YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
2👍1
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍87
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍42
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
4👍3
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ!

መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም እለተ ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከጉንዶ መስቀል ከተማ ወደ ኩቲ 53 በሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 ( 75263 ኦሮ ) የሆነ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላሻ ተሽከርካሪ ፤ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ 30 ባጋጠመዉ የመገልበጥ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡት  8 ወንዶች እና 7 ሴቶች ናቸዉ።

ሌሎች 4 ሰዎች በእጅግ ከባድ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸው በጳዉሎስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኢንስፔክተር ባዩሳ ደበላ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ለአደጋዉ መንስኤ የተሽከርካሪዉ የቴክኒክ ብቃት ማነስ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም በ 30 ሰዎች ላይ 18 ሴት እና 12 ወንዶች ከባድ የተባለ ጉዳት እንዲሁም በ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ነዉ የተባለዉ።

ተሽከርካሪዉ ዳገት በመዉጣት በነበረበት ወቅት ወደ ኋላ በመመለሱ አደጋዉ ማጋጠሙን የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል። በአደጋዉ አሽከርካሪዉ እና ረዳቱ ወዲያዉኑ ህይወታቸዉ ማለፉንም አክለዋል።በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሌሎች 30 ሰዎች በፍቼ እና ጉንዶመስቀል ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ባዩሳ ደበላ ጨምረዉ ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
👍285🔥1
በምዕራብ ጎጃም በምትገኘው የደንበጫ ከተማ ትላንት በተካሄደ የድሮን ጥቃት 16 ወጣቶች ተገድለው 3 መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

የቆሰሉ ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።በደንበጫ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውግያው እንደቀጠለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ገልጸዋል። ውግያው ቅዳሜ በርትቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን አልፎ አልፎ ከሚሰማ የተኩስ ድምጽ በስተቀር ረገብ ማለቱን ነው እኒህ የአይን እማኝ የተናገሩት።

ትናንት እሁድ በከተማዋ በተካሄደ የድሮን ድብደባ ስለሞቱት ወጣቶች ማንነት የተጠየቁት እኚህ የዓይን እማኝ «የፋኖን ኃይል ለመርዳት የተዘጋጁ መሣሪያ ያልታጠቁ ወጣቶች ናቸው» ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ በገጠራማ አካባቢዎች የሄሊኮፕተሮች ድብደባ የነበረ ቢሆንም በቤቶች ላይ ከደረሰ ውሱን ጉዳት በስተቀር በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተናግሯል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍233
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!

የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።

የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርስነት የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።

45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት ታላለቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስነት ማስመዝገቧን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍287👎2
የፌደራሉ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእንባ ጠባቂ ተቋምን ምክረ ሃሳቦች ለመቀበል እምቢተኝነት ያሳያሉ ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ በሰጡት ቃል ከሰዋል።

እንዳለ፣ ኹለቱ የፖሊስ ኮሚሽኖች ተባባሪ ባለመኾናቸው ተቋሙ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመምራት ተገዷል ብለዋል። የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽንም፣ ተመሳሳይ ችግር እንደሚታይበት ዋና እንባ ጠባቂው ጠቅሰዋል።

አንዳንድ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ እንደ ባሕርዳር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ የመሳሰሉ የክልል ከተማ አስተዳደሮችና የክልል ቢሮዎች፣ የሕዝቡን የአስተዳደር በደሎች ለመስማትና የተቋሙን የመፍትሄ ሃሳቦች ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የማይኾኑት፣ "ማን ይነካናል?" በሚል አስተሳሰብ እንደኾነም እንዳለ ለጣቢያው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍434
ኢራን ከዩናትድ ስቴትስ ጋራ የእስረኞች ልውውጥ እንደምታደርግ አስታወቀች!

ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ፣ ዛሬ ሰኞ፣ የእስረኞች ልውውጥ እንደምታደርግ አስታውቃለች። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ተጥሎበት የነበረው ስድስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣ ደቡብ ኮርያ ከሚገኝ የባንክ ሒሳቧ ወደ ኳታር ባንክ እንዲዘዋወር ስትጠብቅ እንደቆየች ገልጸዋል፡፡

የገንዘብ ዝውውር ስምምነቱ፣ በኢራን ታስረው ለሚገኙ አምስት አሜሪካውያንና በዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ አምስት ኢራናውያን የእስረኞች ልውውጥ መንገድ እንደከፈተ ተናግረዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ግለሰቦችን ጠቅሰው የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት፣ ኳታር፣ ገንዘቡ ዛሬ ሰኞ እንደተላለፈ ለኢራንና ለአሜሪካ አሳውቃለች።

በጉዳዩ ላይ፣ እስከ አሁን ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የተገኘ ማረጋገጫ የለም፡፡ የዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ፣ ባለፈው ሳምንት ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የባይደን አስተዳደር፣ የእስረኛ ልውውጡ በቅርብ ጊዜ እንደሚከናወን ያለውን ተስፋ አመልክተው ነበር።

በእስረኛ ልውውጡ የሚለቀቁት ሦስቱ አሜሪካውያን፥ ሲያማክ ናማዚ፣ ኢማድ ሻርጊ እና ሞራድ ታህባዝ ናቸው፡፡ እኒኽ ሦስቱ፣ ከሌላ ስማቸው ካልተገለጹ ሁለት አሜሪካውያን ጋራ፣ ከነበሩበት በታህራን ከሚገኝ እስር ቤት ወጥተው በመኖሪያ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ ተገልጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ አምስቱም አሜሪካውያን ያለአግባብ መታሰራቸውን ትከራከራለች። ኢራን በበኩሏ፣ በስምምነቱ መሠረት እንዲፈቱ የምትፈልጋቸውን አምስት ኢራናውያንን ለይታ አሳውቃለች።

ወደ ኳታር የተላለፈው የኢራን ገንዘብ፣ ለሰብአዊ ጉዳዮች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ነው የተወሰነው፡፡ ኢራን፣ ገንዘቡን ለሌላ ተግባር ልትጠቀምበት ትችላለች፤ የሚለውን ጥርጣሬ፣ የባይደን አስተዳደር፣ ገንዘቡ ለተፈቀደለት ጉዳይ ብቻ ስለመውጣቱ ክትትል ይደረጋል፤ ሲል ውድቅ አድርጓል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍244
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍3
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍4
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍51👎1
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍4👎1
ከየመን ወደ አገራቸው ለመመለስ መንገድ ያጡ ኢትዮጵያውያን አጣብቂኝ ገብተዋል!

በጦርነት በተበታተነችው በየመን ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች፣ ገቢ ለማስገኘት የሚያስችል ሥራም ኾነ ወደ አገራቸው መመለሻ መንገድ ማጣታቸውና በአጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት፣ በክልሎቹ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ፣ ከዐማራ ወይም ከትግራይ ክልል ወደ የመን የመጡ ፍልሰተኞችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመኾኑ፣ ውሳኔውን የተቃወሙ ስደተኞች ወደ አደባባይ እንዲወጡ ምክንያት ኾኗል።

በፈቃደኝነት ከየመን ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ስደተኞች የሚቀርበውን ሰብአዊ ርዳታ የሚቆጣጠረው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ በቅርቡ፣ በክልሎቹ ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ፣ ወደ ትግራይ እና ዐማራ ክልሎች የሚመለሱትን ስደተኞች ማጓጓዝ እንዳቋረጠ ታውቋል። ድርጅቱ፣ ከስደት ተመላሾቹ ወደ አገራቸው የመመለስ ጉዞን ማስቆም ባይችልም፣ ሊመለሱ የሚችሉበትን ኹኔታም ግን እያመቻቸ እንዳልሆነ ተገልጿል።

በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ በየዓመቱ የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ፣ ለሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ሰለባ በሚኾኑበት አደጋ ባልተለየው ጉዞ ወደ አረብ አገሮች ያቀናሉ። ውሳኔውን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ ባለፈው ሳምንት፣ ከየመኗ ዋና ከተማ ዔደን ከሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ደጃፍ ትዕይንተ ሕዝብ ማካሔዳቸውን ተከትሎ፣ ግጭት እንደተፈጠረና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም እንደተገደሉ ተዘግቧል።

አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው፣ የዐማራ ተወላጆች መብቶች ተሟጋቹ “የዐማራ ማኅበር በአሜሪካ” የተባለው ድርጅት ሊቀ መንበር ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ፣ ውሳኔው፥ የዐማራ እና የትግራይ ተወላጆች የኾኑ ስደተኞችን ለይቶ የተፈጸመ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተናጠል ያደረገው አግላይ ፖሊሲ ውጤት ነው፤ ይላሉ።

“እነኚኽ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ አገራቸው ተመልሰው የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች የሚያስፈልጓቸው አገልግሎቶች ተሰጥተዋቸው፣ በዐዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች እንዲኖሩ ሊደረጉ ይችላሉ። የዐማራ ተወላጆች በመኾናቸው ብቻ፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ ሊያቅታቸው አልያም የግድ ወደ ዐማራ ክልል መሔድ የለባቸውም። የዐማራ ተወላጆች፣ በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖራሉ፤” ብለዋል።

በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በፕሪቶርያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት ባለፈው ጥቅምት ተቋጭቷል፡፡ በአንጻሩ በሕዝብ ብዛቱ በአገሪቱ ሁለተኛ በኾነውና የፋኖ ታጣቂ በሚገኝበት የዐማራ ክልል፣ ሌላ ዐዲስ ግጭት መቀስቀሱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሐምሌ ወር መገባደጃ፣ በዐማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት፣ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁ የሚታወስ ነው።

በ18 ዓመቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዘችው ሮማን፣ ምንም እንኳን የሥራ ዕድል ማግኘቱ ቢሳካላትም፣ ሥራ ለመሥራት የሚቻልበት ኹኔታ ግን እጅግ አዳጋች እንደ ነበር አስረድታለች። ዶር. መሳይ ሙሉጌታ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር ናቸው። ዜጎች፣ አደገኛውን የስደት ጉዞ እንዳያደርጉ የማቀብ መፍትሔው፣ ኢኮኖሚያዊ ነው፤ ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሂዩማን ራይትስዎች በቅርቡ ያወጣው አንድ ዘገባ፣ የሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች፣ እ.አ.አ. ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የየመንና የሳዑዲን ድንበር ለማቋረጥ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንደገደሉ አመልክቷል።

የመብቶች ተሟጋቹ ቡድን አክሎም፣ ግድያዎች፣ በሰብአዊነት ላይ ከተፈጸሙ ወንጀሎች እንደሚቆጠሩ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ የተባሉትን ግድያዎች ለማጣራት ምርመራ እንደሚያካሒድ ሲያስታውቅ፣ የሳዑዲ መንግሥት በአንጻሩ፣ ክሡን አስተባብሏል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍231
የምርት ሙከራ የተከናወነባቸዉ ስድስት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምርት ሙከራ ከተከናወነባቸዉ ስድስት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች 25 ሜጋ ዋት ኃይል መገኘቱን አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል የጂኦተርማል ሴክተር ልማት በአሉቶ ላንጋኖ የከርሰምድር ፕሮጀክት ከተቆፈሩት 10 የኃይል ማመንጫ ጉድጓዶች የስድስቱ ቁፋሮ ተጠናቆ ምርት መስጠት ጀምሯል ብሏል።

"ቀሪ የአራት ጉድጓዶች ሙከራ ስራ እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ሊጠናቀቅ እንደሚችል" ተጠቁሟል።

ካፒታል ከተቋሙ ባገኘዉ መረጃ "ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ 70 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ታልሟል በመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሜጋ ዋት ከተከናወነ በኃላ ሁለተኛው ይቀጥላል"።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍19🔥21
በትግራይ ክልል ነገ መደበኛ ትምህርት ይጀመራል!

የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ነገ እንደሚጀመር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የ2016 የትምህርት ዘመንን ነገ ለማስጀመር ለትምህርት ማሕበረሰቡ ሥልጠና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

በዚህም ባለፉት 5 ቀናት ለመምህራን እና ለትምህርት ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን ነው የገለጸው፡፡

ስልጠናው እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ቢሮው ምስጋና አቅርቧል፡፡በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ በየአካባቢው የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሮው ጥሪ አቀርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍357
ሰሞኑን በሱማሌ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ግጭት እንደተከሰተ ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮቿ ተረድታለች።

ግጭቱ የተካሄደው፣ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ወደ ሱማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጅግጅጋ ከተማ በሚወስደው መስመር በባቢሌ ከተማ አቅራቢያ እንደነበር ታውቋል። ግጭቱ በትክክል በየትኞቹ አካላት መካከል እንደተካሄደ ግን ለጊዜው ማረጋገጥ አልተቻለም። በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ላይ ኹለቱ ክልሎች ቀደም በይገባኛል ጥያቄ ሲወዛገቡ የነበረ ሲኾን፣ ከጥቂት ዓመታት በፊትም ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የኾነ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። የሰሞኑን ግጭትና ውጥረት ተከትሎ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው እንደተሠማራ ተሰምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍12🔥1
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ባለፈዉ ዕሁድ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰዉ ተገደለ፤ ቆሰለ፤ በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ።

ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጅቡቲ በሚወስደዉ አዉራ መንገድ ዳር በምትገኘዉ «አዉራ ጎዳና» ወይም «ቆርኬ» ተብላ በምትጠራዉ ከተማና አካባቢዋ በሐብትና በቦታ ይገባኛል ሰበብ የጊዜዉ ግጭት ይነሳል።ባለፈዉ ዕሁድ የተቀሰቀሰዉ ግን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከሚነሳዉ ግጭት የከፋና በከባድ መሳሪያ የታገዘ ዉጊያ እንደነበር የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።ለጠቡ መነሻ ነዋሪዎቹ የሚሰጡት አስተያየት እንዳሉበት አካባቢና እንደየጎሳቸዉ የሚቃረን ነዉ።አንዳዶቹ ነዋሪዎች ግጭቱ የተነሳዉ የፋኖ ታጣቂዎች «በአካባቢዉ የሠፈረዉን የኦሮሚያ ፖሊስ በማጥቃታቸዉ ነዉ» ይላሉ።ሌሎች ግን ባካባቢዉ የፋኖ ታጣቂ አለመኖሩን አስታዉቀዋል።

ቀደም ሲል አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከአካባቢዉ ሲለቅ ሠራዊቱን ተክቶ አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኦሮሚያ ፖሊስ ነዉ።ግጭቱ የተደረገዉም «ባካባቢዉ አርሶ አደርና በኦሮሚያ ፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ነዉ» ባዮች ናቸዉ።

አስተያየት ሰጪዎቹ በግጭቱ መነሻና በተዋጊዎቹ ማንነት ላይ ልዩነት ቢኖራቸዉም በግጭቱ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ወደ መተሐራና ወለንጪቱ ከተማ መወሰዳቸዉን አስታዉቀዋል።በግጭቱ ከ2 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ መፈናቀሉ፣ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሐብትና ንብረት መዉደሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዳግም ባካባቢዉ በመስፈሩ ግጭቱ መብረዱንም ነዋሪዎቹ አስታዉቀዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍316
በጦርነቱ ወቅት የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ኃይል ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስርዓት በቅርቡ በይፋ እንደሚካሄድ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

በጦርነቱ ወቅት የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ኃይል ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስርዓት በቅርቡ በይፋ እንደሚካሄድ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩ በትክክል ባያስቀምጡትም "በሺዎች የሚቆጠሩ" ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸው ተናግረዋል። የሟች ቤተሰቦች ከማርዳት በተጨማሪ፣ የመደገፍ ስራም እንደሚከወን ጠቁመዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍273