YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ከቻይና ኩባንያ ጋር በጥምረት የኮሮና ቫይረስ ክትባት የማምረት ዕቅዱን እንደሰረዘ አስታወቀ!

በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ ክትባት ፍላጎት ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የማምረት ዕቅዱን መሰረዙን የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ሥራ አስፈጻሚ ሞሐመድ ኑሪ (ዶ/ር)፣ ፋብሪካው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማምረት የሚያስችለውን ጥናት በማድረግ ላይ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ክትባቱን የማምረት ዕቅዱን መሰረዙን አስረድተው፣ ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ ክትባት ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን አንደኛው ነው፡፡ ስሙን መግለጽ ካልፈለጉት የቻይና ኩባንያ ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምተው እንደነበር፣ ነገር ግን የኅብረተሰቡ የመከተብ ፍላጎት ዝቅተኛ ከመሆኑም በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት አነስተኛ ሆኗል የሚለው አመለካከት ወደ ማምረት እንዳይገቡ እንዳደረጋቸው ሞሐመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ሌሎች የክትባት ዓይነቶችን ለማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጸው፣ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመድኃኒትና ለሕክምና ግብዓት አምራቾች ፈተና እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
👉 ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች በምዕራብ ትግራይ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ተፈጽሟል አሉ!

ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል አሉ።ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚሉት ከሆነ ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ የአማራ ኃይሎች እና ባለስልጣናት በምዕራብ ትግራይ ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ወንጀሎች ፈጽመዋል።ሁለቱ የመብት ተሟጋቾች በዛሬው ሪፖርታቸው ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ኃይል ምዕራብ ትግራይ እንዲሰማራም ጠይቀዋል።

በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ ተቀሩት አጎራባች ክልሎች በተስፋፋው የእርስ በእርስ ጦርነት ሁሉም ተሳታፊ አካላት በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲጠየቁ ቆይቷል።የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት፣ የትግራይ ኃይሎች እና የአማራ ኃይሎች በሲቪሎች ላይ የመብት ጥሰት በመፈጸም ተጠያቂ ሲደረጉ ቆይተዋል።

ሁለቱ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ዛሬ ይፋ ያደረጉት እና 'ከዚህ ምድር እናስወግዳችኋለን'፡ በሰብዓዊነት የሚፈጸም ወንጀል እና የዘር ማጽዳት በኢትዮጵያዋ ምዕራብ ትግራይ ዞን" የተሰኘው ሪፖርት የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ምዕራብ ትግራይ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች "የዘር ማጽዳት እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ግኝቶችን ይዟል።

"የኢትዮጵያ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች በምዕራብ ትግራይ እየተፈጸሙ ያሉ ወንጀሎችን ክብደት ለማሳየት ሳይችሉ ቀርተዋል" ሲሉ የአምነስቲ ዋና ጸሃፊ አግነስ ካላማርድ ወቅሰዋል።"የሚመለከታቸው መንግሥታት እየተካሄደ ያለው የዘር ማጽዳት ዘመቻን ማስቆም ብሎም ከአካባቢው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በፈቃዳቸው እና ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ወደ ቀዬያቸው እንዲመለሱ ማስቻል አለባቸው" ሲሉ ዋና ጸሃፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።አክለውም ፍትህ ለተበዳዮች እንዲሰጥ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://bbc.in/3JdybOp

@YeneTube @FikerAssefa
HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ!

HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊያን ረቂቅ ሕጎቹ እንዳይፀድቅ እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከኢትዮጵያ የመድን ኩባንያዎች አንዱን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው የኬንያ ግዙፍ የኢንሹራንስ ኩባንያ አስታወቀ!

ጁቢሌ ሆልዲንግስ የተባለው የኬንያ ግዙፍ የመድን አገልግሎት አቅራቢ ተቋም እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፈቃድ ለማግኘት ጥረት እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።የጁቢሌ መድን ድርጅት ሊቀ መንበር ኒዛር ጁማ “በኢትዮጵያ የመድን አገልግሎት ዘርፍ ከ2022 ዓመት ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ይሆናል ብለን እናስባለን ለኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎታችንን በማስታወቃችን ፈቃድ ከተሰጠ የመጀመሪያዎቹ የውጭ የመድን አገልግሎት አቅራቢ እንሆናለን” ማለታቸውን የኬንያው ስታንዳርድ ሚድያ ዘግቧል።

የኬንያው ግዙፍ የመድን አገልግሎት ሰጪ ጁቢሌ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ እየሰሩ ከሚገኙ የመድን አገልግሎት ሰጪዎች መካከል አንዱን በመግዛት ወደስራ ለመግዛት ብንጠይቅም ይህን የሚፈቅድ ህግ የለም ተብለዋል።

ጁቢሌ የመድን ድርጅት በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ከሆኑት መካከል የሚገኙትን ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን ለቢዝነስ ማስፋፊያነት ምቹ መሆናቸውን ገልጿል። በተጨማሪም ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለፈው ሳምንት በቀጠናው ግዙፍ ነፃ የንግድና የሰው ዝውውር አማራጭ የሆነውን የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን (ኢኤሲ) መቀላቀሏ የተሻለ እድል ስለመሆኑ ተናግሯል።

ጁቢሌ የመድን ድርጅት መቀመጫውን ኬንያ ቢያደርግም በታንዛንያ፣ ቡሩንዲ እና ሞሪሽየስ እየሰራ ይገኛል። እንደ ስታንዳርድ ሚድያ ዘገባ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ የኬንያ ንግድ ባንክ (ኬሲቢ) እና ኢኩዊቲ (Equity) የፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፈቃድ ለማግኘት እየተረባረቡ ነው።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀዝቃዛ ኮንቴነሮች ባለቤት ሊሆን ነው፡፡

በኢትዮጵያ ብቸኛው የመልቲሞዳል አንቀሳቃሽ የሆነው ኢባትሎአድ ለመጀመሪያ ጊዜ 31 ባለ አርባ ጫማ ቀዝቃዛ ኮንቴነሮችን ለመግዛት የሚያስችለውን የጨረታ ሂደት እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡በአጭር ጊዜ ውስጥም የኮንቴነር ይዞታውን ወደ 50 እንደሚያሳድግ የኢባትሎአድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ተናግረዋል፡፡

ቀዝቃዛ ኮንቴነር ወደ መግዛት የተገባው በዋናነት የኢኮኖሚውን ፍላጎት ለመደገፍ መሆኑን ያወሱት አቶ ሮባ እንደቢዝነስ አስበነው አይደለም ብለዋል፡፡የኢባትሎአድ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ደንቡ እንደተናገሩት ለ31 ኮንቴነሮች ግዥ ሁለት ጨረታ የወጣ ቢሆንም በሚጠበቀው መልኩ ተሳታፊዎች ስላልቀረቡ ሶስተኛ ጨረታ ወጥቷል ይህ ጨረታም በቀጣይ ሳምንት ይከፈታል ብለዋል፡፡

የኢባትሎአድ ውሳኔ ያደነቀው የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማህበር ለዘርፉ እጅግ ጠቃሚ ነው ብሏል፡፡የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለካፒታል እንደተናገሩት በቀዝቃዛ ኮንቴነር በመታገዝ አትክልት እና ፍራፍሬን በመርከብ መላክ በአለም አቀፍ ገበያ እጅግ ተወዳዳሪ ያደርገናል ብለዋል፡፡
አክለውም ከአበባ ቀጥሎ የአገሪቱ ሰፊ ተስፋ የአትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ ነው ይሄን እምቅ እድል ለመጠቀም እንደዚህ ያሉ የገበያ ሰንሰለቶች መመቻቸት እና መስፋት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት ባከናወነው ፈጣን እንቅስቃሴ ኢባትሎአድ በአጭር ጊዜ የመደበኛ ኮንቴነር ግዢውን ከ 3 ሺ ወደ 14 ሺ ማድረሱ አይዘነጋም፡፡ይህም በአለም ደረጃ በኮንቴነር እጥረት እየተከሰተ ያለውን የጭነት መጓተት እና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና በብልሃት ለማለዘብ ረድቶታል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከእስር ተለቀቀ

ፍርድ ቤቱ ትላንት መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ መወስኑ ይታወሳል።

የተራራ ኔትዎርክ በይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከታሰረ ትላንት 117 ቀናት ቢሆነውም ክስ ሳይመሰረትበትና የዋስ ይግባኝ ጥያቄውም በጊዜ ቀጠሮ እየተላለፈ ዉሳኔ ሳያገኝ እስከ ትላንትና መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ጋዜጠኛው ላይ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኛው በጠበቃው በኩል መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም በዋስ እንዲለቀቅ የሚጠይቅ የዋስ መዝገብ ከፍቶ ነበር፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስ መዝገቡን ከተመለከተ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ለመጋቢት 08, 13, 15, 20 እና 27 ተለዋጭ ቀጠሮ እየሰጠ ቆይቷል።

በመጨረሻም ትላንት መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጋዜጠኛው የዋስትና መብት እንዲከበርለት ውሳኔ አሳልፏል።በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ከእስር መለቀቁ ተሰምቷል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ብሌዝ ኮምፓውሬ በቶማስ ሳንካራ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ቶማስ ሳንካራ የተገደለው በብሌዝ ኮምፓውሬ በተመራ መፈንቅለ መንግሥት ከ35 ዓመት በፊት እአአ በ1987 ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዕሮብ እና አርብን የቅሬታ የመቀበያ ዕለት እንዲሆን ወሰነ!

የመዲናዋ አስተዳደር ዕሮብ እና አርብን የቅሬታ የመቀበያ ዕለት እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።ውሳኔው ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የነዳጅ ድጎማ ሊደረግላቸው ነው!

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የነዳጅ ድጎማ ሊደረግላቸው መሆኑ ተገለፀ።የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በላከው መግለጫ፤ በከተማው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ማድረግ በሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የድጎማ ስርዓቱ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ቢሮው ገልጿል።በድጎማ ስርዓቱ GPS እንዲገጠም መደረጉም የትራንስፖርት ስምሪቱን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቁጥጥሩን ለማሳለጥ ዕድል ይፈጥራል።ድጎማው ከሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆንም የቢሮው መግለጫው ያስረዳል።

ሙሉ ዘገባው: https://am.al-ain.com/article/addis-ababa-to-subsidize-oil-price-for-public-transport

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#በራስ_መተማመን
4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ይህ A Guide to confident Living የተባለው መጽሐፍ በራስ መተማመንን እርካታን መቀዳጀት እንችል ዘንድ ያስችላል።

ቀላል ለማንም ሰው ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተጠቀመው
ዶ/ር ፒል በሕይወታችን ትልቅ መታደስ ማግኘት እንችል ዘንድ አዲስ የሆነ የኃይል መንገድን ይጠቁመናል።

ከሚለግሰን ምክሮች መካከል እንደ፤

* ውስጣዊኃ ይሎቻችንን ነጻ ማውጣት
* ችግሮቻችንን አውጥተን መናገር
* የበታችነት ኮምፕሌክሳችንን መውደድ
* ለሕይወታችን የተረጋጋ ማዕከልን ማግኘት
* የጸሎትን ኃይል መለማመድ
* ከፍርሃትና ሃዘን ነፃነትን ማግኘት
* የትዳር፣ ሙያዊ እና ግለሰባዊ ደስታን ማግኘት ያሉት ይጠቀሳሉ።

ኖርማን ቪንሰንት ፒል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ያስገኘለት The Power of Positive Thinkingን ጨምሮ የ46 ያህል መጽሐፎች ደራሲ ነው።

በኖረበት ዘመን ትልቅ ከተባሉ የሃይማኖት ሰዎች አንዱ የነበረው ዶ/ር ፒል ምንም እንኳ ሕይወቱ ቢያልፍም በስሙ በተከፈተው Peal Center For Chrisitian Living በተባለው ፋውንዴሽን አማካይነት ውርሱ ለመላው ዓለም እየተዳረሰ ይገኛል።

አሳታሚና አከፋፋይ- ዘላለም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በ3 የቀድሞ የሜቴክ የሥራ ኃላፊዎች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈ!

ብርጋዴል ጄነራል ጠና ቁሩንዲን ጨምሮ በ3 የቀድሞ የሜቴክ የሥራ ኃላፊዎች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈ።ተከሳሾች ክስ ተመስረቶባቸው ጥፋተኛ የተባሉት ስልጣንን ያላግባብ በመገልገል፣ የመንግሥት ሥራን በማያመች አኳኋን በመምራት እና የሕዝብ እና የመንግሥትን ጥቅም የጎዳ ተግባር በመፈጸም የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ)፣ 33 እና 407 (1) (ሀ)፣ (2)፣ (3)፣ 411 (1) (ሀ)፣ (ሐ) እና (3) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው ነው።

ተከሳሾቹ የቀድሞው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኮርፖሬት ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ኃላፊ የነበሩት ብ/ጄነራል ጠና ቁሩንዲ߹ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ሌ/ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ እና የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ክንደያ ግርማይ እንዲሁም በቻይና ሕዝባዊት ሪፐብሊክ ቲምስ ኢንተርናሽናል (ሆ.ኮ) ኩባ. ሊሚትድ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩትና (ያልተያዙት) ሚ/ር ዩዋን ሃን ናቸው።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስምንት ቢሊዮን ብር ሊያስገነባቸው የነበሩ ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ በፍርድ ቤት ታገደ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት ያስጀመረውና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ወርቁ ሠፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሊያከናውነው የነበረው የአምስት ሺሕ ተገጣጣሚ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ሕንፃዎች ግንባታ፣ በፍርድ ቤት ዕግድ እንዲቆም መደረጉ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በ21.8 ሔክታር መሬት ላይ የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ቢያስቀምጥም፣ መሬቱ የባለቤትነት ጥያቄ ተነስቶበት ፍርድ ቤት ዕግድ በማውጣቱ ግንባታው እንዲቆም መደረጉን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የቤቶቹን ግንባታ የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥንፉ ሙጬ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ግንባታው ይፋ ከተደረ በኋላ ኮርፖሬሽኑ 291 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተገጣጣሚ ሕንፃ አካላት ኮንክሪትና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ወደ ቦታው አስገብቷል፡፡ በግንባታ ቦታው ላይ አሥር ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፈር ጠረጋና ምንጣሮ ሥራ መካሄዱንም አስረድተዋል፡፡

ይሁንና የመሬቱ ባለቤትነት ይገባኛል ያለ ግለሰብ ጥያቄ በማንሳቱ፣ ኮርፖሬሽኑ ሥራ በጀመረ በቀናት ውስጥ ዕግድ ወጥቶበታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እግዱ ቢወጣም የግንባታ ሥራውን እንደቀጠለ ያስረዱት አቶ ጥንፉ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ዕግድ ከመጣ በኋላ ግን መሬቱ ላይ ያለው ሥራ እንዲቆም መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/3x8hgu4

@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ በጋራ ያወጡትን ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት "በጥንቃቄ እየመረመርኩት ነው" አለ!

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ያወጣው መግለጫ "ሪፖርቱ በሰብአዊ መብት ላይ የሚነሱ ከባድ ጥሰቶች ከሚባሉት በተጨማሪ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱትንና በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸውን የፖለቲካ ለውጦች፣ ሰላምና ደህንነት፣ የውስጥ ወሰን ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል" ያለ ሲሆን "የዘር ማጽዳት፣ የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ክስንም ያቀረበ ሪፖርት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው" ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከሳዑዲ አረቢያ አንድ ሺህ 103 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ዛሬ ተመለሱ!

በሳዑዲ አረቢያ በሪያድ እና ጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችን ወደ ሃገር ቤት የመመለሱ ተግባር ቀጥሎ ፤ በዛሬው ዕለት ከሪያድ 1103 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።በሳምንት ለሶስት ቀናት በቀን ሶስት ጊዜ በሚደረግ በረራ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እንደቀጠለ ነው።

ተመላሾች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞችና ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች የመመለሱ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን እስካሁን የመጡት ሁሉም ተመላሾች ከአዲስ አበባ ወደቀያቸው እንዲሄዱ ተደርገዋል።

የጤና እክል የገጥማቸው በየአካባቢው ባሉ የሕክምና ተቋማት ህክምና እዲያገኙ በመደረግ ላይ ነው። ክልሎችም ተመላሽ ዜጎችን በመቀበል ረገድ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው። በመኖሪያ አካባቢያቸው መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማዕከላት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ 16 መንግሰታዊ ተቋማትን በአባልነት ያቀፈና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋሙ ስራውን በመፈፀም ላይ እንደሆነ የውጭ ጉዳ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor