የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው፡በመሆኑም ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፣ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታ እንደሚያወጣ ተነግሯል፡፡ሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሂደት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
ክሱ በሁለት የተከፈለ ሲሆን፥ ከአቶ እስክንድር ነጋ እስከ 3ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በሽብር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ቀሪዎቹ ማለትም ከ4ኛ እስከ 7ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የተመሰረተው።ተከሳሾቹ በሰኔ 23 እና 24 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ ማደራጀትና ማስተባበር ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲከናወንባቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።በአሁኑ ወቅት ችሎቱ ጉዳያቸውን እየተመለከተ እንደሆነ ፋና ዘግቧል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 508 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሱን አስታወቀ።
የውሳኔ ሀሳቡ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደድር ቀርቦ ተቀባይነት ያገኙ በመሆኑ ከነገ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚለቀቁ በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ የሕግ አገልግት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ንጋቱ ዓለሙ ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።አቶ ንጋቱ እንደተናገሩት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት የስነ ምግባር ለውጥ ያሳዩ ናቸው።
የሚፈቱት በፈጸሙት ወንጀል የተጸጸቱ ይኸንንም ማረሚያ ቤቱ ያረጋገጠላቸው ታራሚዎች ሲሆኑ ከአንድ ዓመት ከአራት ወር እስከ አስራ ሰባት ዓመት በእስር ቤት የቆዩ ናቸው።በዚሁ መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሶስት ዞኖች ከካማሺ ማረሚያ ቤት 69 ታራሚ፣ ከመተከል ዞን 312 እና ከአሶሳ ዞን ደግሞ 127 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ዘግቧል። ከሚፈቱት መካከል ሰባቱ ሴቶች ናቸው።
[DW]

በሊባኖስ የቤይሩት ወደብ አዲስ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ።
ቃጠሎው ከአንድ ወር ገደማ በፊት በተከሰተው ከፍተኛ ፍንዳታ ከድንጋዜ እና ሐዘን ያልተላቀቁ የዋና ከተማዋ ነዋሪዎችን ሥጋት ላይ መጣሉን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።በከተማዋ ዳርቻ በሚገኘው ወደብ ወፍራም ጥቁር ጢስ ወደ ሰማይ ሲትጎለጎል የታየ ሲሆን የአገሪቱ ጦር ነዳጅ እና ጎማ የተከማቸባቸው መጋዘኖች ማውደሙን አስታውቋል። ቃጠሎው በምን ምክንያት እንደተነሳ እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። የሊባኖስ ጦር በትዊተር ባሰፈረው አጭር መግለጫ "እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ተጀምሯል።ወታደራዊ ሔሊኮፕተሮችም በዚህ ጥረት ውስጥ ይሳተፋሉ" ብሏል።ባለፈው ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. አሞኒየም ናይትሬት የተባለ የማዳበሪያ እና የፈንጂ ማምረቻ ግብዓት ምክንያት በተፈጠረው ፍንዳታ ከ190 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቆስለው ነበር። ፍንዳታው ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች አሞኒየም ናይትሬት የተባለው ኬሚካል ክምችቶቻቸውን እንዲፈትሹ አስገድዷቸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የቁም እንስሳት ገበያዎች በበሬ መሸጫ ዋጋ ላይ ከአምስት ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች ገለጹ።
በመዲናይቱ ገበያዎች አንድ በሬ ከ20 ሺህ እስከ 55 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው።የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተዘዋውሮ በተመለከታቸው አቃቂ፣ ካራ እና ፈረንሳይ ጨፌ በተሰኙ የቁም ከብት መሸጫ ስፍራዎች አነስተኛ በሬ ከ20 እስከ 25ሺህ ብር ሲሸጥ ውሏል። በእነዚህ ገበያዎች መካከለኛ በሬ ከ35 ሺህ እስከ 45ሺህ ብር ባለ ዋጋ የሚገኝ ሲሆን ከፍተኛ ለሚባለው ነጋዴዎች እስከ 55ሺህ ብር ዋጋ ሲጠሩ ተስተውሏል። በአንፃራዊነት የዋጋ ቅናሽ በሚታይበት ባለ በአቃቂ በሰቃ፤ ገበያ በሬ ከ22 ሺህ እስከ 35 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።
[Ethiopia Insider]

የዓለም ጤና ድርጅት ለድሆች የኮሮና ክትባት የሚሆን 700 ሚሊዮን ዶላር አሰባሰብኩ አለ!
የአለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በድሃ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማድረግ የሚውልና ከተፈለገው ከግማሽ በታች የሚሆን 700 ሚሊዮን ዶላር ከዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
ዘኮቫክስ አድቫንስድ ማርኬት ኮሚትመንት የተባለው ድርጅት የ 2 ቢሊዮን ዶላር ክትባት ለመግዛት የመጀመሪያ እቅድ አስቀምጧል፡፡
እስካሁን መሰብሰብ የተቻለው 700 ሚሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ የተፈለገውን እርዳታ ለማግኘት ገና ብዙ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ የዓለም ጤና የድርጅቱ አፍሪካ ዳይሬክተር ማትስዲሾ ሞይቲ ገልጸዋል፡፡
ኮቫክስ በፈረንጆቹ 2021፣ 2 ቢሊዮን ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ክትባቶችን የማቅረብ አላማ እንዳለው ገልጿል፡፡ ደቡብ አፍሪካን፤ ጋቦንን፣ ናሚቢያንና ኢኳቶሪያል ጊኒን ጨምሮ በትንሹ 8 የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ወጭ መድሃኒቱን ለመግዛት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
[Al ain]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 878 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 16,665 የላብራቶሪ ምርመራ 878 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡
ባለፋት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 974 አድርሶታል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 586 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 23,640 አድርሶታል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 62,578 ደርሷል፡፡

በትግራይ ምርጫ አጠቃላይ ውጤት ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ ይደረጋል፡፡ እስካሁን የተረጋገጠ፡ ህወሓት 152 ወንበሮች አሸንፏል፡፡ በተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት በሚያዙት ቀሪ 38 ወንበሮች ምናልባት ተቃዋሚዎች የተወሰነ ዕድል አላቸው፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ምርጫ ውጤት:
👉ህወሓት - 98.2 %
👉ባይቶና - 0.8%
👉ውናት - 0.71%
👉ሳወት - 0.27%
👉ዓሲምባ - 0.01%
ከአጠቃላይ ድምፁ አግኝተዋል፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
👉ህወሓት - 98.2 %
👉ባይቶና - 0.8%
👉ውናት - 0.71%
👉ሳወት - 0.27%
👉ዓሲምባ - 0.01%
ከአጠቃላይ ድምፁ አግኝተዋል፡፡
Via Million HaileSelassie
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 789 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ 12 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 12,164 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 789 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
384 ሰዎች ሲያገግሙ 12 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 63 ሺ 367 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 24 ሺ 024 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ986 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የዛሬ 19 አመት ነበር 9/11 በመባል የሚታወቀው ጥቃት የደረሰው።
አሜሪካም ሆነ አለም እስከዛሬ ካስተናገደቻቸው የሽብር ጥቃቶች የከፋው እንደሆነ የሚጠቀስለት በኒውዮርክ የ'World Trade Center' መንታ ህንፃዎች በአልቄይዳ በተጠለፉ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ነበር የወደሙት። በዚህም በአውሮፕላኑ የነበሩ ሰዎች ሁሉም ሲሞቱ በአጠቃላይ ወደ 3000 የሚጠጉ ንጹኃን ዜጎች ሞተዋል፣ የዚህን እጥፍ የሚያክሉት ደግሞ ተጎድተው ነበር። የዚህ ጥቃት ሰለባዎች በየአመቱ ኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ በዓሏን በምታከብርበት ቀን ታስበው ይውላሉ።በዛሬው እለትም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከባለቤታቸው ሜላኒያ ጋር ለጥቃቱ ሰለባዎች በተገነባው መታሰቢያ ተገኝተው ስነ ስርዓቱን ታድመዋል።
ከላይ የምታዩት ይህ የአለምን ታሪክ በብዙ መልኩ እንደቀየረ የሚነገርለት ጥቃት እንደተፈፀመ የተወሰዱና ታሪካዊ የሚባሉ ፎቶዎችን ነው፣ በመጀመሪያው ፎቶ ኖርዘርን ታወር የሚባለው በመጀመሪያ ላይ የተመታው ህንፃን ያሳያል፣ ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ በወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆርጅ ቡሽ ስለጥቃቱ ሲረዱ፣ ቀጥሎ የሚታየው የህንፃዎቹ ፍርስራሽ(from ground zero) ሲሆን ፣የመጨረሻው ደግሞ ከጥቃቱ የተረፈች ሴት በደቀቁ የኮንክሪት ብናኞች ሰውነቷ ተሸፍኖ ያሳያል።
የፎቶዎቹ ባለመብት አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው

የናይጄሪያ ግዛት በህፃናት ደፋሪዎች ላይ የማኮላሸት ህግን ልታፀድቅ ነው!
የናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች በህክምና እንዲኮላሹ የሚያዝ ረቂቅ ህግን አሳልፋለች።ረቂቁ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የግዛቲቷ አስተዳዳሪ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ መፈረም ይኖርባቸዋል።አስተዳዳሪው ከዚህ ቀደም ደፋሪዎች ተግባራቸውን እንደገና እንዳይፈፅሙ ብልታቸው ሊኮላሽ ይገባል ሲሉም ነበር።የናይጀሪያ ፌደራል መንግሥት ደፋሪዎችን ከአስራ አራት አመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ቢቀጣም ግዛቶች ግን የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ።የተደፈሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በማህበረሰቡ ካለው ተጠቂዎችን ጥፋተኛ ከማድረግ እሳቤ አንፃር ብዙዎች ደፍረው ወደ ህግ ቦታ አይሄዱም።ደፍረው ሪፖርት ያደረጉትም ቢሆን ክስ ተመሰርቶ የሚፈረድባቸውም ጥቂቶች ናቸው።
በሰኔ ወር ላይ በርካታ የናይጄሪያ ግዛት አስተዳዳሪዎች እየጨመረ የመጣውን የሴቶች መደፈርና ጥቃት አስመልክቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፈው ነበር።በናይጄሪያ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ የተፈረደባቸው 40 ደፋሪዎች ብቻ እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል።አገሪቷም ህጓን አሻሽላለች።የመድፈር ክስን አስቸጋሪ የሚያደርገው አቃቤ ህግ ማስረጃ ማምጣት ስለሚኖርበት አድካሚና ቴክኒካል ጉዳዪ የተወሳሰበ እንደሚያደርገው ይነገራል።የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቃሴ መገደብም የሚደፈሩ ሴቶችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል።በሃምሌ ወር የ22 አመት እድሜ ያላት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተደፍራ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል።
ይህንንም ተከትሎ ናይጄሪያውያን ንዴታቸውን ለመግለፅ ጎዳና ላይ ወጥተዋል፤ 'ዊ አር ታየርድ' (ደክሞናል) በሚልም በትዊተር ላይ ዘመቻ ተጀምሮም ነበር።በርካቶችም የሞት ቅጣትን ጨምሮ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣም ጠይቀዋል።"ደፋሪዎችን የመኮላሸት ቅጣት ህግ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ያለውን መደፈርን ይቀንሰዋል ብለን እናምናለን" በማለት የካዱና ምክርቤት አባል ሼሁ ዩኑሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።"የካዱና አስተዳዳሪ ከፈረሙና ህጉም ከፀደቀ በኋላ ቀጣዩ ደፋሪ የሚሰለብ ይሆናል" ብለዋል።የስርዓተ-ፆታ መብት ተሟጋችና የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ዶሮቲ ንጄዝማንዜም ህጉ እንዳስደሰታቸው ገልፀው በሌሎች ግዛቶችም ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ብለዋል።"በዚያን ወቅት የደፈሩኝ ቢኮላሹ ኖሮ ሌሎች ደፋሪዎች አይፈጠሩም ነበር፤ ብዙዎችም ከዚህ ጥቃት ይተርፉ ነበር" ብለዋል።በህክምና የመስለብ ቅጣት በአንዳንድ አገራት ተግባራዊ ቢሆንም አወዛጋቢ ነው።
[BBC]

በምስራቅ ኮንጎ በወርቅ ቁፋሮ ላይ ሳሉ በትንሹ 50 ሰዎች ሞቱ!
በምስራቃዊ ዴምክራቲክ ኮንጎ የወርቅ ማእድን ለማውጣት ሲቆፍሩ የነበሩ በትንሹ 50 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ተዘግቧል፡፡ሰዎቹ ሲቆፍሩበት የነበረው ጉድጓድ በከባድ ዝናብ ምክንያት መደርመሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከሟቾቹ ውስጥ 7 ሙሉ መሉ ጉድጓዱ የተደረባባቸው ሲሆን አንዳቸውም መውጣት አለመቻላቸውን የሴቶች ደጋፊና ቁጥጥር ኃላፊ የሆኑት ኢምላኔ ኢቶንግዋ ተናግረዋል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ የነበሩ ምስሎች እንደሚያሳዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጉድጓዱ በር ላይ ሆነው ሲያለቅሱ ተስተውለዋል፡፡ በባለፈው አመት በሀገሪቱ በተፈጠረ ተመሳሳይ አደጋ 16 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

በትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ።
በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ ወንጋ ንፋስማ ቀበሌ ልዩ ቦታው ፍልቅልቅ ከተባለው ሰፍራ መሥከረም 01/01/2013 ዓ ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ከየጁቤ ወደ የትኖራ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ ኤሰ አር(FSR) ቅጥቅጥ መኪና ተገልብጦ የዘጠኝ(9) ሰዎች ህይወታቸው ወዲያውኑ ሲያልፍ።በ20 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ አየተደረገላቸው ይገኛል።የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ ይገኛል።
ዘገባው የአነደድ ወረዳ ፖሊስ ሚዲያ ክፍል ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አንድ የፖሊስ አባል በሚስቱ ቤተሰቦች ላይ በተኮሰው ጥይት የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ!
በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አንድ የፖሊስ አባል በሚስቱ ቤተሰቦች ላይ በተኮሰው ጥይት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የፌዴራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል ረዳት ሳጅን መልሂቁ መኪ የተባለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከነመሳሪያው በቁጥጥር ውሏል፡፡በተጠርጣሪው እና በሚስት መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ሚስት ወደ ቤተሰቦቿ ስትሄድ ተጠርጣሪውም ተከትሎ ወረዳ 6 ወደ ሚገኘው የቤተሰቦቿ ቤት ሄዶ እንዲሰጡት ይጠይቃል፡፡ቤተሰብም እራስዋን ከማነጋገር ውጪ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ሲነግሩት የሚስትን እናት ፣የሚስትን የእንጀራ አባት ፣ የእህት ባል እንዲሁም ከተቀጠረች ሶስት ቀናት የሆናትን የቤት ሰራተኛ በጥይት ተኩሶ ገሏል ብለዋል አቶ ጄላን፡፡በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና በአጭር ጊዜ ለፍትህ አካል በማቅረብ ፍርድ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተዛባና ወንጀሉም ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ጄላን አስረድተው ለሟች ቤተሰቦችም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መፅናናትን ይመኛል ብለዋል፡፡
[ETV & Addis Ababa Police]

ከዋዜማው ጀምሮ በደረሰ የእሳት አደጋ 8 ሚለዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል ተባለ!
በአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ጳጉሜን 5 ቀን 2012 ዓ.ም እና መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም በደረሰ የእሳት አደጋ ስምንት ሚለዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቶ 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል።በቃጠሎው 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉንም ነው አቶ ጉልላት የተናገሩት።
መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በአንድ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋም አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉንም ቡድን መሪው አክለዋል።የተከሰቱትን አደጋዎች ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ ህብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል።በተያያዘ ዜና ጳጉሜን 5 ቀን 2012 አንድ ግለሰብ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በዚያው እለትም የመኪና አደጋም ተከስቷል ብለዋል።
[ETV]