YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ፡፡

የኢትጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2020 በጀት አመት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 100 ባንኮች መካከል የ 17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን ማጠናቀቁን አፍሪካ ቢዝነስ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት በጥናታቸው ይፋ አደረጉ፡፡የአፍሪካ ባንኮች በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው የኢኮኖሚና የንግድ መቀዛቀዝ ሳይበገሩ ከባለፉት 10 ዓመታት የተሻለ የካፒታል መጠን በማስመዝገብ አመቱን አጠናቀዋል፡፡ ባንኮች አማራጭ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች አማካኝነት ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረጉት ጥረት የኮቪድ ተጽዕኖን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻላቸው የጥናት ሪፖርቶቹ አስነብበዋል፡፡

https://african.business/2020/11/finance-services/are-banks-strong-enough-to-weather-the-storm/
https://www.gfmag.com/magazine/may-2020/worlds-best-banks-2020-africa

Via CBE
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ፡፡አየር መንገዱ ለተፈጠረው መጉላላትም ደንበኞቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰው በረራውን የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል፡፡ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰውም በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም በፌስቡክ ገጹ ጠቅሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አኗር መስጅድ አካባቢ ባለ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ከ20 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተቃጠሉ!

በአዲስ አበባ ልዩ ስፍራው ልዩ ስሙ ስሜ ሜዳ (ንጉስ ሚካኤል ሆቴል አካባቢ ) ባለ አኗር መስጅድ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ ዛሬ ጥር 29,2013 ቀን ስድስት ሰአት ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ከ20 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ፊደል ፖስት ከስፍራው የደረሰ መረጃ ያሳያል።የከተማው እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስለተፈጠረው የአደጋ ውድመትና መንስኤ ዝርርዝር መረጃ ባይሰጥም እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ለፊደል ፖሰት ገልፇል።

Via Fidelpost
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ አፍሪካ ማጓጓዝ ጀመረ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ አፍሪካ ማጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ የመጀመሪያውን ክትባት ወደ አፍሪካ መጓጓዝ መጀመሩን ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ እንደሚነቅል ዛሬ ለፕሮጀክት ስንዲኬት በጻፉት መጣጥፍ ገልጠዋል፡፡ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሕወሃት ያወደማቸው የኮምንኬሽን መስመሮች ዕርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉለዋል፤ በዚህ ረገድ የዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አልፋሽጋ አል-ሱግራ በተባለው አወዛጋቢ አካባቢ የሁለቱ ሀገሮች ወታደሮች ሐሙስ’ለት እንደገና እንደተጋጩ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ይዞታ ሥር የነበውን እና ልዩ ስሙ ኩምቦ መልካሙ የተባለ ቦታ አስለቅቄያለሁ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ በግጭቱ አንድ የሱዳን ወታደር ሞቶ፣ ስምንቱ ቆስለዋል ተብሏል፡፡ በዘገባው ስለተጠቀሰው ግጭት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለው ነገር የለም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የቡሬ ኢንዱስትርያል ፓርክ ሥራው በመጀመሪያ ምእራፉ 260.5 ሔክታር መሬት ላይ አርፎ የውኃ፣ የመብራት እና ቴሌኮም መስመሮች እንዲሁም የመንገድ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎች እና የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ ቢሮዎችም ተገንብተውለታል።

በቀጣይ ሁለት ምእራፎች በማካተት እስከ አንድ ሺህ ሔክታር ይለማልም ተብሏል።በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገቡ ፋብሪካዎችም በዋናነት የግብርና ምርቶችን በግብዓትነት የሚጠቀሙ እና የሚያቀነባብሩ ፣ ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ እና ለግብርናው ዘርፍ መዘመን መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውም ተገልጿል።የግብርና ምርቶችን በፋብሪካ በማቀነባበርና እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እገዛው የጎላ መሆኑም በምረቃው ላይ ተገልጿል። የፓርኩ የመጀመሪያ ምእራፍ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ እስከ 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መቐለ ገቡ!

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ መቐለ ከተማ ገብተዋል።ፕሬዝዳንቷ ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ተፈናቅለው በመቐለ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲሁም ሆስፒታሎች ይጎበኛሉ።በተመሳሳይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከመቐለ ያገር ሽማግሌዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደረገ፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከጥር 30 ቀን 2013 ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን አስታውቋል።በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች በሊትር ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ሆኗል፡-

-ቤንዚን 25 ብር ከ82 ሳንቲም

-ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 25 ብር ከ32 ሳንቲም

-ነጭ ናፍጣ 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ኬሮሲን 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ቀላል ጥቁር ናፍጣ 20 ብር ከ27 ሳንቲም

-ከባድ ጥቁር ናፍጣ 19 ብር ከ77 ሳንቲም

-የአውሮፕላን ነዳጅ 35 ከ12 ሳንቲም ሆኗል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች እንደየርቀታቸው መጠን ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መገለፁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አነጋገሩ!

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዝደንት የሆኑትን ፍራንቼስኮ ሮካን ማነጋገራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የምስጋናና የመፅሀፍ ምረቃ መርሀ ግብር ተከናወነ።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ የጥበብ ስራዎች ላይ ያሳረፈውን ደማቅ አሻራ ተከትሎ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል። በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዘፈኖቹ በርካታ መልክቶችን ሲያስተላልፍ የነበረ ጠንካራና ታታሪ ባለሙያ መሆኑንም የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። አክለውም አርቲስቱ ዘፈኖቹን በተለያዩ ብሄር ብሄረሰብ ቋንቋዎች በመጫወት በሀገሪቱ የጥበብ ስራ ውስጥ ያሥቀመጠው አሻራ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የተዘጋጀለት የምስጋና ፕሮግራም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያን በሰበብ-አስባቡ መጎነታተላቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

የሱዳን ጦር ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ግዛት ይዟል መባሉ አወዛግቦ ሳያበቃ ሠሞኑን፣ የካርቱም ባለስልጣናት የሕዳሴዉ ግድብ የዉኃ አሞላልን የአዲስ ማስጠነቀቂያ ሰበብ አድርገዉታል።የሱዳኑ የመስኖና የዉኃ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድን በተናጥል ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ስጋት ትጭራለች።ሚንስትር ያሲር አባስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ሐምሌ ግድቡን ከሞላች ሱዳን ከሁለት ግድቦችዋ የምታመነጨዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ይታወካል፤ የ20 ሚሊዮን ሱዳናዉያን ኑሮም ይቃወሳል።ኢትዮጵያ ባለፈዉ ዓመት ክረምት ግድቡን መሙላት ጀመራለች።ግብፅና ሱዳን የኢትዮጵያን ርምጃ አልፈቀዱትም።ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት የዉኃ ሙሌቱ ይቀጥላል።ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የሱዳኑን ሚንስትር ጠቅሶ እንደዘገበዉ የ3ቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ፣የአዉሮጳ ሕብረት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና እንዲገቡ ካርቱም ሐሳብ አቅርባለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ።

የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል።አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጠዉ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ርዳታ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉን ጥያቄ ለማሟላት ተስማምቷል።ቤስሌይ ትናንት በቲዊተር ባሰራጩት መግለጫ ትግራይ ዉስጥ 3 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ «የኛን ርዳታ እየጠበቀ ነዉ» ብለዋል።«የምናጠፋዉ ጊዜ የለም።» አከሉ ኃላፊዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070
Forwarded from YeneTube
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው!

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ለ3ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

ካምፓሱ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃግብር በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 365 ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 251 ወንድ እና 114 ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ወልቂጤ ከተማ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ!

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ባለ 5 ወለል የማስፋፊያ አዲስ ህንፃ ተጠናቆ ተመርቋል፡፡ህንፃው 2ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችልም ተመልክቷል፡፡

[ደሬቴድ]
@YeneTube @FikerAssefa
የቡድን 20 አገሮች የውጭ ዕዳ ክምችት ለተጫናቸው ታዳጊ አገሮች ማቅለያ ካመቻቹት ዕድል በተጨማሪ፣ ከውጭ የግል አበዳሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ጫና ማቅለያ ኢትዮጵያ ልትጠይቅ እንደምትችል መንግሥት አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በዓለም አቀፉ የገንብ ተቋም አይኤምኤፍ አማካይነት የቡድን 20 አገሮች እ.ኤ.አ. 
በ2020 አጋማሽ ላይ በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ አገሮች ካመቻቹት የዕዳ ማቅለያ በተጨማሪ የውጭ የግል አባደሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ጫና ማቅለያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። 

መንግሥት ይህንን የሚያደርገው የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ ጫና ለመቀነስ እንደሆነ የገለጸው መግለጫው፣ ከዚህ በተጨማሪ የአገሪቱን የውጭ ዕዳ ጫና ለመቀነስ በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድጋፍ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

የግል የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ የሰጡት ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ወይም የመክፈያ ጊዜ እፎይታ እንዲሰጡ የሚጠይቀው የኢትዮጵያን የወደፊት የውጭ ብድር የማግኘት ዕድል በሚያስጠብቅ መንገድ እንደሚሆንም ገልጿል። 

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት በሰሜናዊ ሕንድ በተከሰተው የበረዶ ግግር ናዳ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከ 150 በላይ ሰዎች ጠፍተዋል!

በሰሜን ህንድ በምትገኘው ኡታራካንድ ግዛት በሁለት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጄክቶች ላይ የበረዶ ግግር ተደርምሶ የጎርፍ አደጋም አስከትሏል፡፡በዚህ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 150 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ጎርፉ የግድቡን የተወሰነ ክፍል ፣ ዛፎችን ፣ ድንጋዮችን እና ሌሎችንም በመንገዱ ያገኛቸውን ቁሶች እና ሰዎችን እየያዘ ሲምዘገዘግ በወቅቱ የተነሱ ፎቶዎች እና የቪዲዮ ምስሎች ያሳያሉ፡፡የነፍስ አድን ቡድኖች ሌሊቱን በሙሉ የተረፉ ሰዎችን እና አስከሬኖችን ለማግኘት ሲያፈላልጉ ማደራቸውን የሲኤንኤን ዘገባ ያሳያል፡፡ በዋሻ ውስጥ ውስጥ የተጠለፉ 15 ሰዎችን ማትረፍ እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ዓመታት ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሰባት ውሀማ ስፍራዎች የውሀ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደምታስጀምር አስታወቀች።

ሀገሪቷ አሁን ያሉት እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ይሰራሉ ቀድመው ስራ የጀመሩት ደግሞ በተሻለ ቴክኖሎጂ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል።

በ10 አመቱ መሪ የትራንስፖርት የልማት እቅድ ውስጥ ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ይገኝበታል፡፡

በዚህም በጣና ሀይቅ፣ ባሮ ወንዝ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ተከዜ፣ ህዳሴ ግድብ እና በጊቤ የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ለማልማት ታቅዶ ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በ10 ዓመት የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ የዉሃ ትራንስፖርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

የዉሃ ትራንስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀና በሚፈለገዉ ደረጃ በሀገራችን ያለዉን ለዉሃ ትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ የሆኑ ወንዞችና ሃይቆች በአግባቡ በመጠቀም ለህዝብና ለጭነት ትራንስፖርት አመቺ ሆነው ይለማሉ ተብሏል፡፡

የውሀ ትራንስፖርት አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሆኖ እንዲያገለግል እንዲሁም ለመዝናኛና ለቱሪስት መስህብነትም እንዲያገለግሉ መሰረተ ልማቶች በስፋት ይለማሉ ተብሏል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa