YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ሰለሞን አለሙ ፈለቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በ"አብዬ ዘርጋው" የሬዲዮ ድራማ ይበልጥ የሚታወቀው ሰለሞን አለሙ በ5 ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችን እና መነባንቦችን ሰርቷል።ለአብነትም ከዳንኪራው ጀርባ፣ ፍራሽ ሜዳ፣ ገመዱ እና አዙሪትን የመሳሱሉ ተወዳጅ ሥራዎች አበርክቷል።

በኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ በተለይ ከ1975 እስከ 1980 ገናና ሥራዎችን ያበረከተበት ወርቃማ ዘመኑ ነበር።እንደኢብኮ ዘገባ ሰለሞን በቅርቡ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሌሊቱን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ መታሰሩ ተሰማ !

የቀድሞ የኢትዮ ፎረም አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ መታሰሩን ጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ገለፁ።ጋዜጠኛው ዛሬ ማለዳ ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሰዱን ነው ጠበቃው የተናገሩት።ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ባሳለፍነው ሳምንት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሰጠው የዋስትና መብት ከእስር መፈታቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ታሪክ አዱኛ
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
በትግራይ ቴሌቪዥን የኤርትራ ጦር ምርኮኞች ተብለው በቀረቡ ግለሰቦች ላይ ቤተሰቦቻቸው ጥያቄ አነሱ!

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸው የተገለጸ የኤርትራ የጦር ምርኮኞች የተባሉ ግለሰቦች በትግራይ ቴሌቪዥን መቅረባቸውን ተከትሎ ዘመዶቻቸው ክሱን አጣጥለውታል።በህወሓት የሚተዳደረው የትግራይ ቴሌቪዥን በምዕራብ ትግራይ አዋላ በተባለች ስፍራ አቅራቢያ ተያዙ የተባሉ አራት የኤርትራ ጦር ምርኮኞች ዘገባ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም. ማሰራጨቱን ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች መነጋገሪያ ሆኗል።

“በምዕራብ ትግራይ አዲ አዋላ አቅራቢያ በሚገኘው ገዛ ጊሌ የኤርትራ 57ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ብርጌዶች እና የ21ኛ ክፍለ ጦር ሠራዊት አንድ ሻለቃ ክፍል በትግራይ ወታደሮች ላይ ግንቦት 16/2014 ዓ.ም ጥቃት ፈፅመዋል” ሲል የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።የቴሌቪዥን ጣቢያው የኤርትራ ወታደሮች ናቸው የተባሉትን ሰመረ ገብረ ሕይወት፣ ገብሩ አልዓዛር፣ ኡመር ኡስማንና ይቤዮ ክፍላይ የተባሉ ግለሰቦችን አቅርቧል።በዘገባው ላይ እነዚህም ግለሰቦቹ በኢትዮጵያውያን ላይ ግድያና መድፈር መፈጸማቸውን ሲናገሩም ይሰማሉ።የሁለቱ ግለሰቦች ቤተሰቦች ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ግን ተያዙ የተባሉት ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት ውድቅ አድርገውታል።

“ሰመረ አካል ጉዳተኛ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ የአእምሮ እክል ነበረበት። ሁኔታው እያሽቆለቆለ ሄዶ በሚጥል በሽታም ታመመ። ያለ መድኃኒት ብዙ መስራት አይችልም” ሲል ታናሽ ወንድሙ ህሩይ ገብረ ሕይወት ለቢቢሲ ተናግሯል።የሰመረ ሌላኛው ወንድም ክፍሎም ገብረ ሕይወት ሰመረ በጤናው ምክንያት በብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ለመመዝገብ ብቁ እንዳልነበረ የሚያሳዩ ሰነዶችን ለቢቢሲ ዘጋቢ ልኳል።

ክፍሎም እንደሚናገረው ቤተሰቡ በኢትዮጵያ የትግራይ ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ የሸሸቢት በተባለች የኤርትራ መንደር ነዋሪ ናቸው ይላል።ቢቢሲ በኤርትራ ጋሽ ባርካ የሚገኘውን የብሔራዊ የአእምሮ ህሙማን ማኅበር ተወካይን አነጋግሮ ሰመረ ከጥር ወር ጀምሮ የድርጅቱ አባል እንደነበር አረጋግጧል።

ለተጨማሪ ንባብ: https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7x713ze8o

@YeneTube @FikerAssefa
"የመከላከያ ሠራዊታችን ግዳጁን በሕግና በደንብ የሚወጣ ጀግና መሆኑ እየታወቀ የሠራዊቱን ሥም በሀሠት የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል" ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሰሞኑን በሱዳን ሰራዊት ቃል አቀባይ የተሰጠውን የተሳሳተ መግለጫ በማስመልከት የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ከፍተኛ መኮነኑ ድርጊቱን በማስመልከት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ እና መንግሥት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪካዊ በሆነው የሱዳን የአብዬ የሰላም ማስከበር ተልእኮ በሡዳንና በደቡብ ሡዳን አገሮች የተመረጠ በመሆኑ በአለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ታማኝነቱ  ይበልጥ ጎልቶ እንድታይ አድርጎታል ብለዋል።ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሱዳን መንግሥት ከህወሀት ቡድን ጋር በተናበበ መልኩ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው እስከ መውረር የዘለቀ የኹለቱን ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት የማይመጥን ተግባር ከመፈፀሙ በላይ ፀብ አጫሪ መግለጫ መስጠቱን አንስተዋል።

ኮሎኔል ጌትነት "ዛሬም ድረስ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ቢሆኑም፤ በቀጠናው ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን የመከላከያ ሠራዊታችን ግዳጁን በህግና በደንብ የሚወጣ ጀግና መሆኑ እየታወቀ የሠራዊቱን ሥም በሀሠት የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል" ብለዋል።

"በሠራዊታችን ላይ የሚነዛ የሀሠት ፕሮፖጋንዳን በማስመልከት እውነቱን ለማወቅ አጣራለሁ ለሚል ማንኛውም አካል በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።" ነው ያሉት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው።

በተጨማሪም መንግስታችን ከሱዳን ጋር ያለውን የቀጠና ውጥረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እያደነቅን ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፤ "ሠራዊታችን  አሁንም ቢሆን ትዕዛዝ ከተሰጠው እንደ ሽፍታ ሳይሆን በመደበኛ ውጊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ  ለማስወጣት በሙሉ ቁመና ላይ ይገኛል።" ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነዉ መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረውን በ10 ሺህ ብር በዋስ ከስር እንዲፈታ ፈቀደ።

ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል ተጠርጥሮ ከአንድ ወር በላይ በስር ላይ የነበረው የአልፋ ሚዲያ ባለቤትና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዛሬ በ10 ሺህ ብር ዋስ ከስር እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።

የፖሊስ የምርመራ መዝገብን በይደር መርምሮ በዛሬው ቀጠሮ ዋስትናውን የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕርዳር ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ በሰጡት መግለጫ “በሀገሪቱና በክልሉ ሕግ ለማስከበር እየተንቀሳቀስን እንገኛለን” ብለዋል፡፡በተለይም በአማራ ክልል የተደራጁ ሕገወጦችን ወደ ሕግ ለማቅረብ ሲሠራ ቆይቷል ነው ያሉት።

የኀብረተሰቡን የሰላም ጥያቄ በማዳመጥ በተወሰደው ሕግ የማስከበር ርምጃም አብዛኞች ጥፋተኞች ወደ ሕግ ቀርበው እፎይታ ተገኝቷል ብለዋል።በዚኽ ሕግ የማስከበር ሂደት ሕዝቡ ያገኘውን እፎይታ እየገለጸ ባለበት ወቅት ሰኔ 20/2014 ዓ.ም ምሽት ኅብረተሰቡን ለማሸበር ያለመ ወንጀል መፈፀም የፈለጉ ቀሪ ኀይሎች በባሕርዳር ከተማ በአራት ቦታዎች ላይ ቦንብ እንዳፈነዱ ገልጸዋል።

ፓሊስ ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትልም ወዲያውኑ ስድስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር አውሏል ነው ያሉት።የተጠርጣሪዎች ቤት በሚፈተሽበት ወቅትም 2 ቦንብ፣ 3 ብሬን መሳሪያ እና 3ሺህ 700 ጥይት፣ አንድ ስናይፐርና አምስት መቶ ጥይት እንዲኹም በቀጣይም ተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም የያዙትን እቅድና መመሪያ ፓሊስ መያዙን ኮማንደር መሰረት ጠቁመዋል።

በዚሁ ምሽት ከዚሁ ሽብር ጋር ግንኙነት ያላቸው 14 ተባባሪ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው የክልልና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ፓሊስ የሚደርስበትን የምርመራ ውጤት ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደረግም ተናግረዋል።ሕዝቡ መሰል የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበትም ኮማንደር መሰረት መልዕክት አስተላልፈዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ከጋላፊ እስከ ሰርዶ በየመንገዱ ዳር ተደብቆ የቆዩት 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።በተጨማሪም አንድ ቦቴ ጫካ ውስጥ ነዳጅ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ዘመቻ ከተጀመረ ጌዜ ጀምሮ በየቦታው ተደብቀው የቆዩ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡በዚህም ባለፉት ሦስት ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተዘግቶ የነበሩ የሰመራ ነዳጅ ማደያዎች ሥራ ጀምረዋል ሲል የአፋር መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከሁለት ትሪሊየን በላይ ሃብት አላቸው የተባሉት እና በ8 ንኡስ ዘርፍ ተካተው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲን ባለቤትነት የሚተዳደሩ ድርጅቶች፡-

1. ሆስፒታሊቲ
ግዮን ሆቴል፣ ሂልተን ሆቴል፣ የፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት፣ ገነት ሆቴል
2. ሎጅስቲክስ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎግስቲክስ አገልግሎቶች ድርጅት፣ የኢትዮጵያ የፍጥነት መንገዶች አስተዳደር
3. ንግድ
የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት
4. አምራች
የኢትዮጵያ ፐልፕ እና ወረቀት ፋብሪካ፣ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት፣ ብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
5. ፋይናንስ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
6. ግንባታና ሪል ስቴት
የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
7. ኬሚካል
የኢትዮጵያ ማእድን፣ ነዳጅ እና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን፣ ኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ፣ ብሄዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
8. መገናኛ
ኢትዮ ቴሌኮም
ሲሆኑ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ድርጅቶቹ ወደፊት ትልቅ ሃብት በማፍራት እና አጋሮችን በማካተት ጭምር በርካታ አገራዊ የእድገት ስራዎችን ያከናውናል ለተባለለት ድርጅት (የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ) በአንድ መተዳደር የሚያስችላቸውን ህጋዊ ስራ ከተከናወነ በኋላ የመጀመሪያ የመተዋወቂያ መድረክ ተከናውኗል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ መጅሊስ 13 አባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ የተፈጸሙትን ግድያዎች አጣርቶ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ ተሰይሟል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በንፁሀን ዜጎች ላይ በደረሰው ግድያ በኦሮሚያ ክልል መጅሊስ አስተባባሪነት 13 አባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው በቀድሞው መሪ የተቋቋመው 13 አባላት ያሉት ኮሚቴ የሀገር ሽማግሌዎች፣ታዋቂ የእስልምና መምህራን እና ምሁራን፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እንዲሁም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ነው።

ኮሚቴው ከፌዴራል እና ከክልል መንግስታት ጋር በሦስት ዋና ዋና ተግባራት ላይ ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ይህም የተረፉትን ተጎጂዎችን ለመደገፍ እና መልሶ ለማቋቋም እና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የተፈናቃዮች ማዕከላት ድጋፍን የማስተባበር ስራ ይሰራል ተብሏል።

የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት በዝርዝር በማጣራት የደረሰውን ጉዳት ለህዝብ እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በማሳየት ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ማድረግ፣ በሙስሊሙ ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ያስችላል ተብሏል።

Via Ethio FM/Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
ዓቃቤ ሕግ የሳምንታዊቷ "ፍትህ" መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ክስ መመስረቱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ዘግቧል። ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተው፣ በልደታ ምድብ አንደኛ የሕግ መንግሥትና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት እንደሆነ የተከሳሽ ጠበቃ ኄኖክ አክሊሉ ተናግረዋል። ፖሊስ ተመስገንን ከአንድ ወር በፊት በቁጥጥር ስር ያዋለው፣ በሚያሳትማት መጽሄትና በሌሎች መገናኛ ብዙኀን ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሱ ንግግሮችን አድርጓል በማለት ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለ2015 በጀት ዓመት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ እቅድ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ ውሳኔ አሳለፈ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለ2015 በጀት ዓመት የ100.05 ቢሊዮን ብር የበጀት እቅዱ እንዲፀድቅ ለከተማው ምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አሳልፏል።ካቢኔው በዛሬው እለት ባካሄደው የ1ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰበው በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ ከ2015 እስከ 2017 ዓመታትን ባካተተው የወጪ ማዕቀፍ ዕቅዱ ላይ ተወያይቷል።ለ2015 በጀት ዓመት በከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ100.05 ቢሊዮን ብር በጀትን ተቀብሎ በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት እንዲጸድቅ ውሳኔ ማሳለፉም ነው የተገለፀው።

ከተወሰነው በጀት ውስጥ 29.79 ቢሊዮን ብር ለክፍለ ከተሞች በድጎማ መልክ የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው 70.26 ቢሊዮን ብር ደግሞ በከተማው በማዕከል ደረጃ ለአስፈጻሚ አካላት የተበጀተ ነው ተብሏል።ከተበጀተው 70.26 ቢሊዮን ብር ውስጥ 54.87 በመቶው የካፒታል በጀት ሲሆን 42.29 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ ወጪዎች የሚውል ነው ያለው ካቢኔው ቀሪው 3.87 በመቶ በመጠባበቂያነት የተያዘ በጀት መሆኑ በበጀት እቅዱ ላይ ተመላክቷል።

በጀቱ በከተማ አስተዳደሩ የተቀመጡ ግቦችን ዉጤታማ ለማድረግ የመንግስት ሃብት ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው ዘርፎች መሰረተ ልማት ለፈጠራ እና ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት በመደልደል ሃብትን በቁጠባና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩን ጠቅሶ ኢብኮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቱርክዬ ከፊንላንድ እና ከስዊድን ጋር የሰሜናዊው ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ለመቀላቀል ያስችላል የተባለለትን ስምምነት ተፈራርማለች።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ መደብደቡን የአካባቢው ባለሥልጣንና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።

ባለፈው ሳምንት በሱዳን ሠራዊት እና በአካባቢው ባሉ ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ሱዳን ሰባት ወታደሮቿ እንደተገደሉባት በመግለጽ በኢትዮጵያ ላይ ክስ መሰንዘሯ ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ የሱዳን ጦር በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በመድፍ፣ በሞርታር እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ለቀናት የዘለቀ ድብደባ መፈጸማቸውን በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ነዋሪዎችም በተለይ ሰኞ ዕለት የተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ድብደባ ጠንካራ እንደነበር ተናግረው ማክሰኞ ዕለትም እስከ ከሰዓትበኋላ ጥቃቱ መቀጠሉን ገልጸዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች ከሱዳን በኩል በሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ምክንያት ተደጋጋሚ ተኩስና ፍንዳታ መስማት ከጀመሩ አስከ ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሦስት ቀን እንደሆናቸው አመልክተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://bbc.in/3OuC0SR

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በሳምንት በአማካይ እስከ 10 ሺህ ዜጎች በወባ በሽታ እየተጠቁ ነዉ!

በደቡብ ክልል የወባ በሽታ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተነግሯል። በበሽታዉ ሳምንት በአማካይ ከ9 አስከ 10 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች እየተጠቁ መሆናቸዉን የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር የወባ ማስወገድ ፕሮግራም አማካሪ አቶ ሄኖክ በቀለ ተናግረዋል።

በሽታዉ በክልሉ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ባይሆንም በቀበሌ ደረጃ ግን በወረርሽኝ መልኩ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል። በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ከሚገኝባቸዉ አካባቢዎች ዉስጥ በከንባታ ጠንባሮ ዞን ጠንባሮ ወረዳ ፣ በወላይታ ዞን ገሱባ ፣ ሶሬ እና ቦንዴ ወረዳዎች ፣ ሀድያ ዞን ላይ በደወቾ ወረዳ ፣ በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ ፣ ጋሞ ዞን ደረማሎ ፣ ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ፣ ሰላማጎ እና ባስኬቶ ወረዳዎች ላይ ስርጭቱ እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የሰላማጎ ወረዳ ከፍተኛ የወባ ስርጭት እየተስተዋለበት የሚገኝ ቦታ እንደሆነ ጨምረዉ አንስተዋል። በሌላ በኩል ክልሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የወባ ታማሚ ያለበት መሆኑንም አማካሪዉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሶስት አመታት ዉስጥም የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኝ ባህሪዋን በመለወጥ ድርቅ በሚያጠቃቸዉ አካባቢዎች ላይ ጭምር በክረምት ወቅት እየታየች እንደሆነ አማካሪዉ ገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ በበኩሉ ባለፉት ሳምንታት በሽታዉን ለመከላከል ህብረተሰቡን የማንቃት ስራን ጨምሮ የበሽታዉ ስርጭት ባየለባቸዉ አካባቢዎች የኬሚካል ርጭት እና የአጎበር አቅርቦትን እያከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣይ በተመረጡ 46 ወረዳዎች የኬሚካል ርጭት እንደሚያከናዉኑ እና በ34 ወረዳዎች የአጎበር አቅርቦትን ለማድረስ ታቅዶ በ18 ወረዳዎች ላይ አጎበር እንደደረሰ አማካሪዉ አስታዉቀዋል። የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው የወባ በሽታ ስርጭቱ በወረርሽኝ ደረጃ እንዳይስፋፋ ስጋት ላይ መሆኑን አቶ ሄኖክ በቀለ ጨምረው ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
በአዲስ አበባ ለተፈጠረው የናፍጣ እጥረት የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰጡ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ሪፖርተር ያዘጋጀው ዘገባ የሚከተለውን ይመስላል

ከ2 ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ የናፍጣ እጥረት በአዲስ አበባ ከተማ እየተፈጠረ ሲሆን ለምን እጥረቱ እንደተፈጠረ በሚሰጡት ምላሽ ላይ መንግሥትና የነዳጅ አቅራቢዎች ሊግባቡ አልቻሉም፡፡

ማደያዎችና ነዳጅ አመላላሾች እጥረቱ የተፈጠረው ከጂቡቲ የሚመጣ ነዳጅ በመጥፋቱ ነው በማለት መኪኖቻቸው ለቀናት ነዳጅ አጥተው ጂቡቲ መስመር ላይ መቆማቸውን ገልጸዋል፡፡

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ቦርድ አባል ኤፍሬም ተስፋዬ " ከ2 ሳምንታት ወዲህ በተለይ የናፍጣ እጥረት ተፈጥሯል፡፡ ይህም እጥረት የተከሰተው ጂቡቲ ላይ ተቀብለን የምናመጣው ናፍጣ ስለሌለ ነው፡፡ መኪኖቻችን ለቀናት ያለሥራ እየቆሙ ነው " ብለዋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ኃላፊዎች ደግሞ እጥረቱን የፈጠሩት ነዳጅ አከፋፋዮችና ማደያዎች እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የነዳጅና እነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ወ/ሮ ሳህሬላ አብዱላሂ " ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በየቀኑ የሚጫነው ነዳጅ ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በፊት በቀን ዘጠኝ ሚሊዮን ሊትር (በአማካይ) ይገባ የበረው በዚህ ሳምንት በአማካይ 9.294 ሚሊዮን ሊትር እየባ ነው " ብለዋል።

ከጂቡቲ እየተጫነ ያለው 200 ሺሕ ሊትር ነዳጅ አዲስ አበባ ሳይደርስ በተለያየ ሰበብ መንገድ ላይ ቆይቶ እየተያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. 10 ማደያዎች በአዲስ አበባ ውስጥ ነዳጅ እያላቸው መኪኖችን ሲመልሱ የተገኙ ሲሆን በነጋታው 14 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች አፋር ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ነዳጅ አከፋፋዮችና ማደያዎች አዲሱ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ከሐምሌ 1/2014 ጀምሮ መተግበር እስኪጀምር በእጃቸው ላይ የገባውን ነዳጅ ላለመሸጥ አዝማሚያ ማሳየታቸው እጥረት እየፈጠረ መሆኑ ዋናው ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

መንግሥት የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ ለማንሳት የወሰነው ውሳኔ ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሚገበር ሲሆን ይህም የነዳጅ ውጤቶችን ዋጋ ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ይህም ማለት አከፋፋዮችና ማደያዎች ከቀነ ገደቡ በፊት በድጎማ በዝቅተኛ ዋጋ የገዙትን ነዳጅ ከሐምሌ አንድ በኋላ ከፍ ባለው በአዲሱ ዋጋ ይሸጣል ማለት ነው፡፡

ድጎማው ሲነሳ በሊትር እስከ ዘጠኝ ብር ጭማሪ ሊኖር እንደሚችልና ይህም በአንድ ቦቴ እስከ 450 ሺሕ ብር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡

በነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአቅርቦት እና ሽያጭ ኃላፊ አቶ አባይነህ አወል ፥" ዋናው የእጥረቱ ምክንያት እስከ ድጎማው መነሳት ነዳጅ ለመያዝ መሞከር (Hoarding) ነው፡፡ የመኪና እጥረትም አይደለም፡፡ ጂቡቲ ላይ መዘግየት ያጋጠመው ለአንድ ቀን ሲሆን እሱም የጂቡቲዎች በዓል ቀን ስለነበር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሸጠው ነዳጅ በየቀኑ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን፣ ከጂቡቲ የሚጫነው ግን ጭማሪ አሳይቷል " ብለዋል።

ናፍጣ ከአጠቃላይ የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ውስጥ እጥረት ሲያጋጥም አሁን የመጀመርያው ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜ የሚፈጠረው የዲዝል እጥረት ነበር፡፡

በተለይም ማደያዎች ነዳጅን በብዛት ዴፖ ውስጥ መያዝ እየተው መምጣታቸው ለእጥረቱ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አቶ አባይነህ ይገልጻሉ፡፡ " ማደያዎችና አከፋፋዮች ነዳጅ የሚወስዱት በብድር መሆኑ ቀርቶ በካሽ ክፈሉ ከተባሉ ወዲህ፣ የባንክ ወለድ በመፍራት ነዳጅ በብዛት ዴፖ ውስጥ መያዝ ትተዋል፡፡ "

ወ/ሮ ሳህረላ ድጎማው እስኪነሳ አንሸጥም ብለው በጫካ ውስጥ ጭምር ነዳጅ ጭነው ተደብቀው እየተያዙ ያሉትን እየፈለጉ መያዝና ነዳጅ ወደ ገበያው እንዲደርስ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥር በማውጣትና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል የቀረበበት ክስ ላይ የዋስትና ብይን ለመስጠት ለአርብ ተቀጠረ።

ክሱ በትናንትናው ዕለት የተከፈተ ሲሆን በዛሬው ቀጠሮ ግን ክሱ ለተከሳሽ ደርሶ በችሎት ተነቧል።ክሱን በንባብ ያሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና የህግመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ነው።

በዚህም ክስ ዓቃቢህግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ 44(1) (2) እና 336(1) በመተላለፍ በአንደኛው ክስ የቀረበ ሲሆን በ2ኛ ክስ ደግሞ አንቀጽ 337(1) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እና በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ አንቀጽ 257 በመተላለፍ ሲል ዓቃቢህግ ተደራራቢ ክስ አቅርቧል።

በክሱ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሚሰራበት በፍትህ መጽሔት በተለያዩ የህትመት ቀናት የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥራዊ ተግባራትን በማውጣትና እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት የሚል በክሱ ተካቷል።

ክሱ በችሎት ከተነበበ በኋላ የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ጋዜጠኛ ተመስገን በወ/መ/ስ/ህ 67/ሀ እና በህገመንግስቱ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 6 መሰረት የዋስትና መብት መጠበቅ እንዳለበት ድንጋጌውን አብራርቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ሀሳብን ከመግለጽና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ ከመጻፍ ባለፈ ምንም ወንጀል ፈጽሞ እንደማያውቅ ገልጿል።ከዚህ በፊት በነበረ ስርዓት ታስሮ ዋስትና ተፈቅዶለት ለሶስት አመት ህግን አክብሮ እየተመላለሰ ፍርድ ቤት ይቀርብ እንደነበር ጠበቃው ጠቅሷል።ይህም ህግን አክብሮ እንደሚመጣ ማሳያ ነው ሲል አብራርቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ከሀገር እንዲወጣ በተለያዩ አካላትና መንግስታት ሳይቀር ግፊት ተደርጎ እንደነበር የጠቀሰው ጠበቃ ሄኖክ በጋዜጠኛ ተመስገን በኩል ግን ስራዬና ሞቴ በሀገሬ ላይ ነው ብሎ ከሀገር ሳይወጣ መቀመጡን ገልጿል።ቋሚ አድራሻ ያለው እና ህግን የሚያከብር መሆኑን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲፈቅድለት ጠበቃው ጠይቋል።

ከሳሽ ዓቃቢህግ በበኩሉ በተደራራቢ ክስ በመከሰሱና በልዩ ሁኔታ ዋስትና ሊሚያስከለክል እንደሚችል የወንጀለኛ መቅጪያ ስነስርዓት ህግ ድንጋጌ መኖሩን በመግለጽ እንዲሁም የሰበር ውሳኔ ድንጋጌዎች ዋስትናን ሊያስከለክል እንደሚችል በማብራራት ተከራክሯል።

በተጨማሪም ከሳሽ ዓቃቢህግ በአንደኛና በሶስተኛ ክስ ከብዶ ከታየ እስከ 10 ዓመት በሚያደርስ ዕስራት ያስቀጣል ሲል የገለጸ ሲሆን በሁለተኛ ክስ ደግሞ ከብዶ ከታየ እስከ እድሜ ልክ በሚያደርስ ጽኑ እስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ገልጾ የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ መርምሮ ዋስትናው ብይን ለመስጠት ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል ።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና፣ በወራቤ እና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ እና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።በጉብኝታቸው ወቅት ከተማሪዎች እና ከትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆት እና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በሥራ እና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር፣ ማጥናት እና ማወቅ እንዳለባቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገንዝበዋል።እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይ እና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ ሦስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ችግኝም መትከላቸውን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ውል ለተጨማሪ ስድስት ወራት አራዘመ፡፡

ውሉ ከመጋቢት 4/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ወራት እስከ መስከረም 2/2015 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደ ስራ ከገቡ በኋላ በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ማበርከቱን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት በሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በኩል ስምሪት እየተሰጣቸው የሚገኙ አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ቢሮው ውላቸውን አራዝሟል፡፡ማህበራትም በውሉ መሰረት የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

በሁሉም አውቶቡሶች GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር ስራው የተጠናከረ እና አገልግሎት አሰጣጡም የተሻሻለ እንዲሆን በትኩረት እንዲከወንም ቢሮው አስታውቋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ከጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች በኪራይ መልክ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በፈተናው አሰጣጡ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በከተማዋ በ 792 ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ተነግሯል።ለዚህም 179የ መፈተኛ ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።አቶ ዳኘው አክለውም አጠቃላይ በከተማዋ 71 ሺህ 832 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ነው የተናገሩት።

ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እስካሁን የለውን የፈተናው ዝግጅት ሂደት የገመገመ ሲሆን ፈተናው ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ሂደት ላይ ነውም ተብሏል።ሰኔ 24 ቀንም ለሁሉም ፈተናውን ለሚመለከት የትምህርት ማህበረሰብ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa