YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የ30 ቀን ዕቅድ መሰረት በሸኔ ታጣቂዎች ላይ የተቀናጀና ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ!

የክልሉን ሰላም በማስፈን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላሳ ቀን ዕቅድ መሰረት በሸኔ ታጣቂዎች ላይ የተቀናጀና ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አስታወቁ፡፡

ኮሎኔል አበበ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን በጨፌ ጉባዔ ላይ ሽብር ቡድኑን በአንድ ወር ውስጥ አደብ ለማስገዛት ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በክልሉ አራት ወሳኝ አካባቢዎች ላይ ጠንካራና የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ቢሮው ኃላፊ ገለጻ፤ ሽብር ቡድኑ በስፋት በመንቀሳቀስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ሞትና በደል ያደረሰባቸው በወለጋ፣ በጉጂ፣ በምዕራብና ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ የክልሉና የፌዴራል የፀጥታ አካላት በሽብር ቡድኑ ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

በተጀመረው ኦፕሬሽን በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፡፡ የተመዘገቡ ድሎች በዝርዝር ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ ሲሉም ኮሎኔል አበበ ተናግረዋል፡፡

ሸኔ ከህወሓት ጋር በመሆን ኦሮሚያን የብጥብጥ ቀጠና በማድረግ አገር ለማፍረስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ኮሎኔል አበበ፤ ኦሮሚያ ብሎም ኢትዮጵያን ማፍረስ ከምናባዊ እሳቤና ከቀን ቅዥት ስሌት በዘለለ መቼም ቢሆን ሊሳካ የማይችል የሴረኞች ህልም ነው ብለዋል።

በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰዱ ባሉባቸው የሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጎን መሰለፋቸውን የጠቀሱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ ስንቅ በማቀበል፣ ጥቆማ በመስጠትና ቀጥታ እርምጃ በመውሰድ ህዝቡ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት በጎ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ የክልሉ መንግሥት ሽብተኝነትና ጽንፈኝነት ለክልሉም ሆነ ለአገር ህልውና አደገኛ መሆኑን በጽኑ ያምናል። በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሲጠናቀቅ በሌሎች አካባቢዎች ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ክልሉ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም አስታውቀዋል።

በአንዳንድ ክልሎች የአገር ሰላምና የህዝቦች አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የሽብር ተግባርና አስተሳሰብ በስፋት እየተስዋለ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች ክልሎችም ሰላም ለማስፈን ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን አገር የመገንባት ታሪክ እንጂ ጽንፈኛና ሽብርተኛን የማስታመም ህልውና የለውም ያሉት ኮሎኔል አበበ፤ በሸኔ ላይ የጀመረውን የማያዳግም እርምጃ በመሰሎቹ ላይም እንደሚወስድ አስታውቀዋል።የቡድኑ ታጣቂዎች በድርጊታቸው ተጸጽተው ወደ ሰላማዊ ኑሮ የመመለስ ፍላጎት ካላቸው የክልሉ መንግሥት የሰላም በሩ አሁንም ክፍት መሆኑንም አመልክተዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመጉ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች መጋቢት 25 በተፈጠረ ግጭት 5 ሰዎች እንደተገደሉ እና በ15 ሰዎች ላይ ደሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ባወጣው አዲስ መግለጫ አስታውቋል።

ግጭቱ የተፈጠረው፣ ከኦሮሚያ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች በሲዳማው ጭሪ ወረዳ አንድ የሲዳማ ሽማግሌ መግደላቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ በግጭቱ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። ኢሰመጉ ሁለቱ ክልሎች ችግሩን በቶሎ በሰላም እንዲፈቱት ጠይቋል። በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን አማሮ ልዩ ወረዳ ከኦሮሚያ ጉጂ ዞን የተነሱ ታጣቂዎች ግድያ መፈጸማቸውንም ኢሰመጉ ገልጧል። ኢሰመጉ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ማስከበር አልቻለም በማለት ወቅሷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትድጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 መሠረት የቦርድ አባላት ተሹመዋል፡፡

በዚህም መሰረት
1. ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሰብሳቢ
2. ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፤ አባል
3. ክቡር አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል፤ አባል
4. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
5. ዶ/ር በድሉ ዋቅጀራ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
6. ዶ/ም መሣይ ገ/ማሪያም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
7. ዶ/ር ወዳጀነህ ማዕረነ አማካሪ፤ አባል
8. ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል
9. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል ሆነው በውሳኔ ቁጥር 8/2ዐ14 በተቃውሞ በ11 እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

በዚህም መሠረት ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ምክንያት 3.1 ሚሊዮን ሰዎች ለውሃ እጥረት መዳረጋቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ፣በምእራብ ጉጂ፣ በባሌ፣በምስራቅ ባሌ፣ በምስራቅ ሃረርጌ እና በምዕራብ ሃረርጌ ያጋጠመው ድርቅ 3.2 ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳት ፈላጊ እንዲሆኑ ማድረጉን በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል፡፡

በሰባ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 690 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 3.1 ሚሊዮን ሰዎችች ለውሃ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን ያላቸው የውሃ አማራጭ በቦቴ የሚቀርብ ውሃ በመሆኑ አሁን ላይ በ76 ወረዳዎች በ121 የውሃ ቦቴዎች እደላ እየተከናወነ ይገኛል።ሆኖም ግን ባለው የቦቴ እጥረት የተነሳ ውሃ የማዳረስ ሂደቱ አዳጋች እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል ።

የውሃ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ማሽኖች መበላሸት፣ የጉድጓድ ውሃ መጠን መቀነስ ፣የውሃ ቦቴ ፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን ፣በህጻናት እና እናቶች ላይ የተመጣጣነ ምግብ እጥረት በክልሉ የሚኖረውን የበሽታ ክስተት እንዲጨምረ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 49 ወረዳዎች ከ12 ሚሊዮን በላይ እንስሳት በድርቅ አደጋ ውስጥ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 572ሺህ 967 እንስሳት ሞተዋል፡፡1ሚሊዮን 896 ሺኀ 937 እንስሳት ደግሞ ያለ ሰው ድጋፍ መነሳት እንደማይችሉም አንስተዋል፡፡እንዲሁም በቦረና እና በምስራቅ ባሌ ዞን ብቻ በድርቁ 1079 ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ በዚህም ከ352 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምህርት እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን ጠቁመዋል ፡፡

ከሃምሌ ወር 2013 እሰከ መጋቢት 2014 አጋማሽ በኢትዮጲያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፣በአጋር አካላት ፣ በክልሉ መስተዳዳሩ እና ከህብረተሰቡ በተሰበሰበ ገንዘብ 1ሚሊዮን 473 ሺኀ ኩንታል ምግብ ለተጎጂዎች የተከፋፋለ መሆኑን አቶ ደበበ ዘውዴ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ " ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 % ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን እኤአ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከግማሽ ሚልዮን በላይ ተማሪዎች በድርቅ ሳቢያ ትምህርት አቋርጠዋል ተባለ!

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተ ድርቅ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።አፍሪካኒውስ ዩኒሴፍን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ የተዘጉ ሲሆን 727 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል እየሰሩ ይገኛሉ።

ዩኒሴፍ ህፃናቱን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እየሰራሁ ነው ያለ ሲሆን ‘ቤቴ’ የተሰኘ ስርዓት በመፍጠር ደህንነታቸው የሚጠበቅበት፣ የስነ ልቦና ድጋፍ የሚያገኙበትና ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት ሁኔታ ይመቻቻል ተብሏል።በመንግስታቱ ድርጅት መረጃ መሰረት በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል የመቀንጨር ችግር 20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
#በራስ_መተማመን
4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ይህ A Guide to confident Living የተባለው መጽሐፍ በራስ መተማመንን እርካታን መቀዳጀት እንችል ዘንድ ያስችላል።

ቀላል ለማንም ሰው ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተጠቀመው
ዶ/ር ፒል በሕይወታችን ትልቅ መታደስ ማግኘት እንችል ዘንድ አዲስ የሆነ የኃይል መንገድን ይጠቁመናል።

ከሚለግሰን ምክሮች መካከል እንደ፤

* ውስጣዊኃ ይሎቻችንን ነጻ ማውጣት
* ችግሮቻችንን አውጥተን መናገር
* የበታችነት ኮምፕሌክሳችንን መውደድ
* ለሕይወታችን የተረጋጋ ማዕከልን ማግኘት
* የጸሎትን ኃይል መለማመድ
* ከፍርሃትና ሃዘን ነፃነትን ማግኘት
* የትዳር፣ ሙያዊ እና ግለሰባዊ ደስታን ማግኘት ያሉት ይጠቀሳሉ።

ኖርማን ቪንሰንት ፒል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ያስገኘለት The Power of Positive Thinkingን ጨምሮ የ46 ያህል መጽሐፎች ደራሲ ነው።

በኖረበት ዘመን ትልቅ ከተባሉ የሃይማኖት ሰዎች አንዱ የነበረው ዶ/ር ፒል ምንም እንኳ ሕይወቱ ቢያልፍም በስሙ በተከፈተው Peal Center For Chrisitian Living በተባለው ፋውንዴሽን አማካይነት ውርሱ ለመላው ዓለም እየተዳረሰ ይገኛል።

አሳታሚና አከፋፋይ- ዘላለም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አገደ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ወታደሮቿ መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ይህ ወሳኔ የተላለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ነው፡፡በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ግልጽ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን፤ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በሪፖርት ገልጿል።
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፣ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።

የዩክሬን ሃይሎች ጠንካራ ተቃውሟቸውን የፈጠሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሩሲያ ኃይሏን እንድታስወጣ ከፍተኛ ማዕቀብ ጥለዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አገደ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ወታደሮቿ መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ወሳኔ የተላለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ነው፡፡በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ግልጽ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን፤…
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሩሲያን ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተቃወሙ።

ሩሲያ ከምክር ቤቱ እንድትታገድ 93 አባል አገራት ድጋፍ የሰጡ ሲሆን፤ 24 አገራት ሲቃወሙ 58ቱ ደግሞ ድምጽ አልሰጡም።የሩሲያን ከምክር ቤቱ መታገድ ከተቃወሙ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኢራን፣ ቻይና፣ ሶሪያ፣ ቪዬትናም እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ።በርካታ ምዕራባውያን አገራት ግን ሩሲያ ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እንድትታገድ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor
👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች አልታገቱም!

የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች ታግተዋል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት የሆኑት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ጋር ደውዬ አረጋግጫለሁ እንዳለው፣ ለስራ ጉዳይ በሱዳን እንደሚገኙና የሚባለዉ መረጃ ፍጹም ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ታዲዎስ አክለዉም በቀጣይ በአርባ ምንጭ አካባቢ ለሚሰሩ ስራዎች ከአጋሮች ጋር ለመነጋገር ወደ ሱዳን ማቅናታቸዉን ተናግረዉ፣ እርሳቸዉን በሚመለከት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚናፈሰዉን መረጃ እንደማንኛዉም ሰዉ ዛሬ ጠዋት አካባቢ መመልከታቸዉን ገልጸዋል፡፡

“እኔ ሰላም ነኝ”፤በሚወራዉ ነገር ለተደጋገጡና ትክክለኛዉ መረጃን ለማወቅ ለሚፈለጉ ሰዎች የምለዉም ይህንኑ ነዉ ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ከሳኡዲ አረቢያ 101 ሕጻናት ወደ አገራቸው ተመለሱ!

ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ ዛሬ በተከናወነ ሥራ በመጀመሪያ በረራ 101 ሕጻናት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህ ረገድ መንግስት ዜጎችን ወደ አገር በመመለስ የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።

ይህም የመመለሱ ሥራ እስካሁን አስራ አንደኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፣ ከ 4 ሺህ 900 በላይ ዜጎችን ለመመለስ መቻሉም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርቆት ለመከላከል ፈተናውን በታብሌት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ብርሃኑ ነጋ ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ዘገባ ላይ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አንድ ሚሊዮን ታብሌቶችን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሌላ በየትምህርት ቤቱ ፈተና ከመስጠት ይልቅ ተማሪዎች በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲፈተኑ ለማድረግ አንደ አንድ አማራጭ መፍትሄ መታሰቡንም ተናግረዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ሽግግሩን ለማጨናገፍ አሲረዋል ተብለው ተከስሰው የነበሩ የ13 የቀድሞ ሹሞች ክስ ተቋርጦ በነፃ እንዲሰናበቱ በፍርድ ቤት ታዘዘ፡፡

በነፃ እንዲሰናበቱ በፍርድ ቤት ከታዘዘላቸው መካከል የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዱር አንዱ እንደሆኑ አል አረቢ ፅፏል፡፡ጋንዱር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ከመሆኑም በላይ የአገሪቱ የቀድሞ ገዢ የሱዳን ብሔራዊ ኮንግረስ የፖለቲካ ማህበር መሪ እንደነበሩም መረጃው አስታውሷል፡፡

የሱዳን ሽግግር ራሳቸው የጦር አለቆቹ ባለፈው ጥቅምት ወር ባደረጉት ዳግም የመንግስት ግልበጣ እንደተሰናከለ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡የ13ቱ ግለሰቦች በነፃ መሰናበት የቀድሞ ገዢ የፖለቲካ ማህበር ብሔራዊ ኮንግረስ ዳግም እንዲያንሰራራ ጥርጊያው ሊያቀናለት እንደሚችል ግምት አሳድሯል ተብሏል፡፡

[Sheger]
@YeneTube @FikerAssefa
ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግብርና ላይ ብቻ ትኩረቱን ያደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የግብርና ሥነ ተግባቦትና ቴክኖሎጂ ስርዓትን በማዘጋጀት አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ ለማገዝና ግብርናን በሚመለከት ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን መረጃን በመስጠት ግንዛቤን ለማሳደግ በማሰብ የቴሌቪዥን ጣቢያው ለማቋቋም ማሰቡን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች የመጀመሪያውን ዓመታዊ አግሪ ኢኖቬሽን ኮንፈረንስ ያካሄደ ሲሆን፤ በኮንፈረንሱ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች መንግሥታዊ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰኃ እሸቱ (ዶ/ር) በቀጣይ 6 ወራት ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያው ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልፀው፤ በ24 ሰዓታት ሥርጭቱ አካባቢያዊ ሥነ ምህዳርን ባገናዘበ መልኩ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ የግብና እንቅስቃሴዎች እንደሚዳሰሱበት ተናግረዋል።ከገበሬ ለገበሬ፣ የከተማ ግብርና፣ ገበሬዬ ማነው፣ የገበሬዎች የሥራ እድል ፈጠራና ሌሎች የገበሬውን ህይወት የሚያስቃኙ የተመረጡ ፕሮግራሞችም እንደሚተላለፋበት ዶክተር ፍሰኃ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።በተጨማሪም አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማምጣት እና አገር በቀል የምግብ ሥርዓት ፖሊሲዎችን ለማሻሻል የሚረዱ የተለያዩ መሰናዶዎችም በጣቢያው እንደሚተላለፋ ገልፀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ከሳዑዲ አረቢያ በሶስተኛው በረራ 472 ሰዎች ተመለሱ!

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ጥረት ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በዚሁ መሰረት ዛሬ በ3ኛው በረራ ብቻ 472 ሰዎች የተመለሱ ሲሆን፤ 128ቱ ህጻናት፣ የተቀሩት 344 ደግሞ ሴቶች ናቸው።በዛሬው ዕለት ቀደም ሲል በ2 በረራዎች በድምሩ 850 ዜጎች መመለሳቸው ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa