YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በየክልሉ ሥራ አስፈጻሚዎች የቀረቡትን ሪፖርቶች ለመገምገምና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ሰብሰባ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ።

የፓርቲው ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ፓርቲው በሚቀርቡት ሪፖርቶችና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
@Yenetube @Fikerassefa
ዎጌታ የማህበረሰብ ራዲዮ ወደ ስራ ተመልሷል!

በጸጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ ከአርብ ጀምሮ ስርጭቱን አቋርጦ የነበረው የወላይታ ዎጌታ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስርጭቱ ተመልሷል።ጣቢያው ስራውን የጀመረው ከኮማንድ ፖስት ኃላፊዎች ጋር ከተደረገ ውይይት በኋላ ነው ተብሏል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
በወንጀል የተጠረጠሩ ከስድስት መቶ በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸዋን የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ ገለፁ፡፡

በቅርቡ የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ የሻሸመኔን ከተማ ጨምሮ በአንዳንድ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች የሰው ህይወት መጥፋቱ ፤ ንብረት መውደሙ እንዲሁም ብዙዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ላቹሬ ለአሀዱ እንደተናገሩት የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በከተማው ላይ ከፈተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በዚህ ወንጀል የተጠረጠሩ እና ተሳትፈዋለል የተባሉ ከ ስድስት መቶ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ወንጀለኞችን ለመያዝ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ነው ብለዋል።

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa1
በጋምቤላ ክልል የሚገነባው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈፃፀም 74 ከመቶ ደረሰ!

በጋምቤላ ክልል በአኝዋ ዞን ጆር ወረዳ እንጎጊ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ 74 ከመቶ አፈፃፀም ላይ መድረሱን የጋምቤላ ክልል የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ በ5ሺ 950 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ የሶላር ፕሮጀክት፤ በ425 ሺህ 746 የአሜሪካን ዶላር ወጪ "CET & NR Consotrium" በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ይገኛል፡፡ የግንባታው ሥራ ክትትል የሚያደርገው ደግሞ የሪጅኑ አገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ፅ/ቤት ነው፡፡

እስካሁን 5.9 ኪሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን፤ የሶላር ፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ175KW በላይ ኃይል ማመንጨት የሚችል ነው ተብሏል፡፡ፕሮጀክቱ ከ150 እስከ 200 ለሚጠጉ ደንበኞች እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡የሶላር ኃይል ማመንጫው ከአንድ ወር በኋላ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ያስታወቀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው።

[ኢ.ፕ.ድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ግብርና ሚኒስቴር ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ታብሌቶችና ሌሎች ቁሳቁስ ለክልሎች ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

ግብርና ሚኒስቴር “ዲጂታላይዜሽን ለግብርና ሽግግር” በሚል መሪ መልእክት ዘመናዊ የግብርና መረጃ አያያዝ ሥርዓት ለማስጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል፡፡የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ግብርና ሚኒስቴር የግብርና መረጃ አያያዝ ሥርዓት ለመዘርጋት 336 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የ35 ሺህ 400 ታብሌቶች ግዢ ማከናወኑን ገልፀዋል፡፡ ታብሌቶቹም ለክልሎች፣ ለወረዳዎችና ለእያንዳንዱ ቀበሌ መረጃ አያያዝን ለማዘመን ድጋፍ የሚደረጉ እንደሆነ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ከዚህ በተጨማሪም በ10 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁስ እንዲሁም በ11 ሚሊዮን የአሜርካ ዶላር ወጪ ለእንሰሳት ምርምር፣ ልማትና ጤና ጥበቃ የሚያግዙ የክትባት ቁሳቁስ ማሰቀመጫ፣ የበረዶ ሳጥን፣ አጉሊ መነጽር እና በፀሃይ ብርሃን የሚሰራ ፍሪጅ በእለቱ ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ማህበረሰብ አቀፍ የኮቪድ 19 ምርመራ ዘመቻ ለማካሄድ የሚያገለግሉ የተለያዩ ግብዓቶችን ማሠራጨቱን ተናገረ፡፡

ኤጀንሲው በ8 ቅርንጫፎችና በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት አማካኝነት ለምርመራ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሠራጨቱን የኢጀንሲው የመድኃኒትና ሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ ተናግረዋል፡፡መንግስት 200,000 ሰዎችን ለመመርመር በያዘው ዕቅድ መሠረት ኤጀንሲውና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግብዓቶቹን ከነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አሰራጭቷል ተብሏል፡፡ግብዓቶቹ 4 ሚሊየን 955 ሺ 646 ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል፡፡ሥርጭቱም ለአዲስ አበባ፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ ለሲዳማ፣ ለኦሮሚያ፣ ለአማራ፣ ለትግራይ፣ ለሀረሪ፣ ለደቡብ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ለጋምቤላ፣ ለሶማሌ እንዲሁም ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮዎች መካሄዱ ተነግሯል፡፡

[ሸገር ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ፖሊስ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በሆኑት ልደቱ አያሌው ላይ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት።ፖሊስ 7 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተፈቀደለት የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ 3 ቀናት በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ መብራት እንደሚጠፋ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በላከው መግለጫ ከነገ ጀምሮ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ ረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል::

👉በነገው እለት የሀይል አቅርቦቱ ከሚቋረጥባቸው አካቢዎች መካከል:

በአዲሱ ገበያ፣ በሰሜን ማዘጋጃ፣ በላዛሪስት ትምህርት ቤት፣ በሩፋኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢዎቻቸው፤ አንዲሁም ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በጎላጎል፣ በቺቺኒያ፣ በቦሌ ሚሊኒየም፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም እስከ በፍየል ቤት፣በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤

👉ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፡-

በዘነበወርቅ ቶታል፣ በአለርት ሆፒታል፣ በገርጂ ዩኒቲ ኮሌጅ፣ በቦሌ ሆምስ፣ በቦሌ ሲቪል አቬሽን፣ በጎሮ አለማየሁ ህንፃ፣ በጃክሮስ፣ በተወካዮች ምክር ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣ እንዲሁም በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳላም ሆቴል፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው፣

👉በተጨማሪም ሀሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ፡-

በኢትዮ-ፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ትምህርት ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣ እንዲሁም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በቦሌ መድሀኒያለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ እና አካባቢዎቻቸው፣ በመሆኑም ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ስራ ያቆመው LTV ሰራተኞቹን አሰናበተ!

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሰራጩ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንዱ የሆነው Ltv ባጋጠመው ኪሳራ ምክንያት መዘጋቱን ሠራተኞች አስታወቁ።ሠራተኞች እንደሚናገሩት ሰኞ ሐምሌ 28/2012 በኪሳራ ምክንያት ስለመዘጋቱ የሚገልጽ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መዘጋጃ እንዳልተነገራቸው የገለፁት ሠራተኞቹ ድንገት ሥራውን መቀጠል እንደማይችል እና የሦስት ወር ደሞዝ (ሥራ የማፈላለጊያ) እና የሥራ ልምድ በመስጠት ግንኙነታችን እንደተቋረጠ ነው የተነገረን ሲሉ አስታውቀዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ ማግኘታቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ቆንሉ ጀነራል ተመስገን ዑመር ጽሕፈት ቤቱ በሊባኖስ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች መረጃዎችን ለአገሪቱ ኢምግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አስገብቶ አስፈላጊውን ማጣራት ከተደረገ በኋላ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።ከተመላሾቹ ኢትዮጵያውያን በቤይሩት የወደብ ፍንዳታ ምክንያት በመጠለያ ውስጥ ያሉ እንደሚገኙበትም አመልክተዋል።ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ዜጎችን ዝርዘር በቀጣይ ቀናቶች ውስጥ እንደሚያሳውቅ ጠቁመው፤ የሚመለሱት ዜጎች የትራንስፖርት ወጪያቸውን በራሳቸው የሚሸፍኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።”በስምንተኛው ዙር የሥም ዝርዝራቸውና መረጃቸው ተልኮ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውን አሉ” ብለዋል አቶ ተመስገን።በሊባኖስ ሕግ ወንጀል የሰሩ፣ የፍርድ ቤት ጉዳይ ያለባቸው፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር ውል ያልጨረሱና በሌሎች ምክንያቶች ዜጎች የመመለሻ ፈቃድ እንደማያገኙም ገልጸዋል።

ይሁንና በሊባኖስ አሁን ካለው አሳሳቢ ሁኔታ አንጻር በልዩ ሁኔታ ኢትዮጵያውያኑ ፈቃድ አግኝተው እንዲመለሱ ለኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ እንደሚቀርብ አመልክተዋል።ኢትዮጵያውያኑን ለመመለስ ፈቃድ ቢያገኙም የመውጫ ቪዛ ለማግኘት ከሁለት እስከ ሦስት ወር እንደሚፈጅ ተናግረው፤ በፍጥነት ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አመልክተዋል።ጉዳዩ ከቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ አቅም በላይ የሚሆን ከሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ እንዲቀርብ ሊደረግ እንደሚችል ነው አቶ ተመስገን ያስረዱት።ጽሕፈት ቤቱ በዘጠነኛው ዙር ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ ባቀረበው ጥሪ መሠረት 3 ሺህ 300 ዜጎች መመዝገባቸውንና መረጃቸውም ወደ ሊባኖስ ኢምግሬሽን ጉዳይ መሥሪያ ቤት መላኩን ጠቁመዋል።በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም በሊባኖስ ሕዝባዊ ተቃውሞ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 2 ሺህ 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa1
አዲስ አበባ የመጀመሪያውን የውሃ መውረጃ ማስተር ፕላን እየሰራች ነው!

ለከተማዋ የሚሰራው የመጀመሪያው የውሃ መውረጃ (Drainage) ማስተር ፕላን በከተማዋ የሚታየውን የጎርፍ እክል በተቀናጀ እና ዘላቂ ሁኔታ ለመግታት ያስችላል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ጥበቡ ለካፒታል እንደተናገሩት ከተማዋ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ማስተር ፕላን እውን ለማድረግ የአለም ባንክ የ36 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡የማስተር ፕላን ስራውንም ፓሌርሞ፣ ጣልያን መሰረቱን ያደረገው ሰሪንግ ኢንጂነሪያ ከኢትዮጵያ አጋሩ መታፈሪያ አማካሪ ኢንጂነሪንግ ጋር እያከናወነው ይገኛል፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ከጣያን የሚመጣው ቡድን ከትንሽ መዘግየት በስተቀር የማስተር ፕላን ስራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው የሚሉት የከተማው መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ፤ በተያዘው በጀት አመት ስራው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡ማስተር ፕላኑ በቀዳሚነት የጎርፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችለንን አካሄድ ያመላክታል ያሉት አቶ ሞገስ ይህም የውሃ መውረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ከማስተዳደር ባለፈ በጎርፍ አማካኝነት በመሰረተ ልማቶች ላይ እና በኢኮኖሚ ጥፋቶች ላይ የሚደርሱ ጫናዎችን ያስወግዳል ብለዋል፡፡በዋና ከተማዋ ቀላል የማይባሉ ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ ሆነዋል፡፡ቀደም ሲል እያንዳንዱ መንገድ ዲዛይን ሲሰራ የውሃ መውረጃም ጥናት በተናጠል ይሰራ እንደነበር ይታወሳል፡፡በማስተር ፕላኑ ግን የሁሉም ዲዛይን ይቀናጃል ተብሏል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ!

በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ።ይህ መተግበሪያ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት በመቀለ ከተማ ሙከራ ተደርጎበታል ተብሏል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የተከዜ የብረት ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ የነዋሪዎች እንቅስቃሴ መገደቡን የስሃላ ሰየምት ወረዳ አስታወቀ።

የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎች መጠናታቸውን አስታውቋል።ችግሩ በየዓመቱ ለሦስት እና ለአራት ወራት የሚዘልቅ ቢሆንም አሁን ግን ከፊሉ የብረት ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ ወረዳው ጠይቋል።ከሰቆጣ- ዝቋላ – ስሀላ ሰየምት በሚያደርሰው መንገድ ላይ የተከዜ ሰው ሰራሽ የኃይል ማመንጫ ውሀ ያረፈበት ቦታ ይገኛል። ሰው ሠራሽ ኃይቁን አቋርጦ የተሠራው የብረት ድልድይ በውሀ በመሞላቱ ግን ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ከተቋረጠ ሳምንት ሆኖታል።የስሀላ ሰየምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻው ቸኮለ የብረት ድልድዩ በውሀ መዋጥ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ክፍሎች በጎርፍ መወሰዳቸውን ለአብመድ ተናግረዋል።የፈረሰው ድልድይ ሥራ በአጭር ጊዜ እንዲጀምር ማድረግ ባለመቻሉ ችግሩን ለመቀነስ ካለፉት ከቅዳሜና እሁድ ጀምሮ ትራንስፖርቱን በየብስ እና በጀልባ በመቀባበል ማስቀጠላቸው ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ የኮንትራት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ምሕረት እውነቱ የስሃላ ሰየምት የብረት ድልድይ ላጋጠመው አደጋ ጊዜያዊ መፍትሔ ለመስጠት በባለሙያዎችና በአማካሪዎች ጥናት ተደርጎ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የጥገና ባለሙያዎች እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል ብለዋል።ለድልድዩ ዘላቂ መፍትሔ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከአምባ ጊዮርጊስ-ዐብይ አዲ መገንጠያ የሚል የአስፓልት መንገድ እቅድ ውስጥ ተካትቶ መጠናቱንም ገልጸዋል።የዘርፍ ኃላፊው በክልሉ ክረምትን መሠረት በማድረግ የተጎዱ ድልድዮችን አስቸኳይ ለመጠገን ጥናት ተሠርቶ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።የተከዜ ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎች ተጠንተዋል ቢባልም ጥናቶቹ መቼ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ክልሉ ያስቀመጠው መረጃ የለውም።

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
የውጪ ኩባንያዎች ለህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ገበያው መናር ምክንያት እየሆኑ ነው ተባለ!

መሰረታቸውን ውጭ ያደረጉ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ያላቸው ኩባንያዎች ለህገወጡ /የጎንዮሽ የውጭ ምንዛሬ ማሻቀብ ጉልህ ምክንያት እየሆኑ ነው ተባለ፡፡ከግዜ ወደ ግዜ በጎንዮሽ ገበያ የውጭ ምንዛሬ የሚገዙ የውጭ ኩባንያዎች ቁጥራቸው ጨምሯል የሚሉት ታዛቢዎች ከህጋዊ ገበያው የአስር ብር ልዩነት እንዲኖር የነሱ አስተዋፅኦ አንደኛው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ምንጮች የህገወጥ ገበያው በየቀኑ ከባንክ የምንዛሬ ለውጥ እኩል እያሻቀበ ይገኛል ሲሉም አክለዋል፡፡መሰረታቸውን ውጭ ያደረጉ ኩባንያዎች ለዚህ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን አንስተው፡፡ ይህም ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ሃብት የማሸሽ እሳቤ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ከአገር ውስጥ ባለሃብት ይልቅ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እንደ የአቅራቢ ክፍያ/suppliers’ credit ያሉ የተሻለ እድሎች ለውጭ ባለሃብቶች አላቸው የሚሉት ጉዳዩን የሚከታተሉ፤ በዚህ ምክንያት ጥሬ እቃ በማስገባት ከአገር ውስጥ ተመሳሳይ ድርጅቶች ይልቅ የተሻለ እንቅስቃሴ በገበያው እንዳላቸው እና በዛ የሰበሰቡትን ከፍተኛ የብር ክምችት ወደ ውጭ በውጭ ምንዛሬ ቀይረው ለማውጣት የሚያደርጉት ሂደት የህገወጥ ገበያውን ያለቅጥ እያናረው ነው ብለዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የቅድመ ምርመራ ጉዳያቸው እየታየ ካሉ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል 5ቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ገለጸ።

በተያያዘ ዜና ዛሬ ሰኞ ከሰዓት ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጃዋር መሐመድ "ትላንት ማታ አልተኛሁም። በከፍተኛ ሁኔታ ታምሜ ነው ያለሁት። እስካሁን ማስታገሻ መውሰድ አልቻልኩም" ሲሉ ለችሎት ተናግረዋል።በግል ሀኪማቸው ህክምና ማግኘት ይችሉ ዘንድም ጥያቄ አቅርበዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የክልሉ ህዝብና መንግስት በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተናብቦና ተመካክሮ የመሥራት ዝንባሌ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ ለሀገሪቷ ህዝቦች የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀውና ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ የጀመረው ሁለንተናዊና ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለአንድም ሰከንድ እንዳይጨናገፍ ዘብ የመቆምና የማከናወኑ ሂደት ልዩ ትኩረት አግኝቷልም ነው ያለው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከቀበሌ እስከ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያሉ መዋቅሮችና መላ ህዝቡ በዚህ ወር ሲያካሂዱ በነበረው የሠላም ኮንፈረንስ አንድ ፅኑ አቋም ላይ ደርሰዋል ያለው መግለጫው የሠላም፣ የዴሞክራሲ፣ የልማትና የአብሮነት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በፅኑ መሠረት ላይ እንዲቆሙ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት መወሰኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

ከዚህ በተቃራኒ የህዝቡን ሠላም ለማወክና የለውጥ ግስጋሴውን ጠልፎ ለመጣል የሚታትሩ ኃይሎች ከቻሉ ለአፋቸው ልጓም ለድርጊታቸው ገደብ እንዲያበጁ ሀገራዊ ጥሪ ማስተላለፋቸውንም አውስቷል፡፡ ይህ ካልሆነ መንግሥት ህገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱንና ግዴታው የሆነውን የህግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ እንዲተገብር በሙሉ አቅማቸው ከጎኑ ለመሰለፍ ቃላቸውን አድሰዋልም ብሏል፡፡ በየደረጃው ያለው መዋቅርም ጥሪያቸውን ተቀብሎ በተደራጀ መልኩ እንዲያሰልፋቸው መላ ህዝቡ በአጽንኦት ማሳሰቡንም አንስቷል፡፡

ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት መሰል ጥሪዎች ተላልፈው እንደከሸፉ ሁሉ ሰሞኑን በስመ ቄሮ የሚነዛው የሁከትና ብጥብጥ ጥሪ ይህን የህብረተሰብ ክፍል የማይወክል መሆኑን ለማስታወስ እንሻለንም ነው ያለው፡፡ በዚህ አጋጣሚ መንግስት የፀረ ሠላምና ለውጥ አደናቃፊ ኃይሎችን ጥሪ በማክሸፍ ሂደት ውስጥ ጉልህ ድርሻ ለነበራቸው መላ ህዝቡና የፀጥታ ኃይሉ ምስጋናውን እንደሚያቀብም ገልጿል፡፡

በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኘው ወጣትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ወቅት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና የዕለት ተዕለት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ መሆናቸውንም አትቷል፡፡ ስለሆነም ለፀረ ሠላምና ልማት ጥሪ የሚሰጡት ጆሮና ደቂቃ እንደማይኖራቸውም ነው የገለጸው፡፡

ይህ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታ የማይገደውና የተደላደለ ኑሮ እየኖረ ያለው ጥቂት ኃይል ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በሚዲያ ላይ በሬ ወለደ አሉባልታና የግጭት ነጋሪት በመጎሰም ላይ ይገኛል ያለው መግለጫው ከዚህ ጋር ተያይዞ ህዝቡ በልማት ላይ ተጠምዶ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የፀጥታ አስከባሪ ኃይል የህብረተሰቡን ሠላም ለመጠበቅና ሁለንተናዊ ፀጥታ ለማረጋገጥ በሙሉ ዝግጅትና ቁመና ላይ እንደሚገኙም ጠቅሷል፡፡

ስለዚህ መላ ህዝቡ መደበኛ የልማት ሥራውን ከማከናወን ጎን ለጎን በአካባቢው የሚታዩ ለሠላምና ሠላማዊ እንቅስቃሴ ሥጋት የሆኑ ማናቸውንም ምልክቶች ለሠላም ኃይሉ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የጎታች ኃይሎች ምኞት ህልም ሆኖ ይቀራል፤ ልማት፤ ዴሞክራሲና አብሮነት በፅኑ መሠረት ላይ ይገነባል !!

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ነሐሴ 2012 ዓ.ም
ፊንፊኔ
@Yenetube @Fikerassefa
ከኢፌዴሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት

''12፣12፣12 ''ተብሎ የተፈጠረው ስልፍ ህገወጥ በመሆኑ ህብረተሰብ የጥሪው ዓላማ ህገወጥና ፀረ-ሰላም መሆኑን በመገንዘብ ለዚህ ስልፍ ተባባሪ እንዳይሆን ። በሌላ በኩል አቶ #ጀዋር_ሙሀመድ ተሟል ችግር ደርሶበታል ተብሎ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የሚወራው ሐሰተኛ መረጃ መሆኑንና ግለሰቡ በተሟላ ጤንነት ላይ የሚገኝ መሆኑን እየገለጽን በዚህ በዚህ ሰበብ ሰውን እያወናበዱ በሀሰተኛ ወሬ የፍርድ ሂደቱን ለማዛባት የሚደረገው ጥረት በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ህበረተሰብ ተገንዝቦ ለህገወጥ ጥሪዎችና ቅስቀሳዎች ተባባሪ እንዳይሆንና ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ተግባር ላይ ከተሰማሩ የፀጥታ ሀይሎች ጎን ተሰልፎ ሰላሙን እንዲጠብቅና እንዲያረጋግጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል ።
ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም
@Yenetube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1460 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ16 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 19,747 የላብራቶሪ ምርመራ 1460 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተጨማሪም 165 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 31,336 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 544 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 12,524 ደርሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በደሴ ከተማ ገብያ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በሚቆጣጠሩ ፖሊሶችና በገብያተኞች መመካከል በተፈጠረ አለመግባባት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት በትንሹ 5 ሰዎች መቁሰላቸውን ከኢትዮጵያ ላይቭ አፕዴት ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ሕገ ወጥ መሬት ወረራ ላይ ማስረጃዎችን እንዳሰባሰበ ኢዜማ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የከተማዋ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምላሽ እንዲሰጠው ፓርቲው በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ እስካሁን የደረስኩበትን ውጤት በቀጣዩ ሳምንት ለሕዝብ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል ኢዜማ።

Wazema / Ezema
@Yenetube @Fikerassefa