YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዋልያ ቢራ በአዲስ አበባ በጎርፍ ለተጠቁ እና ሌሎች ወገኖች የበዓል ስጦታ አበረከተ
 
በአዲስ አበባ ቂሊንጦ አካባቢ በቅርቡ በጎርፍ ለተጠቁ ወገኖች እና ሌሎች በከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ዋልያ ቢራ የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡ ስጦታው ለእያንዳንዱ ግለሰብ 1 በግ፣ 5 ኪሎ ዘይት፣ አምስት ኪሎ የስንዴ ዱቄት እና 5 ኪሎ ሽንኩርትን ያካተተ ነው፡፡
 
‹‹በጎ ሥራን በተግባር እንቀላቀል›› በሚል የተዘጋጀው እንቅስቃሴ አካል የሆነው የዋልያ የበአል ድጋፍ ተጠቃሚ የሚያደርገው በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 150 ወገኖችን ነው፡፡ የተደረገው ድጋፍ አጠቃለይ ወጪው 1 ሚሊዮን ብር ይደርሳል፡፡
 
በጎርፍ ከተጠቁት ውጪ የበዓል ስጦታውን ያገኙት ወገኖች የተመረጡት እንዳልክ እና ማህደር በተሰኘው ሬዲዮ ፕሮግራም አማካኝነት በሕዝብ በተደረገ ጥቆማ ነው፡፡
 
  @YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,206 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ 21 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 25,158 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 1,206 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

531 ሰዎች ሲያገግሙ 21 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 58 ሺ 672 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 21 ሺ 307 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ918 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች የዓይን ብሌናቸውን ከህልፈታቸው በኋላ ለመለገስ ቃል ገቡ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ የዓይን ባንኩ የቃልኪዳን ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ለምለም አየለ አባላቱ መጥተው ቃል በመግባታቸው ምስጋናቸውን አቅርበው ሌሎች የህብረተሰብ አካለትም ከህልፈታቸው በኋላ ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል እንደገቡ ጥሪ አቅርበዋል::

 የኢዜማ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩላቸው ከስጦታወች ሁሉ የላቀውን የብርሃን ስጦታ ከህልፈታችን በኋላ ለመልገስ ቃል በመግባታችን ኩራት ይሰማናል በማለት በቀጣይም ሌሎች ማህበረስቦችን በማንቃት ቃል እንድገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ እስካሁን ለ2 ሺህ 465 ወገኖች የብሌን ንቅለ ተከላ ተከናውኖላቸው ብርሃናቸው እንዲመለስ ማድረጉን ባንኩ አስታውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ መንግስት ዝርዝር ነገር እስኪያወጣ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናቸውን እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳሰበ።

በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በተለይም የታክሲ አገልግሎት በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች በእጥፍ እንዲከፍሉ መደረጉ ይታወሳል።ለአምስት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ነሀሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ የተወሰኑ ክልሎች በግማሽ የመጫን አገልግሎቱ መነሳቱን አሳውቀዋል።ይሁንን በአዲስ አበባ ታክሲዎች የአስቸኳይ አዋጁ መጠናቀቁን ተከትሎ ለምን ወደ ቀድሞው የትራስፖርት አገልግሎት አይመለስም ተብሎ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮን ተጠይቋል።የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ እንዳሉት ጉዳዩን በተመለከተ በመግለጫ እስከምናሳውቅ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢሮው ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ የሚሰጥ በመሆኑ ዝርዝር ነገሮችን ይፋ እናደርጋለን ብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የአገሪቱ ክፍል የሚደረጉ አውቶቡሶች በወንበር ልክ መጫን መጀመራቸውን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ።

በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በተለይም የታክሲ አገልግሎት በግማሽ እንዲጭኑ ተሳፋሪዎች በእጥፍ እንዲከፍሉ መደረጉ ይታወሳል።ለአምስት ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ነሀሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ ትራንስፖርቱ በተለይም ከመናሀሪያዎች የሚደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ቀድሞ ይዘቱ መመለሱ ተገልጿል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አውቶቡሶች ከጷግሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም አንስቶ በወንበር ልክ እና በታሪፉ መሰረት ተሳፋሪዎቻቸውን ማስተናገድ መጀመራቸውን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የአማራ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ የአስቸኳይ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በወንበር ልክ እና በተቀመጠላቸው ታሪፍ ተሳፋሪዎችን እንዲጭኑ ማድረጉ ይታወሳል።የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መግለጫ እስከምሰጥ ድረስ ታክሲዎች በግማሽ መጫናችሁን ቀጥሉ ብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት "ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" ብለዋል።ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል።ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር።

ሆኖም ውድድሩን ከፈረንጆቹ 2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል።በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ "ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው" ብለው ነበር።

ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል።ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር።

በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ።

"ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም" ብለዋል ሊቀመንበሩ።የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር።ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ህንድ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ሁለተኛ ሆነች!

ህንድ በትናንትናው ዕለት በ24 ሰዓታት ዉስጥ ብቻ ከ90 ሺ በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ያገኘች ሲሆን ይህም ቫይረሱ ከተከሰተ ወዲህ በአንድ ሀገር የተከሰተ ከፍተኛው የተጠቂዎች ቁጥር ነው፡፡በሀገሪቱ እስካሁን ከ 4.2 ሚሊዮን በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ብራዚልን በመብለጥ ህንድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ በእስካሁኑ ምርመራ ህንድ በቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር ከብራዚል በ 70 ሺ ያህል ብልጫ አሳይታለች ሲል ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡በተጠቂዎች ቁጥር ከአንደኛ እስከሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት አሜሪካ ፣ ህንድ እና ብራዚል በመላው ዓለም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ቁጥር 53 በመቶ የሚሆኑት ይገኙባቸዋል፡፡በዓለማችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ሲበልጥ ከነዚህም ከ19 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ማገገማቸውን እና ከ887 ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ዎርልዶ ሜትርስ አስነብቧል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ!

በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የመስጠት ስነስርአት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።በስነስርአቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተገኝተዋል።መድረኩ ሁሉም አካል ለሰላም መስፈንና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራ ለማሳሰብ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ!

አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሥራት ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ማስተላለፉን አስራት ሚዲያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።ፖሊስ በተደጋጋሚ መረጃ አቀርባለሁ በሚል ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢጠይቅም በተሰጠው ቆጠሮ አለኝ ያለውን መረጃ ማቅረብ አልቻለም።በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስጋናው ከፈለኝ እና ዮናታን ሙሉጌታ በእያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በእንቦጭ አረም በመዘጋቱ አገልግሎት ለጊዜው አቋርጦ የነበረው የአዋሽ II የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡የእንቦጭ አረሙ የውሃ መቀየሻ ግድብ ላይ በመተኛቱ የተነሳ የውሃ መቀበያው (water intake) አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡አረሙን ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ በተገኘ ኤክስካቫተር የማንሳት ሥራ ሲከናወን ቆይቶ የውሃ መቀበያው በመከፈቱ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከአርብ ነሐሴ 29 ጀምሮ ዳግም ኃይል ማምረት ጀምሯል፡፡32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው አዋሽ II የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1966 ዓ.ም ነበር፡፡

[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ለአንድ ቀን ይፋዊ ስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ የመረጃ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡

አል ቡርሃን እና ልዑካቸው አስመራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት አቀባበል እንዳደረጉላቸውም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡

መሪዎቹ በሁለትዮሽ እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ገልጸዋል፡፡ባሳለፍነው ወርሃ ሃምሌ ከፍተኛ የኤርትራ የመከላከያ ኃላፊዎች ወደ ካርቱም አቅንተው ከምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃምዳን ደገሎ (ሄሜቲ) ጋር መምከራቸው ይታወሳል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ማሻሻያውን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ ተወስኗል።የሚኒባስ ታክሲዎች ከኋላ ባለው መቀመጫ ከ2 ሰው በላይ መጫን አይችሉም ብሏል ቢሮው በመግለጫው።

እንዲሁም ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም ነው የተገለፀው።

ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ክፍ እንዲል መደረጉንም አስታውቋል።

ከታሪፍ ጋር በተያያዘም በእጥፍ ሲከፈል የነበረው ቀርቶ መጠነኛ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ እንደሚከተለው ማስተካከያ ተደርጎበታል።

👉እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 1 ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን ላይ 2 ብር

👉ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 3 ብር የነበረው አሁን 4 ብር

👉ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 6 ብር

👉ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር በፊት 6 ብር የበረው አሁን 8 ብር

👉ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 10 ብር

👉ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር በፊት 9 ብር የነበረው አሁን 12 ብር

👉ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 10 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 13 ብር

👉ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር በፊት 12 ብር የነበረው አሁን 15 ብር

👉ከ20 ነጥብ 1 እስከ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 13 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 17 ብር

👉ከ22 ነጥብ 6 እስከ 25 ኪሎ ሜትር በፊት 15 ብር የነበረው አሁን 19 ብር

👉ከ25 ነጥብ 1 እስከ እስከ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 16 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 20 ብር

👉ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር በፊት 18 የነበረው አሁን 22 ብር ሆኖ ማሻሻያ መደረጉንም የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመግለጫው አመላክቷል።

ከተፈቀደው ሰው በላይ መጫን ከ1 ሺህ ብር ጀምሮ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 1 ሺህ 500 ብር ጀምሮ እንደሚያስቀጣም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ይህንን ለመቆጣጠር ከትራፊክ ፖሊስ በዘለለ የፖሊስና የፀጥታ አካላት መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ እና ትርፍ የሚጭኑትን ለመጠቆም የሚጠቁምበት የስክል ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይሆናል ብሏል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ለብሉምበርግ፣ ኒውዮርክ ታይምስ እና ቪኦኤ እንግሊዘኛ የሚፅፈው ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ እና ሌሎች አስር ገደማ ሰዎች ወደ መቐለ ለመሄድ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኙም በፀጥታ አካላት እንዳይጓዙ እንደታገዱ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ሳይመን ወደ መቐለ ሊጓዝ የነበረው ምርጫውን ለመዘገብ እንደነበር መረጃው ያመለክታል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ! በአማራ ክልል ለሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የመስጠት ስነስርአት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።በስነስርአቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተገኝተዋል።መድረኩ…
የአማራ ክልልን ሰላም በማስከበር የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አካላት የማዕረግ ሽልማት ከተለያዩ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙ ተከናውኗል።

ማዕረግ የተሰጣቸው!

አምስት የምክትል ኮሚሽነርነት
አስራ ሶስት የረዳት ኮሚሽነርነት
ሁለት የኮማንደርነት
ሶስት የምክትል ኮማንደርነት
አንድ የዋና ኢንስፔክተርነት
ሁለት የረዳት ኢንስፔክተርነት ማዕረግ ሽልማት ተሰጥቷል።

[አማራ ፓሊስ ኮሚሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የቤት መኪኖች በወንበር ልክ መጫን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ በተደረገው ማሻሻያ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ መወሰኑ ይታወቃል፡፡የቤት መኪኖችን እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸርካሪዎችን በሚመለከት ግን በማሻሻያው ላይ የተጠቀሰ ነገር ባመኖሩ ኢትዮ ኤፍ ኤም በዚሁ ጉዳይ ላይ ቢሮውን ጠይቋል፡፡

የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ እንዳሉት የቤት መኪኖች እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎችም በወንበር ልክ እንዲጭኑ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል የቤት መኪኖች ከሹፌሩ ውጪ መጫን ከሚችሉት የሰው ቁጥር በግማሽ ቀንሰው ይጭኑ እንደነበር ይታወሳል፡፡እንዲሁም ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም ተነግሯል።ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉንም አስታውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ለብሉምበርግ፣ ኒውዮርክ ታይምስ እና ቪኦኤ እንግሊዘኛ የሚፅፈው ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ እና ሌሎች አስር ገደማ ሰዎች ወደ መቐለ ለመሄድ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኙም በፀጥታ አካላት እንዳይጓዙ እንደታገዱ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ሳይመን ወደ መቐለ ሊጓዝ የነበረው ምርጫውን ለመዘገብ እንደነበር መረጃው ያመለክታል። Via Elias Meseret @YeneTube @FikerAssefa
#Update

ከምርጫው ጋር ለተያያዘ ሥራ በአውሮፕላን ሊጓዙ የነበሩት ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ከ10 በላይ እንደሆነም የተነገረ ሲሆን፤ በበረራ መርሃ ግብራቸው መሰረት ወደ አውሮፕላን ከገቡ በኋላ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉ ተገልጿል።

ከጋዜጠኞቹ መካከል አንዱ የሆነው ለብሉምበርግና ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሚሰራው ሳይመን ማርክስ "የተወሰንን ሰዎችን መታወቂያ ካርድ ከተመለከቱ በኋላ ተሳፍረንበት ከነበረው አውሮፕላን ተገደን እንድንወርድ ተደርገናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ መቀለ ሊጓዝ በነበረው አውሮፕላን ውስጥ ሰላሳ የሚደርሱ መንገደኞች የነበሩ ሲሆን የአውሮፕላን ማረፊያው የደኅንነት ሠራተኞች የተሳፋሪዎቹን መታወቂያ ከተመለከቱ በኋላ ተጓዦቹ እንዲወርዱ ማደረጋቸውን አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ተሳፋሪ ገልጸዋል።ቢቢሲ ያናገራቸው አንድ ተጓዥ እንዳሉት ደግሞ የጸጥታ ሠራተኞቹ የመንገደኞቹ ሞባይል እና ላፕቶፕ ሲቀበሉ መመልከታቸውን ተናግረው በረራውም ሳይሰረዝ እንዳልቀረ ገልጸዋል።ወደ መቀለ እንዳይጓዙ ከተደረጉ ተሳፋሪዎች መካከል የዓለም አቀፉ የቀውስ ጉዳዮች አጥኚ ተቋም የኢትዮጵያ ተመራማሪ የሆነው ዊሊያም ዳቪሰንም እንዳለበት ቢቢሲ አረጋግጧል።

ሮይተርስ ወደ መቀሌ ለማምራት በዝግጅት ላይ የነበረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ መንገደኞች ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው ከሆነ አራት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 12 የሚሆኑ ሰዎች ወደ መቀሌ በረራ ለማድረግ ከተዘጋጀው አውሮፕላን ውስጥ እንዲወርዱ ተደርገዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች በትግራይ የሚካሄደውን ምርጫ እንዳንዘግብ ጫና እየደረሰብን ነው ያሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተር ጌታቸው ደንቁ (ዶ/ር) ለድምጸ ወያኔ እንዲህ አይነት ነገር እንደሌለ ባለፈው ቅዳሜ ተናግረው ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም አብን ጠየቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።ንቅናቄው በመግለጫው እንዳስታወቀው የአገሪቱ የዲሞክራሲ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱንም አስታውቋል።በአጠቃላይ አብን በጥናቴ አረጋግጫቸዋለሁ መንግስትም በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃዎችን ሊወስድባቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጧል።

በኦሮሚያ ክልል የተደረገው "የዘር ማጥፋት" ተገቢውን ትኩረት ያለማግኘቱና ችግሩን በአጭር ጊዜም ይሁን በዘለቄታ ለመፍታት የሚታየው ዳተኝነት ፓርቲውን ክፉኛ እንደሚያሳስበውም ገልጿል። በመሆኑም

ሀ) የተፈፀመው ወንጀል "የዘር ማጥፋት" መሆኑ ታምኖበት በስሙ እንዲጠራና ለተፈፀመው ወንጀልም ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤

ለ) መንግሥት የተፈፀመውን "የዘር ፍጅት" የሚያጣራና የሚመረምር ልዩ የምርመራ ኮሚሽንና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት እንዲያቋቁምና ወንጀለኞች የሚዳኙበት ልዩ ችሎት እንዲሰይም፤

ሐ) መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም፤

መ) ችግሩን በዘለቄታ ለመፍታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ማህበረሰቦችና ህዝቦች መካከል የእርቅና የመግባባት ስራዎች እንዲጀመሩ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልልም በክልሉ ለሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦችና ህዝቦች ሰብአዊና ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው የሚከበሩበት ዋስትና እንዲሰጥ ንቅናቄው ጠይቋል።

Via Ethio FM

ሙሉ መግለጫው 👇👇👇

https://telegra.ph/-09-07-523
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድና በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ።ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ ከጳጉሜ 2 እስከ ጳጉሜ 5 2012 ዓ.ም የተሰሙ የምስክር ቃል ተገልብጦ ወስዶ እስከ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም ክስ አንዲመሰርት ነው ብይን የሰጠው።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ሌሎች ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ በ5 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርትባቸውም ትእዛዝ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱ በዛሬ ውሎው ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ትእዛዝ ሳይሰጥ፤ ተጠርጣሪዎቹ በማረፊያ ቤት አንዲቆዩ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 93 መሰረት ትእዛዝ ሰጥቷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ማስክ ሳያደርግ ታክሲ ውስጥ የተገኘ ሰው 500 ብር እንደሚቀጣ ተገለፀ!

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያ ላይ ተሳፋሪዎች ማስክ ሳያደርጉ ትራንሰፖርት መጠቀም እንደማይችሉ ቢከለክልም ባላደረጉት ላይ ያስቀመጠው የቅጣት መጠን አለመኖሩ ይታወሳል፡፡በመመሪያው ላይ ዛሬ በተደረገው ማሻሻያም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ወይም ማስክ በማያደርጉ ተሳፋሪዎች ላይ የ500 ብር ቅጣት መጣሉን የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎችን የጫነ አሽከርካሪና ረዳት ላይም እያንዳንዳቸው 1 ሺ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን አቶ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የተጣለው የምሽት 2 ሰዓት ገደብ ከተነሳ የቆየ ቢሆንም አሁንም ተሳፋሪዎች እንዲሁም አሽርካሪዎች ላይ ብዥታ ተፈጥሯል፡፡ይህንንም ተከትሎ ትራንስፖርት ሰጪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ከተነሳ መቆየቱን እና ይህ ብዥታ ሊኖር እንደማይገባ አክለው ተናግረዋል፣ ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa