ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
በሩሲያ ካምቻትካ ባሕረ ገብ መሬት አካባቢ ረቡዕ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር 11፡25 ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚከ1952 ጀምሮ በክልሉ የተከሰተ ትልቁ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ብሎታል።
የካምቻትካ ገዥ የመሬት መንቀጥቀጡ ‹‹ከባድ እና በአስርት ዓመታት ውስጥ የነበረው በጣም ጠንካራው ነው›› ሲሉ ተደምጠዋል።
በክልሉ የጤና ሚኒስትር ለሩሲያ መንግስት የዜና ወኪል ታስ እንደተናገሩት፤ በካምቻትካ በርካታ ሰዎች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
2ሺህ7መቶ የሚሆኑ ሰዎች ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ ወደ አስተማማኝ ቦታዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል ነዉ የተባለዉ፡፡
ሁሉም ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ምንም አይነት ከባድ ጉዳት አልተመዘገበም ተብሏል ሲል የዘገበዉ አናዶሉ ነዉ፡፡

❤19👀1
የስምረት ፓርቲ ፅ/ቤት በታጣቂዎች ተዘረፈ - ምንጮች
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ስምረት ፓርቲ፣ ባለፈው ሳምንት በመቀሌ ከተማ የከፈተው ዋና ጽ/ቤቱ በታጣቂዎች መዘረፉ ተሰማ፡፡
ትናንት ማታ 4:45 ገደማ ማንታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ዘበኞችን አስፈራርተው ወደ ጽ/ቤቱ በመግባት የፓርቲውን ንብረቶች መዝረፋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የቀሩትን ሰባብረውና ወረቀቶችን ቀዳደው ከስራ ውጪ ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡፡
ፓርቲው በቅርቡ በመቀሌ በከፈተው ዋና ጽ/ቤቱ ሊሰጥ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ ባልታወቀ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ የሚታወስ ነው።
Via Addis Admas

😁16❤14👍6😭6
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸውን ዛሬ ባሰራጩት መግለጫ አመልክተዋል።
ላለፉት አራት ዓመታት ማዕከሉን በሀላፊነት የመሩት አቶ ያሬድ ፤« ባጋጠሙኝ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከኦገስት 1 ቀን 2025 (ሐምሌ 25፣2017) ጀምሮ ከሃላፊነቴ እና ከድርጅቱ ለመልቀቅ መገደዴን ለማሳወቅ እወዳለሁ፡።» ሲሉ በመግለጫቸው አመልክተዋል።ድርጅቱ አገሪቱ ውስጥ ለሚፈጽሙ የመብት ጥሰቶች፤ በተለይም በጋዜጠኞች፣ በሲቪል ማህበረሰብ አባላት እና በመብት ተሟጋቾ ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና መብታቸው እንዲከበር በአደባባይ በመሟገት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ መቆየቱንም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ይህ እንዲቀጥል ከድርጅቱ ጠንካራ ሠራተኞችና የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ቁልፍ ሚና ስጫወቱ መቆየታቸውንም ገልፀዋል።ይሁን እንጅ ከአንድ አመት ወዲህ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በሚገኙ ሚዲያዎች ላይ እየቀረቡ በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሚሰጧቸው መገልጫዎችና ማብራሪያዎች፣ እንዲሁም «በማህበረ ድህረ ገጾች ላይ ዜጎችን ስለ መብታቸው እንዲያውቁና በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማስመልከት የማካፍላቸው ሃሳቦችና የምሰነዝራቸው የሰሉ ትችቶች በአገዛዝ ሥርአቱ ዘንድ በጥሩ ሁኔታ እየታዩ ባለመምጣታቸው የተነሳ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አይነት ጫናዎችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ፡፡» ብለዋል።
Via DW

❤23👍5😭3
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ ከ1200 በላይ እንስሳት ሞቱ፤ በ ደቡብ ጎንደርም ከ175ሺህ በላይ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል!
በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሚገኙ ስድስት ቀበሌዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ፤ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ከፍያለው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
የዝናብ እጥረቱ በምዕራብ በለሳ ወረዳ ከሚገኙ 32 ቀበሌዎች ቆላማ በሆኑ አከባቢዎች መከሰቱን የገለጹት አቶ ዋሲሁን ችግሩ በይበልጥ በስድስት ቀበሌዎች ማለትም በሳሚ፣ ላቫ ማርያም፣ አሳውጋሪ፣ ጃንዳብ፣ ላየ እና ሴራ በተባሉ ቀበሌዎች አስከፊ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ በምዕራብ በለሳ ወረዳ አርባያ ከተማ ዙርያ አርሶአደር፤ “መንግስት በሁለት ወር የሚሰጠን ማሽላ አለች በሷ ነው እንግዲህ እንዳይሞትም እንዳይዳንም ሆነን የምንኖረው። የሚለበስ የለም ራቁት ነው። ዞሮ ዞሮ ግን መቼም መኖር ከተባለ እስኪሞቱ ድረስ የበላም ኑሮ ነው ያልበላም ኑሮ ነው" ሲሉ በአከባቢው ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በክልሉ ደቡብ ጎንደር ዞን 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች 175ሺህ በላይ ወገኖች ለድርቅ መጋለጣቸውን የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

❤15😭9😁1
YeneTube
Photo
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የኤርትራን መንግሥት በትጥቅ ለመታገል በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ!
የኤርትራን መንግሥት ለመጣል ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የገለፀው "የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ" ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የትጥቅ ትግል ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ አባል እና ቃል ዐቀባይ አሊ መሐመድ ዑመር፤ "የኢትዮጵያ መንግሥት የመንቀሳቀስ እና የመናገር ዕድል ሰጥቶናል" ሲሉ ገልጸው፤ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ጽ/ቤት መክፈታቸውንና አዲስ አበባ ላይም ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
ቃል ዐቀባዩ፤ ባለፈው ሳምንት በዋናነት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና ጅቡቲ የሚገኙ አፋሮችን በሚመለከት እና በአካባቢው ቀጣናዊ ኹኔታዎች ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ መደረጉንና ድርጅታቸውም መሳተፉን ገልፀዋል።
"የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ" ከ11 ዓመታት በፊት እ.አ.አ በ 2014 ስዊድን ውስጥ ተመሥርቶ ለዓለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት ኤርትራ ውስጥ ስላለው "ፈታኝ" ያሉት ኹኔታ ሲያስገነዝብ፣ ሲሰባሰቡም መቆቱን የገለፁት አሊ መሐመድ ፤ አሁን ወደዚህ የመጡበት ምክንያት ምን እንደሆነም አስረድተዋል።
"አሁን ደግሞ ወደዚህ [የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና] መጥተን እዚህ ካለው የእኛ ሕዝብ እና ድርጅቶች ጋር አብረን ሆነን የትጥቅ ትግል ለማድረግ ዝግጅት እያደረግን ነው" ብለዋል።
የኤርትራ የጦር ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እያስጠጋ ስለመሆኑም ተናግረዋል። "ድንበር ላይ ኃይለኛ እንቅስቃሴዎች በከባድ መሣሪያ የታገዘ ሠራዊት አቅርቧል [የኤርትራ መንግሥት] ቡሬ አካባቢ። ስለዚህ አሁንም ወደ ጦርነት የመግባት እና ኢትዮጵያን ሰላም የመንሳት ፍላጎቱ እንደቀጠለ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የኤርትራን መንግሥት በኃይል ለመጣል እንደሚንቀሳቀስ በይፋ ያስታወቀው ብርጌድ ንሓመዶ የተባለው የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅት ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይቶችን ሲያደርግ "የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ" መሳተፉንም ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

❤38😁11👎4👍3🔥3
የሊጉ ክለቦች ዓመታዊ የገንዘብ ክፍፍል ይፋ ሆነ...!
በ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስት እና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙት ክፍፍል ይፋ ሆኗል።
በአመቱ ክለቦቹ የሚደርሳቸው ክፍፍል በአፍሪካ በከፍተኛነቱ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሻምፒዮኑ ክለብ ብር 40,295,687.24(አርባ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሺ ስድስት መቶ ሰማኒያ ሰባት ከ24/100) የሚያገኝ ሲሆን የመጨረሻው ተከፋይ ክለብ ብር 19,472,140.78(አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሁለት ሺ አንድ መቶ አርባ ከ78/100) ያገኛል።
©️የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ
@Yenetube

❤27👎5🔥5
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ትግራይ ክልል የሄዱ የሀገር ሽማግሌዎች ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ትግራይ ክልል የሄዱ የሀገር ሽማግሌዎች ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሀገር ሽማግሌዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር የሰላም ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡በተመሳሳይ የሚመለከታቸውን የፌደራል መንግሥት የሥራ ሀላፊዎችን ለማነጋገር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከሰላም ሚኒስትርና ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ ኢድሪስ ከሁሉም ክልሎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡት የሀገር ሽማግሌዎች በራሳቸው ተነሻሽነት ተደራጅተው ሰላም ከማስፈን አንጻር የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸውን አድንቀው በኢትዮጵያዊ ሀገራዊ ባህልና እሴት ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
መንግሥት በትግራይ ክልል አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተው የትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀጥሉ በርካታ ሥራዎችን መስራቱን ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኛ አቋም በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቀየቱንና ለወደፊትም ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸው መሰል ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
Via FBC

❤50😁21👍4🔥1