YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበራቸው አካባቢ የተፈጠረውን ውዝግብ በውይይት እንዲፈቱ አሳሰቡ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ሁለቱም ሀገራት ከወታደራዊ እርምጃ እንዲታቀቡ ማሰሰባቸውን ከኅብረቱ ቲውተር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ሀገራት የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ውይይትን እንዲያስቀድሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ውዝግቡ እየተከሰቱ ያሉ የውስጥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ማደናቀፍ እንደሌለበትም ጠቁመዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በበኩሉ በሀገራቱ መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ ውጥረት እንዲረግብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ጥሪ አቅርቧል።የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሀገራቱ የረጅም ጊዜ የመንድማማችነት ታሪክ እንዳላቸው አንስተው ውጥረቱን የበለጠ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡በጉዳዩ ዙሪያ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን እንዲከተሉ በአጽንኦት ጠይቀዋል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የት እንዳለ አለማወቁን አሳወቀ።

ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሠዱን ከጎረቤቶቹ በደረሰው መረጃ ማወቁን ለአሻም ነግሯታል።የኢትዮ ፎረም የዩቱብ ጣቢያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ሰኔ 21 ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሰዱን ጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ከአሻም ጋር በነበራቸው ቆይታ አረጋግጠው ነበር፡፡

ኮሚሽኑ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ማንነታቸው በማይታወቅ ግለሰቦች መወሰዱን መረጃ ቢኖረውም የት እንዳለ አለማወቁን ጠቅሶ ጉዳዩን እየተከታተለው እንደሆነ በኮሚሽኑ የህግና ፖሊሲ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ከሪፖርተራችን ፍቃዱ በላይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ ተናግረዋል።ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ባለፈው ሳምንት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሰጠው የዋስትና መብት ከስር መፈታቱ ይታወሳል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳኑ መሪ አልቡርሃን ከኢትዮጵያ ጋር “ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን” አሉ!

ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ሱዳን ከጎረቤቷ ጋር ሰላማዊና ሚዛናዊ ግንኙነት እንድኖራት እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡የሀገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ከኢትዮጶያ ጋር ጤናማ ግንኙነት እንድኖር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ አል ቡርሃን ይህንን ያሉት ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በካርቱም በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

የአውሮፓ ሕብረት፤ በአዲስ አበባ እና ካርቱም መካከል ያለውን አለመግባባት ለማርገብ ጥረት እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ሰሞኑን ካርቱም ገብተው ከአል ቡርሃን ጋር ተወያጥተዋል፡፡

ካርቱም ከሰሞኑ ሰባት ወታደሮቿ በኢትዮጵያ እንደተገደሉባት ብትገልጽም አሁን ግን ጉርብትናው ጤናማ እንድሆን ፍላጎት እንዳላት መሪዋ አስታውቀዋል፡፡ ነገርግን የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባቱን እና የፈጸመውን ትንኮሳ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ህይወት ማለፉን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/sudan-says-wants-amicable-relation-with-ethiopia-following-border-skrimish

@YeneTube @FikerAssefa
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ እና የሙዚቃ ሽልማት መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ የተለያዩ ተዋቂ ግለስቦች ፣አርቲስቶች እና የክብር እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።የሀጫሉ ፋውንዴሽን በሀጫሉ አዋርድ አርቲስቶችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑን የገለፁት የአርቲስት ሀጫሉ ባለቤት ፋንቱ ደምሰው የተረሱ አርቲስቶችም እንደሚበረታቱ ገልጸዋል።ፋውንዴሽኑ ሀጫሉ የጀመራችውን ስራዎች እና ያለማችውን ስራዎች ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑንም አንስተዋል።አርቲስት ሀጫሉ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ዛሬ ሁለት አመት አስቆጥሯል።

[Walta]
@yeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ችግራቸውን በወንድማማችነት እና ጉርብትና መንፈስ ለመፍታት አቅሙ አላቸው ሲሉ ዛሬ በግል ፌስቡክ ገጻቸው በዓረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል። ዐቢይ የመንግሥት ዜና አውታሮች በአማርኛ በተረጎሙት በዚሁ መልዕክታቸው፣ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግጭት የሚፈልጉ ሌሎች መንግሥታት አሉ ሲሉ እንደገለጹ እና ሆኖም ግን ሁለቱ አገሮች ከግጭት ሊቆጠቡ እንደሚገባ ማውሳታቸው ተገልጣል። በሁለቱ አገሮች የጋራ ድንበር ላይ ሰሞኑን እንደገና ስላገረሸው ወታደራዊ ውጥረት ዐቢይ አስተያየት ይስጡ አይስጡ የአማርኛ ዘገባዎች አላመለከቱም።

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት በቀጣይ ጦርነት ለማድረግ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ!

በመንግስት በሽብር የሚፈለገውና ትግራይን እያስተዳደረ ያለው ህወሃት ለቀጣይ ጦርነት ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡የቡድኑ ታጣቂዎች አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙኃን 90 ደቂቃዎችን የፈጀ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የቀድሞው የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን እና የአሁኑ የህወሃት ታጣቂዎች አዛዥ አሁን የተዘጋጀው ጦር “የፈለግነውን ነገር መፈጸም የሚችል ነው” ሲሉም ነው ለመገናኛ ብዙሃኑ የገለጹት፡፡

“አሁን ጊዜ አግኝተን ሰርተንበታል” ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ “ሁሉንም ዝግጅታችንን ጨርሰናል” ብለዋል፡፡በቀጣይ የሚደረጉት ጦርነቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት የገዘፉ እንደሚሆኑ ያነሱት ታደሰ “ከትግላችን መጨረሻ የሚያደርሱን ናቸው” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።በማህበራዊ ሚዲያ ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ ጦር ጋር “ይህን ያህል ሞተ ገደልን፤ ገለመሌ የሚባለው ውሸት ነው፤ እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ አንድ ነገር ነው፤ዝግጅታችንን ጨርሰናል” ሲሉም ነው በመግለጫቸው የተናገሩት።

ከተለያየ ወገን “ለምን አታጠቁም? ለምን አትጀምሩም?" የሚሉ ጥያቄዎችንና ጉትጎታዎች እንዳሉ ያነሱት የህወሃት አዛዡ “መቼ እንጀምር? እንዴትና የት? የሚለውን ወታደራዊ ስራ ነው” ም ብለዋል፡፡ህወሃት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ከፍተኛ የተተኳሽ እጥረት እንደነበረበትና የኢትዮጵያ ሰራዊት በፈለገው ሰዓት ሲያጠቃው እንደነበር የገለጹት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ጎሬሮ በሚባልና የኢትዮጵያ ጦር በማያውቀው ስፍራ ተተኳሽ ቀብሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ህወሃት ተተኳሾቹን ካገኘ በኋላ ውስን ቦታዎች እንደሚይዝ እንጂ ብዙ ድል አስመዘግባለሁ ብሎ እንዳልነበረም ነው ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የገለጹት፡፡

የህወሃት ታጣቂዎች ከተንቤን የወጡት ውስን ተራራዎቸን ለማስለቀቅ እንደነበር የገለጹት አዛዡ፤ የትግራይ ሕዝብ “ያለስንቅ የወጣውን የትግራይ ታጣቂ መቀለቡን፤ መሣሪያ መሸከሙንና የተቀበረ መሳሪያ መደበቁን አንስተዋል፡፡የህወሃት ታጣቂዎች፤ የኢትዮጵያን ጦር ማስወጣትና መበተን ላይ ሲያተኩሩ “ሌላውን የመደምሰስ ስራ የሰራው ህዝቡ ነው” ያሉ ሲሆን “የኢትዮጵያን ጦር ያሸነፍነው በእልህ በተሞላው አመራራችንና በህዝቡ ነው” ብለዋል ሌ/ጄ ታደሰ፡፡የኤርትራ ጦር ጥፋት እንደፈጸመና ይህንን ግን እንዳልጠበቁ ያነሱት አዛዡ ቀጣይ የማይቀሩ ጦርነቶች እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

አዛዡ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት፤ በሽብር ከፈረጀው ህወሃት ጋር ለመደራደር ከወሰነና ተደራዳሪዎችን ካሳወቀ በኋላ ነው፡፡በመንግስት የተሰየመው ተደራዳሪ ቡድን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን የፍትህ እና የደህንነት ኃላፊዎች ተካተውበታል፡፡ገዥው ፓርቲ ከህወሃት ጋር ያለው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ስምምነት ላይ መደረሱን የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል፡፡የኢትዮጵያ ዐቃቤ ሕግ የህወሃትን ታጣቂዎች የሚመሩትን ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደንና ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሣኤን ጨምሮ በ 74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱ አይዘነጋም፡፡

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የሁርሶ ኮንቲንጀነት ማሰልጠኛ የሰላም አስከባሪ አባላትን እያስመረቀ ነው!

የሁርሶ የኮንቲንጀነት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የሰላም አስከባሪ አባላት እያስመረቀ ይገኛል፡፡በአፍሪካ ኅብረት ስር በሶማሊያ የሚሰማሩት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በተባበሩት መንግሥታት ህግና በተለያዩ ወታደራዊ ሙያዎች የሰለጠኑ ሦስት ሴክተሮች መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው ያመላክታል።

በሶማሊያ ተሰማርቶ የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል በሀገሪቱ እየታየ የመጣውን የሰላም መሻሻል ተከትሎ መጠሪያውን ከአሚሶም (AMISOM) ወደ አትሚስ (ATMIS) African union transition mission in Somalia ከለወጠ በኋላ በትምህርት ቤቱ ተመርቀው ወደ ግዳጅ የሚሰማሩ የመጀመሪያ የሰላም አስከባሪዎች ናቸው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በንጹሃን ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ዙሪያ በዝግ መምከሩን ሰምቻለሁ ሲል ሸገር ዘግቧል።

በስብሰባው የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካዔል የምክር ቤቱ አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ምክር ቤቱ በጭፍጨፋው ላይ እንዲመክር ወይም ጠቅላይ ሚንስትሩ ወይም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ማብራሪያ እንዲሰጡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ጠይቀው ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በተመሳሳይ ዜና፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ የምክር ቤት አባላቱ በወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነውመረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በእለቱ በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ከተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከልም፡-

የሰላምና የደህንነት ሁኔታዎችን በተመለከተ፤- በሃገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶችን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ህግን የማስከበር የተቀናጀ እርምጃን በሁሉም አካባቢዎች አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በእነዚህ እርምጃዎች የመንግስት የፀጥታ አካላት የሽብር ብድኖችን አባላት በመደምሰስና በማደን ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በተመለከተ ፡- በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ ልዩ ልዩ አሻጥር በመፍጠር ዜጎች እንዲማረሩ እያደረጉ ያሉ ስግብስግ ግለሰቦች፣ ከእኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰቷል፡፡

የሰሜኑን ጦርነት በተመለከተ ፤- የኢትዮጲያ መንግስት ለሰላም መንገድ ሲከፍት ከነሙሉ ብቃቱና ፍላጎት ነው፣ ነገር ግን ይህንን እድል መጠቀም ያለመጠቀም የሌላኛው ወገን ውሳኔ ይሆናል፡፡

የእርዳታ አቅርቦቱን በተመለከተ ፤- በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ በተሳለጠ መልኩ እንዲዳረስ የኢትዮጵያ መንግስት እየሰራ ነው፡፡ የተለያዩ አካባቢዎች በህወሃት ቢያዙም ሰብአዊ ድጋፍ ያለማቋረጥ ቀጥሏል፡፡

የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ፤- የህዳሴ ግድቡ በተያዘው የጊዜ ገደብ እንዳይሞላ የተለያዩ አጀንዳዎች ሲፈጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ይህ ግብግብ የመንግስትን አቅጣጫ ለመቀየርና ግድቡ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ የሚደረግ ጥረት ነው፤ ይህ እቅዳቸዉ ግን መቼም አይሳካም ብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን ባለስልጣኑ አስታወቀ!

ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በተለይ አዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል።

ይህም በህገወጥ መንገድ የነዳጅ ቦቴዎቹ በየመንደሩ ተደብቀው የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጠሩ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፋር፣ መተሃራ፣ በሞጆ፣ በአዳማና በተለያዩ ከተሞች ተደብቀው የተገኙት ቦቴዎች ዛሬ እስከ 10 ሰዓት ድረስ ነዳጁን በሚፈለገው ማደያ ማድረስ እንዳለባቸው ለባለቤቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ እንደሚወስድ ጠቁመው ይህንን ቁጥጥር የሚመራ ግብረሃይል ተቋሟል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ!

የባልደራስ ፓርቲ አመራር የሆነው ስንታየሁ ቸኮል እና ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የአራቱን ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በጊዜ ቀጠሮ የተመለከተ ሲሆን በክርክሩ ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ ተጠርጣሪዎች በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ አዟል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ! የባልደራስ ፓርቲ አመራር የሆነው ስንታየሁ ቸኮል እና ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የአራቱን ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በጊዜ ቀጠሮ የተመለከተ…
#update

ስንታየሁ ቸኮል በፌደራል ፖሊሶች መያዙ ተሰማ!

ከሰዓታት በፊት በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ የተወሰነለት የባልደራስ ፓርቲ አመራሩ ስንታየሁ ቸኮል ከእስር ቢወጣም ማረሚያ ቤቱ በር ላይ የፌደራል ፖሊሶች እንደያዙት ፓርቲው አስታወቀ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ “እገታ” ነው ብሎ የገለፀው ተግባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች በፓትሮል ሆነው፣ ባህርዳር ሳባታሚት ማረሚያ በር ላይ በመጠበቅ እገታ ፈፅመውበታል ብሏል።

እንደፓርቲው ገለፃ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ከበባ ከፈፀሙበት በኋላ ወደ ፓትሮል መኪናቸው ለማስገባት ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ፈጥረዋል።በተጨማሪም አቶ ስንታየሁ ቸኮል ወደ ፓትሮሉ እንዲገባ ሲጠይቁት፣ ማንነታቸውን እንዲያስረዱት ቢጠይቅም ምላሽ ሳያገኝ “ከበው ሲያንገላቱት ታይቷል” ተብሏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የወባ እና የተቅማጥ በሽታ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት ይችላል ተባለ!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሁለት ወረዳዎች እና የተለያዩ ቀበሌዎች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የወባ እና የተቅማጥ በሽታ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ፣በቂ መጠለያ ባለመኖሩ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ጠቁመዋል።በተለይም የክረምት ወቅት በመሆኑ የውሃ ንጽህና ባለመኖሩ እና የመጸዳጃ ቤትች ግር በሰፊው እየተስተዋለ በመምጣቱ የተቅማጥ በሽታ ሊከሰት ይችላል ሲሉ አክለዋል።

እንዲሁም ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የወባ በሽታ ስጋት መኖሩን ኃላፊው አንስተዋል።በዞኑ የከፍ ችግር እንዳይከሰት የተለያዩ ክትባቶች እና
ለወባ በሽታ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ደግሞ የአጎበር ስርጭት እየተከናወነ ይገኛል።ወረርሽኙ ከተከሰተ የሚያሰጋ በመሆኑ አስፈላጊ ግብዓቶች እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ዶ/ር ኪዳት አየለ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በሚገኙ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መውሰዳቸው ተሰምቷል።

በወታደራዊ ርምጃ በርከት ያሉ የቡድኑ ታጣቂዎች ተገድለዋል ተብሏል። በምዕራብ ሸዋ ዞን የተገደሉት አምስት የቡድኑ ታጣቂዎች በሚዳ ቀኝ ወረዳ በተለይ ሃሮ ጎበ በተባለ ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ እና በሰላማዊ ሰዎች ለይ ጥቃት ሲሰነዝሩ የቆዩ እንደሆኑ ታውቋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ሀሙማ ገንዶ ቀበሌ ሮብ ገብያ በተባለ ልዩ ቦታ ደሞ 13 ታጣቂዎች እንደተገደሉ ለመረዳት ተችሏል። የቡድኑ ታጣቂዎች በቅርቡ ከሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ በሕዝብ አውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ መንገደኞችን ማገታቸው ተዘግቦ ነበር።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ አውሮፕላን ማረፊያ እርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ የተደረገው በአውሮፕላን ማረፊያው ነዳጅ ባለመኖሩ የተነሳ እንደሆነ በመግለጽ አሸባሪው ህወሃት የሚያቀርበው ምክንያት ከእውነት የራቀ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ቢልለኔ ስዩም በዛሬው እለት በሀገሪቱ እየተከናወኑ ስለሚገኙ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫቸውም አሸባሪው ህወሃት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ እና የአውሮፕላን ማረፊያው የተዘጋው በአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት ምክኒያት ነው በማለት የሚያናፍሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል።

በመቐለ አውሮፕላን ማረፊያ ምንም አይነት የነዳጅ ሙሌት እንደማይከናወን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።በትግራይ የእርዳታ ስራ ሲያከናውኑ ከነበሩ የእርዳታ ተቋማት መረጃን የማሰባሰብ ስራ ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ፕሬስ ሴክሬተሪዋ፤ እንደ የእርዳታ ተቋማቱ ማብራሪያ አውሮፕላኖቹ የእርዳታ ቁሳቁስ ጭነው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለደርሶ መልስ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት ከአዲስ አበባ መደረጉን አስረድተዋል።የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ሶስት አይነት አውሮፕላኖች ከየአለም ምግብ ፕሮግራ እና የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ወደ መቐለ የተሰማሩ ሲሆን ለአውሮፕላኖቹ አስፈላጊ የሆነ የነዳጅ ሙሌት ቀድሞ ተከናውኗል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
😁1
ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ

አለመግባባቶችን ሰበብ በማድረግ ጽንፈኛ ኃይሎች ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመቀናጀት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት ለማወክ እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ ባገኛቸው መረጃዎች አረጋግጧል።

በዛሬው ዕለት የተደረጁ ኃይሎች የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቢሮን መስታወት በመሰባበር መጠነኛ ጉዳት አድርሰዋል።ፖሊስ እነዚህን ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ይገልፃል።

ከዚህ በተጨማሪ ጽንፈኛ ኃይሎች ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር ተቀናጅተው የሀገራችንን ጸጥታ ለማደፍረስ የተለያዩ መሣሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየደረጉ እንደሆነ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ስለሆነም መላው የሀገራችን ሙስሊም ህብረተሰብ ይህንን ተገንዝቦ የሀገሩንና የሀይማኖቱን ሰላምና ደህንነት እንዳይደፈርስ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እያሳሰብን፣ ፖሊስ ከድርግታቸው በማይቆጠቡት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
@YeneTube @FikerAssefa
በማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር እጦት የትግራይ ግብርና ምርት ከ60 እስከ 70 በመቶ ሊቀንስ ይችላል ተባለ!

የኢትዮጵያ ክረምት ሲቃረብ በአገሪቱ ሰሜን ሲካሔድ የቆየው ጦርነት የተጫናቸው ገበሬዎች የእርሻ ሥራቸውን ጀምረዋል። የትግራይ ገበሬዎች ግን የሚያስፈልጓቸውን የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር የመሳሰሉ የግብርና ግብዓቶች ማግኘት አልቻሉም።

የትግራይ ገበሬዎች የሚያስፈልጋቸው 700 ሺሕ ኩንታል ማዳበርያ፣ 64 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር እና የተለያዩ ፀረ- ተባይ ኬሚካሎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በተጣለው እገዳ ሳቢያ አለመድረሱን የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል። በዚህ ምክንያት የክልሉ የግብርና ምርት ከ60 እስከ 70 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገብረ ስላሴ ተናግረዋል።

ለአራት ዓመታት ባረሱት ማሳቸው "ጥሩ ሥራ፤ ጥሩ ልማት" ላይ እንደነበሩ የሚናገሩት ገብረሚካኤል ወረስ የተባሉ ገበሬ "ዘንድሮ ለሥራችን የሚሆን ማዳበሪያም ይሁን ምርጥ ዘር አላገኘንም" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አቶ ገብረ ሚካኤል "ከዚህ በፊት ከሰኔ ወር በፊት አስቀድሞ ነበር የሚደርሰን። አሁን ምንም ነገር የለም" ሲሉ አክለዋል። በትግራይ በተጣለው ገደብ ምክንያት ለአርሶ አደሮች ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር እና ሌሎች ኬሚካሎች ማዳረስ አለመቻሉን የትግራይ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ይገልጻል።

በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገብረ ስላሴ ክልሉ የሚያስፈልገውን 700 ሺሕ ኩንታል ማዳበሪያ፣ 64 ሺሕ ኩንታል ምርጥ ዘር እንዳላገኘ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።ኃላፊው በግብዓቶች አለመኖር ምክንያት የክልሉ ምርት ከ60 እስከ 70 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በጊንቢው ጥቃት 338 ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ!

ከ13 ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ብዛት 338 መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።ባለፈው ሰኔ 11 ቀን 2014 በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በፈጸመው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ ተዘግቦ ነበር።

በዚህ በአገሪቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከተፈጸሙ ማንነት ተኮር ጥቃቶች መካከል የከፋው እንደሆነ በተነገረለት ጥቃት የተገደሉት ሰዎች አሃዝን የተለያዩ ወገኖች በተለያየ መጠን ሲገልጹት ቆይተዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ትናንት ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2014 ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች 338 መሆኑን ገልጸዋል።

ጨምረውም በጥቃቱ ዙሪያ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አመልክተው፣ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጥቃቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የቀረበውን ጥያቄ “ኢትዮጵያ ምርመራ ለማድረግ አቅም ያለው ተቋም የሌላት ያስመስላል” በማለት መንግሥት እንዳልተቀበለው ተናግረዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ተቋም ባሻገር፣ በአገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ቅዳሜ፣ ሰኔ 11፣ 2014 በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙት ጉቱ፣ ጨቆርሳ፣ ስልሳው፣ በገኔ፣ ጫካ ሰፈር እና ሀያው በተባሉ መንደሮች (ጎጦች) በታጣቂዎች በተፈጸመ ጭፍጨፋ አሶሽየትድ ፕሬስ በአሜሪካ የአማራ ማኅበርን ጠቅሶ እስካሁን 503 ሰዎች መገደላቸውን ዘግቧል።

ማኅበሩ እንደሚለው በጭፍጨፋው 503 ሰዎች መገደላቸውን ከምንጮቹ ማረጋገጡን አመልክቶ፣ ከእነዚህም መካከል የ399 ሰዎችን በሥም እንደለየና የሞቱት ሰዎች ብዛት ግን ወደ 600 መቶ እንደሚጠጋ ለቢቢሲ ገልጿል።

አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት የሆኑ የአማራ ብሔር አባላት ላይ የተፈጸመውን ይህንን ጭፍጨፋ በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት መንግሥት ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መፈጸሙን ከጥቃቱ የተረፉ እና መንግሥት መግለጻቸው ይታወቃል።

ታጣቂ ቡድኑ ግን ድርጊቱን አለመፈጸሙንና ጥቃቱ መንግሥት ባደራጀው ሚሊሻ የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ በጥቃቱ ዙሪያ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽንም በምዕራብ ወለጋው ጭፍጨፋ ወቅት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን አመልክቶ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በጥቃቱ ዙሪያ ፈጣን፣ ገለልተኛና ዝርዝር ምርመራ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ኮሚሽኑ በአብዛኛው የአማራ ብሔር አባላት በሚኖሩበት ቶሌ ቀበሌ ላይ ተፈጽሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ በዋናነት ሴቶችና ህጻናት ስለተገደሉበት ጥቃት እማኞችን ማናገሩን አመልክቶ፣ ታጣቂዎቹ በርካታ ቤቶችን በማቃጠላቸው ቢያንስ 2000 ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ ማግኘቱን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። መንግሥት የኮሚሽኑ መርማሪ ኮሚሽነሮች ከአዲስ አበባ ውጭ ወደ ክልሎች ለመንቀሳቀስ እንዲችሉ ፍቃድ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።ኮሚሽኑ ላለፉት ጥቂት ወራት የደረሰበትን ምርመራ አስመልክቶ ትናንት ለምክር ቤቱ ሪፖርት አቅርቧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa