YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት በመዲናዋ በሕገ ወጥ መንገድ የተወረረ ከ2 ሚሊየን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ለመንግሥት መሬት ባንክ ገቢ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

የመሬት ወረራን ጨምሮ በተለያዩ ደንብ ጥሰቶች ላይ በወሰደው ርምጃ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ ማድረጉንም ገልጿል።

የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለኢዜአ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ 11ዱም ክፍለ ከተሞች የደንብ ጥሰቶችን በፈጸሙ አካላት ጠንካራ እርምጃ ተወስዷል።

በተለይም በመሬት ወረራ፣ ሕገ-ወጥ ግንባታ፣ የጎዳና ላይ ንግድ፣ ሕገ-ወጥ ዕርድን ጨምሮ በርካታ የደንብ ጥሰቶች በፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ340 ሺሕ በላይ ደንብ ጥሰቶች መከታተሉን ገልጸው በተለይም በሕገ ወጥ መንገድ የተወረረ ከ2 ሚሊየን 100 ሺሕ በላይ ካሬ ሜትር መሬትን ለመንግሥት መሬት ባንክ ገቢ ማድረጉን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ዛሬ ወደ አሥመራ እንደተጓዙ ቤተ መንግሥታቸው አስታውቋል።

ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ወደ አሥመራ የተጓዙት፣ በኤርትራ የሥራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት ነው። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ በአሥመራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይነጋገራሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሥልጣን በያዙ ማግስት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመን ወደ ኤርትራ ለሥልጠና የተላኩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱማሊያዊያን ምልምል ወታደሮችን ወደ አገራቸው መመለስ ቀዳሚ ተግባራቸው እንደሚሆን መግለጣቸው ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
👍1
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ

እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።

እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883

https://tttttt.me/meritibe

👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
#ከማን_ጋር_ነህ?
#የስኬት_ቀመር መጽሐፍ 4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደዛሬው ነህ’ ይላል፡፡” አለና በክላንድ ለረጅም ጊዜ እንግዳውን አፍጥጦ ተመለከተ፡፡

ፀጥታውን ለመስበር ይህ አዲሱ አስተዋይ ተማሪ “የትኞቹ ሁለት ነገሮች?” ሲል ጠየቀ፡፡

በክላንድ በፈገግታ ጠረጴዛው ላይ ወዳለው መጽሀፍ እየጠቆመ “ሁለቱ ነገሮችማ የምታገኛቸው ሰዎችና የምታነባቸው መጻህፍት ናቸው፡፡ አስበው እኛ ያለን እውቀትና አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች ድምር ውጤት ነን፡፡ ከጋዜጣ በስተቀር ምንም ነገር የማታነብ ከሆነ፣ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡ የምታነበው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ታሪክና መንፈስን የሚቀሰቅሱ መፃህፍትን ከሆነ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡” አለ፡፡

“እሺ ገባኝ፡፡ ‘የምናገኛቸው ሰዎች’ የሚለውም ነገር እውነት እንደሆነ አስባለሁ፡፡” አለ ግሬግ፡፡

“ትክክል ነህ፡፡ ቻርሊ ሁልጊዜ ‘በተመራማሪዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ ተመራማሪ ትሆናለህ፡፡ በአሸናፊዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አሸናፊ ትሆናለህ፡፡ በሚያማርሩና ችክ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አማራሪና ችክ ያልክ ትሆናለህ’ ይላል፡፡” ሲል ነገረው፡፡

ከመቶ ሚሊየን ኮፒ በላይ በተሸጠው ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች #አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ ላይ የተመሰረተ የናፖሊዮን ሂል ድንቅ ስራ። #የህይወት_መመሪያ በተሰኘው መጽሐፍ የምናውቃት ሀኒም_ኤልያስ ተርጉማዋለች፡፡

ለመሆኑ መቶ አመታትን ያስቆጠረው እና #አሁንም_ድረስ_የሚሰራው ይህ የስኬት ቀመር ምን ይሆን?

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ከ 200 ብር ጀምሮ ጥራት ያላችውን የሆቴል ክፍሎችን ባሉበት ቦታ ሆነው ይያዙ።

ከ 300+ በላይ ጥራት ያላቸውን ሆቴሎች፤ ገስታውሶች እና ፔንሲዮኖችን በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች በቀላሉ Room.et ዌብሳይት | መተግበሪያ | 9883 ላይ በመደወል መያዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

Room.et ተጠቅመው ሲይዙ፡
- ከ200 ብር ጀምሮ የሆቴል ክፍሎች በጥራት ፤ በዋጋ፤ ርቀት እና አገልግሎት አይነት አነጻጽረው መያዝ ያስችላል።
- በካሽ፤ በቴሌብር እና አሞሌ ይክፈሉ
- ሳይንገላቱ ባሉበት ሆነው አቅራቢያ ያለ ሆቴል መያዝ ያስችላል።

Download Room.et 👇
https://bit.ly/3P5seGC

ትክክለኛውን የሩም ማዕበራዊ ገፆች ይከታተሉ።
Telegram : https://bit.ly/3P9SgZj
Tiktok : https://bit.ly/3PdbME3
Instagram : https://bit.ly/3yNt7ON
.
.
ለሆቴል ፍላጎትዎ
Room.et
🎁 #ArtLand_gifts 🎁 Best Gifts


✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት(MDF) እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን

"እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በፖስታ ቤት እንልካለን 📦✉️

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
@artlandengraving
@artlandengraving
ፌዴራል ፖሊስ “በተለያዩ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ሰዎች በ991 ወይም 987 ላይ መረጃ መስጠት ይችላሉ” አለ!

በተለያዩ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ሰዎች በ991 ወይም 987 ላይ ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም ለህግ አስከባሪ አካላት መረጃ መስጠት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የማህበራዊ እና የኦንላይን ሚዲያዎችን በመጠቀም የበርካታ ሰዎችን ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አድራሻቸውን በማጥፋት የተሰወሩ አካላት መኖራቸውን ከደረሰ ጥቆማና ከተለያዩ ምንጮች መረዳት መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ገልፀዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልከቶ ከተለያዩ የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር መረጃ የማጣራት እና የምርመራ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልፀዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ አስተዳደር አምና ወደ ፈንዱ ፈሰስ ያልተደረገ 2.2 ቢሊዮን ብር የጡረታ መዋጮ መኖሩን እንዳረጋገጠ ሪፖርተር ዘግቧል። የፈንዱ አስተዳደር ይህን ያረጋገጠው፣ በ3 ሺህ 106 መስሪያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ምርመራ ነው። ፈንዱ ከአንዳንድ መስሪያ ቤቶች ጋር ባደረገው ንግግር 995 ሚሊዮን የጡረታ መዋጮ ብር ያስመለሰ ሲሆን፣ ጡረታ መዋጮውን ገቢ እንዲያደርጉ ተነግሯቸው ባላስገቡ መስሪያ ቤቶች ላይ ደሞ ክስ መመስረቱን ተናግሯል።የፈንዱ አስተዳደር ዘንድሮ በተሻሻለው አዋጅ የጡረታ መዋጮን ኢንቨስትመንት ላይ በማዋል ትርፍ የማግኘት ሥልጣን ተሰጥቶታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በኤርትራ የሰለጠኑ ወታደሮቻቸውን ጎበኙ!

በአስመራ ጉብኝት ላይ ያሉት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ኤርትራ ያሰለጠነቻቸውን ወታደሮች መጎብኘታቸውን የኤርትራ መንግስት ገለጸ።ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ ትናንት በኤርትራ በስልጠናላይ የነበሩ የሀገራቸውን ወታደሮች መጎብኘታቸውን የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ አቶ የማነ ገብረመስቀል ይፋ ባደረጉት መረጃ መሰረት የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አባላት ላለፉት ሶስት ዓመታት በኤርትራ ስልጠና ላይ ነበሩ።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱ በተፈጠረው ጭጋጋማ አየር ሁኔታ ሳቢያ ከአዲስ አበባ በሚነሱና በሚያርፉ በረራዎች ላይ መዘግየት መፈጠሩን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በተፈጠረው ጭጋጋማ አየር ሁኔታ ሳቢያ ከአዲስ አበባ በሚነሱና አዲስ አበባ በሚያርፉ በረራዎች ላይ መዘግየት መፈጠሩን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ለተፈጠረው የበረራ መዘግየትና መስተጓጎል ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፤ ደንበኞቹም አየር መንገዱ ስለኹኔታው የሚያቀርበውን መረጃ እንዲከታተሉ ጠይቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፋሲል ከነማ በዲሲፕሊን መመሪያ ጥሰት የ100 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለበት!

ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ባደረገው የመጨረሻ ጨዋታ በስፖርታዊ ጨዋነት ምክንያት የመቶ ሺህ ብር (100,000 ብር) ቅጣት በሊጉ ተወሰኖበታል።ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የመጨረሻ እና 30ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠታቸው ሪፖርት ቀርቦበታል።

የዋንጫ ባለቤት እንዲሁም ወራጅ ቡድኖች በተለዩበት የእኩል ሰዓት ጨዋታ ፋሲል ከነማ 2 ለባዶ በድሬዳዋ ከነማ ሲመራ ቢቆይም ከ68ተኛው ደቂቃ በኋላ ሶስት ጎል በማስተናገድ ጨዋታው 3 ለ2 ተጠናቆ ድሬዳዋ ከነማ ከወራጅ ቀጠና እንዲወጣ ሆኗል።

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከዚህ በተጨማሪም ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ሃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አስጣጥ ስነስርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው በድኑ ሪፖርት ቀርቦበት የ100 ሺህ ብር ቅጣቱ ተጥሎበታል። እንዲሁም ፋሲል ከነማ በሜዳዉ የሚያደርጋቸውን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ያለደጋፊ እንዲጫወቱ ተወስኗል።

በሌላ በኩል የድሬዳዋ ከነማ ከባህር ዳር ከተማ ባደረገው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች እና አመራሮች አፀያፊ ቃላት ተናግረዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የ75 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።የፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከነማ ጨዋታን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከነማ እንዲሁም በእግር ኳስ ተከታታዮች ዘንድ በሙሉ አቅም ያለመጫወት እና ጎል የመልቀቅ ቅሬታ መሰማቱ የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የቡና ምርት 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጹ።

ይህ ገቢ የተገኘው ወደ ውጭ ከተላከው 300 ሺህ ቶን የቡና ምርት መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ዓመት የተገኘው ገቢ በዓመት በአማካይ ይገኝ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ግብ እንዲሳካ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና ለስኮላር ሽፕ ዝግጅት ፈላጊዎች
+251921-309530

ለHigh School | Collage | University ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ

IELTS | TOFEl | SAT | GRE ማስተማር ጀምረናል።

ወደ #አሜሪካ#ካናዳ#እንግሊዝ#አውስትራልያ#አውሮፓ#ቻይና
ወቅቱ የስኮላርሽ ጊዜ ስለሆነ ተማሪዎች ይህንን አጋጣሚ ይጠቀሙ።

ወደ መደበኛ ትምህርታችሁ ከመመለሳችሁ በፊት ጊዚያችሁን ተጠቀሙበት

የክረምት ክላስ

ENGLISH. FRENCH. CHINESE. GERMAN. AFAN OROMO

አድራሻ

Mexico:+251919913021/23
Hayahullet:+251919913023/24

Admission Open Now

Get free PDFs, Audio and different references from our Channel
JOIN US
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ቦሪስ ጆንሰን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ከለቀቁ በኋላ ሚሊየነር ሊሆኑ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች

ጆንሰን ስልጣን ላይ ሳሉ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ሳይጨምር 164 ሺ ፓውንድ ነበር አመታዊ ደሞዛቸው
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡
ጆንሰን ስልጣን የሚለቁት የካቢኔ አባሎቻቸው ጭምር ስልጣናቸውን በመለቀቅ ባሳደሩባቸው ጫና ነው፡፡ እርሳቸውን ለመተካትም የካቢኔ አባላቶቻቸውን ጨምሮ 11 ገደማ ፖለቲከኞች በእጩነት መቅረባቸው ተነግሯል፡፡
የቀድሞው ጋዜጠኛ ስልጣን መልቀቅ ግድ ቢሆንባቸውም ሚሊየነር ሆነው የሚለቁበት አጋጣሚ እንዳለ ነው የሚነገረው፡፡
ጆንሰን ስልጣን ላይ ሳሉ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ሳይጨምር 164 ሺ ፓውንድ ነበር አመታዊ ደሞዛቸው፡፡ ይህ ከከፍተኛ ተከፋይ የዓለማችን መሪዎች ተርታ ያሰለፋቸዋል፡፡ ሆኖም አሁን ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ ሊያገኙ የሚችሉት በሚሊየኖች የሚቆጠር ገቢ ይህን የሚያስንቅ እንደሚሆን ነው የሚጠበቀው፡፡

ስልጣናቸውን በይፋ ከለቀቁ በኋላ ሊጻፍ እንደሚችል ከሚጠበቀው የማስታወሻ መጽሃፋቸው፣ ሊያደርጓቸው ከሚችሉ ንግግሮች እና በተጋባዥነት ሊቀርቡ ከሚችሉባቸው የቴሌቪዥንና ሌሎች የብዙሃን መገናኛ ፕሮግራሞች በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብን ሊያጋብሱ እንደሚችሉ ነው የሚጠበቀው፡፡

ልክ ቀደም ሲል ሲያደርጉት እንደነበረው ሁሉ አምደኛ ሆነው ሊጽፉ ከሚችሉባቸው ስመ ጥር ጋዜጦች የተሻለ ክፍያን ሊያገኙ እንደሚችሉም ይጠበቃል፡፡

ከ1990ዎቹ አጋማሽ ወዲህ ብሪታኒያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ፖለቲከኞች እያንዳንዳቸው በእንዲህ ዐይነት መንገድ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ሚሊየኖችን አጋብሰዋል፡፡ ነገር ግን ጆንሰን ከቀድሞው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ካገኙት 100 መሊዮን ፓውንድ የበለጠ ገንዘብን ሊያገኙ እንደሚችሉ ነው እየተጠበቀ ያለው፡፡

ቀለል ያሉና ተጫዋች እንዲሁም ጥሩ ጸሃፊ እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ቦሪስ ጆንሰን ጋር ስምምነትን ለማድረግ ኔትፍሊክስ የተባለውን ታዋቂ የአሜሪካ የፊልም ኩባንያ ጨምሮ ሌሎች እየተፎካከረሩ እንደመገኙም ተነግሯል፡፡

ለሶስት ዓመታት የዘለቀውን የጆንሰንን የስልጣን ዘመን ማስታወሻ ለመጻፍም ተቋማት በመሽቀዳደም ላይ ናቸው፡፡ ይህ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ካገኙት 800 ሺ ፓውንድ የተሻለ ክፍያን እንደሚያስገኝላቸው ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ጆንሰን፤ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራካ ሁሴን ኦባማ ሁለት ማስታወሻዎቻቸው ሲጻፉ ካገኙት 65 ሚሊዮን ዶላር የበለጠ ሊያገኙ አይችሉም ተብሏል፡፡

የዴይሊ ቴሌግራፍ አምደኛ የነበሩት የቀድሞው የለንደን ከንቲባ ጸሃፊና ደራሲ ቦሪስ ጆንሰን በሳምንት ለሚጽፉት አንድ መጣጥፍ (አርቲክል) 275 ሺ ፓውንድ ይከፈላቸው ነበር፡፡ አሁን ግን ሊኖራቸው ከሚችለው መረጃ እና ታዋቂነት አንጻር ከዚህ በእጅጉ የተሻለ ክፍያን እንደሚያገኙ የሚጠበቅ ነው፡፡

አዋዝቶ መናገር የሚችሉበትን ርትዑ አንደበት መታደላቸውም የቀድሞዋ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ካደረጓቸው ንግግሮች ካገኙት 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ፓውንድ የበለጠ ገቢን እንደሚያስገኝላቸውም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት በአንድ መድረክ ንግግር ለማድረግ እስከ 450 ሺ ፓውንድ የሚደርስ ክፍያን ተቀብለዋል፡፡ አሁንም በብሪታኒያ ንግግር ለማድረግ የሚጋበዝ አንድ ታዋቂ ሰው ከ150 ሺ ፓውንድ በላይ ያገኛል፡፡

በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ጆንሰን ከስልጣን መልቀቅ በኋላ ሚሊየነር እንደሚሆኑ ነው የዘ ናሽናል ዘገባ የሚያትተው፡፡

Via :- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታዉቋል፡፡

አየር መንገዱ ለጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱን ጠቁሟል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች በአብዛኛው መጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ነገ ፍርድ ቤት እንደቀርቡ ቀጠሮ ተይዟል።

ባሳለፍነው ሳምንት በነበረ የችሎት ቀጠሮ አቶ ሀይለማርያም በማንኛውም ሰዓት ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ተወካያቸው ወይም የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ከ48 ሰዓት በፊት ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቁ እና ምስክርነታቸው እንዲሰማ መታዘዙ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ተወካያቸው ዛሬ ቀርቦ ወደ ኢትዮጳያ መምጣታቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሪፖርት አድርጓል።

ፍርድ ቤቱም በነገው ቀጠሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአካል ቀርበው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት በመርከብ ግዢና በእርሻ መሳሪያ ግዢ ጉዳይ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ቀጠሮ ይዟል።

በዚህ ቀጠሮ መሰረት አቶ ሀይለማርያም ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይታሰባል።

Via Tarik Adugna
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደተቀሰቀሰ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በግጭቱ የሰው ሕይወት እንደጠፋና ንብረቶች እንደወደሙ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአጣዬ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ነው። ወደ ገጠር ቀበሌዎች ገብቶ ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል።

Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደተቀሰቀሰ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በግጭቱ የሰው ሕይወት እንደጠፋና ንብረቶች እንደወደሙ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአጣዬ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ነው። ወደ ገጠር ቀበሌዎች ገብቶ ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች…
በአማራ ክልል ሁለት አጎራባች ዞኖች መካከል በሚገኙ ቀበሌዎች የተቀሰቀሰው ውጊያ እስካሁን አልቆመም

ውጊያው በጅሌ ጥሙጋ እና ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ያጋጠመ ነው
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቀበሌዎች ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

ግጭቱ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጤ ቀበሌን እና በኤፍራታና ግድም ወረዳ አርሶ አምባ (ዘምቦ) ቀበሌን በሚያጎራብቱ አጎራባች አካባቢዎች (ጎጦች) ያጋጠመ ነው፡፡
ቀበሌዎቹ ከአዲስ አበባ ደሴ በሚያልፈው አውራ የአስፓልት መንገድ ላይ በሰንበቴ እና ጀውሃ ከተሞች መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡
ከትናንት ምሽት ጀምሮ በአጎራባች የቀበሌዎቹ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ለአል ዐይን አማርኛ የተናገሩ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም የማያቋርጥ የጥይት ድምፅ እየሰሙ መሆኑን ገልፀዋል።
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የኤፍሬታ ግድም ወረዳ ነዋሪ ከትናንት ረፋድ ጀምሮ በሁለቱ ቀበሌዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ገልጸው፤ በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡

ግጭቱ አካባቢ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አህመድ የተረጋጋ ሁኔታ እንደሌለ በመጠቆም የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ለመግባትና ሁኔታዎችን ለማረጋጋት፤ ወደ ግጭቱ የሚገቡ ሰዎችንም ለማስቆም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ በበኩላቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ግጭት መቀስቀሱን ተናግረው ግጭቱ ሳይባባስ ለማስቆም ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል፡፡

ከሁለት ወራት በፊት በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ ተመሳሳይ ጥቃት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ያለች ሞላሌ የተባለች መንደር ሙሉ ለሙሉ መውደሟም የሚዘነጋ አይደለም፡፡

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa