YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢሳያስ ተቃዋሚዎች

"ብርጌድ ንሐመዱ" በመባል የሚታወቀው የኤርትራው የተቃውሞ እንቅስቃሴ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የከፈተው ቢሮ፣ "በቀጣይ ወታደራዊ ማዕከሎች ሲቋቋሙ፣ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት" ሆኖ እንደሚያገለግል መግለጹን ቢቢሲ ዛሬ ዘግቧል።
"በኢትዮጵያ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማዕከሎች" ሊኖሩት እንደሚችልም ያስታወቀው እንቅስቃሴው፣  ብርጌድ ንሓመዱን የሚቀላቀሉ ኤርትራውያን፣ "ዋስትና ስለሚያገኙበት መንገድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መነጋገሩን" የእንቅስቃሴው አመራር ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ ገልጿል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ የሚንቀሳቀሰው ብርጌድ ንሓመዱ፣ በአዲስ አበባ ከተማ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንጻ ላይ የከፈተውን ጽህፈት ቤት ሥራ ያስጀመረው ባለፈው የካቲት አጋማሽ  መሆኑን ያስታወሰው የቢቢሲ ዘገባ፣  የጽህፈት ቤቱን የምርቃት ሥነ ሥርዓት በሚያሳይ ቪድዮ ላይ፣ "የብርጌድ ንሓመዱ አመራሮች የቢሮው መከፈት ለእንቅስቃሴው እጥፋት እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል ብሏል።

እንቅስቃሴውን ከፊት ሆነው ከሚመሩ ግለሰቦች አንዱ የሆኑት አቶ በየነ ገብረእግዚአብሔር፤ ጽህፈት ቤቱ "ተበታትኖ ለቆየው" የብርጌድ ንሐመዱ እንቅስቃሴ "አንድ መገናኛ ማዕከል" እንደሆነ መናገራቸውንም በዘገባው ተካቷል።

#ዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
👍39👎8😁52