YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
Forwarded from YeneTube
የሻረግ_ቅመማ_ቅመም
#YesharegSpices

የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ሲፈልጉ የሻረግ ቅመማ ቅመም ብለው ይጠይቁ

🔔 አዲስ አበባ በሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል

☎️ +251 911 66 47 75
+251 911 87 28 27

🔴 የሻረግ ቅመማ ቅመም
ምርጥ ጣዕም❗️
Forwarded from YeneTube
📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct

📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
አሜሪካ ሱዳን የቀይ ባሕር ወደቧን ለሩሲያ የባሕር ኃይል ጣቢያ ማቋቋሚያ ልትፈቅድ ትችላለች የሚል ስጋት እንዳደረባት ዎልስትሪት ጆርናል ዘግቧል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ጀኔራል መሐመድ ደጋሎ ሩሲያ የሱዳንን ብሄራዊ ጥቅም እስካከበረች ድረስ በሱዳን ወደብ ላይ የባሕር ኃይሏን ብታቋቁም ችግር እንደሌለው ከትናንት ወዲያ ተናግረው ነበር። ከሩሲያ ውጭ ሌሎች ሀገራትም ወታደራዊ ጦር ሠፈር ማቋቋም ከፈለጉ ሱዳን ፍቃደኛ እንደሆነች ደጋሎ ጨምረው ተናግረዋል። ሩሲያ በሱዳን የቀይ ባሕር ወደብ ወታደራዊ ጦር ሠፈር እንድታቋቁም ፍቃድ ያገኘችው ከዓመት በፊት ሲሆን፣ ውሳኔው ግን እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንደሚፈጸም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከፑቲን ጋር “የፊት ለፊት እንነጋገር” ጥያቄ አቀረቡ!

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታወቁ።ዜለንስኪ በቀጥታ መነጋገር እንደሚፈልጉ ከመግለጽም ባለፈ ለፕሬዝዳንት ፑቲን “የፊት ለፊት ተገናኝተን እንነጋገር” ጥሪ አቅርበዋል።

ቁጭ ብለው ከፑቲን ጋር ማውራት እንደሚፈልጉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።በቢሯቸው ካለው ጠንከር ያለ ምሽግ ውስጥ መግለጫ የሰጡት ዜለንስኪ ሩሲያ አሁን ባለው ወታደራዊ መስፋፋቷ ከቀጠለች ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትንም ልታጠቃ እንደምትችል ገልጸዋል።“እኔ ፑቲንን ማውራት እፈልጋለሁ፤ ዓለም ፑቲንን ማውራት ይፈልጋል፤ ጦርነቱን ለማስቆም ሌላ አማራጭ የለም” ብለዋል ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ።

[Alain]
@Yenetube @Fikerassefa
በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ!

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራና 16 ተቋማትን ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአርባ ምንጭ ሳምንታዊ መግለጫቸውን ሰጥተዋል፡፡በመግለጫቸውም በሳውዲ እንግልት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ወደ አገራቸው እንዲገቡ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰነድ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ በተመለከተ የጀርመን ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንም አንስተዋል።

ባለፈው ሳምንት የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በአገራቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መምከራቸውንም አመልክተዋል።

በምክክራቸውም በቅርቡ ስለተቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለፃ እንደተደረገና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር በኩል አሁንም እያደረገ ስላለው ትንኮሳ በዝርዝር መነገራቸውን ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Job alert!

El Aenon export and Import
Position: Junior Accountant
Our company wants to Hire Junior Accountant who have minimum experience in peachtree, and know how to handle pharmaceutical financing system.
Must graduated from known university/College
Job type: permanent
Salary: Negotiable
Required quantity 1
CGPA 3.25 for men
3.00 for girl
Address: Tuludimtu
Contact email: elaenon11@gmail.com
0941483948
‘’መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቆራጥ እርምጃዎችን መውሠድ አለበት’’: -ኢዜማ

በአፋር አንዳንድ አከባቢዎች ህወሓት እየፈፀመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቆራጥ እርምጃዎችን መውሠድ አለበት ሲል ኢዜማ ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሠጡት የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አቶ አበበ አካሉ በደቡብ ክልል የሚፈጠሩ ግጭቶች በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት ጭምር ድጋፍ የሚደረግበት በመሆኑ፤መንግስት ራሱን በማጥራት አስቸኳይ የእርምት እርምጃዎችን ሊወሠድ እና የዜጎችን ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል ብለዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከአሶሳ አዲስ አበባ መንገድ ዝግ መሆኑን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

በመተከል ፤ከማሼ፤ማኦ ኮሞ የሚባሉ ወረዳዎች በርካታ ተፈናቃይዎች ያሉ ሲሆን በሸኔ አማካኝነት አንድ ወረዳ ሙሉ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡በካማሺ ዞን ሸኔ እና ጉዴን የተባሉ ታጣቂዎች የጥፋት ተልኳቸውን በጥምረት እየፈጸሙ በመሆኑ የሰብዓዊ እርዳታን ለማድረስ አስቸጋሪ እንደሆነ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ሀላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከ3 መቶ 84 ሺ በላይ ተፈናቃይዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡ከተፈናቃይዎች መካከል ከአጎራባች ክልሎች የመጡ እንዳሉም አቶ መለሰ በየነ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ሸኔ በፈጠረው ችግር ምክንያት ከአሶሳ አዲስ አበባ መንገድ ዝግ በመሆኑ ያን ለማስከፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ሁኔታ መውደማቸውን የተናገሩት ሀላፊው ከተፋናቀይዎች ጋር በተያያዘ ባሉበት ቦታ ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማረድግ ጥረት ቢደረግም ከትምህርት ሚኒስቴርና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚያስፍልግ ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ7ሺህ በላይ የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ደሞዝ ሳይቀበሉ አንድ ዓመት እንዳለፋቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።

መምህራን እና ሰራተኞች ምንም እንኳ የፌደራል መንግሥቱ ቅጥረኛ ቢሆኑም "ደመወዝ ስላልተላከልን የከፋ ችግር ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል።ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከትግራይ ክልል የወጡ መምህራንን ወደ ሌላ ተቋማት ማሸጋገሩን እና በክልሉ ላሉት ግን ምንም ማድረግ እንደማይችል ገልጿል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የቤት ውስጥ የመታሰር ጉዳይን አስመልክቶ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤቶች የጻፈው ደብዳቤ

@YeneTube
ኤዜማ ኦነግ ሸኔ ከተራ እስከ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የዘለቀ ሰርጎ ገብ አደረጃጀት ያለው ነው ሲል መንግስትን ወቀሰ።

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ሸኔ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጣቂ ከ4 እስከ 6 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚያስመርቅ ፓርቲው አሳውቋል፡፡ቡድኑ በጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ በተሰኘ ስፍራ ማዘዣውን በማድረግ ከልካይ ሳይኖረው ሽብር እየፈጸመ ነው ተብሏል፡፡

የቡድኑ አደረጃጀት ውስብስብ እና እስከ ከፍተኛ የመንግስት ባልስልጣናት የተለጠጠ የሰርጎ ገብ አደረጃጀት እንዳለውም ተወስቷል፡፡ሸኔ በተለያዩ አካባቢዎች ታጣቂዎችን እንደሚያሰለጥን ያስታወሰው ኢዜማ በኬንያ ያለውን የሶሎሎ ማስልጠኛንም ስም ጠቅሷል።

በመንግስት መዋቅር ውስጥ አንድ ለ አምስት አደረጃጀት ድረስ ቡድኑ እንደሚገባ እና በጫካ ላለው ተዋጊ ሀይል ጭምር ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ እስከመስጠት የሚደርስ ተግባር እንደሚፈጽም በመድረኩ ላይ ተንጸባርቋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022

Less than a month to go until this Global Hybrid expo & it will take place onsite at the magnificent Abrehot Library as well as Virtually.

Few spots left so make sure you book your booth. Click here and REGISTER NOW: www.backtoschoolafrica.com

If you are one of these, come join us:
Schools, Colleges & Universities, School Management Solution Providers, Software developers, App developers & Coders, Start-ups & TECH Entrepreneurs, Education Consultants, STEM Education Incubators, Digital Service Providers, Education Material Producers & Suppliers, Digital Libraries, NGOs & related.

For more info: +251 974 0820 36/37
ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ 2 አቻ ተለያዩ፡፡

ዛሬ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያን ከባለሜዳዋ ኡጋንዳ አገናኝቷል፡፡ጫዋታውም 2 አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የመልስ ጨዋታ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለተጎዱ ሰዎች ለሚሰጠው ዕርዳታ 205 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልጧል።

ኮሚሽኑ የገንዘብ ዕርዳታውን የጠየቀው፣ ለነፍስ አድን እና ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮችና ኤርትራዊያን ስደተኞች የዕለት ምግብና ተስማሚ መጠለያ ለማቅረብ ነው። ኮሚሽኑ ከጠየቀው ገንዘብ ውስጥ 117 ሚሊዮን ዶላሩ ለአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልል ተፈናቃዮች የሚውል ሲሆን፣ 73 ሚሊዮን ዶላሩ ደሞ በሱዳን በተመድ መጠለያዎች ለተጠለሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይውላል። ኮሚሽኑ መንግሥት በግጭቱ ከመጠለያዎች ለተፈናቀሉ ስደተኞች የአዳዲስ መጠለያ መስሪያ ቦታዎችን እንዲፈቅድም ጠይቋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ ስለ ዩክሬን ግጭት 'ውሸት' እየዘገቡ ያለቻቸውን የውጭ ሚዲያዎችን አገደች!

የሩስያ የሚዲያ ተቆጣጣሪ እ ቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምፅ፣ ራዲዮ ፍሪ አውሮፓ፣ ዶይቸ ቬለ እና መዱዛ የመሳሰሉ የዜና አውታሮችን በሀገሪቷ እንዳይተላለፉ ማገዷን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።

በመካሄድ ላይ ያለውን የሩስያን 'ልዩ ተግባር'፣ የሚያጠቃልለውን የውጊያ አይነቶች እንዲሁም ወታደራዊ እና ሲቪል ሰለባዎችን በተመለከተ ሆን ብለው 'ሐሰተኛ' መረጃ ሲያሰራጩ በመገኘታቸው ነው የታገዱት ተብሏል።

Via Fidel Post (RT)
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ብልፅግና በሙስና ተሳትፈዋል የተባሉ አመራሮቹን አገደ።

የፓርቲው አባል አቶ ፀጋ አራጌ የብልፅግና አመራሮች ላይ ያነሱትን የገንዘብ ምዝበራ ክስ ተከትሎ የተለያዩ ሀሳቦች ሲሰነዘሩ ቢቆዩም ጉዳዪን የመከረበት የአማራ ብልፅግና ችግሩ እውነት ሆኖ ስላገኘው በአመራሮቹ ላይ እርምጃ ወስዷል። እርምጃው ገንዘቡን የወሰዱ አመራሮች በድርጅቱ ጉባዔ እንዳይሳተፉ: የወሰዱትን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፍሉ እና ከስራ እንዲታገዱ ወስኗል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa