YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ያደረገውን የሰብአዊ ድጋፍ አድንቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ላደረገው አጋርነት ያለውን አድናቆት መግለጹን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ወደ ትግራይ ክልል አቀና!

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችንና መማክርትን ያካተተ ልዑክ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየትና ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል ማቅናቱን የጉባኤው ዋና ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ።

ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርትን ያካተተ ልዑክ ወደ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ማቅናቱ ነው የተጠቀሰው።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያይም ነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊው ለኢዜአ ገልጸዋል።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንና፣ በተለይም በቤተ እምነቶች ላይ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ እንደሚመክር ተናግረዋል።

በተጨማሪም ልዑኩ በቀጣይ ምን መሠራት እንዳለበት ከአከባቢው የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ከመንግሥት እና ከጸጥታ አካላት ጋር ምክክር ይደረጋል ብለዋል።

የጉባኤው አባል የሆኑት የሐይማኖት ተቋማትም የድጋፍ ስራዎችን እንደሚያከናውኑና በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ስብከቶችን የሚመሩ ሊቃነ ጳጳሳት በኦን ላይን ያሰባሰቡት ድጋፍም ለህበረተሰቡ እንደሚለገስ ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በሑመራ ከተማ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር መጀመሩን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በሕግ ማስከበር ሂደቱ ከተማዋ ነፃ ከወጣች በኋላ ማኅበረሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ አስፈፃሚ አባል በሪሁን እያሱ ተናግረዋል፡፡ይሕንን ተከትሎም በከተማዋ ትምህርት ለማስጀመር ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ በሪሁን እንዳሉት በትምህርት ቤቶች የነበሩ ችግሮችን በመለዬት ቁሳቁስ እንዲሟሉ ተደርጓል፤ መምሕራንን በማሟላትም ደመወዝ እስከመክፈል ተደርሷል፡፡ በመሆኑም ዛሬ በአምስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም ባለሙያዎችን በመመደብ፣ መምሕራንን በማሟላትና ማኅበረሰቡን በማወያዬት ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማደራጀት ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ደግፏል ብለዋል፡፡ አሁንም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው አቶ በሪሁን ያስታወቁት፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የምርጫ ሥልጠና ያልወሰዱ ፖሊሶች በምርጫ ወቅት ሕግ ለማስከበር አይሰማሩም ተባለ!

በምርጫ ወቅት ሰላም ለማስከበር በ55,220 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሰማሩ የፀጥታ አካላት ተልዕኳቸውን ሳይረዱና አስፈላጊውን ሥልጠና ሳያገኙ እንደማይመደቡ፣ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አስታወቁ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ዘለዓለም መንግሥቴ ሐሙስ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ‹‹የኮሙዩኒኬሽን መንገዶቻችን ለምርጫ ሰላምና ደኅንነት›› በሚል ርዕስ በተካሄደ ውይይት ላይ፣ ‹‹ምርጫ በመንግሥት ቅድሚያ የሚያገኝ ተግባር ነው፤›› ብለዋል፡፡ ለምርጫው ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ የፀጥታ ኃይሉ ሚናውን ለይቶ ይሰማራ ዘንድ፣ መመርያዎችና የሥልጠና ማኑዋሎች ተዘጋጅተዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በእነዚህ መመርያዎችና ማኑዋሎች መሠረት ሥልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ፣ ሥልጠናዎችን ያላለፈና ሚናውን ያልለየ አንድም ፖሊስ ሥምሪት እንደማይሰጠው አስታውቀዋል፡፡

የምርጫ ወቅት ደኅንነትን የሚከታተልና የሚመራ ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መቋቋሙንና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንደሚመራ ያስታወቁት ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ ‹‹በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የፌዴራል ፖሊስ በአባልነት ይገኛሉ፤›› ብለዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የጉምሩክ ኮሚሽን ከመቀሌ ቅርንጫፍ በኹለት ወራት ተኩል 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ማጣቱን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በትግራይ ክልል ጥቅምት 24/2013 በተከሰተው ችግር ምክንያት ላለፉት ኹለት ወራት ተኩል ከመቀሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ መሰብሰብ የነበረበትን አንድ ነጥብ ኹለት ቢሊዮን ብር መሰብሰብ አለመቻሉን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም መሠረተ ልማት ጥገና እና አገልግሎትን የተመለከተ ወቅታዊ መረጃ!

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አዲሱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር “እንኳን ደስ ያለዎት” አሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛን በመተካት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑትን የዲአር.ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲን በአዲስ አበባ አግኝተዋቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው “እንኳን ደስ ያለዎት፤ መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ” ብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ኢትዮጵያ እንደምትደግፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡ ዲአር ኮንጎ የህብረቱ ሊቀመንር በመሆኗ በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ የደቡብ አፍሪካን የማደራደር ሚና ትቀበላለች፡፡የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ደ/ር ኢ/ር ስለሺ ዲአር.ኮንጎ በግድቡ ድርድር ላይ የሚኖራት ሚና ሚዛናዊ እንደሚሆን ከሰሞኑ መሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
17 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ!

የምዕራብ ዞን የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ 17 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዱንና ሶስት ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ከታጣቂዎቹ በተጨማሪም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዙን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል በትግራይ ክልል ለስደተኞች የገነባኋቸው ሕንጻዎች ወድመውብኛል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ አውግዟል።

በሒጻጽ እና ሽመልባ የኤርትራዊያን ስደተኛ ጣቢያዎች፣ በቅርብ ሳምንታት አንድ ትምህርት ቤት እና ክሊኒክም እንደወደሙ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ጃን ኢግላንድ ገልጠዋል። በተቋማቱ እና በዕርዳታ አቅርቦቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት መንግሥት እና ለጋሽ ሀገራት እንዲያጣሩ እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርጉም ድርጅቱ ጠይቋል። ድርጅቱ በምንጭነት የተጠቀመው ግን ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገ ዲ.ኤክስ ኦፕን ኔትወርክ የተባለ ድርጅት ያሰራጫቸውን የሳተላይት ምስሎች ነው። በሌላ በኩል የተመድ ዐለም ምግብ ፕሮግራም በመላው ትግራይ ክልል ለረድዔት ሠራተኞች ተደራሽ እንዲሆን እና የዕርዳታ አቅርቦቱም እንዲያድግ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ዴቪድ ቢዝሊ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥም የዕርዳታ ማጓጓዣዎች በወታደሮች እንዲታጀቡ ስምምነቱ ይፈቅዳል። መንግሥትም ወደ ክልሉ ለመግባት ፍቃድ ለሚጠይቁ የረድዔት ሠራተኞች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተስማምቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ለመጭው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልል እና የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ ባላስረከቡ የክልል መስተዳድሮች በተቀመጠው የጊዜ መርሃ ግብር የዕጩዎች ምዝገባ እንደማያካሂድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ አስታውቋል። እስካሁን የክልል እና ዞን የምርጫ ቢሮዎችን ባላሳወቁት አማራ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች፣ የዕጩዎች ምዝገባ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እና የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት ማከናወን አልቻልኩም- ብሏል ቦርዱ። በተጠቀሱት ክልሎች ሌላ ጊዜ የዕጩዎች ምዝገባ እንዲደረግ፣ እስከ የካቲት 5 ቢሮዎችን እንዲያሳውቁም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመለመሉ የምርጫ ክልል አስፈፃሚዎችን በተመለከተ ፓርቲዎች ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ውሳኔ ሰጠ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ክልል ደረጃ ምርጫ ለማስፈጸም የመለመላቸውን የምርጫ አስፈጻሚዎች ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሁለት ዙር በማቅረብ አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት በጠየቀው መሠረት ከ10 ፓርቲዎች የተሰጡ አስተያየቶችን መርምሮ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።

ከአስሩ መካከል ሦስት ፓርቲዎች ዝርዝር አስተያየት ያቀረቡ መሆኑን ነው ቦርዱ ያስታወቀው።

“የምርጫ አስፈፃሚው ገለልተኛ አይደለም” እና “የሌላ ፓርቲ አባል ነው” በማለት የቀረቡ አቤቱታዎች መኖራቸውን የገለጸው ምርጫ ቦርዱ፣ ያለምንም ማስረጃ የቀረቡትን አቤቱታዎች እንዳልተቀበለው አስታውቋል።

ነገር ግን የፓርቲ አባልነት የከፈሉ ማስረጃ የቀረበባቸውን አስፈጻሚ ከአስፈጻሚነት መሠረዙን በምሳሌነት አንስቷል።

“የምርጫ አስፈፃሚው የራሴ አባል ነው” በማለት ማረጋገጫ ያቀረበ ፓርቲ በአቤቱታው መሠረት አባላቶቼ ናቸው ያሉት ከአስፈጻሚነት እንዲሰረዙ ተደርጓል ብሏል።

“በዞናችን ላሉት ምርጫ ክልሎች የአስፈፃሚዎች ዝርዝር አልተላከም” በሚል ላቀረቡት ቅሬታ ደግሞ በሦስተኛው ዙር እንደሚላክ እንዲገለጽላቸው መወሰኑን ገልጿል።

“የማይታወቁ አስፈፃሚዎች ናቸው” በሚል ለቀረበው ቅሬታ የምርጫ ቦርድ የኦፕሬሽን ክፍል አድራሻቸውን አጣርቶ በሦስተኛው ዙር እንዲልክ እንዲደረግ ተወስኗል ነው ያለው።

“የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን እና ከማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለሥልጣን ከመጡ ዝርዝሮች ውስጥ ምልመላው መከናወን አልነበረበትም” የሚል አቤቱታ የቀረበ መሆኑን እና ተቋማቱ የመንግሥት ተቋማት በመሆናቸው ብቻ የሚመለመሉ ሰዎች ዝርዝር መካተት የለበትም የሚለውን ውሳኔ ቦርዱ እንዳልተቀበለው አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
60 ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች አመራርነት እና አገልጋይነትን በተግባር ሊሰለጥኑ መሆኑ ተገለጸ!

ከሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ 60 ተማሪዎች አመራርነትን እና አገልጋይነትን በተለያዩ ተቋማት ተሰማርተው በተግባር እንደሚሰለጥኑ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ገለጹ።

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጣቶቹን ከሚያሰለጥነው 'ሴንተር ፎር አፍሪካን ሊደርሺፕ' ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል ብለዋል።

ወጣቶቹ 6 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

ፕሮግራሙ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በየዓመቱ የወጣቶቹ ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ወ/ሮ ፊልሰን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070
Forwarded from YeneTube
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
የዱራሜ-ዳንቦያ-አንጋጫ-አመቾ ዋቶ-ሃላባ 65 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል።

በተመሳሳይም የሐዌላ-ቱላ ወተራሬሳ-የዩ እና ወንቻ 85 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ይጀመራል።65 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት ላለው ዱራሜ-ዳንቦያ-አንጋጫ- አመቾ ዋቶ-ሃላባ የመንገድ ፕሮጀክት 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል።ለሐዌላ-ቱላ ወተራሬሳ-የዩ-ወንቻ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተበጅቶለታል።የመንገዶቹ ግንባታ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የመንገድ ግንባታውን ሲከውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ደግሞ በአማካሪነት ይሠራል።

የመንገዶቹ ግንባታው ሶስት ዓመት የሚወስድ ሲሆን እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።ፕሮጀክቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ይገኛል።በፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ መርሃግብር ለመገኘት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በቦታው ተገኝተዋል።የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ የሲዳማና የኦሮሚያ ክልሎችን በማስተሳሰር የጎላ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ በምርጫው ለመሳተፍ እየተፍጨርጨርኩ ነው አለ::

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በውስጣዊ የፖርቲ ቀውስ የተነሳ በ6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ አጣብቂኝ ውስጥ መውደቁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አሳውቋል፡፡የፖርቲው ቃላቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምርጫ ቦርድ ፖርቲው የገጠመውን ችግር ለመቅረፍ አሰቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ቢሰጥም በተቀዳሚ ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እንቢተኛነት ማድረግ እንዳልቻለና እና ልመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ውዝግቡ ከተፈጠረ ወዲህም ምርጫ ቦርድ ጋር በስመ ሊቀመንበርነት የግንባሩ ተወካይ ናቸው በሚል ግንኙነት ስላላቸው ፈጽሞ የጋራ ውሳኔና መመሪያ እየሰጡም ፤እየተቀበልንም አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡እኛ ምርጫ ቦርድ ችግሮን ተገንዝቦ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን እና ወደ ምርጫ ዝግጅቱ እንድንገባ እየጠየቅን ነው ይላሉ፡፡

አሊያም ግን ምርጫ ውስጥ የማይሳተፍ ፖርቲ ጥቅሙ ምን ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡በዚህ አይነት ከሄድንም የእርሳቸው ስብስብ በምርጫው ለመሳተፍ አይችልም ምክንያቱም ህጋዊ አይደለም ባይ ናቸው ፡፡

የእኛ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ከእርሳቸው ጋር የሚያደርገውን ግንኙንት እንዲያጤነውና መፍትሔ እንዲሰጠን ነው ምክንያቱም ይህ ነገር አግባብነትም ሆነ ፍትሐዊ አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡

ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሄድ የግድ መሆኑን የሚያነሱት አቶ ቀጀላ አሁን ድርጅታዊ ቀውስ ውስጥ ስላለን ወደ ምርጫው መግባት አንችልም ከባድ ብለው፡፡ችግሮ እስኪፈታ ምርጫ ቦርድ በልዩ ሆኔታ ቀናትን ገፋ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ምርጫውን መካፈል ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው ያነሱት፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመጪው ሚያዚያ ወር መጀመሪያ 9 ሚሊየን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ::

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ አባል በሆነችበት የአለም አቀፉ የኮቫክስ የጋራ ትስስር በኩል የሚገባውን ክትባት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል::

ክትባቱ በተያዘው አመት ሚያዝያ መጀመሪያ እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሯ ክትባቱም በተለይም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በቅድሚያ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል::

ይሄንን ሃላፊነት የሚወጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱንም ገልፀዋል::ከክትባቱ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ አሁንም ቢሆን መከላከል ላይ ትኩረት እንዲያደርግም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል::

@YeneTube @FikerAssefa
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ከ1ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ ማስመረቁን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ከተማ የ2021 የዓለም አቀፍ ራእይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ሽልማት አሸናፊ መሆኗ ተገለፀ፡፡

የአሜሪካው ብሄራዊ ማእከል ለምቹ መንገድ FIA ከተባለ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ተካሂዷል በተባለው ምርጫ አዲስ አበባ የ2021 የዓለም አቀፍ ራእይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ለወጣቶች አመራር(International vision zero for youth leadership award) ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ሽልማቱ የተበረከተው ኢትዮጲያ ለወጣቶች እና ተማሪዎች የእግርኛ መንገድ አጠቃቀም ፖሊሲ በማውጣት እና በመተግበር ላሳየችው ተምሳሌት ፤ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ፍጥነትን ቀንሶ በማሽከርከር እና የትራፊክ አደጋ መቀነሻ ዘላቂ መንገዶችን በመተግበር ላስመዘገበችው ለውጥ ነው ተብሏል ፡፡

በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የእግረኛ መጠቀሚያ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት እና መኪና አልባ(CAR-FREE ROAD) መንገዶች መርሐግብር በወር አንድ ቀን በመተግበር የሰዎችን አሰተሳሰብ በመቀየር የመኪና መንገዶች ለወጣቶች የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሆኑ በማድረጓ ነው ሲል የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽፅህፈት ቤት ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ጥቅማ ጥቅም የሚያስገኝ ስምምነት ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር ጋር ተስማማ!

ስምምነቱ የባንክ ብድር አገልግሎት በማመቻቸት ሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ያገኙ ዘንድ የሚያስችል ነው።አየር መንገዱ ወደ 17ሺ የሚጠጉ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ፤ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የነበረው ስምምነት ለሁሉም ሰራተኞች ተደራሽ አልነበረም ተብሏል።በመሆኑም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር የተደረገው ስምምነት ሁሉም ሰራተኞችን ተጠቃሚ ሊያደርግ ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ቀዳማዊ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት ኢ/ር ተሊላ ደሬሳ ተናግረዋል።

ስምምነቱ አብዛኛው ሰራተኛ በተሻለ መልኩ የቤት፣ተሽከርካሪ እና ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ያስችላል።የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ይህ ስምምነት እውን ይሆን ዘንድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም በመድረኩ ገልፀዋል። ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኩም ይህንኑ ሲቀርብላቸው ከሌሎች ባንኮች ይልቅ ሃሳቡን በመቀበል ስምምነቱ እውን እንዲሆን በማስቻሉ ለባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ምስጋና ቀርቧል።

በዚህ በኮቪድ 19ወረርሽኙ በቅት ታላላቅ አየር መንገዶች ሰራተኞቻቸውን ሲያባርሩ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን 1,600 ሰራተኞች ቋሚ እንዲሆኑ ማደረጉንም አንስተዋል።የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ምንም እንኳ የአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ቢጎዳም ፤ ያለምንም ድጋፍ አሁንም ስራውን በተገቢው መልኩ ማስቀጠሉን አንስተዋል።ለውጡ እየመጣ የሚገኘው በሰራተኞች ልፋት መሆኑን በመግለፅም ፤ አየር መንገዱ 1,200 ቤቶች ከዚህ ቀደም ለሰራተኛው ሰርቶ አስረክቧል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa