YeneTube
Photo
በመተከል ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት የተሳተፉና በቸልተኝነት ሃላፊነታቸው ባልተወጡ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤዻር ቀበሌ ተከስቶ በነበረው የሰዎች ሞትና ንብረት መውድም መፍትሄ ለመስጠት በግልገል በለስ ከተማ ሲደረግ የነበረው የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት ተጠናቋል።በቀጠናው አንጻራዊ ሰላም ለማስፈን አጥፊዎችን እና ተባባሪ ግለሰቦችን በህግ በቁጥጥር ስር በማዋል የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት እየታየ ያለውን የጸጥታ ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት እና ጉዳዩን በገለልተኛ አካል የተቋቋመ መርማሪ ቡድን ወደ ስፍራው በመላክ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ደመቀ ተናግረዋል።በዞኑ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል በህዝቦች ላይ የተሳሳተ መረጃዎችን በማሰራጨት ግጭት የሚፈጥሩ ሃይሎችን ለማስወገድ መንግስት ከጸጥታ አካላት ጋር በትኩረት ይሰራልም ተብሏል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው ለውጡን ያልተቀበሉና የህብረተሰቡን የአብሮነት ዕሴት የማይፈጉ ሃይሎችን አጀንዳ ተቀበለው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በአካባቢው የሰው ህይወትና ንብረት እንዳወደሙ ገልጸው ይሄን በፈጸሙ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።ከተለያዩ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር በራሳቸው ስነ መግባር ችግር የተባረሩና ህብረተሰቡን በሃይል በማስፈራራት የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም በሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ግጭቱ እንደተፈጠረም አቶ አሻድሊ አክለው ተናገረዋል።በዞኑ ግጭትን በማስነሳትም ሆነ በሰው ህይወት እና ንብረት ማወደም የተጠረጠሩ 300 የሚደሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።
[የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa

ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ!
ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ 400 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 4 ኪሎግራም ኮኬይን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።አገልግሎቱ ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በማይሰራ ላፕቶፕ ቦርሳ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቀጥጥር ሥር ውሏል።ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ በላፕቶፕ ቦርሳ ለማሳለፍ የሞከረው አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በኤክስሬይ ፍተሻ አማካኝነት የተያዘ ሲሆን፤ በወንጀል ድርጊቱ ተባባሪ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሌሎች ሶሰት ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉት አራት ተጠርጣሪዎችና አደንዛዥ እፁ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀረ አደገኛ ዕፅ ዲፓርትመንት መላካቸውም ተመልክቷል።የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በጥናት ላይ የተደገፈ የመረጃ ስራ እያከናወነ መሆኑን በላከው መግለጫ አመልከቷል፡፡
[EBC]

በኢትዮጵያ 616 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 301 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 10 ሺህ 322 የላቦራቶሪ ምርመራ 616 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 68 ሺህ 131 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 301 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ 939 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 89 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 39 ሺህ 101 ሰዎች መካከል 294 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 194 ሺህ 795 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የአፋር ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ አረፉ፡፡
የአፋር ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ባደረባቸው ሕመም የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይዋል።ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የአፋር ሕዝብ ሱልጣን በመሆን አገልግለዋል።ሱልጣን ሀንፈሬ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት በመሆን የመሩ ሲሆን በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆንም ኢትዮጵያን አገልግለዋል።የሱልጣን ሀንፈሬ ሥርአተ ቀብር ነገ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም በአይሰኢታ ከተማ በሀደሌ ጌራ የሚፈፀም መሆኑን የክልሉን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

ከ13.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ!
የገቢዎች ሚኒስቴር 13 ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሰባ ሶስት ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከመስከረም 4-9/2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የጉምሩክ ስነስርዓት ሳይፈፀምበት ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ማሽላ እና ስንዴ፣ ወደ አዲ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ ሲጋራ፣ በህዝብ ማመላሻ ሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ የሽጉጥ ጥይት፣ በጭነት ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ የነበረ የክላሽ ጥይት፣ የሞባይል ስልኮች፣ ከሀገር ሊወጣ ሲሉ የተያዙ የቁም ከብቶች፣ የብር ጌጣጌጥ፣ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ ልባሽ እና አዳዲስ አልባሳት ናቸው።የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተሽከርካሪ ክፍል ውስጥ በመደበቅ እና ጨለማን ተገን አድርጎ ለማሳለፍ ሲሞከ በፍተሻ ተደርሶባቸው፣ ኬላን ጥሶ ለማለፍ ሙከራ በማድረግ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ከተደበቁበት ቦታ ክትትል በማድረግ የተያዙ ናቸው።ዕቃዎቹ በሀረር፣ በነጌሌ ቦረና ፣ በቱሉ ዲምቱ ፣ በጋላፊ፣ በባህርዳር እና በድሬዳዋ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች እና ኬላዎች የተያዙ መሆናቸው ተገልጿል።

የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማእከልና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ!
የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማእከልና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት የመሰረት ድንጋይ በአምቦ ከተማ ተቀመጠ፡፡የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርቲስቱ 80 ቀን የሙት መታሰቢያ ላይ በመገኘት አስቀምጠዋል።የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ይሄው መታሰቢያና ባህልና ታሪክ መዕከል አርቲስቱን ከማስታወስ ባለፈ መጭው ትውልድ ስለ ኦሮሞ ታሪክ የሚያውቅበት በርካታ ነገሮችን ያካትታል ተብሏል።
[FBC]

ሁሉም ባንኮች ለ15 ዓመታት ያልተንቀሳቀሱ ሒሳቦችን ለብሔራዊ ባንክ እንዲያስረክቡ ታዘዙ!
ሁሉም የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በደንበኞቻቸው ተከፍተው ለ15 እና ከዚያ በላይ ዓመታት የባለቤትነት ጥያቄ ሳይቀርብባቸው የቆዩ ተከፋይ ሒሳቦችን፣ ለኢትዮጵያ ለብሔራዊ ባንክ እንዲያስረክቡ ተወሰነ።ውሳኔው የተላለፈው ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመርያ ነው።ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ያወጣው መመርያ በአሁኑ ወቅት ተፈጻሚ መሆን እንደጀመረም ለማወቅ ተችሏል።ሁሉም ንግድ ባንኮች በሥራቸው የሚገኘውን ለ15 ዓመታት እና ከዚያም በላይ ለሆነ ጊዜ የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበትን ተከፋይ ሒሳብ ለብሔራዊ ባንክ ካስረከቡ በኋላ፣ በዚህ ሀብት ላይ የሕግ ተጠያቂነት እንደማይቀርብባቸው መመርያው ይደነግጋል።
የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበት ተከፋይ ሒሳብ ማለት ‹‹ለ15 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተከታታይ ዓመታት የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበት፣ በዋና ገንዘቡ ላይ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ እንቅስቃሴ ያልተደረገበት በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ወይም የገንዘብ ደረጃ ያለው ማንኛውም ተከፋይ ሒሳብ ነው፤›› ሲል መመርያው ትርጓሜ ሰጥቶታል።በመመርያው መሠረት ሁሉም ባንኮች ከላይ የተቀመጠውን ትርጓሜ ያሟሉ በሥራቸው የሚገኙ ተከፋይ ሒሳቦች የተገለጸውን የ15 ዓመታት የጊዜ ገደብ ካሟሉበት ቀን አንስቶ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበት ተከፋይ ሒሳብ መሆኑን የሚገልጽ ማስታወቂያ ተደራሽነት ባላቸው መገናኛ ብዙኃን ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት እንዲያስተዋውቁ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ሒሳቡን የከፈተ ግለሰብ ሊገኝበት በሚችል አድራሻና ስልክ ጥሪ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የተከፋይ ሒሳቡ ባለመብት የመጨረሻው ማስታወቂያና ጥሪ በተደረገለት በ90 ቀናት ውስጥ ያልቀረበ እንደሆነ፣ ባንኩ የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበትን ተከፋይ ሒሳብ ከአምስት ብር ጀምሮ ብሔራዊ ባንክ ለዚህ ብሎ በሚከፍተው የባንክ ሒሳብ ውስጥ የማስገባት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ባንኮቹ የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበትን ተከፋይ ሒሳብ ለብሔራዊ ባንክ ሲያስረክቡ፣ የሕጋዊ ባለመብቱን ሙሉ መረጃም ለብሔራዊ ባንክ ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል።
በተጨማሪም የይገባኛል ጥያቄ ባለመቅረቡ ምክንያት ወደ ብሔራዊ ባንክ የተላለፉ ተከፋይ ሒሳቦችን መረጃ በድረ ገጻቸው ላይ፣ ለተከታታይ አሥር ዓመታት ለሕዝብ ተደራሽ አድርገው ማቆየት ይጠበቅባቸዋል።ባንኮች የተጠቀሰውን ሥነ ሥርዓት አሟልተው ያስተላለፉትን የይገባኛል ጥያቄ ያልቀረበበት ተከፋይ ሒሳብ በተመለከተ የሕግ ተጠያቂነት እንደማይቀርብባቸው መመርያው የሚደነግግ ሲሆን፣ በተከፋይ ሒሳቡ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያለው ግለሰብ ጥያቄውን ማቅረብ የሚችለው ለብሔራዊ ባንክ እንደሆነም ይደነግጋል።
ጥያቄ ያልቀረበበት ሒሳብ ወለድ የሚከፈልበት እንደሆነና ባንኮቹ ለብሔራዊ ባንክ የሚያስተላልፉት ፍሬ ገንዘቡን ብቻ እንደሚሆን መመርያው የሚገልጽ ሲሆን፣ ተከፋይ ሒሳቡ ወለድ የሚከፈልበት ከሆነ ባንኮቹ ወለዱን የራሳቸውን ካፒታል ለማሳደግ እንዲያውሉት ይፈቅድላቸዋል።ይህ በመሆኑም ባንኮች ወደ ብሔራዊ ባንክ ባስተላለፉት ተከፋይ ሒሳብ ላይ የባለቤትነት ጥያቄ ቢረጋገጥ፣ ባለቤቱ ከፍሬ ገንዘቡ ውጪ የወለድ ክፍያ እንደማያገኝ በመመርያው ተመልክቷል።
Via Reporter

ትምህርት ቤቶች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ ጥንቃቄ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቅድሚያ መሰራት እንዳለባቸው ተጠቆመ፡፡
የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች እና የህግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በጤና ሚኒስቴር በኩል በቀረበው የኮቪድ 19 ምክረ ሀሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ቋሚ ኮሚቴው ውይይት ካደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ትምህርት አንዱ ሲሆን በቀጣይ ትምህርትን እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል በተለይ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ ለመጀመር መታቀዱ እንዳለ ሆኖ ግን በዩኒቨርስቲዎችና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከሎችም ላይ ትምህርትን ለማስጀመር ምን ምቹ ሁኔታ አለ በሚለው ላይ ከቋሚ ኮሚቴዎቹ በስፋት ጥያቄ ተነስቷል፡፡
የትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ትምህርት ቤቶች በኮቪድ 19 ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት ውስጥ ዋነኞቹ ሲሆኑ በ2012 ዓ.ም አጋማሽ ለመቋረጥ መገደዳቸውና በዚህም ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ወደየቤታቸው እንደተመለሱና ይህንን ተከትሎ በህጻናት አዕምሯዊ እድገት፣ በትምህርት ፍላጎታቸው ላይ እና ያለእድሜ ጋብቻ ባጠቃላይ ማህበራዊ ቀውሶችን እያስከተለባቸው እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡አክለውም እንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ኮቪድ 19 ከሰዎች ጋር የሚቆይ በሽታ በመሆኑ ትምህርትን ለማስጀመር የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የመማር ማስተማሩን ሂደት ጤናማ ለማድረግ በወጣው መመሪያ አዲስ ስታንዳርድ ወጥቶ ከዚህ በፊት እስከ 60 ተማሪዎችን የሚይዘው የመማሪያ ክፍል ከ20-25 ተማሪዎችን ብቻ እንዲይዝ መደረጉና አስፈላጊውን የበሽታ መከላከያ ቁሳቁስ ለማሟላት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን በዋናነትም ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም የክፍል ተማሪ ጥምርታን በማሻሻል ተጨማሪ ማስፋፊያ ያደረጉ ክልሎች እንዳሉና መጀመሪያም የነበረው ጥምርታ ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎችና ክልሎች ላይ አሁንም ባለው ሁኔታ ትምህርን ማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩንም ገልፀዋል፡፡ የ8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው በመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማስቀጠል በርካታ የትምህርት ቁሳቁስ ባለመኖሩ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተቋረጠ ቢሆንም ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት ባለማስፈለጉ በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርቱ ሲሰጥ መቆየቱንና አብዛኛዎችም እየተመረቁ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ ለተመራቂ ተማሪዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያነሱት፡፡
ይሁን እንጂ አሁን ላይ ምዝገባ ቢጀመርም ትምህርት የሚጀመርበት ቀንና ሁኔታ አሁን ላይ እንደማይታወቅ አንሰተው በቀጣይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ጤናማ የትምህርት አጀማመር ዝግጅቱ ሲጠናቀቅና በትክክለኛው ቁመና ላይ ሲደረስ የሚታወቅ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሀርላ አብዱላሂ በበኩላቸው የኮቪድ 19 በሽታ በዚህ ጊዜ ይቆማል የሚል ሳይንሳዊ የሆነ ምንም ዓይነት መረጃ ባለመኖሩ ትምህርት ቤትን ከመክፈትና አለመከፈት ጋር ተያይዞ የአለም ጤና ድርጅት በአጭር ጊዜ የሚሰሩ የጥንቃቄ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ያስቀመጠውን መሰረት በማድረግ አገሪቱ ዩኒቨርስቲዎችን ለለይቶ ማቆያነት ስትጠቀምባቸው ስለነበር እነዚህን የትምህርት ተቋማት የማጽዳት ስራም መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
አሁን ላይ ዩኒቨርስቲዎች ራሳቸው ሳኒታይዘርና ማስክ የመሳሰሉ የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን እያመረቱ ስለሆነም የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እጥረት ከዚሁ ጋር የሚቀረፍና ለጤናማ የትምህርት ዝግጁነት እንደሚረዳም ነው የተናገሩት፡፡ቋሚ ኮሚቴዎቹ በሰጡት ማጠቃለያ አሁን የተጀመረው የተማሪዎች ምዝገባ ጥሩ ጅማሮ መኖሩን የሚያሳይ ቢሆንም የትምህርት አጀማመሩን በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ የግንዛቤ ክፍተት እንዳለ አንስተው ትምህርት እስኪጀመር ባሉት ጊዜያት ሚኒስቴሩ ከባለድርሻና ከህብረተሰቡ ጋር ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
[HoPR]

የመስቀል በዓል ኮቪድ-19 ለመከላከል ሲባል የተወሰነ ምዕመናን በተገኙበት ይከበራል!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፓትርያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ ÷መስቀል ቤተክርስቲያኗ ከምተከብራቸው የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ነው ብለዋል።የመስቀል ደመራ በየዓመቱ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርአት ብዙ ህዝብ ተገኝቶ የሚያከብረው በዓል መሆኑንም አስታውሰዋል።
የዘንድሮው የደመራ በዓል ግን ስርዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከልን መሰረት ባደረገ መልኩ አነስተኛ ምዕመናን በተገኙበት እንደሚከበር ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ ገልጸዋል።በዚህም በአጠቃላይ እስከ 5 ሺህ ተሳታፊዎች በመስቀል አደባባይ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተናገሩት።
ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ አያይዘውም በዘንድሮ በዓል የተሳታፊ ሰዎች ቁጥር የተወሰነው ካለው ወቅታዊ የወረርሽኙ ሁኔታና መስቀል አደባባይ በአሁኑ ወቅት ማስተናገድ የሚችለውን መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ሲሆን ይህንንም የጠቅላይ ቤተክህነት ለሚመለከተው አካል አሳውቋል ነው ያሉት።የመስቀል አደባባይ ለበዓሉ ዕለት ክፍት እንደሚሆንና ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መግለጹንና ይሄንንም በአካል ተገኝቶ መመልከቱን አስረድተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ዝነኛዋ የእግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ ተሞሸረች!
የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን እና የማልታው ቢርኪርካራ ክለብ ተጫዋች የሆነች ሎዛ አበራ ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2013 ዓ.ም ተሞሽራለች፡፡
ሎዛ የሀዋሳ ከነማ ሴቶች ቡድንን በተቀላቀለችበት ወቅት ከተዋወቀችው የፍቅር አጋሯ ዮሐንስ ፈቃዱ ጋር ነው ዛሬ በይፋ የጋብቻ ስነ ሥርዓቷን የፈጸመችው፡፡
በሀገር ዉስጥም በውጭም በእግር ኳስ ጨዋታ ህይወቷ ስኬታማ የሆነችው ሎዛ አሁን በምትጫወትበት የማልታ ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ግብ አግቢነትን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን አሸንፋለች፡፡
Via Alain Amharic

የሀዲያ ዘመን መለወጫ በዓል “ያሆዴ” እየተከበረ ነው!
የሀዲያ ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” ክብረ በዓል በሀዲያ ዞን እየተከበረ መሆኑን የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል።የዘመን መለወጫ በዓሉ አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በዞኑ ሚሻ ወረዳ መከበር መጀመሩን የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ካሳሁን አባይነህ ለኢቲቪ ገልጸዋል።በዞን ደረጃ ከዛሬ ጀምሮ እየተከበረ የሚገኘው ክብረ በዓል በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት እንደሚቆይ ሃላፊው አክለዋል።
Via ETV

በአፋር ክልል በ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የበልሆ መቆጣጠሪያ ኬላ ዛሬ በይፋ ተመረቀ።
ኬላው የአፋር ክልልን ከጅቡቲ ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርንና ኮትሮባንድን ለመከላከል ያግዛል ተብሏል።የመቆጣጠሪያ ጣቢያው በጀርመንና በአውሮፓ ህብረት በሚደገፈው በጂአይዜድ ድጋፍ እንደተገነባ ተጠቁሟል።ይሄንን ጨምሮም በሀገሪቱ ጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ኬላዎች 12 የደረሱ ሲሆን የመቆጣጠር አቅምን በተወሰነ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጎታል ሲሉ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ተናግረዋል።ኬላው ወደ ጅቡቲ የታጁራ ወደብ የሚያስገባና የሚያስወጣ በር በመሆኑ የሰዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና በጅቡቲ በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረግ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።።የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው በበኩላቸው በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መብዛታቸው በህገወጥ እንቅስቃሴ ለእንግልት የሚዳረጉ ዜጎችን ለመታደግና ኮትሮባንድን ለመቀነስ አስተዋፅኦ አለው ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ 689 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 375 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 23 የላቦራቶሪ ምርመራ 689 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 68 ሺህ 820 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 375 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 314 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 96 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 39 ሺህ 408 ሰዎች መካከል 290 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 202 ሺህ 818 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

"በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖቻችን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 15.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የምግብ እህል፣ ለቀጣይ ምርት ዘመን የሚውል የእህል ዘር እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለአፋር ክልላዊ መንግስት አበርክተናል፡፡"
-አቶ ኡመር ሁሴን (የግብርና ሚንስትር)
@YeneTube @FikerAssefa
-አቶ ኡመር ሁሴን (የግብርና ሚንስትር)
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🌻ከNat Computers አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ የወጣ ታላቅ ቅናሽ 🌻
🔅Gaming Laptops🔅
✅Omen X #41500birr
✅ DELL G5 i7 gaming #41500br
✅ Lenovo legion R720 #41500br
✅ Dell inspiron 7567 i7 #41500birr
እና ሌሎችም
🌻🌻ቅናሹን ለመጠቀም 🌻🌻
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል
ስልክ
+251911522626
+251953120011
+251947885430
Inbox @Natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA
አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከangla burger ፊለፊት

Forwarded from HEY Online Market
iPhone 11 (128GB)
New Packd
Storage: 128GB
Color: Grey , Red, white
📌Dual SIM card
Price:38,500
Contact us
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
091069510 @RoViii
New Packd
Storage: 128GB
Color: Grey , Red, white
📌Dual SIM card
Price:38,500
Contact us
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
091069510 @RoViii
ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የቢሾፍቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ!
ከአዲስ አበባ በ45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው ባለ 400/230/12 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር ገለጹ፡፡አቶ ዳዊት እንደገለፁት የማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡
ከነባሩ አቃቂ - ገላን ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ቢሾፍቱ ማከፋፈያ ድረስ 46 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታም ተከናውኗል፡፡የፕሮጀከቱ የሳይት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ አቶ ዘውዱ ለገሰ እንደገለፁት ማከፋፈያ ጣቢያ ሁለት ባለ 600 ሜጋ ቮልት አምፒር እና ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡ጣቢያው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር እና ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት እንዲሁም 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
የማከፋፋያ ጣቢያውን የገነባው ላርሰን ኤንድ ቱቡሮ የተባለ የህንድ ኩባንያ ሲሆን ግንባታው ለመጨረስ ከ25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡የማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት በቢሾፍቱ ከተማ እና በዙሪዋ ለሚገኙ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችና የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ለህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል፡፡
[EEPCo]

የአሮሚያ ክልል ለዲቦራ ፋውንዴሽን 10 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገባ!
የኦሮሚያ ክልል በቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት በነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ለተመሰረተው ዲቦራ ፋውንዴሽን 10 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገባ። የክልሉ መንግስት ገንዘቡን ለመስጠት ቃል የገባው ፋውንዴሽኑ በለገጣፎ ለሚያሰራው ትምህርት ቤት፣ የጤና አገልግሎት መስጫ እና ማሰልጠኛ ማዕከል ነው።
ዲቦራ ፋውንዴሽን በአቶ አባዱላ አራተኛ ልጅ የተሰየመ እና “ዳውንሲንድረም” ተብሎ በሚታወቀው የአእምሮ ዕድገት ውሱንነት የተጠቁ ህጻናትን ለመደገፍ በሐምሌ 2011 ዓ.ም. የተቋቋመ ነው። በቅዳሜ ምሽቱ የፋውንዴሽኑ የማሰልጠኛ ማዕከል የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከመንግስት እና ከግል ተቋማት ያልተጠበቁ ልገሳዎች በዚያው በመድረኩ ሲሰጡ ታይቷል። ከመንግስት በኩል ከፍተኛውን ድርሻ የወሰደው የኦሮሚያ ክልል ነው። ለማሰልጠኛው ግንባታ የክልሉ መንግስት ለመስጠት ቃል ከገባው 10 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ የክልሉ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የመዋዕለ ህጻናት ግንባታውን ራሱ ለማከናወን መወሰኑን አስታውቋል።
የኦሮሚያ ክልሉ የትምህርት ቢሮ በበኩሉ ሽያጩ ለፋውንዴሽኑ እንዲውል በሚል በአቶ አባዱላ የተጻፉ 10 ሺህ መጽሐፍትን ለመግዛት ቃል ገብቷል።መጽሐፍቱ በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፋፈሉ በስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል። ከትምህርት ቢሮ በተጨማሪ የተለያዩ የግል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ወደ አራት ሺህ ገደማ መጽሐፍት ለመግዛት ቃል ገብተዋል።
Via Ethiopia Insider