YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስካሁን 120 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ተገለጸ!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስካሁን 120 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ተገለጸ። የግድቡ አጠቃላይ ግንባታም 78 በመቶ መድረሱ ተጠቁሟል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ከህዳሴው ግድብ የቦርድ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።በዚሁ መድረክ ላይ እንደተገለጸው የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 78 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ የአሌሌክትሮ ሜካኒካል ስራው 46 ነጥብ 5 በመቶ፤ የሲቪል ስራው ደግሞ 88 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል።

ከወጪም አኳያ ለግድቡ በኮንትራት ደረጃ የተያዘው አጠቃላይ በጀት 78 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ ለግድቡ ግንባታ 120 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የግድቡ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታውቀዋል።ግድቡን ለማጠናቀቅም 160 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ኢንጅነሩ ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ግድቡ በመጪው አመት አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ሁሉ ተደርጎለት ነሀሴ 2013 ላይ 18 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በመያዝ ለህዝቡ ይበሰራል ብለዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ።

በክልሉ ለተቃውሞ በተጠሩ ሰልፎች ምክንያት የሚከሰተው የሰዎች ህይወት መጥፋት በእጅጉ እንደሚያሳስበውም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአሳሳ፣ አሰቦት፣ አወዳይ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጭሮ፣ ደንገጎ፣ ድሬ ጠያራ፣ ዶዶላ፣ ገለምሶ፣ ጊኒር፣ ሀሮማያ፣ ሂርና እና ሻሸመኔ የሞት ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ከተለያዩ ምንጮች መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡የሞት ጉዳቶቹ የደረሱት የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ በተጠሩ የተቃውሞ ሰልፎች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡‹‹የመንግስት አካላት የዜጎችን በሰላማዊ መልኩ ተቃውሞ የማሰማት መብት ማረጋገጥ እንዳለባቸው እና ሕግ የማስከበር ስራ ተመጣጣኝነት እንዲጠብቅ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው›› የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ እና ቃል አቀባይ አቶ አሮን ማሾ ገልፀዋል፡፡

‹‹የኦሮሚያ ክልል በዚህ አመት የተከሰቱ አሳዛኝ ግድያዎች ከፈጠሩት ሰቆቃ አሁንም ፈጽሞ አላገገመም፡፡ እነዚህ ከፍተኛ የመብት ጥሰት አዝማሚያዎች እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም›› በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡እስካሁን በአንዳንድ ሚዲያዎች የወጡ ሪፖርቶች እና በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ መረጃዎች የሞቱ ሰዎችን ቁጥር በሚመለከት የተለያየ አሀዝ አስቀምጠዋል፡፡ኢሰመኮ የደረሰውን ሞትና ጉዳት መጠን ለማረጋገጥ ከየአካባቢው ነዋሪዎች፣ ምስክሮች፣ ሆስፒታሎች እና የአስተዳደር አካላት መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡ኢሰመኮ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ጉዳዩን ለማጣራት በአፋጣኝ ምርመራ እንዲጀምሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ፍርድ ቤት ቀረበች!

ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ቀርባለች።ፖሊስ የጂ.ፒ.ኤስ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን እንዲሁም በተሰጠው ቀጠሮ የሰው ምስክርና ሰነዶች ማሰባሰቡን ገልጿል።ነገር ግን ከወንጀሉ ውስብስብነት አንፃር የሚጠበቁ ውጤቶች በመኖራቸው 14 ቀን ጠይቋል።ተጠርጣሪዋ ፈፅማለች የተባለውን የወንጀል ዝርዝር ለችሎቱ መግለፁ መረጃ ይጠፋል የሚል ስጋት ስለሚኖር ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ በቃል ጉዳዩን መዘርዘር አልቻለም።ነገር ግን ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ሊያጣራው ይችላል ብሏል።ጎን ለጎን የምርመራ መዝገቡን ዐቃቤ ህግ እየመረመረ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።ተጠርጣሪዋ በበኩሏ በወንጀሉ ተጠርጥረው ከተያዙት ሰዎች መካከል በወንጀሉ የተሳተፉትን በመለየት አብራቸው ፎቶ መነሳት መድረሷን ለፍርድ ቤት በመግለጽ በወንጀሉ ተጠያቂ አይደለሁም በማለት ገልጻለች። የዋስትና መብቷ እንዲከበርም ጠይቃለች።የግራ ቀኙን የሰማው ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ተጨማሪ 6 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የኮሮና ክትባትን በርካሽ እንደሚያገኙ ከሚጠበቁ 92 ሃገራት መካከል አንዷ ነች!

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2021 እንደሚደርሱ የሚጠበቁ የኮሮና ክትባቶችን በርካሽ ከሚያገኙ 92 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ዓለም አቀፉ የክትባቶች ትብብር (ጋቪ) መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ጋቪ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ አንድ መቶ ሚሊዬን የቫይረሱን ክትባቶች በፍጥነት ለማምረት የሚያስለውን ስምምነት "ሴረም" ከተሰኘው የህንድ የክትባቶች አምራች ተቋም ጋር ስምምነት ፈጽሟል፡፡

ሴረም አስትራ ዜናካ እና ኖቫቫክስ በተባሉ የምርምር ተቋማት በመዘጋጀት ላይ ያሉ ክትባቶችን ነው የሚያመርተው፡፡የጋቪ ቦርድ እውቅና የሰጣቸው 92ቱ ሃገራትም ኮቫክስ በተሰኘው የትብብሩ አዲስ የፋይናንስ ስርዓት በመታገዝ ክትባቶቹን ከሶስት ዶላር (መቶ አስር ብር ገደማ) ባልበለጠ ዋጋ የሚያገኙ ይሆናል፡፡የስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ 92 ሃገራት ዝርዝርም ባሳለፍነው ሳምንት በጋቢ ቦርድ ጸድቋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ልዩነቱን ለመፍታት በዝግ እየመከረ መሆኑን አስታወቀ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በፖርቲው ውስጥ የተከሰተውን ልዩነት ለመፍታት ውይይት መቀመጡን ተናግሯል፡፡የፓርቲው ቃላ አቀባይ የሆኑት አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት በፓርቲው ውስጥ የተከሰተውን ልዩነት ለመፍታት ውይይት ላይ እንገኛለን ይሁን እንጂ ዝርዝር ጉዳዩን መናገር አልችልም ብለዋል፡፡በዚህ የዝግ ውይይት ላይ አደራዳሪዎች በመሳተፍ ላይ እንዳሉ ተሰምቷል።የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለረዥም ጊዜ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን ያገለገሉትን አቶ ዳውድ ኢብሳን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር በትብብር ለመሥራት ፈቃደኛ አይደሉም በማለት እግድ ጥሎባቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ በበኩላቸው ምክትል የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበሩን አቶ አራርሶ ቢቂላ፣ የሥራ አስፈጻሚው አባሉን አቶ ቶሌራ አዳባንና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ስድስት አመራሮችን ከፓርቲው አግደው ነበር፡፡ፓርቲው ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ክፍፍልና የአመራሮች መተጋገድ የመጣው ከሳምንታት በፊት የኦነግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ያላሳተፈ ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ ነው።በወቅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ለአቶ ዳውድ አስቀድሞ አሳውቆ እሳቸውም ስብሰባው እንዲካሔድ የተስማሙ ቢሆንም፣ በኋላ የስብሰባው ዋዜማ ምሽት ላይ አቶ ዳውድ ስብሰባውን ሕገወጥ እንዳሉትና ስብሰባው እንደሚካሔድም እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡አሁን እንዲህ አይነቱን ልዩነትና ክፍፍል ለመፍታት ይረዳል የተባለ ስብሰባ ነው እያደረግን ያለነው ይላሉ አቶ ቀጀላ፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በነ ጃዋር መሀመድ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን መስማት ጀመረ።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጃዋር መሐመድ "በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም" በማለቱ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ!

አቶ ጃዋር መሐመድ ከአራት ቀን በፊት ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደታመመ ለፍርድ ቤት በማስረዳት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰሙ ለዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በተቀጠረው መሠረት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ ።ምስክሮች ከመሰማታቸው በፊት ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የሰጣቸው ትዕዛዞች መፈጸም አለመፈጸማቸውን አረጋግጧል።በዚህም መሠረት አቶ ጃዋር መንግሥት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሥጋት እንደሆኑበትና ለሕይወቱ ስለሚፈራ በግሉ ሐኪም ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን ቢስት እንኳን በመንግሥት ሐኪም መመርመር እንደማይፈልግ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በጣም መታመሙን፣ ምግብ ሲመገብ እንደሚያስመልሰውና አሁን ላይ ደግሞ እያስቀመጠው መሆኑን አስረድቷል።

ዓቃቤ ሕግ በሰጠው አስተያየት ለአቶ ጃዋር ሕክምና እንዲያገኙ ተጠይቀው በግል ሐኪሜ ካልሆነ አልታከምም እንዳሉ ገልጿል። አቅርቦቱ እያለ አልፈልግም እያሉ ወደሌላ ሐኪም ቤት መውሰድ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም መሆኑን ጠቁሞ በሕግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌም የሚጥስ መሆኑን አክሏል። ወደ ግል ሐኪም ሪፈር ሊደረጉ የሚችሉት ከመንግሥት ሕክምና በላይ የሆነ ሕክምና ሲያስፈልግ ብቻ መሆኑንም ተናግሯል።ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21 ድንጋጌ መሠረት አቶ ጃዋር በግል ሐኪም እንዲታዪ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

[REPORTER]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርት ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት እንዳስታወቀው ሪፖርት ስህተትና መሬት ላይ ያለውን ነገር ያላገናዘበ ነው ብሏል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል ከመጠቀም ይቆጠቡ ሲል ማሳሰቡ የሚታወስ ነው፡፡በክልሉ ለተቃውሞ በተጠሩ ሰልፎች ምክንያት የሚከሰተው የሰዎች ህይወት መጥፋት በእጅጉ እንደሚያሳስበውም ይናገራል ኮሚሽኑ፡፡የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ምክትል ሀላፊ አቶ ግዛቸው ጋቢሳ እንዳሉት የኮሚሽኑ መግለጫ በጣም ስህተት እና ከእውነት የራቀ ነው፡፡መሬት ላይ ያለው የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ግን የሚሰጠው መግለጫ ለሌላ አካል የሚያጎነብስ ነው ፡፡ሲሉም ያክላሉ አቶ ግዛቸው፡፡

ይህ ደግሞ በጣም የተሳሳተ እና ከኮሚሽኑ የማይጠበቅም ነው ብለዋል፡፡የተጠራው አመጽ እና ያለፈውን አይነት ነውረኛ ተግባር እንዲፈጸም የሚሻ ነበር እንጂ ፈጽሞ ሰላማዊ ሰልፍ አይደለም ነው ያሉት አቶ ግዛቸው፡፡እኛ በዚህ መግለጫ ደንግጠናል አዝነናልም ሲሉ አቶ ግዛቸው ተናግረዋል፡፡መግለጫውን ያወጣው አካል ስፍራው ሳይሄድ ከማህበራዊ ድህረ ገጾች በተቃረሙ መረጃዎች በመሆኑ ትልቅ ስህተት ፈጽሟል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ተቋሙ ተከተለው መንገድ ስህተት ነው ፣ መግለጫው ለዜጎች ደህንነትም ስጋት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡በመሆኑም ኮሚሽኑ ይህንን ሀላፊነት የጎደለው ስራ በቶሉ እንዲያርም ጠይቀዋል ፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዋሽ ባንክ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የ25 ሚሊየን ብር ቦንድ መግዛቱ ተገለፀ!

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል 25 ሚሊዮን ብር ቦንድ የገዛ ሲሆን በዛሬው እለት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ /ቤት ጋር የቦንድ እርክክቡን መፈፀሙ ታውቋዋል፡፡

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ምስክሮች ቃላቸዉን እንዲቀይሩ ሲያባብሉ የነበሩ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተከሰሱበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ላይ በሰዉ ምስክር ማስረጃነት የቀረቡ ስድስት ምስክሮችን በማግባባትና በገንዘብ በመደለል ፍርድ ቤት ገብታችሁ ለፖሊስና ለዐቃቤ ህግ የሰጣችሁትን ቃል ቀይሩ አለበለዚያም ፍርድ ቤት ሳትቀርቡ ጥፉ ይህን ካደረጋችሁ ለእያንዳንዳችሁ 500 ሺ ብር እንሰጣችኋለን ብለዉ በማግባባት ሲያባብሉ የነበሩ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ተገለፀ፡፡ከላይ በስም የተጠቀሱት ግለሰቦች ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተከሳሽ ኪዳኔ ዘካርያስ የወንጀል ድርጊት በሊቢያ ዉስጥ ህይወታቸዉ ላለፈ ኢትዮጵያዉያን ቤተሰቦችም 200 ሺ ብር እንሰጣችኋለን ሲሉ ምስክሮችም ከዚህ በፊት የሰጣችሁትን ይህን ቃል ስትቀይሩም ምንም አይነት የህግ ተጠያቂነት አያስከትልባችሁም በማለት ምስክሮችን ሲያባብሉ የነበሩ መሆኑንም ከምስክሮቹ የድምፅ ቅጅ እንደተገኘም ተመልክቷል፡፡

ሁለተኛ ተጠርጣሪ ጠበቃ ደስታ መስፍን እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ተከሳሽ ኪዳኔን በፍርድ ቤት በጠበቃነት ወክሎ ሲከራከር ቆይቶ በተከሳሽ ጉዳይ የማስረጃ ዝርዝር ላይ የተጠቀሱትን ምስክሮች ከተጠርጣሪ ታረቀኝ ሙሉ ጋር በመሆን ምስክሮቹ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለፖሊስ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ቢክዱ የሚመጣባቸዉ ኃላፊነት የሌለዉ መሆኑን፣ በችሎት በዐቃቤ ህግ ሊጠየቋቸዉ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በመግለፅ፣ ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 5/2012 ዓ.ም ምስክር ለመስማት ይዞ የነበረዉን ቀጠሮ በማስለወጥ፣ ለምስክሮቹም ይህንን ቀጠሮ ያስለወጠዉ ከምስክሮቹ ጋር ለመደራደር ጊዜ ለማግኘት እንዲያመች መሆኑን በመግለፅ እና ምስክሮቹን በማግባባት ባጠቃላይ ለፍትህ አሠጣጥ ሂደቱ እንቅፋት በመሆን ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡በዚሁም መሰረት ተጠርጣሪ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ በቀን 11/2012 በቁጥጥር ስር ዉሎ ጉዳዩ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎት ቀርቦ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተሰጠበት ሲሆን ጠበቃ ደስታ መስፍን በዛሬዉ እለት በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናቶችም ፍርድ ቤት የሚቀርብ ይሆናል፡፡

[FDRE Attorney General]
@YeneTube @FikerAssefa
ከኒው ዴልሂ ነዋሪዎች ሩብ ያህሉ በኮሮና ተይዘዋል- ጥናት

ከህንድ ርዕሰ መዲና ኒው ዴልሂ 20 ሚሊዬን ገደማ ነዋሪዎች መካከል 5.8 ሚሊዬኑ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ጥናት አመለከተ፡፡ቁጥሩ ሪፖርት ሲደረግ ከነበረው በ37 እጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
አቶ ጃዋር መሐመድ "በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም" በማለቱ በግል ሐኪም እንዲታከም ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ! አቶ ጃዋር መሐመድ ከአራት ቀን በፊት ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደታመመ ለፍርድ ቤት በማስረዳት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰሙ ለዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በተቀጠረው መሠረት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ ።ምስክሮች ከመሰማታቸው በፊት ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 11 ቀን 2012…
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በእነ ጃዋር መሐመድ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮች አሰማ!

ችሎቱ ወደ ምስክር ሂደት ከመግባቱ በፊት ባለፈው ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ትእዛዝ አፈጻጸም ተመልክቷል።ከዚህ ጋር ተያይዞ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 9 ተጠርጣሪዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲያደርጉ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ምርመራ ማድረጋቸውንም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።በሌላ በኩል አቶ በቀለ ገርባ እና ሀምዛ አዳነ እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበት የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ ክፍል ካሜራ በመኖሩ ጋር ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን አቤቱታ በማቅረባቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ተመልክቷል።

ፖሊስ በበኩሉ ካሜራው የተቀመጠው ግቢው አዲስ በመሆኑ እና በተለይም በላይብረሪ ውድ የሆኑ መጻሕፍት በመገኘታቸው መሆኑን ጠቅሶ ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበት ክፍል መመቻቸቱን ገልጿል።ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ምሥጢራቸውን መጠበቅ በሚያስችል መልኩ ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ያድርግ ብሏል።ይህ ትእዛዙ የማይፈጸም ከሆነ በቀጣዩ ቀጠሮ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት የሁለት ምስክሮች ቃል የሰማ ሲሆን፣ በቀጣይ የሌሎች ምስክሮችን ቃል ለመስማት ለነሐሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,778 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 20 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 21,456 የላብራቶሪ ምርመራ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 228 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 35,836 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 620 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13,536 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋ ዳግም የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መጠለያ መመለሳቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ መገናኛ ዜዴች  የተሰራጨዉ ዘገባ ስህተት መሆኑን የዞኑ አስተዳደደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር  ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡የካማሽ እና የአሶሳ ዞኖች ነዋሪዎች፣ መፈናቀላቸውንና በምዕራብ ወለጋ ዞን መጠለያ ጣቢያዎች የሰፈሩ ሰዎች ዳግም ተፈናቀሉ የሚለዉ መረጃ የተሰራጨዉ፣ የተባበሩት መንግስታት  የሰብዓዊ ርዳታ  ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ባለፈው ሳምንት ከዘገባ በኋላ ነዉ። የምዕራብ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/በ ት ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ከድር እንደሚሉት ግን ባሁኑ ጊዜ ከዞናቸው የተፈናቀለ ሰው የለም፡፡ በኦቻ የተገለጸው መረጃም መስተካከል አለበት ብለዋል፡፡

[ዶይቼ ቨለ]
@YeneTube @FikerAssefa
#የስሜት_ትኩሳት
#አዲስ_መጽሐፍ_በገበያ_ላይ

ከዘ-አልኬሚስት ቀጥሎ እጅግ ተወዳጅ የሆነ የፓውሎ ኮኤልሆ ድንቅ መጽሐፍ!!!

የ ”ኒው ውመን ማጋዚን” ሪቪው አራት ኮከብ ተሸላሚ መጽሐፍ።
በፍቅርና በወሲብ ጉዳይ ላይ በድፍረት የተመዘዘ የዘመናችን ብዕር ውጤት . . . የራሱ የሆነ እንግዳ፣ ግን ደግሞ ውብ ኬሚስትሪ አለው።
#ዘ_ኦብዘርቨር

ጸሐፊው በተለመደው የሚያባብል ብዕሩ.... ያልተለመደውን ርዕስ አሽሞንሙኖታል።
#ግላስኮ_ኢቭኒንግ_ታይምስ

በፍቅር አውድ ውስጥ ያለው ልዩ የሆነው የወሲብ ተፈጥሮዊ እምቅ አቅም ልብን በሚይዝ መልኩ የተቃኘበት መጽሐፍ
#ቡክ_ሊስት

#አሁን_በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች_እጅ_ይገኛል፡፡
ይቀላቀሉን 👉 http://tttttt.me/teklutilahun
#መከረኞች
#እምዩ
ዘመን የማይሽራቸው መጽሐፍት በገበያ ላይ!!

#መከረኞች በአንድ ፊቱ የህብረተሰብ ታሪክ፣ በሌላ ፊቱ ፍልስፍና፣ በሶስተኛ መልኩ የጥበብ ስራ፣ ከዚህም ውጪ በብዙ አንጻር ሊተረጎም የሚችል ‹‹ዘላለማዊ›› ተብለው ከሚጠሩ ስነ-ፅሁፎች የሚመደብ፡፡

#እምዩ #የእናት_ፍቅርና_መስዋዕትነት ከባድ ፈተና ውስጥ የሚገባበት… እጅግ መሳጭ ታሪክ የያዘ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር መጽሐፍ!!!

#የመጽሐፍ_ቅርስ_ካስፈለገዎት
#መከረኞችና_እምዩ_መጽሐፍት_አሉልዎት፡፡

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡

ይቀላቀሉን 👉 http://tttttt.me/teklutilahun
Forwarded from HEY Online Market
🔹Samsung Galaxy A10S (2019)
Storage: 32 GB #RAM: 2GB
Price: 6,500 birr

🔸Samsung Galaxy A20S (2019)
Storage: 32 GB #Ram: 3 GB
Price : 7,900 Birr

🔹Samsung Galaxy A30S (2019)
Storage: 64 GB #Ram: 4 GB
Price : 9900

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii
@HEYOnlinemarket
የሚታጠቡ አልባሳትዎን እናድርስልዎ GoFlex Delivery ከ ፓሽ ላውንደሪ ጋር በመተባበር።

📞6101 ላይ ይደውሉ

የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱ⬇️
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.goflex.app
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቀጣዩ ዓመት 84 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እንደሚገነባ ገለጸ፡፡

በክልሉ 40 ልዩ ትምህርት ቤቶችም እንደሚከፈቱ ተጠቅሷል።በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት አንድ ቢሊዮን ብር በጀት መድቧል።የክልሉ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሰጠው ትኩረት የሚገነቡት ትምህርት ቤቶችን ግንባታቸው ከአንድ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል፡፡በክልሉ ሁሉም ዞኖች የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ለአገልግሎት ሲበቁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋንን ያሻሽላሉ ብለዋል፡፡በቀጣዩ የትምህርት ዘመን በክልሉ የተለየ ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች ብቻ የሚያስተምሩ 40 ”ልዩ” ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱም አቶ አዲሱ አስታውቀዋል፡፡ትምህርት ቤቶቹ ከስምንተኛ ወደ ዘጠነኛ ክፍል የሚዛወሩ ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አስረድተዋል፡፡ክልሉ በቀጣዩ ዓመት ሰባት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

[ኦቢኤን]
@YeneTube @FikerAssefa