YeneTube
የአማራ ብልፅግና በሙስና ተሳትፈዋል የተባሉ አመራሮቹን አገደ። የፓርቲው አባል አቶ ፀጋ አራጌ የብልፅግና አመራሮች ላይ ያነሱትን የገንዘብ ምዝበራ ክስ ተከትሎ የተለያዩ ሀሳቦች ሲሰነዘሩ ቢቆዩም ጉዳዪን የመከረበት የአማራ ብልፅግና ችግሩ እውነት ሆኖ ስላገኘው በአመራሮቹ ላይ እርምጃ ወስዷል። እርምጃው ገንዘቡን የወሰዱ አመራሮች በድርጅቱ ጉባዔ እንዳይሳተፉ: የወሰዱትን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፍሉ እና…
"በአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፓርቲው ሃብት የሆነ ተቀማጭ ገንዘብ ለአመራሮችና ሠራተኞች የረጅም ጊዜ ብድር አሠራር ስርዓት በመዘርጋት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመዋዋል ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይኸው አሠራር ከፓርቲ የገንዘብና ሃብት አስተዳደር ስርዓት አኳያ ህገ ደንቡን የሚጣረስ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የውሳኔ አሰጣጥና የስራው አፈፃፀም ከፓርቲው ህገ ደንብና አሠራር ጋር የሚቃረን መሆኑም ተረጋግጧል፡፡
በመሆኑም በብድር ስም የወጣው የፓርቲው ገንዘብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከነ ወለዱ ታስቦ ተመላሽ እንዲደረግና ዝርዝር ሁኔታው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በብድር ስም ገንዘብ የወሰዱ አመራርና ሰራተኞችም ከያዙት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነት ከየካቲት 25/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ሆኖም ለአሰራሩ ተገዥ በመሆን ተፈፃሚ የማያደርጉ ግለሰቦች ካጋጠሙ በህጉ መሰረት ተጠያቂነታቸው የሚከናወን ይሆናል፡፡
ይህ የማጣራትና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በፓርቲው ህገ ደንብና አሰራር መሰረት በኦዲት ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን መርማሪነት የውሳኔ ሃሳብ አቅራቢነት ተመስርቶ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ መርምሮ ውሳኔ የሰጠበት ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በፓርቲው የውስጥ አሠራር መሰረት ለመላ የፓርቲው አባላትና አመራሮች በተዋረድ በግልጽ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡"
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
የካቲት 25/2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር
@YeneTube @FikerAssefa

አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

የሻረግ_ቅመማ_ቅመም
#YesharegSpices
የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ሲፈልጉ የሻረግ ቅመማ ቅመም ብለው ይጠይቁ
🔔 አዲስ አበባ በሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል
☎️ +251 911 66 47 75
+251 911 87 28 27
🔴 የሻረግ ቅመማ ቅመም
ምርጥ ጣዕም❗️

📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct
📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነዳጅ ቆጣቢ ነው የተባለለትን የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ከቦይንግ ሊገዛ ነው!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 Freighter የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላንን ለመግዛት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ብለዋል።
አዲሱ ቦይንግ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ እንደሚረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ57 በላይ የጭነት አገልግሎት መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ በዓመት እስከ 490 ሺህ ቶን ድረስ ወደመዳረሻዎቹ ያጓጉዛል።በአፍሪካ ግዙፉ የጭነት አጓጓዥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት አገልግሎቱን እ.አ.አ በ2035 ከዓለም ምርጥ 20 የጭነት አጓጓዥ አየር መንገዶች መካከል ለመሆን ራዕይ አስቀምጧል።
[@AddisZeyebe]

የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት መታሰቢያ እየተከበረ ነው!
ኢትዮጵያውያን የዚያድባሬን ወራሪ ጦር ያሸነፉበት የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡የዚያድባሬ ጦር ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረበትና ድል የተደረገበት የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው።በዓሉ አዲስ አበባ በሚገኘው በኢትዮ ኩባ ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ የጦር ጄኔራሎች፣ መኮንኖች እና ወታደሮች እንዲሁም ወጣቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
[FBC]

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ደካማ እና በራስ መተማመን የሌለው ሲሉ ወረፉት፡፡
ዜሌንስኪ ኔቶን ያብጠለጠሉት የአገራቸው የአየር ክልል ከበረራ ዕግድ እንዲሆን በተደጋጋሚ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ ምክንያት እንደሆነ ኒውስ ማክስ ፅፏል፡፡ምዕራባዊያን ዩክሬይንን አይዞሽ አይዞሽ ሲሏት ቢቆዩም የጦር መሳሪያ እንሰጥሻለን ከማለት ባለፈ በጦር ተግባር ይሄ ነው የተባለ እርዳታ አላደረጉላትም፡፡
በዚህም የተነሳ የዩክሬይኑ ፕሬዝዳንት ብቻችን ነው የምንታገለው ሲሉ አማርረዋል፡፡ዩክሬይን ከሩሲያ የሚሰነዘርባትን ጥቃት በመከላከሉ ከምዕራባዊያን በኩል ብዙ ጠብቃ ነበር፡፡ኔቶ ግን በዩክሬይን ከበረራ ዕግድ የአየር ክልል ማጠሩ በድፍን አውሮፓ ጦርነት ሊያስነሳ ስለሚችል አልቀበለውም ማለቱ ተሰምቷል፡፡
በዩክሬይን ሰማይ የሩሲያ የጦር ጄቶች እና ሂሊኮፕተሮች እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው፡፡የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ልዩ ያሉትን የዩክሬይን ዘመቻ ሲጀምሩ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክር 3ኛ ወገን ካለ ውርድ ከራሴ ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ሩሲያ በዩክሬይኖቹ ማሪዮፖል እና ቮልኖቭካ ከተሞች ሰላማዊ ሰዎች ለቅቀው እንዲወጡ ጊዜያዊ የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
✍Sheger

በዳውሮ ዞን የድንጋይ ከሰል ማጠቢያና ማበልፀጊያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና በማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራው ልዑክ በማዕድን ዘርፍ ኩባንያዎች ለሚለማው የድንጋይ ከሰል ማጠቢያና ማበልፀጊያ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ ለማስቀመጥ ዳውሮ ዞን ገብቷል።ፋብሪካው የሀገርቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ ከማሳደግም ባለፈ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።ልዑኩ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ሲደርስ በከተማው ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ርዕሰ መስተዳደሩና ሚኒስትሩ በታርጫ ከተማ ዙሪያ ወረዳ ለሚገነባው የድንጋይ ከሰል ማጠቢያና ማበልፀጊያ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩ አስታወቀ።
ባልደራስ ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ "ዛሬ የካቲት 26 የሚከበረውን የካራማራ የድል በዓል ለማክበር በድላችን ሀውልት የተገኘው የባልደራስ ቡድን ወደ አደባባዩ እንዳይገባ ከተደረገ በኋላ፣ የቡድኑ አባላት በሙሉ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።" ሲል አሳውቋል።
ፓርቲው፤ ፕሬዘደንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል ሲል ነው የገለፀው።
ባልደራስ አጠቃላይ ታሰሩብኝ ያላቸውን አባላት ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡-
1. ስንታየሁ ቸኮል
2. አስቴር ስዩም
3. አስካል ደምሌ
4. ፋሲል ማሞ
5. ፋሲል ውሂብ
6. ሳሙኤል ዲሚትሪ
7. አንተነህ አማረ
8. ሶስና ፈቃዱ
9. ማህሌት እሸቱ
10. ቢኒያም ታደሰ
11. ሰለሞን አላምኔ
12. ጌጥዬ ያለው
13. ወግደረስ ጤናው
14. አንተነህ ሞትባይኖር
15. መአዛ ታደሰ
16. አዶኒያስ ገሠሠ
17. ፍቅረማርያም ሙላቱ
18. ናትናኤል አቤል
19. ነብይልዑል ይልማ
20. ኩራ ገብሬ
21. አቤል አለምነህ
22. አለም ደመቀ /አሌክስ ሸገር/
23. ስንታየሁ ለማ
24. ብሩክ ጫኔ
25. ተስፋዬ ከበደ
26. ዳዊት ታዬ
27. ቴዎድሮስ አንተነህ
28. ሊዲያ አበበ ሲሆኑ፤ አባላቱ ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ መታሰራቸውን ፓርቲው ገልጿል።

በኢትዮጵያ በዓመት እስከ 20 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በስኳር በሽታ ህይወታቸው ያጣሉ ተባለ!
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 2 ሚሊዮን ሰዎች ከስኳር በሽታ ጋር የሚኖሩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው ሲል የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ተላለፊ ካልሆኑት በሽታዎች መካከል አንዱ በሆነው በስኳር ህመም ሳቢያ በኢትዮጵያ ቁጥራቸው እስከ 20ሺህ የሚደርሱ ዜጎች በየዓመቱ በስኳር በሽታ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡
በእድሜ የገፉ ሰዎች ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉ ቢገለጽም የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መዉሰድ ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ ለበሽታው ተጋላጭ የሚያደርጉ ሌሎች ዋና ዋና መንስኤዎች መሆናቸዉን በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አዲሱ ወርቁ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም በመባል የሚታወቀው በኢትዮጵያ አሳሳቢቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ገልጸው የክብደት መጨመር ዋነኛው የበሽታው አጋላጭ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የስኳር ህመምን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን 80 በመቶ ያህሉን መከላከል እንደሚቻል የተናገሩት ቡድን መሪው ህብረተሰቡ በበሽታው እንዳይያዝ የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት ሚኒስቴርመስሪያ ቤቱ እቅድ ስለመያዙም አስታውቀዋል፡፡የበሽታ አይነቱ ምልክት የማያሳይ በመሆኑም በጤና ጣቢያዎች፣ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች ላይ የሚደረጉ የምርመራ ውጤት ስራዎችን ለማሻሻል ብሎም ህበረተሰቡ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ የግንዛቤ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
[ዳጉ ጆርናል]

#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022
Less than a month to go until this Global Hybrid expo & it will take place onsite at the magnificent Abrehot Library as well as Virtually.
Few spots left so make sure you book your booth. Click here and REGISTER NOW: www.backtoschoolafrica.com
If you are one of these, come join us:
Schools, Colleges & Universities, School Management Solution Providers, Software developers, App developers & Coders, Start-ups & TECH Entrepreneurs, Education Consultants, STEM Education Incubators, Digital Service Providers, Education Material Producers & Suppliers, Digital Libraries, NGOs & related.
For more info: +251 974 0820 36/37

Job alert!
El Aenon export and Import
Position: Junior Accountant
Our company wants to Hire Junior Accountant who have minimum experience in peachtree, and know how to handle pharmaceutical financing system.
Must graduated from known university/College
Job type: permanent
Salary: Negotiable
Required quantity 1
CGPA 3.25 for men
3.00 for girl
Address: Tuludimtu
Contact email: elaenon11@gmail.com
0941483948

ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ የሚያደርግ አካል ከራሺያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ይገጥማል ሲሉ አስጠነቀቁ!
የራሺያው ፕረዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው መልዕክታቸው እንዳሉት በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ እቀባ(No Fly Zone) የመጣል እቅድ ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ካልሆነ ግን በጦርነቱ ቀጥታ እየተሳተፉ መሆናቸውን ይወቁ ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የዩክሬን ባለስልጣናት ኔቶ በዩክሬን ከበረራ ነፃ ቀጠና እንዲፈጥር መወትወታቸው ከተሰማ በኋላ ነዉ። ምንም እንኳን የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በዩክሬን የበረራ እቀባ መጣል ማለት የራሺያን የጦር ጄቶች በቀጥታ መትቶ መጣል እንደማለት ስለሆነ ይህን ማድረግ ጉዳዩን ያወሳስበዋል በማለት ይህንን እንደማያደርጉ ቢገልፁም።ዘገባው የዘ ቴሌግራፍ ነዉ

በጋምቤላ ከተማ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያባዙ ነበር የተባሉ 2 የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡
የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ እንዳሉት ÷ግለሰቦቹ የናይጀሪያ እና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ÷ኅብረተሰቡ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት የፌደራልና የክልሉ ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ ክትትል በማድረግ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በወቅቱም ባለ 100 የአሜሪካ ዶላር፣ 5 ሺህ የኡጋንዳ ገንዘብ፣ አንድ የደቡብ ሱዳን ፓውንድ፣ 200 የኢትዮጵያ ብር በተለያዩ ብልቃጦች የተዘጋጀ ፈሳሽና ዱቄት ኬሚካል መሳይ፣ ማስመሪያ እና በርካታ ካኪ ፖስታዎችን በማስረጃነት መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡
የኮንጎ ዜግነት ያለው ግለሠብ የስደተኛ መታወቂያ የያዘ መሆኑን አቶ ኡገቱ አስታውቀው ግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አመልክተዋል።ኅብረተሰቡ መሰል የማጭበርበር የወንጀል ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግና ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም ጥቆማ እንዲሰጥም ጥሪ ቀርቧል።
Via FBC

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ፈጸሙት የተባለው ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ለሕግ መቅረብ እንዳለበት አንድ በፌደራል ደረጃ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ለዋዜማ ተናግረዋል።
ፓርቲው በግምገማው በምዝበራው ስማቸው በሚነሳ በፌደራል ደረጃ ባሉ አመራሮች ላይ እንዳልተነጋገረ ዋዜማ ተረድታለች። በምዝበራው ከሃላፊነት ከታገዱትና በብድር ስም የወሰዱትን ገንዘብ ከእነ ወለዱ እንዲመልሱ ከታዘዙት መካከል፣ የፋይናንስ መምሪያ ሃላፊው ባሕሩ ፈጠነ 8.9 ሚሊዮን ብር፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ ጌትነት አይቸው 8.4 ሚሊዮን ብር፣ የቀድሞው የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ጎሹ እንዳላማው 5 ሚሊዮን ብር እና የፓርቲው ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሃላፊ ፍቃዴ ዳምጤ 1.5 ሚሊዮን ብር መዝብረዋል ተብሏል። በድርጊቱ የትኛው የፓርቲው የፋይናንስ ወይም የስነ ምግባር ሕግ እንደተጣሰ ለጊዜው አልተብራራም።
Via Wazema

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሜቴክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከተከሰሱበት ወንጀል በነፃ ተሰናበቱ!
የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውኃ ከሚያርፍበት 123,189 ሔክታር ሪዘርቬየር (ውኃ መያዣ) ቦታ ደን ምንጣሮ ጋር በተያያዘ ከ1.983 ቢሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን (ሜቴክ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤል፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር) ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ሙስና ወንጀል ችሎት የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ብይን ሰጠ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአጠቃላይ 50 ተከሳሾች ላይ ክስ መሥርቶ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲከራከር የከረመ ሲሆን፣ ክርክሩን በአካል ተገኝተው የተከራከሩት ጥቂት ሲሆኑ ወ/ሮ አዜብ (ኢንጂነር)ን ጨምሮ በርካቶች ክሳቸው የቀጠለው በሌሉበት ነበር፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/24865

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ አስታወቀ።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በነገው እለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ ነው ያስታወቀው፡፡የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳድር ከንቲባ ኮሜቴ ባካሄደው አስችኳይ ስብሰባ ለሸማቾች ኅብረት ሥራ ዩኒየን 10 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር በጀት በመመድበ የግብርና ምርቶችና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተለይም መሠረታዊ የፍጁታ ዕቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ሥራ የተሠራ ነው ብሏል፡፡
በተመጣጣኝ ዋጋ ምግብ የሚሸጡ ቢያንስ በሦስት ክፍለ ከተሞች የቀበሌ ምግብ ቤቶችንና ሥጋ ቤቶችን እንዲከፍቱ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።
በዚህም መሰረት በባለ ሀብት በላየነህ ክንዴ ለባሕር ዳር የሚቀርበው የፊቤላ ዘይት በወቅቱና በበቂ መጠን እየቀረበ ባለመሆኑ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር 883 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ ተገዝቶ "በአለ በጅምላ" በኩል ቀርቧል።
በመሆኑም በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዘይት ይሰራጫል።
ከተማ አሥተዳደሩ ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት አላስፈላጊ ወጭ እንዳያወጡ አሳስቧል፡፡ ኅብረተሰቡ ለሚደረገው የሕግ ማስከበር ሥራ ኹሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪውን አስተላልፏል።
Via AMC

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በይዲድያ አርት ሚኒስትሪ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው "ፈገግ ቢል " የተሠኘው ኘሮግራም በቅርብ ቀን!!!!
በቅርብ ቀን ይጠብቁ
በቅርብ ቀን ይጠብቁ
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ዐረፉ።
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ዐረፉ።
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ዐርፈዋል።
በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡