YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአለም ባንክ የጅቡቲ ወደብን ለመሃል አገር ይበልጥ ቅርብ ማድረግ ለሚያስችል የፈጣን መንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ብድር አፀደቀ።

ባንኩ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የፈቀደው 730 ሚሊየን ዶላር ብድር የሚኤሶ ድሬዳዋ 142 ኪሜ መንገድን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዝ ከመሆኑ ባለፈ ወደ ጅቡቲ በጋላፊ በኩል የሚደረገውን ጊዞ በ146 ኪሜ የሚያሳጥር ነው።የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ ጅቢቲ የፈጣን መንገድ እቅድ አካል ሲሆን ከዚህ ክፍል ውስጥ የአዲስ አዳማ እና ድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገዶች አገልግሎት እየሰጡ ነው።

ቀሪው የአዳማ አዋሽ እና አዋሽ ሚኤሶ የፈጠን መንገድን በቀጣይ በተለያየ የግንባታ መርህ እንደሚገነባ ይጠበቃል።ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተገኘው መረጃ መሰረት የጨረታ ሂደትን በማለፍ የሚኤሶ ድሬዳዋ አስፓልት መንገድ ግንባታ በበጀት አመቱ ሁለተኛ አጋማብ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

የመንገዱ ግንባታ ቀደም ሲል በጠጠር ደረጃ የነበረውን መንገድ ወደ አስፋልት የሚያሳድግ ከመሆን ባለፈ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወደብ መዳረሻ የሆነችውን ጅቡቲን በአካባቢው ካሉ አማራጭ አገራት ወደቦች ለመሃል አገር እጅግ ቅርብ የሚያደርግ ነው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ኤም ፔሳ በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ደምበኞች እንደሚኖሩኝ ጠብቃለሁ አለ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤም ፔሳ ( M-pesa ) አገልግሎቱ በሞባይል የሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉርን ለማከናወን ፈቃድ ከተሰጠዉ በኋላ እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ 2 ሚሊዮን ደምበኞች እንደሚያፈራ የሳፋሪኮም ፋይናንስ ኦፊሰር ዲሊፕ ፓል መናገራቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን (The East African) ጽፏል።

ፋይናንስ ኦፊሰሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ብርቱ ፉክክር እንደሚገጥማቸዉ የገለጹ ሲሆን ፤ የኤም ፔሳ አገልግሎትን እስከ መስከረም መጠናቀቂያ ድረስ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እቅድ መያዙንም ነዉ የተናገሩት።

በተጨማሪም እስከ ቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድረስ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደምበኞች 10 ሚሊዮን እንደሚደርስ ግምታቸዉን አስቀምጠዋል። ብስራት ራዲዮ በቅርቡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሶስት ሚሊዮን የደምበኞች ቁጥር ላይ መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል።

የፋይናንስ ኦፊሰሩ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር የሞባይል ገንዘብ ዝዉዉር በኩል ቴክኖሎጂዉን ለህዝቡ በማሳወቅ እያደረገ ያለዉ አስተዋጽኦ እና እየታየ ያለዉ መነቃቃት ፤ ኤም ፔሳ ወደ ሀገር ዉሰጥ ሲገባ ስራዉን እንደሚያቀልለት ተናግረዋል።


#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍2
አስራ ሦስት ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ኔትዎርክ ይዘረጋል ተባለ

በኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት አስራ ሦስት ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ኔትዎርክ ይዘረጋል ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻም ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ2016 ዕቅድ አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ የተያዘው ዕቅድ፣ ተቋሙ ቀድሞ የነበረውን 78 ሚሊዮን ደንበኛ ወደ 92 ሚሊዮን ማድረስ ይስችላል ያሉ ሲሆን፤ በዚህም በቀጣይ ዓመት 8 ነጥብ 3 በመቶ የደንበኛ ዕድገት ይመዘገባል ብለዋል።

እንዲሁም 998 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች (ታወር) ይገነባሉ ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ እነዚህም በ140 የገጠር ከተሞች የሚገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍1
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ለአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ አዲስ ተቋራጭ ጨረታ ሊወጣ ነው

👉በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል!

ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመት እንደገና ለማስጀመር በጀት መያዙን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።

በቅርቡም ሥራ ተቋራጭ ለመምረጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ የሚወጣ መሆኑ ተመልክቷል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በ48 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና 62ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ለማስቀጠል በ2016 ዓ.ም በጀት የተያዘለት በመሆኑ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ግንባታው ይጀመራል።

የብሔራዊ ስታዲየሙ ግንባታ በቻይናው ኩባንያ ይካሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ግንባታው በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን ገልፀዋል።

በኋላም የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው ያቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ከገበያ በላይ የተጋነነ በመሆኑ መንግሥት ከያዘው በጀት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም። በዚህም ከግንባታ ተቋራጩ ጋር ያለው ውል እንዲቋረጥ መደረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ተቋራጩ ኮቪድ-19ን እንደ ምክንያት በማድረግ ስራውን አቀርጦ በመቆየቱ ግንባታውን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ እንደነበር የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው አስታውሰዋል።

የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው አሳማኝ ያልሆነና ከገበያ በላይ የሆነ የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ መጠየቁን አውስተው፤ የተጠየቀው የዋጋ ማስተካከያ የተጋነነ በመሆኑ ብዙ ድርድር በማድረግ ውል ከማቋረጥ ጋር ተያይዞ ችግሮች እንዳያጋጥሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል።

በዚህም ከተቋራጩ ጋር የነበረው ውል በዚህ ዓመት በመጋቢት ወር 2015ዓ.ም መቋረጡን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ግንባታውን የጎበኙ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች አስተያየትም ሥራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መከናወኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ስታዲየሙ በውስጡ በርካታ ነገሮችን የያዘ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመው፤ የበጀት እጥረት ችግር ካላጋጠመ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

የስታዲየሙን ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ለማስቀጠል ምን ያህል በጀት እንደተያዘ ይፋ አልሆነም።
የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር በጀት ታህሳስ 2008 ዓ.ም እንደተጀመረ የሚታወስ ሲሆን ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በ5 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር በጀት መጋቢት 2012 ዓ.ም ተጀምሮ በዘጠኝ መቶ ቀናት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከ2016 ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልጿል።

በባለስልጣኑ የከፍተኛ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ክትትል እና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው አድነው ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደተናገሩት፥ የመማር ማስተማር ስራው ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን አዲስ መመሪያ እና መስፈርት ተዘጋጅቷል።

የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የሚጠበቀውን ደረጃ እና ጥራት ማስጠበቅ ያስችላል የተባለው አዲስ መመሪያ እና መስፈርትም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።

በመመሪያው የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ በርካታ መለኪያዎች የተቀመጡ ሲሆን፥ አንዱ የመውጫ ፈተናን የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም እያንዳንዱ ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው በማንሳት ይህ ካልሆነ ግን የትምህርት ፕሮግራሙ ይሰረዛል ብለዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት 50 እና ከዛ በላይ ያመጡት 12 ሺህ 422 ወይም 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወቃል።

@Yenetube @FikerAssefa
1
የፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የልብ አድናቂ እንደሆነ የሚናገረው አሜሪካዊ እውቅ ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ ከባድ የራስ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል መግባቱ ተገልጿል።

የ 18ዓመቱ ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ ባጋጠመው ከባድ የራስ ህመም ምክንያት የቀዶ ጥገና ሊደረግልት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቤተሰቦቹ ከአሜሪካ ወደ ቶክዮ በማምራት ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

አይ ሾው ስፒድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ በለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስልም " ከባድ በሆነ የራስ ህመም እየተሰቃየሁ ነው አይኔን መግለጥ አልቻልኩም ፣ መመገብም አልችልም።"ሲል ተናግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665