ሚስተር ባምቢስ አረፉ!
"ልቤን ብትከፍቱት ኢትዮጵያዊ ነኝ” -
በአገሪቱ የመጀመሪያው ሱፐር ማርኬት እ.ኤ.አ. በ1931 የተከፈተው በአዲስ አበባ ፍትሕ ሚኒስቴር አካባቢ የተተከለው ሱፐር ማርኬት ነው፡፡
የዚህ ሱፐር ማርኬት መከፈት ለአካባቢው ባምቢስ የሚለውን መጠሪያም አጋብቶበታል ።
ባምቢስ የሱፐርማርኬቱ ይዞታም ቻራ ላምቦስ ሲማስ በተባሉ ግሪካዊ ባለሀብት ሥር ነበር፡፡
ግሪካዊው ሚስተር ባምቢስ ቺማስ ከአገራቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ1944 ዓ.ም ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገና የ21 ዓመት አፍላ ወጣት ነበሩ ፡፡ ባምቢስ ሱፐር ማርኬትን ከከፈቱበት ጊዜ ጀምሮ አካባቢው በስማቸው መጠራቱ ደስታ እንደሚሰጣቸውና እሳቸው ካለፉም በኋላ፣ ስማቸው ለዘላለም ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠሉን ሲያስቡት ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረው ነበር፡፡
ሚስተር ባምቢስ፤ ከሱፐር ማርኬት ስራቸው ጎን ለጎን ኢትዮጵዊያንን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርተዋለወ። ‹‹ሞት በኩላሊት ይብቃ››ለተሰኘው የኩላሊት ህሙማን ማህበር የ1 ሚሊዮን ብር ‹በሮተሪ ክለብ በኩል ለግሰዋል፡፡
ሰበታ ውስጥ ለአይነ ስውራን ህክምና የሚያገለግል በ5 ሚሊዮን 120 አልጋዎች ያሉትና ባለ ሶስት ፎቅ ሆስፒታል አሰርተዋል፡፡ 3 ትላልቅ አምቡላንሶችን ለሆስፒታል ለግሰዋል። ሁለቱን ለፖሊስ ሆስፒታል፣ አንዱን ደግሞ ለየካቲት ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡
የኢትዮጵያው ወዳጅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በትናንትናው ዕለት ነው።
ነፍስ ይማር ሚስተር ባምቢስ!
Via:- Petros Ashenafi
@Yenetube @Fikerassefa

በትግራይ ክልል የተከናወነውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግ መንግሥት ያቀረበው አገራዊ ጥሪን መሠረት በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን እስካሁን ድረስ 100.7 ሚሊዮን ብር እንደሰበሰበ አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://bit.ly/39DtOfA
@Yenetube @Fikerassefa
ተጨማሪ ያንብቡ: https://bit.ly/39DtOfA
@Yenetube @Fikerassefa
በመተከል ዞን ሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ!
በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች መደምሰሳቸውን በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አስታወቀ። በተጨማሪም በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉም ተገልጿል።በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አባል ብርጋዴል ጄነራል አለማየሁ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለጹት በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካቶች ሲደመሰሱ ከፊሎቹ እንደተማረኩ እና ያመለጡ የታጣቂ ቡድኑን አባላት የማደን ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በመተከል ዞን የሚንቀሳቁ የጥፋት ቡድኖችን በማደን በ17 ቀበሌዎች የሚገኙ ሽፍቶችን ሙሉ በሙሉ መደምሰስ እንደተቻለም አስታውሰዋል።ከሁለት ቀን በፊት በዞኑ የኦነግ ሸኔና የህወሃት ተላላኪ ታጣቂ ቡድን አባላት በፈጸሙት ጥቃት የ74 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን ብርጋዴል ጄነራል አለማየሁ ገልጸዋል።
ግብረ ሃይሉ የታጣቂውን የሽፍታ ቡድን እንቅስቃሴ በመከታተል የተቀናጀ የህግ ማስከበር እርምጃ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።ብርጋዴል ጄነራል አለማየሁ እንዳሉት ከትናንት ጀምሮ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን በከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይፈቀድና ይህንን ገደብ ተላልፎ የሚገኝ እግረኛም ሆነ ተሽከርካሪ ካለ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል።
[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa

አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ!
አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።የፌዴራል መካከለኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው እለት የቀረቡት የህወሃት ቁልፍ አመራሮች ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል።
ተጠርጣሪዎቹ በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።ፖሊስ በጠየቀው መሰረትም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በኢንዶኔዢያ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ።አንድ ሆስፒታልም በአደጋው ፈርሶ ሀኪሞቹ እና ታማሚዎች በፍርስራሽ ውስጥ ታግተዋል፡፡6.2 ማግኒቱድ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጡ በርካታ ህንጻዎችን አፈራርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ኢትዮጵያ ለሥራ የሚጓዙ ግብጻውያን በቅድሚያ ካይሮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የመግቢያ ቪዛ ማግኘት እንዳለባቸው በአዲስ አበባ የግብጽ ኢምባሲ ማሳሰቡን አሕራም ጋዜጣ ዘግቧል። ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ሥራ ያላቸውም፣ ለመግቢያቸው በቅድሚያ ኅብረቱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ ማግኘቱን እንዲያረጋግጡ ኢምባሲው መክሯል። እስካሁን ባለው አሠራር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ግብጻውያን ቪዛ የሚያገኙት ቦሌ ዐለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ነበር።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን የአርሶአደሮች የሙዝ ማሳ ተጨፈጨፈ።
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ላንቴ ቀበሌ ትናንት ሐሙስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የአርሶ አደሮች የሙዝ ማሳ ተጨፍጭፎ ማደሩን የዞኑ ኮሚዩኔክሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ እሸቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጠዋል፡፡የተጨፈጨፈው የሙዝ ማሳ የስንት አርሶ አደሮች እንደሆነ እና ጉዳቱ የደረሰው በማን እንደሆነ በፖሊስ እየተጣራ ነው ያሉት ሃላፊው አቶ እያሱ ፖሊስ ማጣራቱን እንደጨረሰ ስለደረሰው ጉዳት ስፋትና መጠን እናሳውቃለን ብለዋል፡፡
[Ethio FM]

#"የተሳሳተ ውሳኔ ወስነን ወደነሱ ወጥመድ እንድንገባ የሚፈልጉ ወገኖች አሉ!!"
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
****
በሱዳን መንግሥት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች የሦስተኛ ወገን አጀንዳ ለማስፈጸም እየሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።
“እየተላላከ ያለ” ሲሉ የገለፁት ቡድን የሱዳን እና የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ወዳልሆነ ነገር ለማስገባት እየሰራ ነው በማለት ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ አውሮፕላን የሱዳንን የአየር ክልል ጥሶ ገብቷል በሚል ከካርቱም ወገን የተሰነዘረውን ውንጀላም አጣጥለዋል።
“ወደ ጦርነት የምንገባ ከሆነም በግልፅ እንጅ በድብቅ አይሆንም” ሲሉም ነው ኢትዮጵያዊው ጄነራል ለአሜሪካ ድምፅ ያስረዱት።
የተሳሳተ ውሳኔ ወስነን ወደነሱ ወጥመድ እንድንገባ የሚፈልጉ ወገኖች አሉ ያሉት ጄነራል ብርሃኑ ጦርነት በፈለገ ትንሽ ቡድን ፍላጎት ግን ወደነሱ ቀለበት አንገባም ብለዋል።
ሰከን የማለትን አስፈላጊነት የጠቀሱት ኤታማዦር ሹሙ መሬታችን ደግሞ የትም አይሄድም በማለትም አክለዋል።
Source፦VOA

ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
🇪🇹ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
04:00 | ባህር ዳር ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
09:00 | ሲዳማ ቡና ከ ድሬደዋ ከተማ
@Yenetube @Fikerassefa
🇪🇹ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
04:00 | ባህር ዳር ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
09:00 | ሲዳማ ቡና ከ ድሬደዋ ከተማ
@Yenetube @Fikerassefa
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል ስራዎች እየተከናወኑ ነው ተባለ!
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በክልሉ የተደረገውን የህግ ማስከበር ተከትሎ መቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያስመረቁ መሆኑን ገልጸው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 07/2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ መደረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም የመቀሌና አዲግራት ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በሚቻልበት ሁኔታና ለተቋማቱ መደረግ ባለባቸው ድጋፎች ላይ ውይይትና የስራ ክፍፍል ተደርጓል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግ ማስከበር ወቅት የደረሰውን ጉዳት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ከተማሪዎችና የዩኒቨርሰቲዉ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው!
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 1ሺህ 769 ወንድ እንዲሁም 954 ሴት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛ ዙር በሚያከናውነው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
[Walta]

በትግራይ ክልል መብራት፣ ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እስካሁን መልሶ ሥራ ባልጀመረባቸው አካባቢዎች ውስጥ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ አገልግሎቶቹን እንደሚያገኙ የመብራት ኃይልና የኢትዮቴሌኮም ኃላፊዎች ለቢቢሲ ገለፁ።
ከሁለት ወራት በፊት በክልሉ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ተቋርጠው የነበሩት የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በከፊል የተመለሱባቸው አካባቢዎች ቢኖሩም፤ በበርካታ ከተሞች ውስጥ እስካሁን አለመመለሳቸውን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።
አገልግሎቶቹን መልሶ በቶሎ ለማስጀመር ያልተቻለው በመሠረተ ልማቶቹ ላይ "የደረሰው ውድመት በጣም ከፍተኛ" የሚባል በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያዎች መስመሮች በመቆረጣቸውና ኢንሱሌተሮች [የኃይል ተሸካሚዎቹ እንዳይነካኩ የሚያደርጉ ስኒዎች] በመሰባበራቸው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌትሪክ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል።
የስልክና ኢንተርኔት አቅርቦትን በተመለከተም የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩም በክልሉ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሱ ከፍተኛ ጉዳቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ አስካሁንም ጥገና እየተካሄደ መሆኑንና "ባለው ነባራዊ ሁኔታ እንደልብ ተንቀሳቅሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥገናዎችን ማድረግ ያስቸጋሪ ስለነበር" በቶሎ ሥራ ማስጀመር አለመቻሉን ተናግረዋል።
[BBC]

የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ለመጀመሪያ እያስመረቀ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪ ጊዜ 8 መቶ 24 ተማሪዎችን ነው ለምረቃ ብቁ ያደረገው፡፡በዚህም በዛሬው ዕለት በዋናዉ ግቢ በተፈጥሮ ሳይንስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 4 መቶ 80 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡በነገው የምረቃ መርሀ ግብር ደግሞ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢው 3 መቶ 44 ተማሪዎች እደሚመረቁ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፍልስጤም ከ15 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ መሆኑን አስታወቀች
የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አባስ እንዳስታወቁት በ15 አመታት ጊዜ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍልስጤም ህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላትና የፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ታከናዉናለች ብለዋል፡፡
የአባስ ቢሮ ባወጣው መግለጫ መሠረት በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ ውስጥ የራስ አገዛዝ አስተዳደር በሆነው ግዛት በግንቦት ወር የሕግ አውጪዎቹ ምርጫ እንዲሁም በወርሃ ሐምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ መያዙን ይፋ አድርጓል፡፡
በ2006 ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደዉ የፍልስጤም ምርጫ ባልተጠበቀ መልኩ ሀማስ ማሸነፉ ውስጣዊ የፖለቲካ አለመግባባት እንዲሰፋ በማስገደድ ምርጫዉ እንዲራዘም አድርጓል፡፡ሀማስ የጋዛ ሰርጥን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡
የሐማስ እንቅስቃሴ አካባቢውን መቆጣጠር ከጀመረበት ከ2007 አንስቶ ጋዛ በእስራኤል እገዳ ውስጥ ትገኛለች ፡፡
የሙሃሙድ አባስ አስተዳደር በምስራቃዊ እየሩሳሌም ምርጫዉ እንደሚደረግ ያስታወቀ ሲሆን በኢየሩሳሌም ምርጫ ለማከናዉን የሚያስችል ምንም ፍንጫ ከእስራኤል ዘንድ አልታየም፡፡
[ዳጉ ጆርናል]

ሱዳን ደቡብ ሱዳን ያቀረበችውን የአደራዳሪነት ጥያቄ እንደሚቀበሉት አስታወቁ
የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳን መከላከያ ወደ ትግራይ ክልል በመሰማራቱ የተፈጠረውን ክፍተት ተከትሎ የኢትዮጵያን ድንበር መጣሷን እየገለጸች ነው
ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸውን የድንበር ግጭት በሰላም እንዲፈቱ ለማደራደር ያቀረበችውን ጥያቄ ሀገራቸው እንደምትቀበል የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አስታወቁ፡፡
ጁባ ያቀረበችውን ሃሳብ በበጎ እንደሚቀበሉት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ“የአፍሪካን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት” የተወሰደ ጥረት ነውም ብለውታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴንግ አሎር ኩኦልን በካርቱም ማነጋገራቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የተላከ የአደራዳሪነት ጥያቄን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አስረክበዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ሀገራቱ ያላቸውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላም እንዲፈቱ ቀደም ሲል መጠየቋ የሚታወስ ነው፡፡ ጁባ በኋላ ላይ አዲስ አበባና ካርቱም የድንበር ላይ ውዝግባቸውን በሰላም እንዲፈቱ ያደራዳሪ ሚና እንደምትወጣ ገልጻለች፡፡ ሀገሪቱ አደራዳሪ መሆን እችላለሁ ያለችውን ሀሳብ ሱዳን በበጎ እንደምትቀበለው ነው ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የገለጹት፡፡
አብደላ ሃምዶክም ጁባ ሀገራቱን ለማነጋገር ላቀረበችው ሃሳብ ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ ድርጊት የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማረጋገጥ የተወሰደ ቁርጠኝነት እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡ ከደቡብ ሱዳን የቀረበውን ሀሳብ ሀገራቸው እንደምትቀበል ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ይህ የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሄ ለመፍታት የተወሰደ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል፡፡
የሱዳን ባለሥልጣናት ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ላይ ውዝግብ ለሌሎች ሀገራት ለማሳወቅ ወደ ካይሮ፣አስመራ፣ጁባና ሳዑዲ አረቢያ መላካቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሱዳን ጋር የገባችበት የድንበር ላይ ውዝግብ በፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንደሚፈታ እንደምትፈልግ መግለጿ ይታወሳል፡፡
አምባሳደር ዲና ሱዳን ድንበር ጥሳ መግባቷንና ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ኢትጵዮጵያ እንደምትፈልግና ለጦርነት እንደማትቸኩልም መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር መጣሷንና ይህን ያደረገችው ጦሩ በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ዘመቻ መሰማራቱን ተከትሎ የተፈጠረውን ክፍተት በማየት መሆኑን ገልጿል፡፡
Via:- Alian
@Yenetue @Fikerassefa

ብልጽግና 10 ሚሊዮን አባላት አሉኝ አለ!
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ትናንት ባቀረበው የ6 ወር የስራ አፈፃጸም ሪፖርት፤ በአሁኑ ሰዓት በመላው አገሪቱ የተመዘገቡ 9 ሚሊዮን 941 ሺህ 467 አባላትና አመራሮች እንዳሉት አስታውቋል፡፡የፓርቲው የማዕከላዊ ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በሸራተን ሆቴል በተደረገው የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ባቀረበው በዚህ ሪፖርቱ፤ መዋቅሩን በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በመዘርጋቱ ነው ብሏል፡፡አስር ሚሊዮን ገደማ አመራርና አባላትን በመላ ሃገሪቱ ያፈራው ብልጽግና፤ በአሁኑ ወቅት ውስጣዊ ድርጅታዊ አንድነቱን በማጠናከር ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡በቀጣዩ ምርጫም በመላ ሃገሪቱ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ የሚያስችሉትን የምርጫ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑም በመድረኩ ተወስቷል፡፡በኢህአዴግ ፍራሽ ላይ የተመሰረተው ብልጽግና፤ በሃገሪቱ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ አላማና ግብ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡
[Addis Admas]

ዮዌሪ ሙሴቬኒ ምርጫውን ማሸነፋቸው ተገለፀ!
በኡዳንዳ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ማሸነፋቸውን ቢቢሲ በሰበር ዜናው አስነብቧል፡፡“ምርጫው ተጭበርብሯል” የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ግን ለስድስተኛ ጊዜ ምርጫውን ማሸነፋቸው ተሰምቷል፡፡የፕሬዚዳንቱ ተፎካካሪ ሙዚቀኛው ሮበርት ክያጉላኒ ወይም በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን“ምርጫው ተጭበርብሯል” የሚል ቅሬታ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ አንዳንድ የዜና አውታሮች ደግሞ የዮዌሪ ሙሴቬኒ ተፎካካሪ ሮበርት ክያጉላኒ በዋና ከተማዋ ካምፓላ የፓርላማ መቀመጫዎችን ማሸነፉን ዘግበዋል፡፡

ኮሚሽኑ የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ!
ኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በሃገሪቱ በየዓመቱ የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይደሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንደኛው መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡
ይህ ታላቅ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሀይማኖታዊ በዓል ከመሆኑም በላይ የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገሪቱን መልካም ገፅታ በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብሏል፡፡
በዓላቱ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር የፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ #ፌዴራል_ፖሊስ _ኮሚሽን አስታውቋል።

በመተከል ዞን ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ!
በዛሬው እለት ጥር 8/2013 በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኤኮንቲ እና በቁጂ ቀበሌ ዘጠኝ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን የአዲስ ማለዳ ታማኝ ምንጮች ተናገሩ።ማንም ሰው መሳሪያ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ እና የሰአት ገደብ በተጣለበት መተከል ዞን ዛሬም ግድያ ተፈፅሟል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።የተገደሉትም ዜጎች መሳሪያ መያዝ ክልክል መሆኑን ተከትሎ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ወደ እርሻ ቦታቸው በማቅናት ሳሉ መገደላቸውን ነው የአዲስ ማለዳ ምንጭ የተናገሩት።

በአማራ ክልል የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ መከላከያ ክትባት ለ307 ሺህ ሴቶች ከጥር 17 እስከ ጥር 22/2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ከሚዲያ ባለሙያዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ከመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባሕር ዳር ቅርንጫፍና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በእንጅባራ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት እድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ሁሉም ሴቶች ከጥር 17 እስከ ጥር 22/2013 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከላትና በሁሉም ጤና ተቋማት እንደሚሰጥ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የክትባት ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ አድማሱ አመላክተዋል፡፡በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ክትባት ከወሰዱ በኋላ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሁለተኛ ዙር ላልወሰዱ እና በ2013 ዓ.ም ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት ለሞላቸው ሴቶች ደግሞ የ1ኛ ዙር ክትባት በትምህርት ቤቶች፣ በአቅራቢያቸው በሚገኙ የክትባት ጣቢያዎችና ጤና ተቋማት እንደሚከተቡ ባለሙያው በውይይቱ ላይ ገልጸዋል፡፡
[AMMA]