YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በቀድሞው ገዥ ፓርቲ አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል መጠነ ሰፊ ዘመቻ እንደጀመሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ መንግሥት የዘመቻ አዋጅ ያወጣው፣ ሰሞኑን በሀገሪቱ በርካታ ግዛቶች በኑሮ ውድነት ሳቢያ በተቀሰቀሰው ከባድ ሕዝባዊ አመጽ ውስጥ የቀድሞው ገዥ ፓርቲ እጅ አለበት በማለት ነው፡፡ ሁሉም ግዛቶች የቀድሞውን ገዥ ፓርቲ መሪዎች እና ቀንደኛ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲያውሉም ታዘዋል፡፡

ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ቲክቶክ የተሰኘው የቪዲዮ ምስሎች ማጋሪያ የማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ የቀጣዩ የአውሮጳ ዋንጫ ስፖንሰር እንደሆነ የአውሮጳ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት (UEFA) ይፋ አደረገ። ውድድሩን በገንዘብ በመደገፍ ቲክቶክ አራተኛው የቻይና ድርጅት ኾኗል። ቲክ ቶክ የአውሮጳ የእግር ኳስ ዋንጫን ለመደገፍ ምን ያህል ገንዘብ እንደበጀተ ግን አልተገለጠም። የ2020 አውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070
የእንግሊዙ የመገናኛ ብዙኀን ተቋም ቢቢሲ በቻይና ታገደ፡፡

የቻይና የብድካስት ተቆጣጣሪ፤ የቢቢሲን የዜና ጣቢያ በቻይና ስርጭቱ እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡የመገናኛ ብዙኀን በቻይና ዘገባዎችን ሲሰሩ ማክበር ያለባቸዉን መመሪያ ቢቢሲ ጥሷል ተብሏል፡፡የዜና ጣቢያዉ በቻይና የዊገር ግፉአኖች ላይ የሠራዉን ዘገባ ተከትሎ ነዉ የአየር እንዲወርድ የተደረገዉ፡፡

የቻይና ብሄራዊ የፊልም፣ ቴሌቭዥን እና ሬድዮ አስተዳዳር በበኩሉ፤ ቢቢሲ ወርልድ የተሰኘዉ የቴሌቭዥን ጣቢያ በቻይና ላይ የሰራዉ ዘገባ፤ የብሮድካስት መመሪያን የሚጥስ፣ ከሀቅ የራቀ እና የቻይናን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነዉ ማለታቸዉን አሶሼትድ ፕረስ ገልጿል፡፡

አስተዳደሩ እንዳስታወቀዉ ቢቢሲ ከእዚህ በኋላ በቻይና ስርጭቱን አይቀጥልም፤ እንደዉም ለእዚህ ዓመት ያስገበባዉ ቅፅም ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡ ከቀናት በፊት የእንግሊዝ መንግስት፤ የሀገሬን የመገናኛ ብዙኀን መተዳደሪያ ደንብ ጥሷል በማለት የቻይናዉን ሲ ጂ ቲ ኤን የቴሌቭዥን ጣብያ ማገዷ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የሥራ ሠዓት ለውጥ መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፒተር ሆዎ እንደገለጹት የሙቀቱ መጠን እየጨመር በመምጣቱና ለስራ አመቺ ባለመሆኑ ከየካቲት 3 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ ጊዜያዊ የመንግስት ሥራ ስዓት ለውጥ ተደርጓል።

በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል በመደበኛው የሥራ ስዓት ከጠዋቱ አንድ ሠዓት እስከ ስድስት ሠዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሠዓት እስከ አምስት ሠዓት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል።

እንዲሁም ከሠዓት በኋላ ከዘጠኝ ሠዓት እስከ አስራ አንድ ሠዓት ተኩል የነበረው ከአስር ሠዓት እስከ አስራ ሁለት ሠዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን ኃላፊው አስታውቀዋል።

የስራ ሠዓት ለውጡ ወይናደጋ የሆነውን የማጃንግ ዞን እንደማይጨምር ጠቁመው የመንግስት ሠራተኞች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደውን ሥራቸውን እንዲያከናኑ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

በብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ የጋምቤላ ክልል አገልግሎት ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት የክልሉ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 40 ነጥብ 4 ዲግሪ ሴልሽየስ፣ የሌሊቱ ደግሞ 16 ነጥብ 6 ዲግሪ ሴልሽየስ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዋና ኃላፊ ሴቶችን በተመለከተ በሰጡት ጸብ ጫሩ አስተያየት ስልጣናቸዉን ለቀቁ!

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶችን በተመለከተ በተናገሩት አስተያየት በዛሬዉ እለት ስልጣናቸዉን ለቀዋል፡፡በዛሬዉ እለት የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ እና ምክር ቤት ስራዉን ሲጀምር ንግግር ያደረጉት ሞሪ ከዛሬ ጀምሮ የፕሬዝዳንት ስልጣን ቦታዉን እለቃለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሞሪን ማን እንደምተካቸዉ ግን እስካሁን በግልጽ የተነገረ መረጃ የለም፡፡ሞሪ ከቀናቶች በፊት በሴቶች ዙሪያ የሰነዘሩት አስተያየት በጃፓን እና በሌሎች ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስከትሎባቸዋል፡፡

ከስልጣን እንዲለቁ ምክንያት ሆኗል የተባለዉ አስተያየታቸዉ “ሴቶች ከመጠን በላይ ያወራሉ እንዲሁም ጠንካራ የውድድር ስሜት” አላቸው ሲሉ በቦርድ ስብሰባ ላይ መናገራቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

የ83 ዓመቱ አዛዉንት ሞሪ ለንግግራቸዉ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሞሪ ንግግር ተገቢ አይደለም ሲል ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ይህ ዉዝግብ እየተደመጠ የሚገኘዉ የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ሊካሄድ ከስድስት ወር ባነሰ ጊዜ ላይ ሆኖ ነዉ፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ወደትግራይ ክልል በመግባት የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ ተሰጥቷል- የሰላም ሚኒስቴር

የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሰላም ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ላለፋት 3 ወራት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ26 በላይ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራን ለማገዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት ቦታው ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ወደትግራይ ክልል መግባትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት (UN-OCHA) በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (ECC) በምክትል ሰብሳቢነት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፉንና የመልሶ ማቋቋም ሂደቱን የማስተባበር ሂደቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እያስተባባረ እንደሚገኝም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወጪ ሆኗል የተባለው 53 ቢሊዮን ብር ምን ላይ ወጪ እንደሆነ እንደማይታወቅ ተገለጸ።

ይህን ያለው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ለባለ እድለኞች ተላልፈው የሚሰጡበትን ውስብስብ ጉዳዮች እንዲያጠና የተጠየቀው ቡድን ነው።ይህን ጥናት ያካሄደው ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ሲሆን፤ የጥናት ቡድኑን ሲመሩ የቆዩት ቱሉ ቶላ (ዶ/ር) ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና መኖሪያ ቤቶቹ ተላልፈው የሚሰጡበትን ውስብስብ ችግር ለማጥናት ከአራት ወራት በላይ መፍጀቱን ይናገራሉ።

በጥናት ውጤቱም መሠረት ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ወጪ ሆኗል የተባለ 53 ቢሊዮን ብር አለመወራረዱን፣ አልያም ለወጪው ሰነድ አለመገኘቱን ቱሉ ቶላ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል።በተመሳሳይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ21ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን በጥናት መረጋገጡን አስታውቆ ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ እና ተመድ በትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያን ጥረት መደገፍ እንደሚቀጥሉ ገለጹ!

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ከተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡ በርካታ ድርጅቶች እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ወደ ትግራይ የመግባት ፈቃድ ማግኘታቸውን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ 75 የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጠ!

ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት በቦታው ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱና አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ ትግራይ ክልል በመግባትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ ተሰጥቷል።

የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሰላም ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በክልሉ ላለፉት 3 ወራት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ26 በላይ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራትን ለማገዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል በምክትል ሰብሳቢነት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፉንና የመልሶ ማቋቋም ሂደቱን የማስተባበር ሂደቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እያስተባባረ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ ድረ-ገጽ አገልግሎት ላይ ዋለ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በትብብር ለህብረተሰቡ ዕለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃ የሚሰጥ አዲስ ድረ-ገፅ ይፋ አድርጓል፡፡

ድረ-ገጹ በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክ እና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት ማድረግ ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛው የገበያ ስፍራ በምን አይነት ምርት በምን ዋጋ እንደሚሸጥ ካለበት ሆኖ ለማወቅ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡

"www.aaminfo.gov.et" በሚል ይፋ የተደረገው የመረጃ ድረ-ገጽ ከ28 በላይ የገበያ ማዕከላት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚያስመዘግበው እጩ ተወዳዳሪ እንደሌለው አስታወቀ።

ከአራት ወራት በኋላ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ፓርቲዎች የእጩ ተወዳዳሪዎቻቸውን ከሰኞ ከየካቲት 8 እስከ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ማስመዝገብ እንዳለባቸው የምርጫ ቦርድ ጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል።በውዝግብ ውስጥ የሚገኘው ኦነግ ደግሞ የውስጥ ችግሩን ሳይፈታ የእጩ ምዝገባ ወቅት ደርሷል።በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቀናት በቀሩት የእጩዎች ምዝገባ የማስመዘግበው እጩ እንደሌለው ገልጿል።ፓርቲው እንዳስታወቀው ከሆነ በየምርጫ ክልሎች ላስመዘግባቸው ያሰብኳቸው እጩ ተወዳዳሪዎቼ በሙሉ በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡

ምርጫ ስለመካሄዱ በራሱ እርግጠኛ አይደለሁም የሚለው ኦነግ በፖርቲያችን ላይ ከፍተኛ ጫና ከገዢው ፖርቲ እየደረሰበት እንደሆነ ተናግሯል።የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ በቴ ኡርጌሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አስፈላጊ የሚባሉ የምርጫ ዝግጅቶችን ተንቀሳቅሰው ማከናወን እንዳልቻሉ ተናግረዋል።ኦነግ የገጠመው ውስጣዊ መፈረካከስም በራሱ በብልጽግና ፓርቲ ጣልቃ ገብነት የተፈጸመ ነው የሚል ዕምነት እንዳላቸውም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።ብልፅግና የራሱን ከፍተኛ አባላት ከማዕከላዊ አባልነት ሲያግድ ማንም በጸጋ ነው የተቀበለው እኛ በፖርቲያችን ውስጥ ያንን ውሳኔ ስንሰጥ ግን ማንም ሊያከብርልን አልቻለም ብለዋል፡፡ይህም ፓርቲያችን አላስፈላጊ ችግር ውስጥ ለመግባቱ ዋናው ምክንያት መሆኑን አቶ በቴ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች የሚገኘው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሜቲ ፅህፈት ቤት በፖሊስ መጠበቅ ከጀመረ ስድስት ወራት እንዳለፈውም ተናግረዋል።በዚህ ሁኔታ ስራችንን መስራት አንችልም በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፖርቲው ሀላፊዎችና አባላት እየታሰሩ የምናስመዘግበው እጩ የለንም ብለዋል።እጩ ካላስመዘገባችሁ በምርጫው ላትወዳደሩ ትችላላችሁ? ብሎ ጣቢያው ላነሳላቸው ጥያቄ ግን እኛ ምርጫ አንሳተፍም አላልንም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ምክትል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ ኦነግ ባነሳው ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡ ጣቢያው ጠይቋል።እሳቸው እንዳሉትም ታሰሩ የተባሉት ሰዎች እንደ ግለሰብ በሰሩት ወንጀል ተጠርጥረው አንጂ በኦነግ አባልነታቸው አይደለም ብለዋል።ማንም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው ያሉት አቶ ግዛቸው ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ 646 የብልጽግና አመራሮች ህግ በመተላለፋቸው ታስረዋል ብለዋል።ከምርጫ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደሩ ሁሉም ፓርቲዎች ጽህፈት ቤታቸውን ከፍተው እየተንቀሳቀሱ ነው የክልሉ መንግስትም ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ህብረተሰቡ የህገመንግስት ትርጉም የሚስፈልጋቸውን ጥያቄዎች ባግባቡ መገንዘብ ባለመቻሉ ባለፉት 5 ዓመታት የቀረቡ አቤቱታዎች በጣም ዝቅተኛ መሆናቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፍርድ ቤቱ ፕረዚደንትና የአማራ ክልል ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ አቶ አብዬ ካሳሁን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከ2008 ዓ ም ጀምሮ 14 ብቻ የህገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች ቀርበዋል፡፡ከዚህ ውስጥ 4ቱ የህገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው አቤቱታዎች ሆነው በመገኘታቸው በውሳኔ ሀሳብ በማስደገፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ለአማራ ክልል ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ተልከው የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል እንዲፀኑ መደረጉንም አቶ አብዬ ተናግረዋል፡፡10ሩ ደግሞ እንደማያስፈልጋቸው የውሳኔ ሀሳብ እንደቀረበባቸውም አስረድተዋል፡፡ የአቤቱታዎቹ ቁጥር አናሳነት ችግር አለመኖሩን የሚያሳዩ እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕረዚደንቱ፣ በየደረጃው የህገመንግስት ትርጉም የሚሹ ኢ ህገመንግስታዊ ህጎች፣ የተዛቡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና የፍርድ ቤት ዳኝነቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ መብቱን ወደ ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አቤት ማለት አለባቸው ሲሉ አመልክተዋል፡፡በአጠቃላይ በክልሉ ካለው የህዝብ ቁጥር አኳያ የህገመንግስት ትርጉም አቤቱታዎች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘታቸው ህብረተሰቡ ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንደሌለው ማሳያ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዬ፣ የህግ አዋቂዎች፣ ብዙሀን መገናኛና የህግ ተቋማት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል፡፡አማራ ክልል 11 አባላት ያሉት የህገ መንግስት አጣሪ ጉበኤ አሉት፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዶላር በሆነ ወጪ የክትባት ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎችን ልትገዛ መሆኑን አስታወቀች።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በ6 .4 ሚለዮን ዶላር የግዥ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡በዚህ ገንዘብም የማቀዝቀዣ ክፍል የተገጠመላቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚያለግሉ ግብአቶች ግዢ እንደሚፈፀም ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

የጋራ ስምምነቱን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ እና በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ተፈራርመዋል፡ለግዥው 6.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተመደበ ሲሆን የበጀት ድጋፋ የተገኘው ከአለም አቀፉ የክትባት ድጋፍ ድርጅት መሆኑን ኤጀንሲው አስተውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ንግድ ባንክ የወለድ ምጣኔ ጭማሪ አደረገ!

ንግድ ባንክ በየአመቱ በአማካኝ የማስመዘግበው የእድገት መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጌያለሁ ሲል በዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ አቤ ሳኖ በኩል አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ለቤቶች ልማት 9.5 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10.5 በመቶ፣ የማዳበሪያ 9.25 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10 በመቶ፣ የኮርፖሬት ቦንድ ብድር 9 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10 በመቶ፣ የዉጭ ምንዛሬ በአንድ ፔሬድ ማለትም በ90 ቀናት 5.5 በመቶ የነበረዉ ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ማድረጉን ባንኩ ተናግሯል።

በሌላ በኩል ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለመድሀኒት አቅርቦት፣ ለስኳር፣ ለማዳበሪያ እንዲሁም ለዘይት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሬዎች ላይ ያለው የወለድ መጠን ወደ 4.5 በመቶ ዝቅ ማድረጉን ባንኩ ገልጿል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ፊች የተባለው ዐለማቀፍ የሀገራት ብድር ከፋይነት ደረጃ አውጭ ሰሞኑን የኢትዮጵያን የብድር ከፋይነት ደረጃ በ2 ነጥብ ዝቅ እንዳደረገ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ድርጅቱ የኢትዮጵያን ደረጃ ያወረደው፣ መንግሥት የብድር ቅነሳ እንዲደረግለት ወይም የመክፈያ ጊዜ እንዲሸጋሸግለት ቡድን 20 ሀገራትን እንደሚጠይቅ መማሳወቁን ተከትሎ ነው፡፡ ሌሎች ሀገራትም የኢትዮጵያን መስመር ከተከተሉ ደረጃቸውን ዝቅ እንደሚያደርገው ድርጅቱ ገልጧል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካ ኮንግሬስን እና የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደርን የሚያግባባለት ኩባንያ መቅጠሩን ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት ዘግቧል፡፡በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ቬኔብል ከተባለው የፖሊሲ አግባቢ ኩባንያ ጋር የ3 ወራት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ለአገልግሎቱ ኢምባሲው በወር 35 ሺህ ዶላር ይከፍላል ተብሏል፡፡ ኩባንያው የተቀጠረው በሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በትግራዩ ግጭት ላይ የአሜሪካ መንግሥትን ለማግባባት ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሠላም አስከባሪ የሠራዊት አባላትን እያስመረቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጦሯን ለዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ማዝመቷን አጠናክራ መቀጠሏን የመከላከያ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ በማስመረቅ ላይ ነው።ሕግን በማስከበር እና በህልውና ዘመቻ ላይ የቆየው የመከላከያ ሠራዊት የጎረቤት ሀገርን ሠላም ለማስፈን ወደ ጁባ ለመዝመት 15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ስልጠናውን ማጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ቀብሪ ደሀር ፣ ወለጋ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 311 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 3ሺህ 950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1ሺህ 530 ሴቶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሶሰት ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ እና አራት ተማሪዎች ደግሞ የ “ሰብ ስፔሻሊቲ” ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ጥቅምት ወር 1ሺህ 409 ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 13፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 23 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይም የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 39 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa