YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኮሚሽኑ ገለጸ!

ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች በጎርፍ ሊጎዱ ይችላሉ የሚል ጥናት ቀርቦ ነበርበኢትዮጵያ በተለይ በነሀሴ ወር የጣለውነ ከባድ ዝናብ ተከትሎ የመጣ ጎርፍ በተለያዩ አካባቢዎች በርካቶችን ለጉዳት ዳርገዋል፡፡በተለይ በአፋር፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰተው ጎርፍ የሞትና የፈናቀል አደጋ አስከትሏል፡፡በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን እንዲሁም በአፋር ክልል ሁሉም ዞኖች የተከሰቱ ዜጎች እንዲፈናቀሉና ማሳዎቻቸው በጎርፍ እንዲወሰዱ አድርጓል፡፡ ጉርፉ ነዋሪዎችን ከማፈናቀል ባሻገር እንስሶቻቸው ወስዶባቸዋል፡፡

በክረምቱ በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች ዜጎች ለጉዳት ሲዳረጉ ሙሉ ለሙሉ መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው እንዲፈናቀሉም አድርጓል፡፡ በተለይ ይህ በቅርቡ በአዋሽ ወንዝ አካባቢ ባሉ ነዋሪዎች ላይ ጫናው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በክረምት ወቅት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለጉዳት ሊዳረጉ እንደሚችሉ የሚያመለክት ጥናት አቅርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በጎርፉ ምክንያት ለጉዳት ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱት ሁለት ሚሊዮን 66ሺ 683 ሰዎች መካከል 434 ሺ የሚሆኑ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉም ቅድመ ግምት መቀመጡን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቅና ምላሽ ዳይሬክተሯ ወ/ሮ አልማዝ ደምሴ እንዳሉት አሁን ላይ በርከቶች ማሳቸው በጎርፍ መበላሸቱን እንዲሁም ዜጎች ለመፈናቀል መገደዳቸውን ገልጸዋል

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ህንድ በሃገሯ የተጀመሩ የኮሮና ክትባት የሙከራ ሂደቶች እንዲቆሙ አዘዘች!

ህንድ ሴረም የተሰኘው የክትባት መድሃኒቶች አምራች ተቋሟ የጀመረውን የኮሮና ክትባቶች የሙከራ ሂደት እንዲያቆም አዘዘች፡፡ተቋሙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጃቸው የኮሮና ክትባቶች ላይ የጀመረውን የምዕራፍ 2 እና 3 ክሊኒካዊ የሙከራ ሂደት እንዲያቆምም የሃገሪቱ የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡መድሃኒቶቹ አስትራዜናካ በተሰኘው ግዙፍ የመድሃኒት አምራች ተቋም በኩል ለሴረም ኢንስቲትዩት የደረሱ ሲሆን ተጓዳኝ የጤና እክሎችን አስከትለዋል በሚል የሙከራ ሂደታቸው ቆሟል፡፡ይህን ታሳቢ በማድረግ በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ የክሊኒካል ሙከራ ሂደቶች እንዲቆሙ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ቀደም ሲል ለተደረጉ ሙከራዎች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥና ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡ሂደቱ ዳግም ፍቃድ እስኪያገኝ ድረስ ይቁም ያለም ሲሆን በእንግሊዝና ህንድ ከሚገኙ የመረጃ እና የደህንነት ቁጥጥር ተቋማት “ክሊራንስ” እንዲቀርብለት ጠይቋል እንደ ሂንዱስታን ታይምስ ዘገባ፡፡አስትራዜናካ የጀመረውን የሙከራ ሂደት በጊዜያዊነት እንዳወቆመ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 8,191 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 469 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

345 ሰዎች ሲያገግሙ 10 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 63 ሺ 888 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 24 ሺ 493 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ996 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኮረና ቫይረስ መመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ከፈቱ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መርቀው የከፈቱት የኮረና መመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ነው፡፡በኢትዮጵያና በቻይና መንግስት ትብብር የተቋቋመው ፋብሪካው በዓመት 10 ሚሊየን የኮቪድ 19 ኪቶችን እንደሚያመርት ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኮረና ቫይረስ መመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ከፈቱ! ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መርቀው የከፈቱት የኮረና መመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ነው፡፡በኢትዮጵያና በቻይና መንግስት ትብብር የተቋቋመው ፋብሪካው በዓመት 10 ሚሊየን የኮቪድ 19 ኪቶችን እንደሚያመርት ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
ቢ.ጂ.አይ ጤና ኢትዮጵያ ለሀገራችን እንዲሁም ለውጪ ሀገራት ገበያ የሚሆኑ የኮቪድ-19 ፖሊመሬስ ቼይን ሪአክሽን (ፒ.ሲ.አር) መመርመሪያ ኪቶችን ማምረት ጀምሯል።ለውጪ ሀገራት በሚደረገው ሽያጭ ለአፍሪካ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል። በተጨማሪም፣ ፋብሪካው ቁጥራቸው በአጠቃላይ 3 ሚሊየን ለሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለሚያልፉ መንገደኞች በክፍያ የላብራቶሪ አገልግሎት ይሰጣል።ይህም የኢትዮጵያን እና የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን የመመርመር አቅም ከፍ ያደርጋል።የኮቪድ19 ስርጭት ከተገታ በኋላ፣ የማምረቻ ማዕከሉ የኤድስ ፣ የሳንባ ነቀርሳ እንዲሁም ሌሎች የሪል ታይም (አር.ቲ.) ፒ.ሲ.አር መመርመሪያ ኪቶችን ጨምሮ ሌሎች ኒዩክሊክ አሲድን መለያ ኬሚካሎችን ወደ ማምረት ይሸጋገራል።

-ጠ/ሚር አብይ አህመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ።የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ አቶ ዳውድ በፓርቲው አንድነትና ሰላማዊ ትግል ላይ እየፈጠሩት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም ያሉባቸውን ችግሮች ከማስተካከል ይልቅ ፓርቲውን የመከፋፈልና አንጃ የመፍጠር አካሄዶችን ሲከተሉ ቆይተዋል።በመሆኑም ለፓርቲው ህልውናና ጥንካሬ ሲባል የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው አግዷቸዋል።

በቀጣይ በፓርቲው ህገ ደንብና አሰራር መሰረት የሚከናወኑ ተግባራት መኖራቸውን ያስታወቁት አቶ ቀጃላ፤ ሁሉንም ሂደቶች በተመለከተ ፓርቲው ለምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ሰነድና መረጃ ማስገባቱን አስታውቀዋል።አቶ ዳውድ ላለፉት 20 አመታት በፓርቲው ላይ ተደጋጋሚ አደጋ መደቀናቸውን የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፤ ቀደም ባሉት አመታት ሶስት ጊዜ ለፓርቲው መከፋፈል ዋናው ምክንያት እርሳቸው እንደነበሩና አሁንም ለአራተኛ ጊዜ ፓርቲውን ለመከፋፈል አንጃ ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ ይተዋል።ይህንን ለማስተካከል ጥረት ሲደረግም በተጨባጭ የፓርቲውን ንብረትና ገንዘብ ወደግላቸው የማዘዋወር እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል።ስለሆነም ፓርቲውን ለመታደግ ሲባል እርምጃው ተወስዶባቸዋል።

አቶ ዳውድ በፓርቲው ውስጥ ችግር መፍጠር የጀመሩት ከሀምሌ ወር ጀምሮ እንደነበር የተናገሩት አቶ ቀጀላ፤ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በእርሳቸው በኩል ችግሩን ለመፍታት ባለመተባበራቸው ፓርቲው ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል።እንደ አቶ ቀጀላ ገለጻ፤ ፓርቲ ከአቶ ዳውድ ጋር ያለው ትልቅ ልዩነት በትግል አካሄድ ላይ ነው። ኦነግ ወደ አገር ቤት ከገባ በኋላ ሰራዊቱ በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት ወደ መንግስት የጸጥታ አካላት እንዲቀላቀል ስምምነት ቢደረግም፤ አቶ ዳውድ ግን በዚህ ላይ ግልጽ አቋም አልነበራቸውም፤ በአንድ በኩል ሰላማዊ ትግሉን ይፈልጋሉ፤ የትጥቅ ትግሉንም በኪስ አድርጎ በድብቅ መሄድ ይፈልጋሉ።

በተጨባጭም በምዕራብና በደቡብ ጫካ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል።ይሄ አካሄድ አግባብ አይደለም በሚል ስራ አስፈጻሚው ሲነጋገርበት ቆይቷል።ምክንያቱም የትጥቅና ሰላማዊ ትግል ድንበር ሊበጅለት ይገባልና ብለዋል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጠቅላላ ጉባዔ ተደርጎ አዲስ መሪ ኣስኪመረጥ ድረስ የድርጅቱ ተወካይና መሪ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ እንደሆኑ አቶ ቀጀላ ጠቅሰው፤ በአቶ ዳውድ በኩል እስከዛሬ የነበሩ የዲስፕሊን ጥሰቶችን በተመለከተ ፓርቲው ዝርዝር መግለጫ ማውጣቱን አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተባለ!

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ይህም ፍርድ ቤቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከመጋቢት 10 - እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው ከቆዩበት ሁኔታ ለመውጣትና ተቋርጦው የነበሩት አገልግሎቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስጀመር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሰረት ዳኞች በመስከረም ወር እረፍት አንዲያደርጉ በመወሰኑ ነው ተብሏል፡፡

ዳኞች ዓመታዊ እረፍታቸውን በነሃሴ እና በመስከረም ወር የሚወስዱ በመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎቶች በማስተናገድ በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ማድረግ የተለመደ አሰራር መሆኑን ያስታወሰው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፤ በዚህ ዓመት ዳኞች አጭር የእረፍት ጊዜ እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የመስከረም ወር 20 የስራ ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡

ለአብነትም እንደ የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች እንዲሁም ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ወር ለዳኞች የእረፍት ጊዜያቸው አንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም በፍርድ ቤቶች የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቹ ዳኞች በፈቃዳቸው ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ የሚቆዩ መሆናቸውን ፋና ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ ሆኗል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 162 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 413 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።17 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፣ 342 ሰዎችም አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኖርዌያዊው ተመራማሪ ጀቲል ትሬንቮል በቦሌ አየር ማረፊያ ከሚገኙ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ሰዎች ጋር ሰፋ ያለ "ምርመራ እና ውይይት" ካደረጉ በሗላ መስማሚያ ነጥብ ላይ ደርሰው አሁን ወደ ሀገራቸው እያቀኑ እንደሆነ ከደቂቃዎች በፊት ትዊተር ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ግለሰቡ "በህገወጥ መንገድ የትግራይን ምርጫ ሊታዘቡ መቐለ ሄደዋል" የሚል ክስ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲቀርብባቸው እና እርሳቸውም መልስ ሲሰጡ ነበር።በአንዳንድ ግለሰቦች "ከቦሌ አየር ማረፊያ ታፍነው ተወስደዋል" ቢባልም እርሳቸው ግን ከደህንነት ሰዎቹ ጋር "በወንድምነት" መንፈስ እንደተለያዩ በፅሁፋቸው ገልፀዋል።አክለውም ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ከፀጥታ አካላት ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ይኼኛው "ጥሩ እና አስደሳች የሚባል" ነው ብለው ፅፈዋል።

"ከደህንነት ሰዎች በተሰጠኝ ምክር መሰረት አሁን ጉብኝቴን አቋርጬ ወደ ሀገሬ እየሄድኩ ነው። ተባርሬ አይደለም፣ በቅርቡም ተመልሼ ምርምሬን እቀጥላለሁ" ብለዋል።በመጨረሻም የኢትዮጵያ መንግስት የአካዳሚክ ነፃነትን ማስከበር እንደሚገባው ጠቁመው ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያላቸውን የረዥም ግዜ ትብብር መቀጠል እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ሳውዲ አረቢያ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስረጃ ያላቸው መንገደኞች ወደ አገሯ መግባት እንደሚችሉ አስታወቀች።

ሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የጣለቻቸውን የአለም አቀፍ የበረራ ገደቦች ከነገ ጀምሮ ለተፈቀዱ ሀገሮች የአየር ድንበሯን ትከፍታለች ተብሏል።ኢትዮጲያም ከተፈቀደላቸው ሀገራቶች አንዷ ስትሆን የኮሮና ምርመራ ውጤታቸውን በመያዝ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መግባት እንደሚችሉ አረቢያን ቢዝነስ የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል።በሌላ መልኩ ሀገሪቱ በመጪው ዓመት ከጥር 1 በኋላ ለሳውዲ ዜጎች የአየር ፣ የየብስ እና የባህር ትራንስፖርት ላይ የተጣሉ ሁሉንም ገደቦች ለማቆም እቅድ መያዟ ታውቋል፡፡የባህረ-ሰላጤው ዜጎች እንዲሁም ትክክለኛ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ቪዛ ያላቸው የሳዑዲ ዜግነት የሌላቸው ሰዎች በቫይረሱ እስካልተያዙ ድረስ ከነገ ጀምሮ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ እንደተፈቀደ በየሳውዲ ፕሬስ ድርጅት በይፋ የወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መጠን ሪፖርት አደረገ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በ24 ሰዓታት ብቻ 307 ሺህ 930 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው እንደተገለጸለት ሪፖርት አደረገ፤ ይህም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የታዬ ከፍተኛው ዕለታዊ ቁጥር መሆኑ ታውቋል፡፡ በዕለቱ በዓለም ላይ 5 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውን ተከትሎም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 917 ሺህ 417 ደርሷል፡፡በዓለም ከፍተኛውን ዕለታዊ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ያስመዘገቡት ህንድ፣ አሜሪካና ብራዚል እንደሆኑም መረጃው ያሳያል፡፡ በዓለም ላይ ከ28 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀውን የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው ከዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆነው በአሜሪካ አህጉሮች ይገኛል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!!

ኢትዮጵያ ነባሮቹን የብር ኖቶች ቀየረች!

ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ። በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ያግዛሉ።

-ጠ/ሚር አብይ አህመድ
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ሰበር ዜና!! ኢትዮጵያ ነባሮቹን የብር ኖቶች ቀየረች! ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ…
የኢትዮጵያ መንግሥት አዳዲስ የደህንነት ገጽታዎች እና ሌሎችም መለያዎች የተካተቱባቸው የገንዘብ ዓይነቶችን ለግብይት እንደሚያውል በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

ነባሮቹ የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ የሚተኩ ይሆናል። አዲስ የ200 ብር ገንዘብም በተጨማሪነት ለግልጋሎት ይውላል።የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል። ይህ የገንዘብ ቅያሪ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ የታለመ ነው።የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም ያግዛል።በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል።

የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት የሚተገበር ይሆናል። በገንዘብ ቅያሬው ሂደት የጸጥታ ማስከበር አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ። ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑም ይጠበቃል።ኢትዮጵያ ገንዘቧን የሚወክል ምልክት እንዳልነበራት ይታወቃል።በቅርቡ ለብር መለያ የሚሆን አዲስ ምልክት ተዘጋጅቶ በጥቅም ላይ ይውላል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ከሳውዲ አረቢያ የመውጫ ቪዛ አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመስማማት ከነሃሴ 17/2012 ጀምሮ አስፈላጊው የጉዞ ሰነድና የትብብር ደብዳቤ በመያዝ ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በሳውዲ ኢሚግሬሽን በኩል መቋረጡን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዮሺሂዴ ሱጋ ቀጣዩ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ገዥው ፓርቲ ወሰነ!

የጃፓን መንግስት የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ጸሐፊ የነበሩት ዮሺሂዴ ሱጋ ቀጣዩ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ፓርቲያቸው እንደመረጣቸው ተሰማ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በራሳቸው ፈቃድ ከኃላፊነት እንደሚነሱ ከገለጹ በኋላ ጃፓንን ማን ይመራል የሚለው ጉዳይ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡ገዢው ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ባደረገው ምርጫ ታዲያ ዮሺሂዴ ሱጋ ከ 534 ድምጽ ሰጪዎች 377 በማግኘት ሲመረጡ የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ሁለተኛ እንድሁም የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ሺጌሩ ኢሽባ ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ከምርጫው በኋላ ዮሺሂዴ ሱጋ በጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የተጀመሩ ስራዎች የመስራት ተልዕኮ እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡ከነገ በስቲያ በምክር ቤት ቀርበው ኃላፊነታቸውን በይፋ እንደሚረከቡም ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡ ዮሺሂዴ ሱጋ የጃፓን መንግስት የሀገር ውስጥ ጉዳይና የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር እንዲሁም የካቢኔ ዋን ጸሐፊ በመሆን ማገልገላቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ጽፏል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
“ብር ቅያሬውን በተመለከተ የደረሰን የተሟላ መረጃ የለም”-የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ያስታወቁትን የግብይት ገንዘብ ዓይነቶች ለውጥን በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንደሌለ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር (Ethiopian Bankers Association) አስታወቀ፡፡ጉዳዩን በተመለከተ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ቀርበውልናል ያሉት የማህበሩ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ግርማ “በይፋ የደረሰን ነገር የለም፡፡ የተሟላ መረጃም እያገኘን አይደለም፡፡ ስለፋይዳና ተጽዕኖው ልንናገርም አንችልም” ሲሉ በተለይ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል የብር ለውጡን በተመለከተ በዚህ ሳምንት ሊሰጡ የሚችሉት መግለጫ እንደሚኖር በመጠቆም፡፡

ማህበሩ የሃገሪቱ ባንኮች ገጥሟቸዋል ያለውን የገንዘብ እጥረት (ሊኩዲቲ) ችግር በተመለከተ ከወራት በፊት መግለጫን ሰጥቶ ነበር፡፡በመግለጫው የችግሩ ምንጮች ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች ያስቀመጠ ሲሆን ብሄራዊ ባንክ ሊወስዳቸው ይገባል ያላቸውንም ምክረ ሃሳቦችን አቅርቧል፡፡ለገጠመው ችግር መንስዔ ናቸው ከተባሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከፋይናንስ ተቋማት ውጭ ይዘዋወራል የተባለው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ነበር፡፡

ከ5 ዓመታት በፊት ማለትም እ.ኤ.አ በ2016 ከባንክ ውጭ ሲዘዋወር የነበረው 63 ቢሊዬን ጥሬ ብር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት (2020) 113 ቢሊዬን ብር ደርሷል ሲልም ነበር ማህበሩ በመግለጫው ያስታወቀው፡፡ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደ ፋይናንስ ተቋማቱ የሚመለሰው “ብርን በመቀየር” እንደሆነና ጥያቄው ይመለሳል ብሎ እንደሚጠብቅም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ይህን በመጥቀስ ማህበሩ ከአሁን ቀደም ስለ ብር ቅያሬ ጠይቆ እንደነበር አል ዐይን ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ኤርሚያስ “ምክረ ሃሳቡን አቀረብን እንጂ የመገበያያ የብር ኖቶችን በተመለከተ ያልነው ነገር የለም” ሲሉ መልሰዋል፡፡

“አንዱ ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ብሄራዊ ባንክ የራሱን እርምጃ ቢወስድ፤ በረጅም ጊዜ ደግሞ ብር ቢቀየር የሚል ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ግን ብሄራዊ ባንክ ራሳችን ያከማቸነውን ገንዘብ እንዲሰጠን የሚል ነበር፡፡ ለዚህም 15 ቢሊዬን ብር ተለቀቀ፡፡ ስለዚህ የዛን ጊዜ የነበረው ችግር የብር መጠኑ ላይ እጥረቱን የማስቀረት እንጂ ኖቱ ላይ አልነበረም፡፡ ይሄ ኖት ይደረግ ይሄ ይሁን መቶ ብር ይሁን 500 ብር ይሁን የሚል አንድም ነገር ግን አላልንም” ሲሉም ነው የሚያስቀምጡት፡፡“ጉዳዩ ለእኛም አዲስ ነገር ነው” የሚሉም ሲሆን “የሚቀየረው ብር በምን ያህል ጊዜ ከ ‘ሲስተም’ ይወጣል? በምን ያህል ጊዜስ ሊሰበሰብ ይችላል? ምን ያህል ተጽዕኖ አለው? ያልተቀየሩ የገንዘብ ኖቶችን በተመለከተስ? የሚለውን ገና ማየት አለብን በመላ ምት ልንናገር አንችልም” በሚል ስለ ጉዳዩ አብራርተዋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱን የብር ለውጥ አስመልክቶ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ከኢቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ

Size: 11mb
@YeneTube @FikerAssefa