ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ።
ቦርዱ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እስካሁን የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትን ዘርዝሯል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በማድነቅ በየጊዜው ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፈጣን እና በደብዳቤ ምላሽ አለመስጠቱን ወቅሰዋል። በጽሑፍ ለሚቀርቡ አቤቱታዎች በጽሑፍ ምላሽ አለመሰጠቱን በተመለከተ፦ ቅሬታውን የተቀበሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፦ «ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ» በመጠየቅ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እጅግ መብዛታቸውን ጠቊመዋል።
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa

ምርጫ ቦርዱ ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የ49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ!
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው 6ኛው አገር አቀፍ የምርጫ ሰሌዳ ላይ በተገለጸው መሰረት የካቲት 03 ቀን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ ቀን ነው። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ቦርዱ የምርጫ ምልክት በመውሰድ ለምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በፍላሽ እንዲደርሳቸው ማድረጕን አስታወቋል።
የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በምርጫ ቦርዱ ድረ-ገፅ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በዚህ መሰረት:
በአዲስ አበባ ከተማ - 1,848
በሲዳማ ክልል - 2,247
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 699
አፋር ክልል- 1,432
አማራ ክልል- 12,199
ድሬዳዋ ክልል- 305
ጋምቤላ ክልል- 431
ሃረሪ ክልል- 285
ኦሮሚያ ክልል- 17,623
ደ/ብ/ብ/ህ ክልል- 8,281
ሶማሌ ክልል- 4,057
በአጠቃላይ 49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎች ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር ከስር ከሚገኘው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል።
https://nebe.org.et/am/polling-stations

300 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ!
300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከሰሞኑ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከሌሎች ሃገራት ኢትዮጵያውያን ዜጎች መመለሳቸው ይታወሳል።
[FBC]

ዛሬ ለአስራ አራተኛ ቀን በረሀብ አድማ የቀጠሉትን እነ አቶ ጀዋር ሳራጅ መሐመድን ምግብ እንዲበሉ ሊያግባቧቸው ቃሊቲ ማረምያ ሄደው የነበሩ ሽማግሌዎች እና የእምነት አባቶች ሊያሳምኗቸው አለመቻላቸውን ገለፁ።
የረሀብ አድማው ከቀጠለ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትንም ለማወያየት መታሰቡ ተገልጿል።በእስር ቤት በረሀብ አድማው ከተሳተፉት ውስጥ ታመው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ መኖራቸውም ተገልጿል።
[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የረሀብ አድማው ከቀጠለ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትንም ለማወያየት መታሰቡ ተገልጿል።በእስር ቤት በረሀብ አድማው ከተሳተፉት ውስጥ ታመው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ መኖራቸውም ተገልጿል።
[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በትግራይ ክልል በዕለት ደራሽ ምግቦች የፍትሐዊነት ችግሮች መስተዋላቸውን፣ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በክልሉ የዕለት ደራሽ ምግቦች አቅርቦት ሥርዓቱን ጠብቆ እየሄደ ባለመሆኑ ምክንያት አቅርቦቱን ማግኘት ለሌለባቸው ሰዎች ማስተላለፍ፣ ድጋፉን ማግኘት ያለባቸው ሰዎች አለማግኘትና ከተሰጠው መመርያ ውጪ የቤተሰብ ቁጥርን መሠረት ሳያደርግ ዕርዳታ መስጠትና መሰል ዓይነት ችግሮች እንደሚስተዋሉ ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ : https://bit.ly/2NeaRZF

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሚየንማር መፈንቅለ መንግሥት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችላቸውን ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
ጆ ባይደን ያሳለፉት እቀባ የጦሩ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና ከነሱ ጋር የንግድ ሽርኪያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት ሁሉ ላይ ነው።ከዚህም በተጨማሪ በአሜሪካ ተቀማጭ የሆነ የሚየንማር 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ጦሩ እንዳያገኘው ለማድረግ እግድ ለመጣል በሂደት ላይ ነው ተብሏል።መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ አንዲት ግለሰብ ጭንቅላቷ ላይ በጥይት ተመትታ በመዲናዋ ናይ ፓይ ታው በሚገኝ ሆስፒታል ህይወቷ አልፏል።በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ፣ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት በመተኮስ በሚሞክርበት ወቅት ነው ሴትዮዋ የቆሰለችው።
ግለሰቧ በጥይት እንደተመታች ማስረጃ መኖሩን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ።
[BBC]

በኦንላይን ሊሰጥ የነበረው የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በወረቀት ይሰጣል ተባለ።
ፈተናው ከፊታችን የካቲት 29፣2013— መጋቢት 2፣2013 ይሰጣል።ፈተናው በተዘጋጁ 1185 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ሰምተናል።በወረቀት እንዲሰጥ የተወሰነው ታብሌቶች ወደሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው ነው ተብሏል።ለተፈጠረው መዘግየትም የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር) ይቅርታ ጠይቀዋል።
በትግራይ ክልል ያሉ 12,000 ተማሪዎች ከፊታችን ሳምንት ጀምሮ በክልሉ ባሉ 4 ዩንቨርሲቲዎች ገብተው ይፈተናሉ ተብሏል።

ዚምባብዌ 600ሺ ሚሊዮን የሲኖፋርም የኮሮና ክትባት መግዛቷን አስታወቀች!
ዚምባብዌ ቻይና በእርዳታ መልክ ከሰጠቻት 200ሺ ክትባቶች በተጨማሪ 600ሺ የሲኖፋርም ክትባት መግዛቷን የሀገሪቱ የመረጃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ እንዳለው የተገዛው መድኃኒት በፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ዚምባብዌ ይገባል ተብሏል፡፡ሚኒስትር ሞኒካ ሙትስቫንግዋ እንደተናገሩት ዚምባብዌ የስፑትኒክ ክትባትን ለመግዛት ከሩሲያ ጋር በመደራደር ላይ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ በመጋቢት መጨረሻ 800ሺ የሚሆን ክትባት ከውጭ ይገባል፡፡
[Al-ain]

በአንኮበር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በአንኮበር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ተጨማሪ 30 ሰዎች ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳ ደርሶባቸዋል፡፡የትራፊክ አደጋው የደረሰው ትናንት ለሊቱን በጭነት ላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሀርአምባ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ ወደ ጎረቤላ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሸከርካሪ ተገልብጦ ነው፡፡ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደጤና ጣቢያ ተወስደው ርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ከወረዳው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

በትግራይ ክልል ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ ብቻ 108 የአስገድዶ ደፈራ ወንጀሎች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከጥር 2 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ እና በደቡባዊው የትግራይ ዞን አላማጣ፣ መሆኒ እና ኩኩፍቶ ከተሞች ክትትል እና ምርመራ በማድረግ፣ በተለይም በመቀሌ የሚገኙ ከፍተኛ ወታደራዊ እና ሲቪል አመራሮችን፣ የጤና ዘርፍ ሰራተኞችን፣ ነዋሪዎችን፣ ተጎጂዎችን እና ተፈናቃዮችን አነጋግሬያለሁ ብሏል።
ኢሰመኮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በትግራይ ክልል መቀሌን ጨምሮ በአራት ሆስፒታሎች በተገኘ መረጃ መሰረት ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ ብቻ 108 የአስገድዶ ደፈራ ወንጀሎች ተፈጽመዋል።
እንዲሁም በመቀሌ እና የኢሰመኮ ክትትል ቡድን በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ በማዳረስ ረገድ አበረታች እርምጃዎች አሉ ብሏል።
ይሁንና አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎቱ አሁንም አልተሟላም ያለው ኮሚሽኑ ከሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወደ መቀሌ የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃ እና የጤና አገልግሎት አቅርቦት እጥረት አለባቸው።
በተለይም በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና የጤና ተቋማት አገልግሎት መቋረጥ፣ ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች የህክምና እርዳታ ለማግኘት ረዥም የእግር መንገድ እንዲያደርጉ አስገድዷል።
ኢሰመኮ በአይደር ሆስፒታል የሕፃናት ተኝቶ መታከሚያ ከፍልን በጎበኘበት ወቅት፣ ተኝተው በመታከም ላይ ከነበሩት 20 ከፍተኛ የአዕምሮ ጭንቀት እና ድንጋጤ (trauma) ታካሚ ሕፃናት መካከል 16ቱ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።
ከሕፃናቱ መካከል እጃቸውን፣ እግራቸውንና እና አይናቸውን ጨምሮ የአካላቸውን ክፍል ያጡ ወይም የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት የደረሱባቸው የሚገኙ ሲሆን፣ በተለይ በሕፃናት ላይ ለደረሱት ጉዳቶች አንዱ ምክንያት በመሬት ውስጥ “የተቀበሩ እና በሜዳ ላይ የተጣሉ ፈንጂዎች” የሚደርስ ጉዳት ነው።
ትግራይ ክልል የመሰረታዊ ልማት፣ የማኅበራዊ እና የአስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ የመመለሱ ተግባር ልዩ ትኩረት ይሻል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
[Ethio FM]

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ!
የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም በኦንላይን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ፒ ኤች ዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቀሌ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
[MoE]

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በግብርና ዘርፍ በኩል ያዘጋጀውን የሁለት ቀናት የፖሊሲ አውደ ጥናት ዛሬ የካቲት 04 ቀን 2013 ዓ.ም በኤልያና ሆቴል ማቅረብ ጀመረ።
ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው አውደ ጥናት የግብርና ፖሊሲ፣ የገጠር ልማት ፖሊሲ፣ የአርብቶ አደር ፖሊሲ፣ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ፣ የምግብ ዋስትናና የስርዓተ-ምግብ ፖሊሲ፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳና አመራር ፖሊሲ፣ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ እና የውሀና ኢነርጂ ፖሊሲዎች ይቀርባሉ።
ኢዜማ ባዘጋጀው የግብርና እና የገጠር ልማትን በኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ለማሸጋገር በሚረዱ የፖሊሲ ሀሳቦች ላይ ከ30 በላይ ባለሙያዎች ተሳታፊ እንደሆኑበት ተገልጿል።
Via EthZema

የምርጫ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲደላደል የሚያስችል ሶፍት ዌር ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱአለም ለአሐዱ እንደገለጹት ከምርጫ ጋር በተያያዘ ባለስልጣኑ ሁለት ዋና ዋና ተግባሮች ማቀዱን ተናግረዋል፡፡ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን መገናኛ ብዙኃኑ የተፈካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳብና እቅድን ማስተናገድ የሚያስችላቸውን የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምዶች ድልደላ የማመቻቸት ስራ አንዱ መሆኑን አቶ ወንድወሰን ገልጸዋል፡፡

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደፈለጉ እየገቡና እየወጡ ነው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ በክልሉ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ስፍራው ባቀናበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡ፓርቲው የአካባቢው ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ እንደተናገረው ባሁኑ ሰአት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደፈለጉ ይንቀሳቀሳሉ ሲል አስታውቋል፡፡
እንደዚሁም የሁመራ አካባቢ ነዋሪዎች ለፓርቲው እንደተናገሩትም የኤርትራ ወታደሮች ባካባቢው ባይገኙ ኖሮ በነዋሪው ዘንድ ከፍተኛ እልቂት ይፈጠር ነበር ሲሉ ነግረውናል ሲል ነው ፓርቲው ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ ወደ ኮንሶ፣ መተከል፣ ማይካድራ እና መቐለ ልዑክ ቡድን በመላክ በስፍራዎቹ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማጣራት ሙከራ አድርጎ በዛሬው እለት ምልከታውን ይፋ አድርጓል፡፡
ወደ መቐለ የተጓዘው የኢዜማ ከፍተኛ ቡድን በመጠለያ ያሉ ወገኖች ተዟዙሮ ከማየት ጎን ለጎን በቦታው ከነበሩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር አሁን ስላለው ነባራዊ ሁኔታ እና መፍትሔዎች ላይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል፡፡ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዶ/ር ሙሉ ነጋ ጋር በመገናኘት ‹‹በክልሉ አመራር የነበሩ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ፤ ታዋቂ ግለሰቦችን እና የሌሎች ፓርቲዎች አባላት በመዋቅሩ ውስጥ አካተው ቢጠቀሙባቸው ጥሩ እንደሚሆን ፓርቲው ጠቁሟል፡፡
Via Ethio FM

26 አለም አቀፍ የሰብአዊ ዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች መንግስት ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት ፈቃድ አግኝተው ዕርዳታውን ለማዳረስ እየሰሩ መሆኑ ተገልፃል።
የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መከፈል መጀመሩን፣ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን፣ መሆኑን፣ የንግድ እንቅስቃሴ ከዕለት ወደ ዕለት እየተሻሻለ መምጣቱን እና በክልሉ የተረጋጋ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑ ተነግሯል።የመልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን በመሥራት ዜጎች ወደ መደበኛ ኑሮአቸው እንዲመለሱ መንግስት ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከጊዜያዊ አስተዳደርና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር ስራዎቹን እያሳለጠ ናው ተብላል።
[አሐዱ ራዲዮ 94.3]

በትግራይ ክልል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ ጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት መስጠት እየተመለሱ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በትግራይ ክልል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ ጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት መስጠት እየተመለሱ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የጤና ሚንስቴር እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመሆን የቀን ተቀን ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ተቋማቱን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችሉ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያዎች የሚያሰራጩ የመቀሌ እና የሽሬ የመድሀኒት አቅርቦት ቅርንጫፎች የግብዐት ስርጭት እንዲፋጠን በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ሲሆን ተቋማት ወደ አገልግሎት ሲገቡ የደም አቅርቦት ላይ ችግር እንዳይፈጠር በክልሉ የሚገኙትን የደም ባንኮች ወደ ስራ ማስገባት መቻሉንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
ሚኒስትሯ በክልሉ በሚገኙ ደም ባንኮች ለማይሸፈኑ ፍላጎቶች ከማዕከል ደም እየተላከ ይገኛል ብለዋል፡፡
እስካሁን በተደረገው ድጋፍ እና ክትትል የመድሀኒትና ግብአት ስርጭት ተደርጎ ወደ ስራ የገቡ ጤና ተቋማት 88 መድረሳቸውን የገለጹ ሲሆን በአምስቱም ዞኖች በአጠቃላይ ካሉት 40 ሆስፒታሎች ውስጥ 15 ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ እና 5 ሆስፒታሎች በከፊል አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገልጿል፡፡እንዲሁም ካሉት 224 ጤና ጣቢያዎች 68 ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
[AMN]

የህዳሴ ግድብ በታቀደለት መሰረት እየተከናወነ መሆኑንና በቀጣይ ሀምሌ ወር ግዱቡን ውሃ የመሙላት ዕቅድ የማይዘለል መሆኑ ተገለፀ፡፡
ከሶስትዬሽ ድርድር ጋር በተያያዘ ደቡብ አፍሪካ ለተጫወተችው ሚና አመስግነው፤ የታችኞቹን ተፋሰስ አገራት በማይጎዳ መልኩ ፍትሃዊን እኩል ተጠቃሚነት መርህን በመከተል ሁሉንም ተጠቃሚ የሆነ ስምምነት እንዲደረስ የኢትዮጵያ ጽኑ አቋም መሆኑን የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በሰጡት ገለጻ ተናግረዋል፡፡
[አሐዱ ራዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሶስትዬሽ ድርድር ጋር በተያያዘ ደቡብ አፍሪካ ለተጫወተችው ሚና አመስግነው፤ የታችኞቹን ተፋሰስ አገራት በማይጎዳ መልኩ ፍትሃዊን እኩል ተጠቃሚነት መርህን በመከተል ሁሉንም ተጠቃሚ የሆነ ስምምነት እንዲደረስ የኢትዮጵያ ጽኑ አቋም መሆኑን የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በሰጡት ገለጻ ተናግረዋል፡፡
[አሐዱ ራዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ክፍል በመጪው እሑድ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ክፍል በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በስፔሻሊስት ሐኪሞች ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል።
በዚሁ መሠረት ማንኛውም የእይታ ችግር ያለበት ሰው እሑድ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል በመገኘት እና ምርመራ በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ከተሞችን በዘፈቀደ በከባድ ጦር መሳሪያ ደብድበዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል፡፡ በመቀሌ፣ ሑመራ እና ሽሬ ከተሞች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ገበያዎች በከባድ መሳሪያ መደብደባቸውን የገለጠው ድርጅቱ፣ በድምሩም 83 ሰላማዊ ሰዎች ሞተው 300 ሰዎች ቆስለዋል- ብሏል ድርጅቱ፡፡ ሪፖቱን ለመንግሥት አቅርቦ ምላሽ እንዳላገኘ ገልጧል፡፡ ተመድ የተፋላሚ ወገኖችን ድርጊት የሚያጣራ ቡድን እንዲልክ መንግሥት እዲፈቅድ ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa