YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አንጋፋው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርሲቲነት ማደጉ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ግምገማ ሲካሄድበት ከቆየ በኋላ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ መገኘቱን የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ በማረጋገጡ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲነት የተሸጋገረበትን እውቅና የሰጠው መሆኑ ታውቋል፡፡ወደ ዩኒቨርሲቲነት ስለመሸጋገሩ በተካሄደ የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ 74 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ትኩረት በመነፈጉ የሚፈለገው ደረጃ ላይ ሳይደርስ መቅረቱን አስታውሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ወደ ዩኒቨርሲቲነት እንዲሸጋገር ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡በቀጣይም ዩኒቨርሲቲውን በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕክል ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አዲስ ዙር የበረሃ አንበጣ ወረራ ስጋት እንደተጋረጠበት አስጠነቀቀ፡፡

ፋኦ በመግለጫው እንዳለው በምስራቅ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ሶማሊያ የበረሃ አንበጣው እየተፈለፈለ ነው፡፡በአሁኑ ወቅትም የበረሃ አንበጣው መንጋ የተወሰኑ የሰሜናዊ ኬኒያ አካባቢዎችን መውረር ጀምሯል፡፡የበረሃ አንበጣ ወረራው ከኬንያ በተጨማሪ እንደ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ ያሉ አገሮችንም እንደሚወር ፋኦ አስጠንቅቋል፡፡የምግብ እና የእርሻ ድርጅቱ የበረሃ አንበጣ ወረራው የሚያሰጋቸው አገሮች ለመከላከሉ እንዲተጉ መክሯል፡፡ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በተደጋጋሚ በአንበጣ መንጋ እየተወረረ መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡

Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአጊቱ ጉደታ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ!

የአጊቱ ጉደታ የቀብር ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው በዮሴፍ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ዛሬ ተፈጽሟል፡፡የአጊቱ ጉደታ ከጣሊያን አዲስ አበባ ሲገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን እና በም/ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አስክሬኑን መቀበላቸው ይታወሳል፡፡

በጣልያን ፍየል እያረባች የፍየል ተዋጽኦዎችንና የቆዳ ቅባቶችን በመሸጥ የጠንካራ ሠራተኛነት ተምሳሌት የነበረችው አጊቱ ጉደታ መገደሏ ተገልጾ ነበር፡፡ኢትዮጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ ወደ ጣሊያን በስደት ያመራችው እ.አ.አ በ2010 እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡የዛሬ 10 ዓመት ገደማ በስደት ወደ ጣልያን የሄደችው አጊቱ ጉደታ የስደት ህይወትን ወደ ስኬት በመለወጥ ተምሳሌት መሆን ችላ ነበር፡፡ በሰሜን ጣልያን ትሬንቲኖ በሚገኝ 11 ሄክታር መሬት ላይ በርካታ ፍየሎችን በማርባት፣ በኋላ ደግሞ La capra felice “ደስተኛ ፍየሎች” የተሰኘ የፍየል አይብ መሸጫ መደብር በመክፈት የሞቀ ንግድ ስራ በማከናወን የሀገሬው እና የመላ አውሮፓ መነጋገሪያ ሆና ነበር። አጊቱ ‘የደስተኛ ፍየሎች ንግስት’ በመባልም ትታወቅ ነበር፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ጨለያ ቀበሌ 27 ሰዎች ተገደሉ ተባለ!

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጨለያ ቀበሌ ዳሊቲ በተባለ ጎጥ በዛሬው ዕለት 27 ሰዎች መገደላቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።የዓይን እማኙ ግድያው ዛሬ ንጋት በግምት 11 ስዓት ላይ መፈጸሙን፣ጥቃት አድራሾቹ ግድያውን የፈፀሙት በቀስት መሆኑን ከግድያው አምልጠው ከመጡ ዘመዶቻቸው መስማታቸውን ገልጸዋል።በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አስከሬን በጨለያ ቀበሌ አስከሬናቸው መሰብሰቡንም ገልፀዋል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በርካታ ቁስለኞች በአካባቢው በሚገኝ የጤና ተቋም ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።በርካታ ቁጥር ያላቸው የአጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎችም ጥቃቱን በመፍራት ቀያቸውን ለቀው እየሸሹ ነው ብለዋል።

አስከሬናቸው ከተሰበሰቡ 27ቱ ሟቾች ውጭ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው አስከሬን እየተፈለገ በመሰብሰብ ላይ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም አስረድተዋል።በአካባቢው እስካሁን የመከላከያ ሰራዊት አለመግባቱንም ጨምረው ገልፀዋል።ጉዳዩን በተመለከተ የአካባቢውን ባለስልጣናት ጨምሮ የኮማንድ ፖስቱን መሪ ሌትናል ጀነራል አስራት ደነሮን ለማግኘት የእጅ ስልካቸው ላይ ቢደወልምም ምላሽ ባለማገኘቱ አስተያየታቸውን ሊካተት አልተቻለም።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በእነ እስክንድር ላይ ምስክሮች የሚቀርቡበት ጊዜ ተቀየረ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብርና በህገ መንግስት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት ዛሬ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ጉዳይ ተሰይሞ ቀጣይ የችሎት ቀጠሮውን አሳጥሯል።ችሎቱ የአቃቢ ህግን ምስክሮች ለመስማት ለመጋቢት መጨረሻ ሰጥቶ የነበረውን ቀጠሮ ዛሬ ወደ ጥር 26 ቀይሮታል።

ይህን ያደረገበት ምክያትም ችሎቱ ያሉበትን ሌሎች መዝገቦች ከሌሎች ችሎቶች ጋር ተከፋፍሎ በአፋጣኝ ፍርድ ለመስጠት እየሰራ በመሆኑ እንደሆነ ዳኞች አስረድተዋል።በእነ እስኪንድር ነጋ የክስ መዝገብ ስር የተካተቱት ተከሳሾች ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በተፈጠረው ሁከት እና ግጭት መከሰሳቸው ይታወሳል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ሴት አስጠኚ ይፈልጋሉ ??

ከKG እስከ 12ኛ ክፍል ልጆትን ብቁ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

አገልግሎታችንን ማግኘት ከፈለጉ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን ⬇️

💥 0961312250

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ደቡብ ሱዳን ጁባ አቀኑ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር ማያርዲትና ሃይለማርያም ደሳለኝ በጁባ መምከራቸዉ ተሰምቷል፡፡፡የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር ማያርዲትና የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱን ሀገራት በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡በዉይይታቸዉም አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተረጋጋ ሰላም መስፈኑን አስረድተዋል፡፡

ከዉይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የደቡብ ሱዳን የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቤትሪስ ካምሳ እንዳሉት፣ ሃገራቸዉ ሰላምን በማረጋገጥ ወደ ፊቷን ማዞሯንና ከኢትዮጵያ ጋርም ትብብሯን የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡ለዚህ ደግሞ ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ወሳኝ መሆናቸዉን ነዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተናገሩት፡፡

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ በንግድ፣በኢንቨስትመንትና በመሰረተ ልማት እንዲተሳሰር እያደረጉት ያለዉ እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነዉ ብለዉታል፡፡አቶ ሃይለማርያም ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አረጋግጠዉላቸዋል ብለዋል፡፡አቶ ሃይለማርያም በደቡብ ሱዳን የተረጋጋ ሰላም እንዲፈጠር ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር የሰሩት ስራ የሚደነቅ መሆኑንም ጨምረዉ መናገራቸዉን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ህይወት ጠፋ!

ግጭቱ የተቀሰቀሰው በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በመነጠል የራሳችን ያሉትን ልዩ ወረዳ እንመሰርታለን በሚሉና ጥያቄውን በሚቃወሙ ቡድኖች መካከል ነው።በግጭቱ የሰው ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ገለቦ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።በዞኑ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ገለቦ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በተቀሰቀሰውና አሁን ድረስ በቀጠለው በዚሁ ግጭት እስከአሁን ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ መኖሪያ ቤቶች በአሳት መጋየታቸውን ለዶቼ አረጋግጠዋል። የአሁኑ ግጭት የተቀሰቀሰው ቀደም ሲል በመሬት ይገባኛል ሰበብ በአካባቢው ለወራት ሲካሄድ የነበረው ግጭት በሽማግሌዎች ጥረት ከረገበ ከሁለት ሳምንት በኋለ ነው ተብሏል።የአካባቢው ነዋሪዎችና የአይን እማኞች በበኩላቸው በግጭቱ የተደራጁ ቡድኖች ወደ መንደሮች በመዝለቅ ግድያ መፈፀማቸውንና ንብረት ማውደማቸውን ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!!

ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀዬና አስመላሽ ወልደሥላሴ ተደመሰሱ።

በመካለከያ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም ጥቃት እንዲሰነዘር ያደረጉ ቁልፍ የህወሓት አመራሮች የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሀዬ፣ አስመላሽ ወልደሥላሴ እና ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎሥ መደምሰሳቸው ተገልፃል።

በተከዜ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ ተደብቀው የነበሩት አመራሮች ከነ ጠባቂዎቻቸው እና ከወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ተብለው የተዘረዘሩት የሚከተሉት ናቸው።

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ፣

2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዱ፣

3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዱ፣

4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበሩና

5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበሩ

@YeneTube @FikerAssefa
አንድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊ አውሮፕላን ዛሬ ወደ ሱዳን ግዛት ዘልቆ እንደገባ አል-ዐረቢያ ጋዜጣ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል።ድርጊቱ ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት አደገኛ መዘዝ ስላለው፣ ድጋሚ መደገም የለበትም ሲል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ማስጠንቀቁን ዘገባው ጠቅሷል። ሱዳን የኢትዮጵያ ተዋጊ አውሮፕላን ድንበሬን ጥሶ ገብቷል ያለችው፣ በቅርቡ በወታደራዊ ሃይል የተቆጣጠረችውን የኢትዮጵያ ግዛት ይሁን አይሁን ግን ዘገባው አላብራራም። በተያያዘ፣ ትናንት አንድ የሱዳን ወታደራዊ ሔሊኮፕተር የኢትዮጵያ አዋሳኝ በሆነችው ገዳሪፍ ግዛት እንደተከሰከሰባት ሱዳን አስታውቃለች።

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን የሟቾች ቁጥር አሻቀበ!

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጨለያ ቀበሌ ዳሊቲ በተባለ ጎጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 81 መድረሱን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።ነዋሪዉ ዛሬ ጠዋት በጥቃቱ የተገደሉ lየ27 ሰዎችን አስከሬን ተመልክተው እንደነበር ገልፀው፤ቆይቶ ግን በየጥሻው የወዳደቁ አስከሬኖች እንዲሰበሰብ በመደረጉ ቁጥሩ 81 መድረሱን ተናግረዋል።በአሁኑ ስዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በስፍራው መድረሳቸውንም አመልክተዋል።ጉዳዩን በተመለከተ የአካባቢውን ባለስልጣናትና የኮማንድ ፖስቱን መሪ ለማግኜት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢደረግም ሊሳካ ባለመቻሉ አስተያየታቸውም ማካተት አልተቻለም።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ "100 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሞብናል" ሲል ዘኒት ገብስ እሸት አስታወቀ።

በትግራይ ሽሬ ከተማ ተገንብቶ ሥራ ለመጀመር ዝግጅት ላይ የነበረው የዘኒት ገብስ እሸት ፋብሪካ 100 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጉዳት እንደደረሰበት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ተናግረዋል። ሰማየታ የእምነ በረድ ፋብሪካ እና ጎዳ ጠርሙስና እና ብርጭቆ ፋብሪካ ጉዳት እንደገጠማቸው ዶይቼ ቬለ አዲስ አበባ የሚገኙ ኃላፊዎቻቸውን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችያለው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 463 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4,919 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 463 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 129,455 ደርሷል።በሌላ በኩል 305 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 114,567 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@YeneTube @FIkerAssefa
አሜሪካ ዜጎቿ ወደ እንጦጦ ፓርክ እና ጉለሌ የእጸዋት ማዕከል እንዳይሄዱ አስጠነቀቀች።

አገሪቱ ዜጎቿ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀችው በጎብኝዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል እንደሆነ የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

እንደ ማስጠንቀቂያው ከሆነ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ጥቃት እየተፈጸመ ነው።

በመሆኑም አሜሪካውያን እና ሌሎች ዜጎች ወደ እንጦጦ ፓርክ፣ የካ ተራራ፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል እና ሌሎች የተራራ መውጣት እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ አስጠንቅቃለች።

Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል ።

በዚሁ መሰረት ፦

1- የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለታካሚ ህፃናት እና ቤተሰቦች ስቃይን ለመቀነስ በነፃ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የበጎ አድራጎት ስራ በዘላቂነት ለመደገፍ ያስችል ዘንድ የታክስ የዕዳ ምህረትና ከኪራይ ገቢ ግብር ነፃ እንዲደረግ ካቢኔው ወስኗል ።

2- በከተማዋ ለሚገኙ ዝቅተኛ የተማሪዎች የምገባ ስራ ላይ ለተሰማሩ እናቶች የአንድ አመት የገቢ ግብር ወጪን የዕዳ ምህረት እንዲደረግም ውሳኔ ተላልፏል

3. በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለቢሮ አገልግሎት በአመት 746 ሚሊዮን ብር በላይ የኪራይ ወጪ የሚያወጣባቸውና እነዚህ ቢሮዎች በተበታተኑ ቦታዎች በመሆናቸው ለተገልጋይ ከፍተኛ እንግልትን እና የህዝብ ገንዘብ ብክነት እያስከተለ ስለሆነ እነዚህ ቢሮዎች ሁሉንም ሰብሰብ አድርጎ በሁለት ክላስተር ለተገልጋዮች ለአገልግሎት ምቹ እና ወጪ ቆጣቢ የሚሆኑ ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት እንዲጀመር መወሰኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

@YeneTube @FikerAssefa
ለፀሐይ ሪል ስቴትና ለነዋሪዎቹ ማኅበር በተሰጠ ብድር ዙሪያ ከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጀመረ!

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ፀሐይ ሪል ስቴት ገንብቶ የሸጣቸውንም ሆነ ያልሸጣቸው ሕንፃዎች እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና ለሦስተኛም ወገን እንዳይተላለፉ ዕግድ ጠይቋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አፓርትመንቶቹ የተገነቡበትን የካርታ ቁጥር ካ8/178178/05 የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) በመያዣነት (ኮላተራል) በመያዝ፣ ሕግን በጣሰ አኳኃን 28 ሚሊዮን ብር ለሁለት የተለያዩ አካላት በማበደሩና ይህ ደግሞ ከባድ የሙስና ወንጀል ስለሆነና ይህንኑ እያጣራ በመሆኑ እንደሆነ አብራርቷል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው፣ ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/35VGLRd

@YeneTube @FikerAssefa
የኔቫዳ ግዛት የተወካዮች ምክርቤት አባል ነበረው ትውልደ ኢትጵያዊው አሜሪካዊው አሌክሳንደር አሰፋ በማጭበርበር ወንጀል ከምክርቤት አባልነቱ እንዲለቅ ተደረገ፡፡

አሌክሳንደር ምክርቤቱን እንዲለቅ ያስገደዱት ምክንያቶች በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት የተዋጣለትን ገንዘብ መዋጮ ባልተገባ መልኩ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል ምክንያት ነው።በምርጫው አግባብበነት በሌለው መኖሪያ አድራሻ ተወዳድሯል ፣የተሳሳተ የጋብቻ ማስረጃ አቅርቧል እና አጭበርብሯል በሚሉ ተጨማሪ ምክንያቶች ከምክር ቤቱ እንዲለቅ ተገዷል ፡፡ፖሊስ በርከት ተደራራቢ ጥፋቶች ክስ እንደሚመሰርትበት ይጠበቃል።

አሌክሳንደር የዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክሎ በኔቫዳ ግዛት ተወካዮች ምክርቤት የዲስትሪክት 42 ተመራጭ በመሆን ለሁለት የስራ ዘመን የምክርቤቱ አባል በመሆን ቆይቷል።አሌክሳንደር በላስቬጋስ እና በአካባቢው የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ላቅ ያለ ተሳትፎ እና አገልግሎት የነበረው ሲሆን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጰያውያን አንዲሁም በምርጫ የወከለውን የማህበረሰብ ክፍል በታታሪነተት እና በታማኝነት ሲገለግል ቆይቷል፡፡

የ 38 አመቱ ጎልማሳ አሌክሳንደር በላስቬጋስ ከተማ የኢትጰያውያን የንግድ ተቋማት በብዛት የሚገኙበት መንደር ሊትል ኢትዮጵያ ተብሎ በይፋ እንዲሰየም በግንባር ቀደምትነት ሲሰራ ቆየ የምክር ቤት አባል ነው፡፡ኢትዮጰያ ውስጥ በዶዶላ ከተማ ተወልዶ ያደገው ኤከልሳንደር አውሮፕላን የማብረር የካፒቴንነት ፈቃድ ያለው ሲሆን በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን በቨርጂኒያ ግዛት ከሚገኘው ከአቨርት ዩኒቨርስቲ አግኝቷል አማርኛ ኦሮምኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ይናገራል።

[ብስራት ሬድዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በዛሬው እለት ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው፡፡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስልጣን እንዲነሱ ኮንግረሱ ወሰነ!

ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የተካሔደባቸው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።ከሳምንት በፊት ታህሣሥ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሺንግተኑ ካፒቶል ሂል የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድርጊት ጋር በተያያዘ በርካታ ትችቶችን ከማስተናገዳቸውም ባለፈ ፣ የፈጸሙት ድርጊት ትክክል መሆኑን መናገራቸው ደግሞ ይበልጥ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ በዚሁ ድርጊታቸው ሳቢያ በ25ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ከስልጣን እንዲነሱ የተወካዮች ምክር ቤቱ ቢወስንም ፣ ይህን ውሳኔ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ አልተቀበሉትም፡፡

ይህን ተከትሎ ፣ ትራምፕ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ተከሰው ፣ በኢምፒችመንት ከስልጣን እንዲነሱ ምክር ቤቱ ትናንት ምሽት ወስኗል፡፡ለ5 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የካፒቶል አመጽ በመቀስቀስ የተወቀሱት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወንጀል መስራታቸው ተረጋግጦ በኢምፒችመንት ከስልጣን እንዲነሱ በሴኔቱ ከጸደቀ ፣ ከዚህ በኋላ በምርጫ መወዳደር አይችሉም፡፡ሴኔቱ በኢምፒችመንቱ ላይ ድምጽ የሚሰጠው ከባይደን በዓለ ሲመት በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 266 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

በሁለተኛ ዙር ከተመረቁት ከነዚህ ተማሪዎች መካከል 555ቱ ሴቶች ሲሆኑ የተቀሩት ወንዶች ናቸው፡፡ዩኒቨርሲቲው በአምስት ኮሌጆቹ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸው የነዚህ ተማሪዎች ምረቃ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ እንደነበር ተገልጿል።ዛሬ የተመረቁት ተማሪዎች በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በጤና ሳይንስ ኮሌጆች የሰለጠኑ መሆናቸው ተመልክቷል።በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa