YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መረሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 1043 ተማሪዎች አስመረቀ::

በዛሬውም ቀን በመደበኛና በተከታተይ መረሃ ግብሮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን 283 እንዲሁም በሰርተፊኬት 760 በጥቅሉ 1043 ተማሪዎችን አስመርቋል::

[Bule Hora University]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና የማንነት ጉዳዮች ቃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወርቁ አዳሙ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ስልጣኑን በመጠቀም በሰጠው ውሳኔ መሠረት እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃረን ምርጫ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በተመለከተ ሦስት የውሳኔ ሐሳቦች ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ…
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም እንደ ራያ ዴሞክራሲያው ፓርቲና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫውን በሙሉ ዝግጅት ለመሳተፍ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታ ሳይኖር በዚህ ወቅት ምርጫ መደረጉ አግባብነት የለውም ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጉባኤው በውሳኔ ሀሳብነት አካቶታል፡፡

እንደ ወልቃይትና ራያ ባሉ አካባቢዎች ከማንነት ጉዳይ ጋር የተነሱ ቅሬታዎች ከምርጫው ጋር ተያይዞ በአካባቢዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው በሚል የቀረቡ አቤቱታዎችም ህገ መንግስታዊ መሰረት ያላቸው በመሆኑ ሊጤኑ እንደሚገባ ጉባኤው አመልክቷል፡፡የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ያቀረባቸውን የውሳኔ ሀሳቦችን ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት ይበጃል ያለውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤትም ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳቦች ዙሪያ በዝግ እየመከረ ይገኛል፤ ይህን ተከትሎም የምክር ውይይት ካደረገበት በኋላ ውሳኔም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ከ900 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

የሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲ የሆነው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 929 ተማሪዎች ዛሬ ለ7ኛ ጊዜ ባካሄደው የምረቃ ፕሮግራም አስመርቋል።

[MoSHE]
@YeneTube @FikerAssefa
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 326 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 621 በመጀመሪያ፣705 ደግሞ በሁለተኛ ድግሪ ሲሆን ከመካከላቸውም 503 ሴቶች ናቸው።ተመራቂዎቹ በምህንድስና፣ ጤና፣ ተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች በመደበኛ፣ ክረምት፣ ኤክስቴንሽንና ርቀት መረሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ገልጸዋል።ተማሪዎቹ ለዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ፈተና ውስጥ ሆነው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ለምረቃ መብቃታቸውን አስታውቀዋል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም እንደ ራያ ዴሞክራሲያው ፓርቲና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫውን በሙሉ ዝግጅት ለመሳተፍ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታ ሳይኖር በዚህ ወቅት ምርጫ መደረጉ አግባብነት የለውም ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጉባኤው በውሳኔ ሀሳብነት አካቶታል፡፡ እንደ ወልቃይትና ራያ ባሉ አካባቢዎች ከማንነት ጉዳይ ጋር የተነሱ ቅሬታዎች…
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር የፓርላማ ዘመን 5ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሰረት አድርጎ ያቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን፣ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የፈፃማቸው ተግባራት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለምክር ቤቱ በሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች በኩል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም ላይ በእስከ አሁኑ ሂደት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንና ህገወጥ አካላት በሚፈፅሙት ድርጊት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ብሎ የሚያምን መሆኑ እና በቀጣይም ችግሮችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡በሌላ በኩል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ እና የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመጥቀስ የትግራይ ክልል እያካሄደ ካለው ህገወጥ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት አለማክበር ተቀባይነት የሌለውና ሊታረም የሚገባው መሆኑ ከማስቀመጡም ባሻገር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በደብዳቤ ሕገ መንግስቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር የሰጡትን ማሳሰቢያ አለመቀበሉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ አፅድቋል፡፡

1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤

2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤

3) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን ኮሮና እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ት/ቤቶችን ከፈተች!

በኢራን ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እተባባሰ ቢሄድም ሀገሪቱ ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ትምህርት ቤቶችን ከተዘጉ ከ7 ወራት በኋላ ልትከፍት ነው፡፡በመንግስት የተሾሙት የኢራን ሜዲካል ካውንስል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሬዛ ዛፋርጋንዲ ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ በጻፉት መልእክት የትምህርት ቤቶች በድንገት መከፈት በጤና ባለሙያዎች ላይ ጫና እንደሚያሳድር ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን የአዋሽ ወንዝ ባደረሰዉ የጎርፍ አደጋ ከ130ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተገለጸ!

በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን በአምስት ወረዳዎች የአዋሽ ወንዝ ባደረሰዉ የጎርፍ አደጋ ከ130ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉን ክልሉ አስታውቋል፡፡የአዋሽ ወንዝ ሊያስከትለዉ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት እና አዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ጋር ሰፊ ስራዎች ቢሰሩም የዘንድሮዉ ክረምት ዝናብ ከፍተኛ በመሆኑ ከክልሉ አቅም በላይ ሆኗል ተብሏል፡፡አሁን ላይ በውሃ የተከበቡ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ በሁለት ሄሊኮፕተሮች በመታገዝ ተጎጂዎችን የማውጣት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የተለያዩ የአገልግሎት ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን እና በሺዎች ሄክታር የሚቆጠር ማሳ ከጥቅም ውጪ ሆኗል ተብሏል፡፡ተፈናቃዮችም መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 950 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፣ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል፣ 164 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። በኢትዮጵያ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ከ1 ሚሊዮን አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሳማ ቢን ላድን የእህት ልጅ የሆነችው ኑር ቢን ላዲን የመስከረም 11 አይነት ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት መከላከል የሚችለው ትራምፕ ብቻ ነው ማለቷ እያነጋገረ ይገኛል።የ33 አመቷ ኑር ራሷ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ እንደሆነች የተናገረች ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ካልተመረጠ ከሳምንት በኋላ ከተከሰተ 19 አመት የሚሞላውና በአጎቷ ጠንሳሽነት የተፈፀመው የመስከረም 11 ጥቃት አይነት ሊደገም እንደሚችል ለኒውዮርክ ፖስት ግምቷን ተናግራለች።ኑር አሁን ላይ ስዊዘርላንድ ውስጥ ነው የምትኖረው።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ እንዲገናኙ ትዕዛዝ ተሰጠ!

ከኦሮሚኛ ሙዚቃ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ለየብቻቸው ታስረው የቆዩ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት እንዲቀላቀሉ ወይም እንዲገናኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ አቶ በቀለ ገርባ ቀደም ብሎ በነበረው ችሎት ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ነው፡፡

አቶ በቀለ በአቤቱታቸው ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት፣ እሳቸውና አቶ ጃዋር የታሰሩት ለየብቻቸው ነው፡፡አየርም ሆነ የፀሐይ ብርሃን እያገኙ አይደለም፡፡ በመሆኑም አብረው እንዲሆኑ፣ አየርና የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኙ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ፣ እንዲቀላቀሉ ወይም እንዲገናኙ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ኪት ማምረት ልትጀምር ነው፡- ጤና ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ኪት ከአንድ ወር በኋላ ማምረት እንደሚጀመር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለኢዜአ እንደተናገሩት ኮሮናቫይረስን የመመርመር አቅምን ከፍ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ነው።በአሁኑ ወቅትም ከአንድ ወር በኋላ ከቻይና መንግሥት ጋር በመተባበር የመመርመሪያ ኪት ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።ለእዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ድጋፉን ከምታደርገው የቻይና መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል።“የመመርመሪያ ኪቱን በአገር ውስጥ ማምረት ሲጀመር ከውጭ የሚገባውን ኪት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል” ያሉት ዶክተር ደረጀ፣ ምርቱ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት እንደሚዳረስም ተናግረዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የመመርመር አቅም በእጅጉ ከፍ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት የኢንፌክሽን መከላከያ ግብዓቶች በኢትዮጵያ በስፋት መመረት መጀመራቸውን ጠቁመው፣ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሶችን ወደ ውጭ አገራት መላክ መጀመሩንም ገልጸዋል።በሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እነዚህን ቁሶች የሚያመርቱ ኩባንያዎች ቀዳሚ መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል።በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 52 የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከላት የሚገኙ ሲሆን በእነዚህም በቀን ከ20 ሺህ በላይ ናሙናዎችን መመርመር ተችሏል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ጉዳት ለደረሰባቸው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ማቋቋሚያና ለቀጣይ ዕርዳታ የሦስት ቢሊዮን ብር ዕቅድ ይፋ ተደረገ!

ከጠቅላይ ቤተክህነትና የአገር ሽማግሌዎች ተውጣጥቶ የተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ማቋቋሚያና ድንገተኛ ለሆኑ አደጋዎች የሚውል የሦስት ቢሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቢያ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበትና የእሳቸውን ይሁንታ ያገኘው ዕቅድ ይፋ የተደረገው ነሐሴ 28 ቀን ሲሆን፣ በማግስቱ ከነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ መገባቱን፣ የዓብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሕግ ባለሙያው አቶ መኮንን ሰሙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሦስት ቢሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተግባራዊ የሚደረገው ወይም ለማግኘት የታቀደው፣ ከአብያተ ክርስቲያን፣ ከምዕመናን፣ ከቤተ ክርስቲያኒቷ አገልጋዮች ከዩኒቨርሲቲ ኮሌጆችና ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ወገኖች መሆኑንና በእርግጠኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሰቡትን እንደሚያሳኩ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም መነሻው በኦሮሚያ ክልል ከሰባት በላይ ዞኖችና ከ25 በላይ ወረዳዎች ላይ እምነታቸውን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለደረሰባቸውና ቤታቸውን፣ ንብረታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ላጡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ማቋቋሚያ ቢሆንም፣ ሌሎች ያልታሰቡና ድንገተኛ ችግሮች ሲያጋጥሙ መርጃ የሚሆን ዘለቄታነት ያለው መተማመኛ የዕርዳታ ገንዘብ እንዲሆን ማድረግ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በክልሉ ላይ የደረሰውን በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በመለየት የደረሰባቸውን ግድያ፣ የአካል መጉደል፣ ንብረት መዝረፍና ማቃጠል፣ ከቤተ ክህነትና ከአገር ሽማግሌዎች የተውጣጣው ቡድን፣ የመገናኛ ብዙኃንና ሌሎችም ወገኖች ሆነው በ25 ወረዳዎች ተዘዋውረው በመጎብኘትና በአካል በመገኘት የማጽናናትና የማረጋጋት ሥራ መሠራቱን የገለጹት አቶ መኮንን፣ በአካባቢው ባለው ሀገረ ስብከት አካውንት ተከፍቶ 42 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህ የተሰበሰበ ገንዘብ በማንም እጅ ሳይገባ በቀጥታ ተጎጂዎቹ በሚከፍቱት አካውንት ከአዲስ ዓመት በፊት ገቢ እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል፡፡ እጃቸውን ለዘረጉ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉ ወገኖችንም አመስግነዋል፡፡ለተጎጂዎቹ የሚሰጠው ገንዘብ በሥፍራው ተገኝቶ የእያንዳንዱን ተጎጂ ወገን የጉዳት መጠን አጥንቶ የመጣ ቡድን ባቀረበው የጉዳት መጠን ላይ ተመሥርቶ መሆኑንም አቶ መኮንን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ላይ በተለይ ሃይማኖትንና ማንነትን መሠረት በማድረግ በደረሰው ግፍ የተመላበት የጭካኔ ድርጊት፣ መላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችንና ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን እንዳሳዘነ ጠቁመው፣ መንግሥት በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ሕግን የማስከበርና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየወሰደ ያለው ዕርምጃ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በቀጥታ በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦችና በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ያሉ አመራሮች በመኖራቸው፣ የክልሉ መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት በመተባበር በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ምንም ሳያጠፉ ታስረው እየተንገላቱ ያሉ ወገኖች በመኖራቸው እነሱም እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
መሐመድ አል አሩሲ ተሸለመ!

ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በሳዑዲ አረቢያ የተወለደውና የሕዳሴ ጎድብን በሚመለከት ስለኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኅን ሙግት ያደርጋል። ይህንንም በራሱ ተነሳሽትን ያደረገው ነው።አረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑም የኢትዮጵያን ሐሳብና እውነት በዛው ቋንቋ ለሰሚው ሲያስረዳና ሲከራከር የቆየው አሕመድ አል አሩሲ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አምስት ወራት በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የገዛ መኖሪያ ግቢያቸውን ሳይቀር በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩት ካሊድ ናስር በ8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

በሁለተኛም ልዩ ተሸላሚ የሆኑት ኪሮስ አስፋው ናቸው። እኚህ ግለሰብ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ባደረጉት በጎ ሥራ የተሸለሙ ሲሆን፤ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ መቶ ጊዜ ቦንድ የገዙ መሆናቸውም በመድረኩ ተጠቅሷል።

የንባብ ለሕይወት መሥራችና አዘጋጆች መካከል የሚገኘው ጋዜጠኛ ቢንያም ከበደ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።ይልቁንም በኮቪድ 19 ወቅት ልጆች በየቤታቸው ሲሆኑ የሚመለከቱት የሚመጥናቸውና በተለያየ ቋንቋ መሰናዶዎች የሚቀርብበት የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥንን ከመክፈት ጀምሮ ያደረጉት አስተዋፅኦም የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

[@AddisMaleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በሁለተኛ ዙር የሽልማት መሰናዶ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህርነትና ተመራማሪነትን ጨምሮ በተለያየ ኃላፊነት አገልግለዋል። አሁንም በኢትዮጵያ በተለያዩና በርካታ ኃላፊነቶች እያገለገሉ ነው። የውሃ ዲፕሎማሲ ባለሞያ ሲሆኑ ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ ገለፃ በመስጠት ይታወቃሉ። ድርድር ላይ ይሳተፋሉ፤ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በሚነሳባቸው በመድረኮችም ይሳተፉሉ። በጉዳዩ በማማከርም ይጠቀሳሉ።በድርድሩ ሂደት በዓለም መገናኛ ብዙኅን ሳይቀር የኢትዮጵያ ድምፅ ሆነው የተሟገቱም ናቸው።አባይን በሚመለከት የፅፉትን መፅሐፍም በበይነ መረብ በነፃ አሰራጭተዋል። ዶክተር ያዕቆቦ አርሳኖ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው በከፊል የመጫን ዕገዳ ተነሳ!

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የቆየው በግማሽ የመጫን ዕገዳ መነሳቱን የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ውቤ አጥናፉ ለኢዜአ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክስተት ተከትሎ ላላፉት አምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጎ መቆየቱ ይታወሳል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የከተማ ታክሲዎች፣ ባለሦስት እግር ባጃጅ ታክሲዎች፣ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶችና ሌሎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ እንዲቀንሱ አስገዳጅ መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይሁንና የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የአዋጁ ጊዜ መጠናቀቁን በማስመልከት ዕገዳው የተነሳ መሆኑን ዛሬ ለቢሮው በላከው ደብዳቤ በማሳወቁ ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች ዕገዳው መነሳቱን እንዲያውቁት ተደርጎ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን አስታውቀዋል።ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች በከፊል የመጫን ዕገዳው በመነሳቱ በወንበራቸው ልክ በመጫን ተጠቃሚዎችን በመደበኛው ታሪፍ የሚያስከፍሉ ይሆናል” ብለዋል።አሽከርካሪዎች፣ ረዳቶችና ተገልጋዮች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን በመገንዘብ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa