"የኬንያ ዜጎች እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጓጉዘው ሀገራቸው ገብተዋል"- በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች በስልክ ከነገሩኝ
በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢም፣ አስገራሚም እየሆነ ነው። ከ740 በላይ ዜጎቻችን ተይዘውበት ከነበረው አደገኛ ካምፕ በአንድ ታጣቂ ቡድን ነፃ ሆነው አሁን ላይ በግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢገኙም ተረክቧቸው ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል አጥተው እንዳሉ በርካቶች በአጭር ፅሁፍ መልዕክት እና በስልክ ነግረውኛል።
አንዳንዶቹ በተስፋ መቁረጥ ራስን የማጥፋት ሙከራ አርገዋል፣ ኮማ ውስጥ ያሉ አሉ፣ የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ። ውጭ ጉዳይ አንድ ሰሞን ጉዳዩን ይዞት እንደነበር ሰምተን ነበር፣ አሁን ላይ ምንም ነገር የለም፣ ሲጠየቁ "ፕሮሰስ ላይ ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ።
ዜጎቻችንን ከካምፑ ነፃ ያወጡት ታጣቂዎች እንኳን "መንግስታችሁ በፍጥነት ካልወሰዳችሁ ወደነበራችሁበት ካምፕ ከመመለስ ውጭ ምርጫ የለንም" እያሏቸው ነው።
ኬንያን ጨምሮ ሌሎች 25 ሀገራት ዜጎቻቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በመጠቀም አጓገዘው አውጥተዋል። ጉዳዩን በቶክዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይዞት ነበር ተብሎ ነበር፣ አሁን ደህሞ ህንድ ያለው ኤምባሲ እየተከታተለው ነው ከሚል ውጭ ምላሽ የለም።
የሚገርመው 400 የሚሆኑት የመመለሻ ትኬት አላቸው፣ ሊረዷቸው የሚችሉ NGO ድርጅቶችም አሉ፣ ነገር ግን መንግስት የመመለስ (repatriation) ሂደቱን ካልጀመረ ምንም ማድረግ አይቻልም።
ልጆቹ አንዴ ተታለው ተወስደዋል፣ መንግስት ግን ሊደርስላቸው አይገባም? ሀገር ማለት ህዝብ ማለት አልነበር?
በአፋጣኝ ትኩረት ካልተሰጠው አሳዛኝ ውጤት ይታየኛል።
መረጃው የኤልያስ መሰረት ነው።

👍18❤3🔥1😭1
ፓኬጅ
Gift For Her ❤
Gift sets
- የእጅ ሰዓት Brand Watch
- ፅጌረዳ አበባ Roses bouquet 💐
- ሕማማት መፅሀፍ Book spiritual
FREE DELIVERY
ይደውሉ
Inbox for Order @Fikerassefa
Gift For Her ❤
Gift sets
- የእጅ ሰዓት Brand Watch
- ፅጌረዳ አበባ Roses bouquet 💐
- ሕማማት መፅሀፍ Book spiritual
FREE DELIVERY
ይደውሉ
Inbox for Order @Fikerassefa
👍12👎4
በምስራቅ ወለጋ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል በመንግስት የጸጥታ ሀይል መገደሉን ተከትሎ ታጣቂዎቹ በወሰዱት የበቀል ጥቃት 29 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሐሮ ሊሙ ወረዳ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል እና የቡድኑ መሪ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) "የቅርብ ሰው" የነበሩት ሾዴ በመንግስት የጸጥታ አካላት መገደላቸውን ተከትሎ በተፈጸመ የበቀል ጥቃት 29 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የሟች ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
እንደ ነዋሪዎች እና የሟች ቤተሰቦች ገለጻ፣ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሐሮ ሊሙ ወረዳ ጎርባ ጉዲና እና ሱጌ ቀበሌዎች የተፈጸሙት ጥቃቶች "የሾዴን ሞት ለመበቀል በኦነሠ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል" ብለዋል።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እና በጋብቻ ከሟች ቤተሰቦች ጋር ዝምድና እንዳላቸው የገለጹልን በጎርባ ጉዲና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት፣ ከመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች ቢያንስ የአሥር ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል።
የአካባቢው ነዋሪ አክለውም በ"ኦነሰ ታጣቂዎች" የሚፈጸሙ ጥቃቶች በአካባቢው እንደቀጠሉና በዚህም ምክንያት የአቶ ፋይሳ ተጨማሪ ሰባት ዘመዶች መገደላቸውን ገልጸዋል፤ "እነዚህ ሰዎች ሾዴን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎችን ረድተዋል ተብለው ስለተጠረጠሩ ነው ኢላማ የተደረጉት" ሲሉም አክለዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7615

👍15😭2
ትራምፕ በቻይና ላይ የጀመሩትን ታሪፍ 245 ከመቶ አደረሱ
አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችዉን ቀረጥ ወደ 245 በመቶ አሳድጋለች።
አሜሪካ በቻይና ላይ እየጣለች ያለችዉን ቀረጥ ወደ 245 በመቶ ከፍ ማድረጓን የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሳወቃቸዉን ኢንዲያ ደይሊ ዘግቧል።
ዛሬ በነጩ ቤተ መንግስት ፕሬዚዳንት ትራምፕ እንደገለፁት፤ ቻይና ከሰሞኑ ወደ አገሯ የሚገቡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ ያሳየችዉን አፀፋዊ ምላሽ ለመቀልበስ ጭማሪውን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ትራምፕ፣ ይህ ርምጃ አሜሪካን በኃያልነቷ ለማስቀጠል ከተያዘዉ መርህ አንዱ ነዉ ብለዋል።
75 የሚሆኑ አገራት በቀረጥ ዙሪያ ንግግር ማድረግ እንደሚችሉ ጠቅሰዉ፤ ቻይና ግን ቀረጥ በመጨመር ምላሽ ስለሰጠች ጭማሪዉ ተደርጎባታል ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍18👀5😁3
ክልሉ ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ምህረት አደረገ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ ፡፡
ቢሮው እንዳስታወቀው ታራሚዎቹ ምህረቱን ያገኙት መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው ፡፡
ታራሚዎቹ ይቅርታው ሊደረግላቸው የቻለው በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት ያቀረቡትን የይቅርታ ማመልከቻ በመመርመር መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው “ በተለይም በማረሚያ ተቋማቱ በነበራቸዉ ቆይታ ስለመታረማቸዉ፣ ስለመታነጻቸዉና ስለመልካም ጠባያቸዉ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት ማረጋገጫ አግኝተዋል ነው የተባለው፡፡
በቀጣይ ለህብረተሰቡ የወንጀል ስጋት ሳይሆኑ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ ሆነው በሰላም መኖር እንዳለባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል መባሉን ከDW ተመልክተናል።

👍20❤1
በአዲስ ሊተኩ ነው በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች በአዲስ ሊተኩ ነው።
በሥራው የተሰማሩ ወጣቶች ወዴት እንደምንሄድ አናውቅም ብለዋል
‹‹በየሁለት ዓመቱ መተካት ግዴታ ነው››
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ
‹‹የእኛ ሥራ ተደራጅቶ የመጣልንን ወጣት መመደብ ብቻ ነው››
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ሥፍራዎች ላይ የተሰማሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተራ አስከባሪዎች፣ በሌሎች በተደራጁ ወጣቶች እንደሚተኩ ታወቀ።
በከተማ አስተዳደሩ ሥር በየወረዳቸው በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በመደራጀት፣ ላለፉት 24 ዓመታት በታክሲ ተራ ማስከበር ሥራ የተሰማሩ ወጣቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዘርፉ በመውጣት ሽግግር ለማድረግ መስማማታቸውን ለየወረዳቸው እንዲያሳውቁ የተለያየ ቀነ ገደብ ተቀምጦላቸዋል።
Via:- Reporter

👍41👀16❤7👎6😁3
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን መስሪያቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ "የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት እና የአማራ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዛሬ ሚያዝያ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ህገ መንግስቱን በመጣስ ሁመራን የአማራ ክልል አካል አድርጎ በማቅረብ የፕሪቶሪያ ውልን የሚጻረር ዜና ይዘው ወጥተዋል።" አለ።
"ይህ ድርጊት ቀላል አይደለም" ያለው የትግራይ ክልል፣ "ነገር ግን ሆን ብለው የትግራይን ህገ-መንግስታዊ ክልል፣ የአማራ ክልል አካል አድርገው ደጋግመው መጥቀሳቸውን ቀጥለዋል።"ብሏል።
"ይህ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ህገ መንግስቱን የሚጻረር እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን በቀጥታ የሚጻረር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም" ሲል "በአስቸኳይ መታረም እንዳለበት" ያሳሰበው የትግራይ ክልል "የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት እና የአማራ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሁለቱንም ክልል ህዝቦች አብሮ የመኖር ህልውና የሚያናጋ እና በቀጥታ ወደ ሌላ ግጭት የሚጋብዙ ሀላፊነት የጎደላቸው የዜና ዘገባዎችን በማረም ይህን ህገ-መንግስታዊ ጥሰት በሚፈጽሙ አካላት ላይ የፌደራል መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።" ሲል ክልሉ በኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤቱ በኩል መግለጫ አውጥቶ ተመልክተናል።

👎51👍40😁5😭1
Forwarded from YeneTube
🌿🌿እንኳን አደረሳችሁ 🌿🌿
በአልን ምክንያት በማድረግ እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ!!!
በ 900,000 ብር ምን ያደርጋሉ❗️
በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።
እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።
ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።
ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።
ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።
ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።
ፈጥነው ይደውሉ!
እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን
📍 ሊሴ ገብረማርያም ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ
ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ
ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር ለኢንቨስትመንት ምቹ
⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ
ለአንድ ሳምንት የሚቆይ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ
ቴምር ሪልስቴት
ለበለጠ መረጃ
+251 950 05 56 55
ወይም በቴሌግራም
TG @Davehomes
What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1

👍6
Forwarded from YeneTube
ዛራ ሽቶዎች
በተለያዩ ፍሌቨሮች
Red Zara temptation ,Zara golden decade and Zara hypnotic vanilla
Europe standard
Size: 80ml
በብዛት ወይም በችርቻሮ መረከብ ሚፈልግ እናስረክባለን
ዋጋ በችርቻሮ:7000br
በብዛት:6000br
ስልክ: +251919492435 & +251934003462
ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል 👇
https://tttttt.me/+zRyCg_U0QGZmMzY0
ቲክቶክ አካዉንት 👇
www.tiktok.com/@bt_onlineshopping

👍1
የኢሳያስ ተቃዋሚዎች
"ብርጌድ ንሐመዱ" በመባል የሚታወቀው የኤርትራው የተቃውሞ እንቅስቃሴ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የከፈተው ቢሮ፣ "በቀጣይ ወታደራዊ ማዕከሎች ሲቋቋሙ፣ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት" ሆኖ እንደሚያገለግል መግለጹን ቢቢሲ ዛሬ ዘግቧል።
"በኢትዮጵያ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማዕከሎች" ሊኖሩት እንደሚችልም ያስታወቀው እንቅስቃሴው፣ ብርጌድ ንሓመዱን የሚቀላቀሉ ኤርትራውያን፣ "ዋስትና ስለሚያገኙበት መንገድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መነጋገሩን" የእንቅስቃሴው አመራር ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ ገልጿል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ የሚንቀሳቀሰው ብርጌድ ንሓመዱ፣ በአዲስ አበባ ከተማ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንጻ ላይ የከፈተውን ጽህፈት ቤት ሥራ ያስጀመረው ባለፈው የካቲት አጋማሽ መሆኑን ያስታወሰው የቢቢሲ ዘገባ፣ የጽህፈት ቤቱን የምርቃት ሥነ ሥርዓት በሚያሳይ ቪድዮ ላይ፣ "የብርጌድ ንሓመዱ አመራሮች የቢሮው መከፈት ለእንቅስቃሴው እጥፋት እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል ብሏል።
እንቅስቃሴውን ከፊት ሆነው ከሚመሩ ግለሰቦች አንዱ የሆኑት አቶ በየነ ገብረእግዚአብሔር፤ ጽህፈት ቤቱ "ተበታትኖ ለቆየው" የብርጌድ ንሐመዱ እንቅስቃሴ "አንድ መገናኛ ማዕከል" እንደሆነ መናገራቸውንም በዘገባው ተካቷል።
#ዘሀበሻ

👍39👎8😁5❤2
ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የታይም መፅሄት የአመቱ 100 ተፅእኖ ፈጣሪዎች ስብስብስ ውስጥ ተካተቱ
- በዘንድሮው ስብስብስ ውስጥ ዶናልድ ትረምፕ እና ኤሎን መስክ ተካተዋል
@Yenetube @Fikerassefa
- በዘንድሮው ስብስብስ ውስጥ ዶናልድ ትረምፕ እና ኤሎን መስክ ተካተዋል
@Yenetube @Fikerassefa
👍76❤17👎9😁5
በሕብረተሰቡ ላይ ያልተገባ ክፍያ የሚጠይቁ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ!
ከዚህ በፊት ሕብረተሰቡን ላልተገባ ግጭት እና ለከፍተኛ ወጭ ሲዳርጉ በነበሩ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ በወጣው መመሪያና ደንብ መሠረት እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሚደቅሳ ከበደ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የአገልግሎት አሰጣጡ የተሳለጠ እንዲሆን በሕገ-ወጥ ጫኝና አውራጆች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመወሰዱ በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ቁጥር ቀንሷል፡፡
በዚህም አሰራት መሠረት ከሕብረተሰቡ ጋር ተግባብተው የሚሰሩ ሕጋዊ ጫኝና አውራጆችን መፍጠር መቻሉን አክለዋል።
"በዘርፉ ሕዝቡ እፎይ ያለበት አገልግሎት ቢሆንም፤ አሁንም በአንድ አንድ አካባቢዎች ከአቅም በላይ ገንዘብ በመጠየቅ ሕዝቡን የሚያማርሩ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች መኖራቸውን ባደረግነው የዳሰሳ ጥናት አረጋግጠናል" ሲሉም አቶ ሚደቅሳ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ሕጋዊ የሆነ ፍቃድ ያላቸው ጫኝና አውራጆች ሕግን ተላልፈው ሲገኙ፤ የጥፋት ደረጃው ተገምግሞ የወሰዱትን ፍቃድ እስከመሰረዝ ብሎም በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚውሉበት ሁኔታ እንዳለም ጠቁመዋል።
ከከተማ ውጭ የሚሰራ ሥራ እና አሳቻ ሰዓትን ጠብቀው እየሰሩ ያሉ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች በዘርፉ ላይ ተግዳሮት መሆናቸውን አስረድተዋል።ሁሉም ሰው ለሠላም ዘብ እንድቆም እና ሕብረተሰቡ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት መረጃን በመስጠት የጎላ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሚደቅሳ ከበደ ጠይቀዋል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

👍49❤3😁3
ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`
LINK -
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1🔥75👍35❤7
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ። ⭐️ ⭐️
የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!
📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን
በካሬ 64,200 ብር ብቻ
ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ
ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን
ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!
ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!
+251 950 05 56 55
ወይም በቴሌግራም
TG @Davehomes
What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!
📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን
በካሬ 64,200 ብር ብቻ
ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ
ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን
ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!
ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!
+251 950 05 56 55
ወይም በቴሌግራም
TG @Davehomes
What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍13
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ አቤቱታዎችን መቀበሉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ
በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ዉስጥ 2,890 አቤቱታዎችን ለመቀበል አቅዶ 1,716 አቤቱታዎች ብቻ ነው የቀረበልኝ ብሏል፡፡
እናም የዕቅዴን 60% ብቻ ነው ማሳካት የቻልኩት ሲል በ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ገልጧል፡፡
በበጀት እጥረት ተቋሙን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ባለመሆኑ፣ የተቋሙ ነጻ የቅሬታ መቀበያ በሚፈለገው መልኩ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑና የተቋሙ የማስፈጸም አቅም በበጀት፣ ቁሳቁስና የሰው ሀይል የተሟለ አለመሆን ለስኬቱ ማነስ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሷል፡፤
ከቀረቡት 1,716 አቤቱታዎች ውስጥ 564 አቤቱታዎች ተቀባይነት ባለማግኘታቸው (በተቋሙ ስልጣን ስር የማይወድቁ ማለትመ በፍርድ ቤት የታዩ፣የወንጅል ጉዲዮች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች በመሆናቸው)
ተገቢው የህግ ምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል ይላል ሪፖርቱ፡፡
469 አቤቱታዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቀሪ 683 አቤቱታዎች ደግሞ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ለመርማሪዎች የተመሩ መሆኑን ጣያችን ከሪፖርቱ ተመክልቷል፡፡

👍13❤1😁1