በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ!
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ፔይተን ክኖፍ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ታማኝ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል ቢቢሲ።ፔይተን አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሰየም ከጀመረችበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ምክትል በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ነው በዚህ ሳምንት ኃላፊነታቸውን የለቀቁት።
ይህም በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ቡድኑ ሥራቸውን የለቀቁ ሦስተኛው የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል።ፔይተን ከምክትል ልዩ መልዕክተኝነታቸው ባሻገር ከሦስት ወራት በፊት ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ በጊዜያዊነት የዋና ወኪልነት ቦታውን ሸፍነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
“እነዚህ ሦስት በርካታ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶች ይህንን ወሳኝ ኃላፊነት ወስደው በማገልገላቸው ደስተኞች ነን” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።“በአፍሪካ ቀንድ ያለው ያለመረጋጋት እንዲሁም በቀጠናው ያሉት የፖለቲካ፣ የፀጥታ እንዲሁም የሰብአዊ ጉዳዮች ፈተናዎች የአሜሪካን ያልተቋረጠ ትኩረት ይፈልጋሉ” ሲሉም ፕራይስ ለቢቢሲ ገልጸዋል።አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ፔይተን ክኖፍ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ እንዲሁም ከመንግሥት ሥራ መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል።ነገር ግን ለፔይተን ከኃላፊነታቸው መልቀቅ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከእራሳቸውም ሆነ ከሌሎች ምንጮች የተባለ ነገር የለም።
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa

‘ፊያስ’ በተባለ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ሰዎች ለህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጠየቀ።
‘በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ እናደርጋችኋለን’ በሚል የማህበራዊ እና የኦንላይን ሚዲያዎችን በመጠቀም የማጭበርበር ተግባራት የሚፈፅሙ አካላት ቁጥራቸው እየጨመረ በመምጣቱ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በመተባበር የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ እንዳለ አሰፋ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ገልፀዋል።
የማህበራዊ እና የኦንላይን ሚዲያዎችን በመጠቀም የበርካታ ሰዎችን ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አድራሻቸውን በማጥፋት የተሰወሩ አካላት መኖራቸውን ከደረሰ ጥቆማና ከተለያዩ ምንጮች መረዳት መቻሉን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ይህን ጉዳይ አስመልከቶ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል።
በቅርቡ ‘ፊያስ’ እየተባለ የሚጠራው የኦንላይን ድርጊት እንደሌሎች በማህበራዊ እና በኦንላይን ሚዲያዎች በመጠቀም ከሚፈፀሙ የማጭበርበሪያ ድርጊቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ኃላፊው ጠቁመዋል።
Via EBC

ቅዲስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሆኗል!
ፈረሰኞቹ የ 2014 የውድድር ዓመት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት በጉጉት በተጠበቀው መርሐ ግብር አዲስ አበባ ከተማን በመርታት የሊጉን ዋንጫ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን አውጀዋል ።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ፋሲል ከነማ በቀጣይ ዓመት ሀገራችን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።
አዲስ አበባ ከተማ ሽንፈት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ በሊጉ ወደታችው እርከን መውረዳቸውን ያረጋገጡ ሶስተኛው ክለብ ሆነዋል ።

1 ሺሕ 133 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!
ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺሕ 133 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ሦስት ህጻናትና 1 ሺሕ 130 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 45 ሺሕ 325 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ
እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን
እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
https://tttttt.me/meritibe
👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ

ቻይና የፌደራል መንግስትና ህወሃትን ማደራደር እንደምትፈልግ ገለጸች!
ቻይና የፌደራል መንግስት እና ህወሃትን ማደራደር እንደምትፈልግ ገለጸች።ቻይና በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ በቅርቡ የሾመች ሲሆን ከሌላው የአፍሪካ ክፍላተ አህጉር የተለየ ፍላጎት እና ጥቅም እንዳላት ይገለጻል።በቅርቡም የምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ልማት ጉባኤ በአዲስ አበባ ያካሄደች ሲሆን፤ ቻይና ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ግንኙነቷን የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጻለች።
በምስራቅ አፍሪካ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዢዮ ቢንግ በፌደራል መንግስት እና ህወሃት መካከል ያለውን ልዩነት በማደራደር ወደ ስምምነት እንዲመጡ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ቪኦኤ ዘግቧል።
ቻይና በምስራቅ አፍሪካ ሰላም እንዲመጣ ድጋፍ እንደምታደርግ የተገለጸ ሲሆን በህወሃት እና ፌደራል መንግስት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እና ወደ ስምምነት እንዲመጡ ድጋፍ እንደምታደርግ አምባሳደሩ መናገራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።ይሁንና አምባሳደሩ በሁለቱ አካላት መካከል እንዴት ለማደራደር እንዳሰበች ዝርዝር ነገር ከመናገር ተቆጥበዋልም ተብሏል።የቻይና አዲሱን አቅድ ተከትሎም ከዚህ በፊት ከነበራት በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ላለመግባት የነበራትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለውጥ ለማድረጓ ማስረጃ ይሆናልም ተብሏል።
[VOA/Alain]

የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በንጹሃን ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ላይ ምርመራ መጀመሩን ትናንት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የመርማሪ ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ኬንያዊቷ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ፣ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም ሊዘነጋው እንደማይገባ አውስተዋል። በአገሪቱ ግጭቶችን የሚያቀጣጥሉ የጥላቻ ንግግሮች እና ጎሳን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ከባድ ዓለማቀፍ ወንጀሎች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ምልክቶች ናቸው በማለት ለተመድ ሰብዓዊ ምክር ቤት ተናግረዋል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
መድሃኒትን ጨምሮ የተለያየ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደረሱ!
መድሃኒትን ጨምሮ የተለያየ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ የዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደረሱ።የዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር የኢትዮጵያ ቢሮ በትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ ተሽከርካሪዎቹ መድሃኒት፣ ጤፍና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ጭነው መቀሌ ደርሰዋል።
(ኢዜአ)

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በዶክተሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 2 ሺ 509 ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ÷ ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ በዶክተሬት ድግሪ የተመረቁ የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ67 ኛ ጊዜ በተለያዩ ትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በዶክትሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲም በመደበኛው፣ በክረምት እና በዕረፍት ቀናት መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡ዩኒቨርስቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 650 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
[FBC]

YeneTube
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በዶክተሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 2 ሺ 509 ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ÷ ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ በዶክተሬት ድግሪ የተመረቁ የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ…
በተመሳሳይ ዜና፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምና የትምህርት ዘርፍ ያለጠናቸውን 7 የስፔሻሊቲ ዶክተሮችን ጨምሮ 334 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡
በ1947 ዓ.ም የማኅበረሰብ ጤና ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማዕከል በሚል የተመሰረተው አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጀርመን ሀገር ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከአዲስ አበበ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ1971 ዓ.ም ከጤና ትምህርት ዘርፎች በተጨማሪ የህክምና ትምህርት መስጠት መጀመሩን የዩኒቨርሲተው መረጃ አመላክቷል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምና ትምህርት ቤት ብቻ በ7 የቅድመ ምረቃ፣ በ8 የሁለተኛ ዲግሪ፣ በ1 የፒ ኤች ዲ፣ በ10 የስፔሻሊቲ እና በ4 የሰብስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 997 ተማሪዎች ለ14ኛ ጊዜ ዛሬ እያስመረቀ ነው።
በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ፣ በኢንጂነሪግ፣ በጤና እና ህክምና እንዲሁም ሌሎች ሙያዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው እየተመረቁ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል 241 ሴቶች ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ፣ በኢንጂነሪግ፣ በጤና እና ህክምና እንዲሁም ሌሎች ሙያዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው እየተመረቁ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል 241 ሴቶች ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በአዲሱ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Monkeypox በሽታ ተጠርጥረው የተለየ ክፍል ውስጥ እንደተኙ ሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ በዛሬ ዕትሙ አስነብቧል ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል 80 ወጣቶች በታጣቂዎች ታግተዋል!
በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ሜራ ቀበሌ በቀን ሥራ የተሰማሩ 80 ወጣቶች በጋምቤላ ነጻ አውጪ ንቅናቄ ታጣቂዎችና በኦነግ ሸኔ መታገታቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።
የቀን ሠራተኞቹ ከታገቱ አምስት ቀን ቢያስቆጥሩም፣ እስከ አሁን ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ሲሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች መካካል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል።
በታጣቂዎች የታገቱት 80 ወጣቶች መሆናቸውን ነዋሪዎቹ የገለጹ ሲሆን፤ ታጣቂ ቡድኑ እገታውን ያከናወነው በጋምቤላ ክልል እና በቄለም ወለጋ መካከል በምትገኘው ኢታንግ ልዩ ወረዳ ሜራ ቀበሌ መሆኑንም አብራርተዋል።
[Addis Maleda]

አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ በኢትዮዽያ ዘመናዊ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ አበርክቶ አላቸው።
ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ዓመታት በእንግሊዝኛው የኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ ሰርተዋል።
ጋዜጠኛ ፀጋዬ በተለይ በፓርላማ እና በአፍሪካ ህብረት ዘጋቢነታቸው ይታወቃሉ።ለመጀመሪያ ጊዜ የስፖርት ዓምድን የከፈቱም መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡
አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ በኢትዮዽያ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የውጪ ሚዲያ ዘጋቢ (correspondent)መሆናቸውን የህይወት ታሪካቸው ያሳያል።
ዋና መቀመጫው እንግሊዝ ለሆነው ሮይተርስ የሚዲያ ተቋም ከ37 ዓመት በላይ ሰርተዋል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ በ2010 ዓ.ም ለ6ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የበጎ ሰው ሽልማት በጋዜጠኝነት ዘርፍ አሸናፊ ሆነዋል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ታደሰ የቀበር ስነስርዓት ነገ እሁድ ሰኔ 26፣ 2014 ዓ.ም በመናገሻ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 የሚፈፀም መሆኑን ከቤተሰቦቻቸው ሰምተናል።
[Sheger FM]

👍1
በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የሚመራው የትግራይ መስተዳድር ከኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ድርድር ከሕዝብ ጋር በመመካከር ተወካዮቹን እንደሚመርጥ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።
ከክልሉ መስተዳድር ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው የተደራዳሪዎቹ ማንነት በህውሓት ብቻ እንደማይወሰን ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት እና በዛሬው ዕለት በተላለፈ መግለጫቸው ተናግረዋል። ትግራይን የሚመራው የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈው ሰኔ 6 ቀን 2014 በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ በናይሮቢ በኬንያው ፕሬዝደንት ኡኹሩ ኬንያታ አመቻቺነት ለሚደረግ ድርድር የክልሉ መንግሥት ተወካዮቹን ለመላክ ፈቃደኛ መሆኑን አስታውቀው ነበር።
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማብቃት የሚደረገው ድርድር በአፍሪካ ኅብረት በኩል ሊደረግ ይገባል የሚል አቋም ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ሰባት አባላት ያሉት የፌድራል መንግስት ተወካዮች ባለፈው ሣምንት መርጧል። የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትን ወክሎ በድርድሩ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን በምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ነው።አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ቅዳሜ በተላለፈ መግለጫቸው "ድርድር በተፈጥሮው በሰጥቶ መቀበል መርኅ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ምንድነው የምንሰጠው? ምንድነው የምንቀበለው? ከምንሰጣቸው መሰረታዊ የማይዘለሉ የሚባሉ መሠረታዊ ነገሮች ውጪ ባሉ ጉዳዮች ላይ መወያየት ይቻላል። እሱን ለማድረግ በእኛ እምነት ህወሓት የሚባል ፓርቲ ብቻ የሚያደርገው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። "ሕዝብን አሳትፈን፤ እነ ማንናቸው ወክለውኝ ሊደራደሩ የሚችሉ ብሎ ወስኖ የምናደርገው ነው የሚሆነው" ያሉት አቶ ጌታቸው "ጊዜ አንገብጋቢ ነው ብለን እናምናለን። ወደዚህ ጉዳይ በአስቸኳይ መግባት አለብን ብለን እናምናለን። ለእኛ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተሟላ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግልጽ ስዕል ተፈጥሮልናል ብለን አናምንም" ሲሉ የክልሉን መንግሥት አቋም አብራርተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በአደራዳሪዎች ማንነት ላይ ያላቸው ልዩነት እንዴት መፍትሔ እንደሚያገኝ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ለአፍሪካ ቀንድ በሾሟቸው ልዩ መልዕክተኞች በኩል የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድርድር እንዲቋጭ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በድርድሩ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊሳተፉ እንደሚገባ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠቅሰዋል።
[DW]

ከ36 የነዳጅ ኩባንያዎች 26ቱ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ነዳጅ ማደያቸው ስላስገቡት ነዳጅ መጠን ሪፖርት እንዳላቀረቡ ኢፒድ የነዳጅ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል።
ባለሥልጣኑ ሪፖርት ላላደረጉ የነዳጅ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል። የነዳጅ ኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የነዳጅ ኩባንያዎች ከወደብ ተረክበው ወደ ማደያዎቻቸው የሚያጓጉዙትን እና የሚያከፋፍሉትን የነዳጅ መጠን ሪፖርት እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ ቀደም ሲል ማዘዙ ይታወሳል። ባለሥልጣኑ ትዕዛዙን የማያከብሩ ኩባንያዎችን ከነዳጅ ኮታ ድልድል ከማስወጣት እስከ ፍቃድ መንጠቅ የሚደርስ ርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል።

በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባውን የለገዳዲ ክፍል ሁለት የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባውን የለገዳዲ ክፍል ሁለት የውሃ ፕሮጀክት ዛሬ መረቁ፡የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የአዲስ አበባን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የምናሻሽለው እንዲህ ያሉ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ ነው ብለዋል ።
ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ተሳትፎ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል።ፕሮጀክቱ የመጀመሪያው ግዙፍ የከርሰ ምድር ውሃ እንደሆነና ለ860 ሺህ ዜጎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የተካሄደ ሲሆን÷ በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም አለው፡፡ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን በቀን ውሃ የማምረት አቅም ከ674 ሺህ ወደ 760 ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል፡፡
16 ጥልቅ ጉድጓዶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 10 የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖችም ተገንብተዋል፡፡
የ12 ኪሎ ሜትር ዋና የውሃ መስመር፣ 72 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰባሰቢያ መስመር፣ 99 ኪሎ ሜትር የስርጭት መስመር ዝርጋታ፣ ሁለት ግዙፍ የግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና 38 ኪሎ ሜትር የመዳረሻ መንገድን ያቀፈ ፕሮጀክት መሆኑም በምረቃው ወቅት ተገልጿል፡፡ግንባታው በተጨማሪም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች እና በጉድጓዶቹ አካባቢ የሚሰሩ የሲቪል ስራዎችንም የያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
Via FBC

በኢትዮጵያ በአዲሱ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Monkeypox በሽታ ተጠርጥረው የተለየ ክፍል ውስጥ እንደተኙ ሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ በዛሬ ዕትሙ አስነብቧል ። @YeneTube @FikerAssefa
#update
በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በመባል የሚታወቀው እና በተለያዩ ሀገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሀገራችን ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ “በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በሀገራችን እስከ አሁን በበሽታው የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን” ብሏል።
ኃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠ እና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም አሳስቧል።
ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማኅበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች ጥሪ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋቾች ዳንኤል ተሾመ (አዲስ አበባ ከተማ)፣ አብዱልባሲጥ ከማል (ሃዋሳ ከተማ) እና ጀማል ጣሰው (አዳማ ከተማ) በ5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 1 ሺሕ 500 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።
በ30ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ጽ/ቤት እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል።
በዚህም ለሦስት የጨዋታ ታዛቢዎች ሻለቃ በልሁ ኃይለማሪያም፣ ሰላሙ በቀለ እና አበጋዝ ነብየልዑል ሲሆን ከዳኞች ለኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው (ፒኤችዲ)፣ ለኢንተርናሽናል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ፣ ለፌዴራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ፣ ለፌዴራል ዳኛ ባህሩ ተካ ለፌዴራል ዳኛ ዮናስ ካሳሁን እና ለፌዴራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ጥሪ ቀርቧል።
[Walta]