ደህንነቱ የሚያጠራጥር 1 ሺ ኩንታል የማር ምርት አግኝቻለሁ ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።
ናሙና በመውሰድ የላብራቶሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን አስታውቋል፡፡በተለይም በዓላትን ተገን አድርጎ የማህበረሰቡ ፍላጎት የሚጨምር በመሆኑ ምግብን ከበዓድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ይስተዋላሉ፡፡የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሌሎች ቦታዎች ላይ ምግብን ከበዓድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል አዲስ አበባ ደግሞ የመሸጫ ቦታ በማድረግ ይጠቀሙታል ብሏል፡፡በአዲስ አበባም በተደረገው የቁጥጥር ስራም ደህንነቱ የሚያጠራጥር 1 ሺ ኩንታል የማር ምርት በመገኘቱ ናሙና በመውሰድ የላብራቶሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው፡፡እንደዚህ ዓይነት ህገ-ወጥ ድርጊት የሚፈጸምበት ምንጩን ለማወቅና በዚህ ድረጊት እነማን ተባባሪ ናቸው የሚለውን ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል።
[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa

ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ለመግባት እየሞከሩ ነው፡፡
በጋምቤላ ክልል በምትገኘው ኢንታንግ ልዩ ወረዳ በምትዋሰንበት ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከነ ከብቶቻቸው ወደ ኢንታንግ ልዩ ወረዳ ለመግባት ሲሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች እንዳይገቡ ተደርገዋል።እነዚሁ የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች አሁንም በድንበር በኩል ለመግባት እየሞከሩ ነው።
[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል በምትገኘው ኢንታንግ ልዩ ወረዳ በምትዋሰንበት ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከነ ከብቶቻቸው ወደ ኢንታንግ ልዩ ወረዳ ለመግባት ሲሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች እንዳይገቡ ተደርገዋል።እነዚሁ የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች አሁንም በድንበር በኩል ለመግባት እየሞከሩ ነው።
[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
10 ሺህ በላይ የአሜሪካ ወታደሮች የጆ ባይደንን በዓለ ሲመት ያጅባሉ ተባለ፡፡
46ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጡት ጆ ባይደን በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአለ ሲመታቸው በሚከበርበት በዋሽንግተን ከተማም ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወታደሮችም ጆ ባይደንን ያጅባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ CNBC ዘግቧል፡፡
በቴሌቪዥን በቀጥታ ለህዝብ በሚደርሰው የጆ ባይደን በአለ ሲመት ታዋቂው የፊልም ሰው ቶም ሀንከስ ዝግጅቱን የሚመራው ይሆናል፡፡
በዚህ ዝግጅት ታዋቂ አቀንቃኞች ዝግጅቱን እንደሚያደምቁት የሚጠበቅ ሲሆን ከተጋባዥ ዝነኛ አቀንቃኞች መካከልም ጀስቲን ቲምበርሌክ እና ዲሚ ሎቫቶ ይገኙበታል፡፡
ጀስቲን ቲምበርሌክ በዝግጅቱ አዲስ ስራ እንደሚያቀርብ በቲውተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡
ከኮሮና ጋር በተገናኝ የሰራው አዲሱ ሙዚቃው የተሸለ ቀን እናያለን የሚል መጠርያም እንደሰጠው ነው ጀስቲን ቲምበርሌክ የተናገረው፡፡
ለ90 ደቂቃ ያህል በሚቆየው የጆ ባይደን በአለ ሲመት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንቶች እና ባለቤቶቻቸው ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችና የነጭ ዘር የበላይነት አቀንቃኞች ፕሬዝዳንታዊ ሽግግሩን እንዳያስተጓጉሉ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል፡፡
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆ ባይደን በአለ ሲመት እንደማይገኙም ከዚህ በፊት ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡
Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

በትግራይ ክልል ተፈጽሟል የተባለዉ ዘረፋና የሴቶች መደፈር በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኢዜማ ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በወቅታዊ ጉዳይ እና በ2013 በሚካሄደዉን ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡በመግለጫዉ ላይ የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት፣በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የሌላ ሀገር ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ መንግስት ግልጽ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ከዚህም ባሻገር በክልሉ ተፈጽሟል የተባለዉ የንብረት ዘረፋና የሴቶች መደፈርን በተመለከተም በገለልተኛ አካል እንዲጣራ መደረግ እንዳለበት ኢዜማ ጠይቋል፡፡
መንግስት የዜጎችን ደህንነት ሊያረጋግጥ ይገባል ያለዉ ፓርቲዉ፣ በምዕራብ ወለጋ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የንጹሃን ግድያና መፈናቀልን በተመለከተ መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡
ከሁሉም በፊት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠዉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ከፍተኛ ፍይዳ እንዳለዉ እንደሚገነዘብ ኢዜማ ተናግሯል፡፡ይሁንና አመራሮቻቸው በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው እና በመጪው ምርጫ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ ሲገልጹ መሰማቱ፣ በመጪው ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ኢዜማ ጠቁሟል፡፡ኢዜማ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተከሰቱ ግጭቶች እና መፈናቀሎች የደረሰዉን የጉዳት መጠን የሚያጣራ ቡድን ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑንም አስታዉቋል፡፡

በድሬዳዋ የአፍና አፍንጫ ጭምብል (ማስክ) ሣይጠቀሙ አገልግሎት መስጠትም ሆነ ማግኘት የሚከለክል ውሳኔ ተላለፈ፡፡
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ተቋማት፣ በማህበረሰቡና በሌሎችም ቦታዎች ሁሉ በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶችን መተግበር እየተዘነጋ መሆኑን እና ወረርሽኙን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችም እየተጣሱ መሆኑ ተነግሯል።ይህም በሽታው እንዲስፋፋ ምክኒያት ሆኗል።
ለዚህም በከተማዋ ‹‹እንድናገለግልዎ ማስኮን ያድርጉ›› (NO Mask No Service) የሚል ንቅናቄ ነው የተጀመረው፡፡የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃለፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህም “በከተማችን ችግሩ ዋጋ ከማስከፈሉ በፊት ያለውን ቸልተኝነት ለማስቆም በአስተዳደራችን የሚገኙ ሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመመሪያ-30/2013 ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል።
እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞቻቸውን ማስክ በማስደረግና አገልግሎት ፈላጊዎችን ያለማስክ ባለማስተናገድ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን።” ብላለች በፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተወካይ የሆነው አቶ በላይነህ ከበደ በበኩሉ ወረርሽኙን ለመከላከል የወጡትን መመሪያዎች በማያከብሩ ላይ እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ እስራትና ሌሎች ቅጣቶችን ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግሯል።
[@addiszeybe]

በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ከአንድ ሚሊየን 500 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።
የቃጠሎው መንስዔ እየተጣራ እንደሆነ እና በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል።የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ሳጅን ሬድዋን ደኑር ለኢዜአ እንደገለጹት የእሳት ቃጠሎው የተነሳው ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ በከተማው መልካሜ ቀበሌ በተለምዶ አጠራር ሚቶ መውጫ በተባለው ሥፍራ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር በተገናኘ ነው።በአደጋው በ21 መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ላይ በደረሰ ቃጠሎ ከአንድ ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የግድያና አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆኑን የሲቪል ማህበራት ገለጹ፡፡
ማህበራቱ እንዳሉት፣በክልሉ ንጹሃን ሴቶች እየተገደሉ፣የአስገድዶ መድፈር እየተፈጸመባቸዉና ንብረታቸዉም እየተዘረፉ ነዉ ብለዋል፡፡ማህበራቱ ይህን የገለፁት በግጭት ምክንያት ህይዎታቸውን፣ ክብራቸውን፣ ንብረታቸውን እና ማህበራዊ አግልግሎታቸውን ላጡ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሰ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምፅ እንሁንላቸው የሚል መግለጫ በጋራ በሰጡበት ወቅት ነው።
ማህበራቱ በሃገራችን በትግራይ ክልል፣ በመተከል፣ በጉራፈርዳ፣ በሲዳማ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች የደረሱትን የሰብኣዊ ጥቃቶችን አውግዘዋል።በግጭቱ በተለይ ለአዳጋ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ ህፃናትና አረጋውያን ደግሞ በከፋ ሁኔታ ተጎድተዋል፣ ከግጭቱ የተረፉትም ቢሆኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
የሲቪል ማሀበራቱ መንግስት ዜጎች የሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲጠበቅ እንዲሰራም አሳስበዋል።በግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ፣አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣ የህክምናና ሌሎችንም የቁሳቁስ ድጋፍና በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ሰዎችም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ነው ያሳሰቡት።
በትግራይ ክልል ጉዳዩ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን የነበረው መሆኑን የገለጹት ማህበራቱ፣ በሌሎች የነበሩት ግን ትኩረት አላገኙም ብለዋል።በሃገር ዉስጥም ይሁን በውጪ ያሉ መንግስታዊና መንግስታ ያልሆኑ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም ቢሆኑ፣ በነበሩት ግጭቶች ጉዳት ለገጠማቸው ወገኖቻችን እንዲያገግሙ የሚያስችል የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
[Ethio FM]

የሚዲያ አካላት የስም ማጥፋት ሲፈጽሙ በወንጀል እንዲቀጡ የፓርላማ አባላት ጠየቁ!
የመገናኛ ብዙኃን በስም ማጥፋት ተግባር ፈጽመው ሲገኙ መልስ ወይም እርማት እንዲሰጡ ሕጉ ያስገድዳቸዋል ያሉት ዓቃቤ ሕጉ፣ አሠራሩ ዓለም አቀፍ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ለአብነትም የኬንያና የጋናን አሠራር በመጥቀስ ስም ማጥፋትን ሙሉ በሙሉ በፍትሐ ብሔር እንዲታይ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
ስም ማጥፋትን በወንጀል ሕጉ እንዲዳኝ ማድረግ የፕሬስ ነፃነትና ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ላይ፣ ከፍተኛ የሆነ ጫና ያስከትላል በሚል የተወሰደ እንደሆነ አስረድተዋል።
የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በስም ማጥፋት ድርጊት የተገኙ አካላት ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር በወንጀል ሕጉ ይጠየቁ እንደነበር፣ አሁን እየተሻሻለ ያለው ረቂቅ ሕግ ግን በዘርፉ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚታሰብ ገልጸዋል፡፡
[Reporter]

በኩዌት የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ኢትዮጵያዊት በምህረት ተለቀቀች!
ከ8 አመታት በፊት በኩዌት አገር በወንጀል ተከሳ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት ሉባባ ኑረዲን የተባለች ኢትዮጵያዊት በምህረት እንዲትፈታ መደረጉን በኪዌት የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ፡፡ኤምባሲው ላለፉት ዓመታት ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የኩዌት የፍትህ ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምህረት እንደተደረገላት ገልጸዋል፡፡በመሆኑም ሉባባ ኑረዲንን ወደ ሀገር ቤት እንድትመለስ የጉዞ ሂደቱን በማስጨረስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በሰላም እንድትሳፈር አድርጓል።ኤምባሲው በኩዌት የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበርን ጨምሮ በሂደቱ ለተባበሩ ሁሉ ምሥጋና ማቅረቡን ከኢምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በ2012 የ2ተኛ እና ከዚያ በላይ ዓመት ተማሪዎች የነበራቹ እስከ ጥር 9 ድረስ ወደ ዩንቨርስቲ በመግባት ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳስባለን።
Via:- ጅማ ዩንቨርስቲ
@Yenetube @FikerAssefa
Via:- ጅማ ዩንቨርስቲ
@Yenetube @FikerAssefa
YeneTube
አሜሪካ ዜጎቿ ወደ እንጦጦ ፓርክ እና ጉለሌ የእጸዋት ማዕከል እንዳይሄዱ አስጠነቀቀች። አገሪቱ ዜጎቿ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀችው በጎብኝዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል እንደሆነ የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በትዊተር ገጹ አስታውቋል። እንደ ማስጠንቀቂያው ከሆነ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ጥቃት እየተፈጸመ ነው። በመሆኑም አሜሪካውያን እና ሌሎች ዜጎች ወደ እንጦጦ…
በአዲስ አበባ አንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እየተፈፀመ እንደሆነ የተናፈሰው ወሬ የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ሲል ፖሊስ አስታወቀ።
ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊት አልፎ አልፎ ሊያጋጥም እንደሚችልና የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡
ከዚው ጋር በተያያዘ አሜሪካ ዜጎቿ ወደ እንጦጦ ፓርክ እና ጉለሌ የእጸዋት ማዕከል እንዳይሄዱ ማስጠንቀቋን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ስብሃት “አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችንን ነው በማስፈጸም ላይ ያላችሁት” ማለታቸውን ሌ/ጄኔራል ባጫ ገለጹ!
አቶ ስብሃት በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል፡፡በርካቶችም አቶ ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር፡፡ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡አቶ ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
አቶ ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግስቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት“ የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ እንደነበር ተናግረዋል፡፡አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላም እንደተገመተው፣ አንደኛው ጄኔራል ሲያናግሯቸው “ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው፤ ተወያዩበት“ እያሉ ሲያወሩ እንደነበር የምዕራብ ዕዝ አዛዥ እንደገለጹላቸው ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ ገልጸዋል፡፡
ሌ/ጄኔራል ባጫ ተጫዋች ያሉት የምዕራብ ዕዝ ሌላ ጄኔራል አቶ ስብሃትን “ስለ ሕገ መንግስቱ ተወውና አንተ እስኪ ምን ይሰማሃል“ ብሎ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ስብሃት ሲመልሱ “እኔ የሚሰማኝ እኛ ከሞትን እኮ ቆይተናል“ የሚል ነው፡፡
“መቸ ነው የሞታችሁት“ የሚል ጥያቄ እንደተነሳላቸው ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ባጫ “እኛ የሞትነውማ ኢህአዴግ የሚባለው የጠፋ ጊዜ ነው ፤ አሁን የምታደርጉት ምን እንደሆነ ልንገርህ? አሁን እያደረጋችሁ ያላችሁት የቀብር ሥነ ስነስርዓታችን እየፈጸማችሁ ነው“ ሲሉ መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡
Via Al-ain
@YeneTube

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
የደቡብ ፣ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣6ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል ።
ምክር ቤቱ በአንድ ቀን ውሎው የክልሉን ተጨማሪ በጀት፣በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት ተወካይ አባላትን ብዛት ለመወሰን የወጣን አዋጅ፣የዋና ኦዲተር ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻያ፣የአስፈጻሚ አካላትን ሹመትን እና የዳኞች ሹመትና ስንብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Via:- Fbc

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፓራክ አለፐ ጋር ተወያዩ፡፡ አቶ አደም ፋራህ መንግስት በትግራይ ክልል ስላካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለአምባሳደር ያፓራክ አለፐ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፓራክ አለፐ ጋር ተወያዩ፡፡ አቶ አደም ፋራህ መንግስት በትግራይ ክልል ስላካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለአምባሳደር ያፓራክ አለፐ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በሻሸመኔ ከተማ ራሱን ሬንጀርስ ቡድን ብሎ የሚጠራ 38 አባላት ያሉት የማፊያ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ።
የሻሸመኔ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በሞተር የታገዘ ከባድ ዝርፊያን ሲፈጽሙ የነበሩና ራሳቸወንን ሬንጀርስ ሲሉ የሚጠሩ የማፊያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ይህ የማፊያ ድድን ከከተማዋ ወጣ ብሎ ባሉ የጨረቃ ቤቶች ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡
አሁን ደግሞ ራሳቸውን የበለጠ በማደራጀት በጦር መሳሪያ በመታገዝ ተመሳሳይ ቁልፎችን በማስቀረጽ የግለሰብ ቤቶችን ሲበርብሩ ፤ባለሶስት እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችን በመስረቅ በአጎራባች ክልሉች ጨምሮ እስከ ጠረፍ በመውሰድ ሲሽጡ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡
የከተማዋ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመምከርም ባደረገው እልህ አስጨራሽ ጥረት ከ38 የቡድኑ አባላት ውስጥም 33ቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
በከተማዋ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከባድ የንጥቂያና የዝርፊያ ወንጀሎች መበራከታቸውን ተናግረው በስርቆት ያገኙትንም ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች ወደ አጎራባች ክልሎች እስከ ጠረፍ ድረስ በመውሰድ ሲሸጡ እንደነበር ሃላፊው ተናግረዋል።
ይህንን ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ከከተማዋ ወጣ ካሉ የገጠር ከተሞች የመጡ እንጂ የከተማዋ ወጣቶች እንዳልሆኑ የሚናገሩት አቶ ስንታየሁ አሁን ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ብለዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ በሰላም የመንቀሳቀስ ችግር እንዳለባቸው ሲናገሩ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ከፖሊስ መዋቅሩ ጋር በተደረገው የተቀናጀ ጥረት 33ቱን ይዘናል ብለዋል አቶ ስንታዩ፡፡

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!
የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሥራው ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።
በየእርከኑ ከሚገኙ የአስተዳደር አካላት፣ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም የፀጥታው ዋና ባለቤት ከሆነው ሰላም ወዳዱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ጋር እየሠራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በዚህም ለወንጀል እና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱንም አሳውቋል።ታቦታት በሚያልፉበት ወቅት አሽከርካሪዎች የፀጥታ አካላት ለሚሰጧቸው ተዕዛዝ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።
ህብረተሰቡ በማንኛው ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያያዥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙትም ይሁን ጥቆማ ለመስጠት እንዲሁም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 01-11-26-43-77፣ 01-11-26-43-59፣ 01-18-27-41-51፣ 01-11-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የአሜሪካው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ፔኤችዲ) በላከው ደብዳቤ በእስር የሚገኙ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳሰብ።
ምክር ቤቱ በደብዳቤው የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴን(CPJ) ዋቢ አድርጎ ቢያንስ ሰባት ጋዜጠኞች ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት ታስረዋል ብሏል።ከነዚህ ጋዜጠኞች ዉስጥ ስድስቱ በትግራይ ክልል በተነሳው ጦርነት ላይ ዘገባ በመስራት ላይ የተሳተፉ መሆናቸውንም ገልጿል።
ምክር ቤቱ አክሎም የጋዜጠኞችን ያለምንም ማስረጃ ለምርመራ በሚል ምክንያት ለቀናት እንደታሰሩ ገልጾ ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት መጨረሻ ወር ላይ የሮይተርሱ የምስል ቀረጻ ባልደረባ የሆነው ኩመራ ገመቹን ለ12 ቀናት ያለምንም ክስ እና ማስረጃ በእስር መቆየቱን እንዲሁም በሁለት የፖሊስ አባላት በሌሎች የሮይተርስ ጋዜጠኞች ላይ የተደረገውን ድብደባ መረጃ አስታውሷል።
ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጎዳና እንደሚደግፍ ገልጾ እንደነዚህ አይነት ክስተቶች የሃገሪቱን የጋዜጠኞችን ማሰር እና ማገላታት የኋላ ታሪክ የሚያስታውስ መሆኑን እና በዚህም ከቀጠለ ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንደሚደርስ አሳቧል። ሆኖም የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውሶ የፀረ ሽብር ህጉን በመጠቀም ጋዜጠኞችን ማፈን እና ማሰር ሂደቱን ወደኋላ እንደሚጎትት ገልጿል። የመረጃ ነፃነት እንዲከበርም አሳስቧል።

በትግራይ ክልል የተከናወነውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግ መንግሥት ያቀረበው አገራዊ ጥሪን መሠረት በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን እስካሁን ድረስ 100.7 ሚሊዮን ብር እንደሰበሰበ አስታወቀ፡፡
‹‹ኢትዮጵያን በፈለግናት መንገድ ብቻ ልንዘውራት፣ ልንቃኛት ይገባል›› የሚሉ ኃይሎች፣ ለውጡን በመገዳደር እስከመጨረሻው ድረስ የተፋለሙበት ሒደት እንደሚታወቅ የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፣ አሁን በአገራችን ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ እየተሠራ ያለው ዋና ሥራ የማቋቋምና ሰብዓዊ ዕርዳታ የማቅረብ ሥራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
‹‹ኢትዮጵያን በፈለግናት መንገድ ብቻ ልንዘውራት፣ ልንቃኛት ይገባል›› የሚሉ ኃይሎች፣ ለውጡን በመገዳደር እስከመጨረሻው ድረስ የተፋለሙበት ሒደት እንደሚታወቅ የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፣ አሁን በአገራችን ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ እየተሠራ ያለው ዋና ሥራ የማቋቋምና ሰብዓዊ ዕርዳታ የማቅረብ ሥራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ያለውን 6ኛ ዓመት 3ኛ ዙር ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረው ጉባኤ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦችን ያጸድቃል ፣ ሹምሽሮችንም ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።የክልሉን የ2013 ዓም ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ተጨማሪ በጀት እንደሚያጸድቅም በጉባኤው የቀረበው የውይይት አጀንዳ ያመለክታል።በምስረታው ወቅት 348 መቀመጫዎች የነበሩት የደቡብ ክልል ምክር ቤት 57 አባላቱ ወደ አዲሱ የሲዳማ ክልል በመዛወራቸውና ፣ 38 የዎላይታ ዞን ተመራጮች ደግሞ << በምክር ቤቱ ሀሳባችን አልተደመጠም >> በሚል እራሳቸውን በማግለላቸው ያለፈውን ጉባኤ በቀሪ አባላቱ ነበር ያከናወነው።በአሁኑ አስቸኳይ ጉባኤው ግን ቀደም ሲል ራሳቸውን አቅበው የቆዩት የዎላይታ ተወካዮች ዳግም ወደ ምክር ቤቱ ተቀላቅለዋል።
[DW]

ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያንና ሱዳንን በድንበሩ ጉዳይ ለማደራደር ዝግጅ መሆኗን ገለጸች
ደቡብ ሱዳን የማደራደር ፍላጎቷን የገለጸችው የፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የጸጥታ አማካሪ ከአልቡርሃን ጋር ተገናኝተዋል
ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸውን የድንበር ግጭት በሰላም እንዲፈቱ ለማደራደር ዝግጁ መሆኗን ደቡብ ሱዳን አስታወቀች፡፡ደቡብ ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግባቸውን በሰላም እንዲፈቱ መጠየቋ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አዲስ አበባና ካርቱም የድንበር ላይ ውዝግባቸውን በሰላም ይፈቱ ዘንድ የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግ ገልጻለች፡፡
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት የጸጥታ አማካሪ ቱት ጋትሉዋክ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው ጁባ ሀገራቱን ለማደራደር ዝግጁነቷን የገለጸችው፡፡
ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አዲስ አበባና ካርቱም ችግሩን ፖለቲካዊና በዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ላይ በመመስረት እንዲፈቱና ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ በጸጥታ አማካሪያቸው በኩል አስታውቀዋል፡፡ ችግሩን በሚታወቀው ዓለም አቀፍ ድንበር መሰረት መፍታት እንዲቻል የማደራደር ሚና እንዲወጡ ነው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት የገለጹት፡፡
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ችግሩ ወዳጅነትንና ወንድማማችነትን ተከትሎ እንዲፈታ ትኩረት ይደረጋል ማለታቸውን ሽንዋ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባሳለፍነው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ችግሩን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገልጸው ሱዳንም ይህንኑ ማስቀደም ብትችል ለሁለቱ ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ማለታቸው ይታወሳል፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል የሆኑትን ቼምስ አል ዲን ካባሽ እና ተጠባባቂ የሱዳን ተጠባባቂ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦማር ቀመረዲንን በጁባ ባነጋገሩበት ወቅት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ በሰላም መፍታት እንዳለባት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዚዳንት ኪር ካርቱምና አዲስ አበባ የድንበር እሰጥ አገባውን በድርድርና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንዳለባቸው መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ሀገራቸው ሁለቱን ጎረቤታሞች ለማደራደር ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡
Via:- Alian