YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
#በራስ_መተማመን
4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ይህ A Guide to confident Living የተባለው መጽሐፍ በራስ መተማመንን እርካታን መቀዳጀት እንችል ዘንድ ያስችላል።

ቀላል ለማንም ሰው ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተጠቀመው
ዶ/ር ፒል በሕይወታችን ትልቅ መታደስ ማግኘት እንችል ዘንድ አዲስ የሆነ የኃይል መንገድን ይጠቁመናል።

ከሚለግሰን ምክሮች መካከል እንደ፤

* ውስጣዊኃ ይሎቻችንን ነጻ ማውጣት
* ችግሮቻችንን አውጥተን መናገር
* የበታችነት ኮምፕሌክሳችንን መውደድ
* ለሕይወታችን የተረጋጋ ማዕከልን ማግኘት
* የጸሎትን ኃይል መለማመድ
* ከፍርሃትና ሃዘን ነፃነትን ማግኘት
* የትዳር፣ ሙያዊ እና ግለሰባዊ ደስታን ማግኘት ያሉት ይጠቀሳሉ።

ኖርማን ቪንሰንት ፒል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ያስገኘለት The Power of Positive Thinkingን ጨምሮ የ46 ያህል መጽሐፎች ደራሲ ነው።

በኖረበት ዘመን ትልቅ ከተባሉ የሃይማኖት ሰዎች አንዱ የነበረው ዶ/ር ፒል ምንም እንኳ ሕይወቱ ቢያልፍም በስሙ በተከፈተው Peal Center For Chrisitian Living በተባለው ፋውንዴሽን አማካይነት ውርሱ ለመላው ዓለም እየተዳረሰ ይገኛል።

አሳታሚና አከፋፋይ- ዘላለም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በጅማ ከተማ አዲስ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሊገነባ ነው!

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዘጠነኛ የደረቅ ወደብና ተርሚናል መዳረሻውን በጅማ ከተማ እንደሚገነባ አስታወቀ፡፡በጅማ ከተማ የሚገነባው ደረቅ ወደብና ተርሚናል በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚገኙ ተገልጋዮች በቅርበት አገልግሎት በመስጠት የወጪና ገቢ ንግዱን ለማሳለጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በተለይ አካባቢው በቡናና በሌሎችም የግብርና ምርቶች በእጅጉ የሚታወቅ በመሆኑ እነዚህ የግብርና ምርቶች ቀልጣፋ የሎጂስቲክስ አገልግሎት አግኝተው ለውጭ ገበያ እንዲደርሱ በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክና አየር መንገድን ማዕከል አድርጎ ከጅማ ወደ ቦንጋ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ለደረቅ ወደቡ ግንባታ የሚሆን 20 ሄክታር መሬት መመረጡን ከባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድርጅቱ ለመሬቱ የካሳ ክፍያና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ሂደት ላይ እንደሆነና የመሬት ርክክቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብና ፋሲሊቲ ልማት መምሪያ ኢንጂነር አሰፋ ወርቅነህ ገልፀዋል፡፡የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ስምንት ወደብና ተርሚናሎች ያሉት ሲሆን በጅማ ከተማ የሚገነባው ዘጠነኛው መሆኑ ታውቋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር የሥራ ማቆም አድማ ጠርቶ ከነበረው የነዳጅ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማኅበር ጋር መግባባት ላይ መድረሱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ማኅበሩ በትርፍ እየሰሩ ላሉት ነዳጅ አመላላሽ ቦቴዎች መንግሥት ዝቅተኛ የትርፍ መጠን ይወሰንላቸው በማለት ላነሳው ጥያቄ፣ ሚንስቴሩ ምን ምላሽ እንደሰጠ ግን መግለጫው አላብራራም። ማኅበሩ የነዳጅ ቤቴ ባለንብረቶች በኪሳራ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሶ ባለፈው ሳምንት የጠራውን አድማ ከትራንስፖርት ሚንስቴር ጋር ገንቢ ውይይት መጀመሩን በመግለጽ መሰረዙን ትናንት ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ከአፍሪካ 100 ምርጥ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች አንዷ ሆኑ!

የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የ2021 ምርጥ 100 አፍሪካዊያን ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች አንዷ ሆነው በሪሴት ግሎባል ፒፕል እና አቫንስ ሚዲያ ተመረጡ።ይህ ዓመታዊ ምርጫ በተባበሩት መንግስታት ዘላቂ ልማት ግቦች ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን በአፍሪካ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ እና ስኬታማ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ዕውቅና የሚሰጥ ነው።

የ2021 ምርጥ 100 አፍሪካዊያን ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እንስት አመራሮች ያላቸውን አርአያነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንዲሁም ትርፋማነተን በማሳደግ እና አጠቃላይ ዘላቄታዊ የልማት ግቦችን ለማስመዝገብ በኩባንያቸው፣ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የነበራቸውን አበርክቶት ከግምት ውስጥ በማስገባት የቀጣዩን ትውልድ ሴት ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ለማነቃቃት ያለመ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor
👍1
👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሪ ፍቃድ በጉምሩክ በኩል እንዲገቡ ተወሰነ!

መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች፤ ዘይት፣ ስኳር፣ ስንዴ፣ የሕፃናት ወተት እና ሩዝ ያለውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መንግስት ወሰነ። መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦቹ ያለውጭ ምንዛሪ ፈቃድ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል እየተፈቀደ እንዲገቡ ተወስኗል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ “በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት እንዲቻል” እንዲሁም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተወሰነ ነው።

ሚኒስቴሩ ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ጀምሮ መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ምንጩ በብሔራዊ ባንክ እየተረጋገጠ እንዲገቡ ለስድስት ወራት መወሰኑን አስታውሷል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
"የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችን የጣሰ ነው።"፦ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት ምክር ቤቱ መጋቢት 2013 ባወጣው ‹‹የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ›› (አዋጅ ቁጥር 1238/2013) ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችን የጣሰ ሆኖ አግኝቶታል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አስታወቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 29 ቀን 2014 ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ሥብሰባው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት ማፅደቁ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል።

የመግለጫውም ሙሉ ቃል እንደሚከተው ቀርቧል፦

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት በተመለከተ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 29 ቀን 2014 ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል፡፡

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ባደረገው ምርመራ የቦርድ አባላቱ ሹመት ምክር ቤቱ መጋቢት 2013 ባወጣው ‹‹የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ›› (አዋጅ ቁጥር 1238/2013) ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችን የጣሰ ሆኖ አግኝቶታል።

በአዋጁ ክፍል 2፣ ቁጥር 9፣ ንዑስ ቁጥር 2 (ሀ እና ለ)፤ ንዑስ ቁጥር 5 (ሀ)፤ ንዑስ ቁጥር 6 እንዲሁም በዚሁ ክፍል ቁጥር 11፣ ንዑስ ቁጥር 6 ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች በቦርድ አባላት ሹመቱ ከተጣሱ የአዋጁ ድንጋጌዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ለአብነትም የቦርድ አባላት እጩዎችን የመመልመልና የማፅደቁ ሂደት ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን እንደሚኖርበት፤ ሕዝብ እጩ ግለሰቦችን ለመጠቆምና በእጩዎችም ላይ አስተያየት እንዲሰጥ እንዲደረግ እንዲሁም፣ የእጩዎች አመራረጥ ሂደትና የተመረጡ እጩዎች ዝርዝር በመገናኛ ብዙኃን ወይም በሌሎች ኤሌክትሮኒክ ማሰራጫዎች ታትሞ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ በአዋጁ ክፍል 2 ቁጥር 9፣ ንዑስ ቁጥር 2 (ሀ እና ለ) ላይ የተደነገገ ቢሆንም የቦርድ አባላቱ ምልመላና ሹመት ይህንን ድንጋጌ አላከበረም።

እንዲሁም ከቦርዱ አባላት መካከል ሁለቱ ከመገናኛ ብዙኃን እንደሚሾሙ በአዋጁ ሁለተኛ ክፍል፣ ቁጥር 9፣ ንዑስ ቁጥር 5 (ሀ) ላይ የተመለከተ ቢሆንም አንድም የመገናኛ ብዙኃን አባል በዚሁ ሹመት
አልተካተተም።

ከዚህ በተጨማሪም የቦርድ አባላት የሚመረጡበትን መስፈርት በሚደነግገው የአዋጁ ክፍል (ክፍል ሁለት፣ ቁጥር 11፣ ንዑስ ቁጥር 6) ላይ ለቦርድ አባልነት የሚመረጥ ማንኛውም ሰው የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም ተቀጣሪ መሆን እንደሌለበት በግልፅ ሰፍሮ የሚገኝ ቢሆንም ሶስት የገዢው ፓርቲ አባላት የቦርዱ አባል በመሆን ተሹመዋል።

ይህም የቦርዱ አባላት ሹመት የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን የጣሰ እንደሆነ ተጨማሪ
ማሳያ ሆኖ በግልፅ ታይቷል፡፡

የዚህ ድንጋጌ ገቢራዊ ባለመሆኑ ደግሞ በአዋጁ ክፍል 2፣ ቁጥር 6 ላይ ‹‹የቦርዱ አባላት ሥራቸውን ሲያከናውኑ ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጣልቃ ገብነት ወይም ተፅዕኖ ገለልተኛና ነፃ መሆን አለባቸው›› በሚለው ድንጋጌ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና ድንጋጌውን የሚፃረር ተጨማሪ ስህተት እንዲፈፀም አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ይህ ግልፅ የሆነና የማያሻማ የሕግ ጥሰት ያለበት የቦርድ ሹመት ሕግን ሳይሸራረፍ መተግበር ያለመቻልን ችግር አጉልቶ ከማሳየቱ ባሻገር የአገራችንን የሚዲያ እድገት በእጅጉ የሚጎዳ እንደሆነ ያምናል። ሕዝብም በሕግ አውጭው ተቋም ላይ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ እንደሆነ ይገነዘባል።

ከዚህ በተጨማሪም የሙያ ማኅበራችን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቃቸውን አዋጆችንና ድንጋጌዎችን ተፈፃሚነታቸውን በትኩረት መከታተል ስለመቻሉ ጥያቄ የሚያጭር ሆኖ አግኝቶታል።

ስለሆነም ማኅበራችን ይህ ግልፅ የሕግ ጥሰት የተስተዋለበት የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሹመት እና የሥራ ምደባ በአመዛኙ መስተካከል ያለበት መሆኑን በአፅንዖት ሲገልፅ የመገናኛ ብዙኃንን ቁልፍ አገራዊ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

በግልፅ የታየው እርምት የሚሻው እና ውስን የምክር ቤት አባላት ተቃውሞ እና ድምፀ ተዓቅቦ ያቀረቡበት ሹመት ማኅበራችንን እንደሚያሳስበው እየገለፀ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን ዳግም የሚያጤንበትን አማራጭ እንዲመለከት በአፅንዖት ይጠይቃል!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮች ቢሮ ዘግተው መጥፋታቸውን ባለድርሻዎች ገለጹ!

በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የባንኩ ባለድርሻዎች የገዙትን አክሲዮን ገንዘብ ሳይመልሱ ተከራይተውት የነበረውን ቢሮ ለቀው እንደጠፉና ስልካቸውንም እንዳጠፉባቸው አክሲዎን የገዙ ሰዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት፣ ጃኖ ባንክን ለመመስረት ከኹለት ዓመት በፊት አክሲዮን መሸጥ የተጀመረ ሲሆን፣ የተወሰነ ከተሸጠ በኋላ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የሚመሠረቱ ባንኮች የመነሻ ካፒታላቸው አምስት ቢሊዮን ብር ማድረስ እንዳለባቸው መመሪያ ማውጣቱን ተክትሎ በምሥረታ ላይ የነበረው ባንክ ይህንን ማሟላት ባለመቻሉ ወደ ማይክሮ ፋይናንስ እንዲወርድ ተወስኖ ነበር።

ነገር ግን፣ በምሥረታ ላይ የነበረው ጃኖ ባንክ ይህን ለማድረግ መሥራቾችን እንዲያስፍርም ከብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ ቢሰጠውም፣ አብዛኛዎቹ መሥራቾች የባንኩ ምስረታ ወደ ማይክሮ ፋይናንስ በመቀየሩ ላይ አለመስማማታቸው ተሠምቷል።በዚህም፣ መሥራቾቹ ብሔራዊ ባንክ የገባው ሰነድ ፈርሶ ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢፈልጉም አመራሮቹን ማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰው መፍትሔ ይሰጠን እያሉ ነው።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:
https://bit.ly/3jjW2RS

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሰብስቤ ዋሻ በሚባል አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉን ኦቢኤን ዘግቧል።አደጋው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሮቤ ከተማ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በስፍራው በመገልበጡ የደረሰ ነዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
የመርከቦች የወደብ ቆይታ ከ12 ቀናት ወደ 9 ቀናት መቀነሱ ተገለጸ!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመርከብቦችን የወደብ ቆይታ ከነበረበት 12 ቀናት ወደ 9 ቀናት ለመቀመስ መቻሉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሰታወቀ።

በሎጂስቲክሰ ዘርፍ ባለፉት 9 ወራት የመርከብቦችን የወደብ ቆይታ ከነበረበት 12 ቀናት ወደ 9 ቀናት መቀነስ መቻሉን የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ምርቶችን በኮንቴነር አሽጎ ከመላክ አንጻር አፈፃፀሙን በማሻሻል ድርሻዉን ወደ 62 ነጥብ 5 በመቶ ማድረስ መቻሉ ፤ እንዲሁም አንድ ነጥብ 34 ሚሊየን ቶን ካርጎ በባቡር ማጓጓዝ መቻሉን ተችሏል፡፡

በአቪየሽን ዘርፍ ለማሳካት የታቀደዉን የብቃት ማረጋገጫ የመስጠት አገልግሎት ማሳካት የተቻለ ሲሆን የበረራ ደህንነትን ከአለም አቀፍ ደረጃ አንጻር ማስጠበቅ ተችሏል፡፡ የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖር አገልግሎት ለአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የሚሰጠዉን አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ በማከናወን እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡ በዘርፉ ለ71 ሺህ 300 ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ62 ሺህ 420 ጎጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጥቃት መፈጸሙን ተመድ አስታወቀ!

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ በሚገኘው የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ በታጣቂዎች ጥቃት እንደደረሰበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በምስራቅ አፍሪካ እና በግሬት ሌክስ የስደተኞች ተጠሪ ቃል አቀባይ ፌይዝ ኪሲንጋ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ታጣቂዎቹ አዲስ በተከፈተው መጠለያ በመግባት በፈፀሙት ጥቃት ስምንት ስደተኞች በጥይት እንደተመቱ እና እንደቆሰሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ስደተኞች ሕክምና እንደተደረገላቸው እና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ኃላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል።ታጣቂዎቹ በቁጥር ስድስት እንደነበሩ የገለፁት ኃላፊዋ ዓላማቸው ምን እነደነበር ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በትግራይ መጠለያ ጣብያዎች ውስጥ የሚገኙትን ስደተኞች የተሻለ ሰላም ወዳለባቸው አካባቢዎች ለማዘዋወር በሚል ነበር ይህንን መጠለያ ጣብያ ያቋቋመው።ከዚህ ቀደም በማይጸብሪ በሚገኙት ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ስደተኞችን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ ወደተገነባው አዲስ ጣቢያ እንደሚዘዋወሩ ተቋሙ ገልፆ ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍21
በጅንካ እና አካባቢው በሚገኙ ከተሞች የተከሰተው ምንድን ነው?

ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ ክልል ካሉ ዞኖች መካከል አንዷ ስትሆን፤ ጅንካ ከተማ ደግሞ የዚህ ዞን አስተዳድር ዋና መቀመጫ ነች።በዚህ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ ከሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ደግሞ የአሪ ማህበረሰብ አንዱ ሲሆን፤ ይህ ማህበረሰብ በራሱ ዞን እንዲተዳደር የዞንነት ጥያቄ ለደቡብ ኦሞ ዞን እና ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቦም ነበር።

ይሁንና ይህ የዞንነት ጥያቄያችን አልተፈታም በሚል የአሪ ማህበረሰብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ግጭት መቀስቀሱን አል ዐይን አማርኛ ከነዋሪዎች አረጋግጧል።ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የጅንካ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው፤ የአሪ ማህበረሰብ የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወደ ዞን ይደግ በሚል መነሻነት በደቡብ ኦሞ ዞን ሁከት መከሰቱን ተናግረዋል።

ሁከቱ ጅንካን ጨምሮ የአሪ ማህበረሰብ በሚኖሩባቸው ሶስት ወረዳዎች ላይ ከትናንት 9 ሰዓት ጀምሮ ማንነቶችን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የተናገሩት ነዋሪው፤ ለብዙ ዓመታት የተለፋባቸው ንብረቶች የዘረፋ እና በእሳት ማውደምን ጨምሮ ድብደባ ተፈጽሟልም ብለዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://am.al-ain.com/article/identity-based-attacks-have-been-reported-in-four-cities-including-jinka-ethiopia

@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ!

የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በግል ባንኮች ውስጥ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ነው ለተባሉ መሥሪያ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ በግል ባንኮች ውስጥ ያላቸውን ሒሳብ ካልዘጉ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተጻፈው ይኼው ደብዳቤ፣ በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ መሠረት፣ የመንግሥት ገንዘብ ወይም ገቢ የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚወክለው ባንክ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በዚህ ድንጋጌ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሰየመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቻ መሆኑን የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ በግል ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ላይ መሆናቸውንና ይህንን ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው በመታመኑ ዕርምጃው እንደተወሰደ ታውቋል፡፡

በመሆኑም ይህንን ተግባር የፈጸሙ፣ እንዲሁም በዚህ በሒደት ላይ የሚገኙ መሥሪያ ቤቶች የከፈቱትን የባንክ ሒሳብ በመዝጋት ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧቸዋል፡፡

መሥሪያ ቤቶቹ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን በሚደረገው ማጣራት፣ በግል ባንኮች ውስጥ የተከፈተ የባንክ የሒሳብ ቁጥር ከተገኘባቸው፣ ዕርምጃ እንደሚወስድባቸውም የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ሩሲያ ወደ ውጭ በምትልከው ስንዴ ላይ በታሪክ ከፍተኛ የተባለ የታክስ ጭማሪ አደረገች!

የሩሲያ መንግስት ወደ ውጭ በሚላከው ስንዴ ላይ የታክስ ጭማሪ ማደረጉን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ፤ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ ላይ የታክስ ጭማሪ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ይህም በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ቶን ስንዴ ወደ ውጭ ሲላክ 101 ነጥብ 4 ዶላር እንዲከፈል መንግስት ወስኗል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በጂንካ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ከትናንት ጀምሮ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ!

ከሰሞኑ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ወረዳዎች በተነሳ አመጽ ምክኒያት ከትናንትናዉ እለት ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተቋቋመው ኮማንድፖስት እንደታወጀ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰይፉ አየለ ተናግረዋል።

በትናንትናው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል የጸጥታ አካላት ወደ ዞኑ እንደገቡም አረጋግጠዋል። በዚህም በከተማዋ በሚገኙ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንደታገደ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ማንኛቸዉም እንቅስቃሴዎች ለጊዜዉ እንደታገዱ አብራርተዋል።

በተነሳዉ አመጽም እስከአሁን ድረስ የአንድ ሰዉ ህይወት እንዳለፈም ሀላፊዉ አረጋግጠዋል።በአመጹ መኖሪያ ቤታቸዉ እና የንግድ ሱቆቻቸዉ የወደመባቸዉ ዜጎች መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ጸጥታ አካላት በሚገኙበት አካባቢዎች ተጠልለው እንደሚገኝም ተናግረዋል። በጂንካ ከተማ የሚገኘው የቀይመስቀልም ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።

በከተማዋ በዛሬዉ እለት አንጻራዊ ሰላም እንደሚታይባት እና አንዳንድ ባንኮች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የነዋሪዎች እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ሰይፉ አየለ አክለዉ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
“ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ “ ኦፌኮ

ኦፌኮ መንግስት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የማይሰጥ ነው ብሏል።

በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት ፖለቲካዊ መንስዔ ያለው ሲሆን መፍትሄውም ፖለቲካዊ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምንም አሳውቋል፡፡ በአጎራባች የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግር እየተባባሰ ነው ያለው መግለጫው፣ ከሰሞኑ ይፋ እየተደረጉ ካሉ ዘገባዎች መረዳት እንደሚቻለው ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ ስፍራዎች በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን የታወቀ ወሰን በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብሏል ኦፌኮ በመግለጫው፡፡

እነዚህ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል፤አርሷደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ክልሉን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት እንደሚገኙ፣ በተለይም ይህ የጦር ዘመቻና የመሬት ወረራ በምስራቅ ወለጋ፤ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፤ሰሜን ሸዋ፤ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሚገኝ ከአባሎቻችን እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመረዳት ችለናል ብሏል፡፡

ታጥቀው ወረራ እያካሔዱ ባሉ የአማራ ክልል ኃይሎች በሚዲያ የሚሰጡት መግለጫም ይህንኑ ያረጋግጣል ብሏል፡፡ ይህን ወረራ የሚያካሂዱት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጪ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ “ጽንፈኛ” ኃይሎች ናቸው ቢባልም ይህ እውነት እንዳልሆነ የሚያመላክቱ ማስረጃዎች አሉ ካለ በኃላ፣ እንዲህ ያለው አሰራር ህገመንግስቱን ከመፃረር አልፎ የሁለቱ ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች ወደለየለት ጦርነት እንዲገቡ በር የሚከፍት መሆኑን ኦፌኮ አበክሮ ያስጠነቅቃል፡፡

ይህ በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እየታገዘ የሚካሔደው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ዘመቻ ቀድሞውንም ባልሻረ ቁስል ላይ ጨው በመነስነስ የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ወደከፋ የመጠፋፋት ጦርነት ሊገፋ እንደሚችል ሁለቱም ወገኖች ሊገነዘቡ ይገባል ሲል ገልጿል፡፡

በሁለቱ ክልሎችና እነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መካከል የሚደረገው ጦርነት አገሪቱንም ለብተና፤ የአፍሪካን ቀንድ ደግሞ ለከፋ አለመረጋጋት የሚያጋልጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👎9👍8