በትግራይ ክልል ምርጫ ጳጉሜ 4 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡
መቐለ ነሃሴ 08 2012 ዓ/ም
የትግራይ ክልል የሚያካሂደው 6ኛ ክልላዊ ምርጫ ጳጉሜ 4 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ እና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የተፈቀደው የበጀት ድልድል ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቅላቸው የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ምንጭ :- ትግራይ ቴሌቭዥን
@Yenetube @Fikerassefa

ለ16 ዓመት ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን በኡጋንዳዊው ወጣት ተሰበረ
ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕቴጌ ትናንት በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ16 ዓመታት በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የ5ሺህ ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንድ ማሻሻል ችሏል።
የ23 ዓመቱ ወጣት ባላፈው ዓመት በዶሃ የዓለም ሻምፒዮና ላይ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በሆነበት ወቅት የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጾ የነበረ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ያሳካዋል ተብሎ አልተገመተም።
ነገር ግን በትላንቱ የሞናኮው ውድድር ላይ 5 ሺህ ሜትሩን 12 ደቂቃ 35 ሰከንድ 36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ የቀነኒሳን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።
ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ 16 ዓመት ክብረ ወሰኑን ሲያስመዘግብ ውድድሩን የጨረሰው በ12 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።
በሚያስገርም ሁኔታ ቼፕቴጌ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን ሲሰብር ይሄ ሁለተኛው ሲሆን ባለፈው የካቲት ወር ላይ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሰዓት ማሻሻል እንደቻለ በመረጃው ሰፍሯል።
“በዚህ ዓመት በእውነቱ ሞራልን ሰብሰብ አድርጎ ለመስራት ትንሽ ይከብዳል፤ ምክንያቱም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው አይወጡም፤ ብዙ ነገሮችም በፊት እንደነበሩት አይደሉም፤ ተቀይረዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ሲል ተናግሯል።
ታናሽ ወንድሙ ጆሴፈስ ደግሞ በመጀመሪያው የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው እሱን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል።
ኖርዌያዊው ዓለም ሻምፒዮን ካርስተን ዋርሆልም ደግሞ በ400 ሜትር መሰናክል ውድድር በአውሮፓውያኑ 1992 በኬቨን ያንግ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል።
ለብቻው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሲሮጥ የነበረው ካርስተን ውድድሩን በ47 ሰከንድ ከ10 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል።
ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ደግሞ ጥቂት ዙሮች ሲቀሩት ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች።
5 ሺህ ብቻ ሰዎች እንዲመለከቱት በተፈቀደው የሞናኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ተካሄዷል።
Via:- Epa

በአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ሰመራ ገባ፡፡
በአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለመድረግ ዛሬ ጠዋት ሰመራ-አፋር ገብቷል፡፡
የልዑኩ አባላት ሰመራ-ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በጉዞው የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በርዕሰ መሥተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የተመራው ልዑክ ትናንት በኦሮሚያ ክልል ጉዳት ለደረሳባው ዜጎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
Via:- AMMA

የቤት ውስጥ ራስን ለይቶ ህክምና (ውሸባ) እና እንክብካቤ (Home Based Isolation and Care) በኢትዮጵያ አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ
የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ማለት አንድ የኮቪድ-19 ታማሚ መሆኑ በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠ ሰው የህመም ምልክት ሳያሳይ ወይም ቀለል ያሉ የህመም ምልክቶች ያሉት እንዲሁም በቤት ውስጥ መሞላት ያለበትን መስፈርቶች የሚያሞሉ የህብረተሰብ ክፍል የቤት ውስጥ እንክብካቤ ማድረግ ሲጀምር በቤት ውስጥ ውሸባ እንክብካቤ ማድረግ ጀምራል ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በተደረጉ 567,442 የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራዎች 27,242 በቫይረሱ የተያዙ ታማሚዎች ሲገኙ ከዚህም ውስጥ እስከ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ከነበሩት 5,000 ታማሚዎች 76 በመቶ ምንም ምልክት የሌለባቸው እና 21 በመቶ መለስተኛ ህመም ያላቸው እና ቀሪውቹ ከባድ እና በፅኑ ህመም ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡
በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ማስተባበሪያ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ታይካ አለሙ በአሁኑ ሠአት 2000 በላይ የቤት ውስጥ የውሸባ እና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ታካሚዎች እንደሚገኙ እና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ከ400 በላይ የሚሆኑት አገግመው መውጣታቸውን ገልፅዋል፡፡
በተጨማሪም በቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ጊዜ ከታካሚው ጋር በሚኖረን ግንኙነት ንክኪን ማስወገድ፣ እጃችንን ከአልኮል በተሰራ የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ማፅዳት፣ ከታካሚው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ የህክምና የአፍና የአፍንጫ ጭንብል በአግባቡ ማድረግ እደሚኖርብን አሳስበዋል፡፡
እንዲሁም ታካሚዎቹ ማንኛውም የህመም መባባስ ሲኖራቸው ወደ 8335/952 ወይም ለሚከታተላቸው ክፍል በመደወል ማሳወቅ ወይም አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኝት እደሚችሉ አሳውቀዋል፡፡
በቅድሚያ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ ለማግኘት ስለታካሚው ተገቢውን መረጃ መስጠት የሚችል የቤት ውስጥ ተንከባካቢ ወይም የማህበረሰብ በጎ ፍቃደኛ መኖር፣ ቫየረሱ እንዳይሰራጭ ቤቱ በተገቢው ሁኔታ የተዋቀረ መሆን፣ ለታካሚው ቤተሰብ በቂ የአፍና አፍንጫ ጭንብል፣ ጓንት መኖሩን ማረጋረጥ የምግብ እና መሰረታዊ አቅርቦቶች ሞሟላት በተጨማሪም ተንከባካቢው እንዲሁም ታማሚው ተጓዳኝ በሽታ እንደሌለበት ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
ህብረተሰቡ የቤት ውስጥ ውሸባ እና እንክብካቤ መጀመሩን አውቆ ከጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን ምክር በሚገባ መተግበር እንዳለበት እና ለቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ባለመሆን እንዲጠነቀቁ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡
Via:- Ethiopian Public Health Institute

23 ሺህ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በትናትናው ዕለት 46 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 23 ሺህ ግራም ወርቅ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። 23 ሺህ ግራም ወርቁ ናይጄሪያ ዜግነት ባለው ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቦሌ አየር መንገድ መያዙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ግለሰቡ ወርቆቹን በህገወጥ መንገድ ወደ ዱባይ ይዞ ለመሄድ ሲሞክር ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። ይህን ህገ-ወጥ ተግባር በቁጥጥር ስር ለዋሉ የቦሌ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞችና የጸጥታ አካላት የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምንጭ : AMN

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሃፊ ስለ ህዳሴው ግድብ ጉዳይ ተወያዩ
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሃፊ ስቴቨን ሙኒሽን ጋር በግድቡ የድርድር ሂደት ዙሪያ ተወያዩ፡፡
Via:- አል አየን
@Yenetube @Fikerassefa
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሃፊ ስቴቨን ሙኒሽን ጋር በግድቡ የድርድር ሂደት ዙሪያ ተወያዩ፡፡
Via:- አል አየን
@Yenetube @Fikerassefa
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በሳምንቱ ለ2ኛ ጊዜ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 3550 ሰዎች መፈናቀላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። ጎርፉ 640 ሔክታር የእርሻ ማሳ እና የግጦሽ መሬት አጥለቅልቋል። ተፈናቃዮች በትምህርት ቤት እና በየዘመዶቻቸው ቤት ተጠልለዋል።
Via:- Eshet bekele
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- Eshet bekele
@YeneTube @Fikerassefa
በዓለም ደረጃ #የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር 21 ሚሊዮን ደረሰ
በዓለምአቀፍ ደረጃ #የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ21 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን 764ሺ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በዓለምአቀፍ ደረጃ #የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ21 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን 764ሺ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ሱዳን በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገውን ድርድር ለመቀጠል መስማማቷን የግብጹ አል-አረቢያ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዘገበ።
ውሳኔው የተሰማው የግብጹ ጠቅላይ ምኒስትር ሙስጠፋ ማዶብሊ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው።
Via:- Eshet Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
ውሳኔው የተሰማው የግብጹ ጠቅላይ ምኒስትር ሙስጠፋ ማዶብሊ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው።
Via:- Eshet Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 22,252 የላብራቶሪ ምርመራ 1652 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 28,894 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 509 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 12,037 ደርሰዋል።
@YeneTube @FikerAssefa1

የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት አራት "የፈንጂና ተቀጽላ ተጠቃሚ" ድርጅቶች ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ። በኢትዮጵያ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችና አሞንየም ናይትሬት መሰል ኬሚካሎች ለማዕድን ቁፋሮና ለግንባታ የሚጠቀሙ 252 ተቋማት ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል።
Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
በቻይና እየበለፀገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ተስፋ ሰጭ መሆኑ ተነገረ።
ሀገራት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የክትባትና የሕክምና መድኃኒቶችን በማበልጸግ ላይ ናቸው። በዚህም በርካታ ሀገራት ተስፋ ሰጭ ሂደት ላይ መሆናቸው እየተገለጸ ነው፤ አንዳንዶቹም የምርት ትዕዛዝ እስከመቀበል ደርሰዋል፤ ምንም እንኳ የክትባቶቹ ውጤታማነት የመጨረሻውን ማረጋገጫ በዓለም ጤና ድርጅት በኩል ባያገኝም።
የኮሮናቫይረስ መነሻዋ ቻይናም ክትባት ለማግኘት እየሄደችበት ያለው ርቀት ተስፋ ሰጭ መሆኑን አስታውቃለች። ከሰሞኑ በአሜሪካው የሕክምና ማኅበር መጽሔት (ጆርናል ኦፍ አሜሪካን ሜዲካል አሶሴሽን) የታተመው ጽሑፍም ይህን አረጋግጧል።
መጽሔቱ በቻይናው ብሔራዊ ሥነ ሕይወታዊ ቴክኖሎጅ ቡድን ስር በሚገኘው 'የውኃን ሥነ ሕይወት ምርምር ተቋም' እና ሌሎችም ጥምረት እየተሠራ ያለው የክትባት ምርምር መልካም ሂደት ላይ ይገኛል ሲል አስነብቧል። በክሊኒካል ደረጃ 1 እና 2 ተፈትሾ ውጤታማ መሆኑ እንደተረጋገጠም መጽሔቱን ዋቢ አድርጎ ዥንዋ ዘግቧል።
በምርምር ሂደት ላይ በሚገኘው ክትባት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 59 ዓመት የሆኑ 320 በጎ ፈቃደኞች በሁለቱ ዙሮች መሳተፋቸውም ታውቋል። ክትባቱን በዝቅተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ መጠን የወሰዱት በጎ ፈቃደኞቹ የበሽታ መከላከል አቅማቸው ላይ ለውጥ መታዬቱም ተመላክቷል። ለውጡ እንደወሰዱት የክትባት መጠን ልዩነት ማመልከቱንም ዘገባው አስረድቷል። ይህም ክትባቱ ውጤታማ መሆኑን ያረጋገጠ እውነታ ነው ተብሏል።
የክትባቱን የጎንዮሽ ጉዳት በተመለከተም ጥናት መደረጉንና አስተማማኝ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል። በበጎ ፈቃደኞቹ ላይ ተመራማሪዎቹ በክትትል ያገኙት ጉልህ የጎንዮሽ ጉዳት የለም፤ ተሳታፊዎቹም የገለጹት የጎንዮሽ ጉዳት ክትባቱን የተወጉበት አካባቢ ያጋጠመውን ሕመምና መጠነኛ ሙቀት (ትኩሳት) መሰማት ነው።
via:- AMMA

**ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻን የማስዋብ ፕሮጀክቶች በመጪው ዓመት ይጀመራሉ*
ሸገርን በማስዋብ ፕሮጀክት የተገኘውን ልምድ በአገር ደረጃ በማሳደግ “ገበታ ለሀገር” በሚል ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻ የማስዋብ ፕሮጀክቶች በመጪው ዓመት ይጀመራሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ “ገበታ ለሀገር” በሚል ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ውይይት ሲያደርጉ እንደገለጹት በመጪው ዓመት ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻ አካባቢዎችን የማስዋብ ፕሮጀክቶች ይጀመራሉ።
አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ እናደርጋታለን የሚል ሃሳብ ታልሞ በሸገር ፕሮጀክት ስኬት አገኝተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገበታ ሸገርን ልምድ ወደ "ገበታ ለሀገር" ለማሻገር መነሻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ገበታ ለሀገር የሚተገበሩባቸው አካባቢዎች ሶስት መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህም በአማራ ክልል ጎርጎራ፣ በኦሮሚያ ክልል ወንጪ እና በደቡብ ክልል ደግሞ ኮይሻ ናቸው።
ለፕሮጀክቶቹ ስኬታማነት ባለሃብቶች፣ ህብረተሰቡ፣ ዳያስፖራዎች እና የልማት አጋሮች ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።
ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ ቢያንስ ስድስት ቢሊዮን ብር ያህል ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከባለሃብቶች፣ ህብረተሰቡና ዳያስፖራው ሶስት ቢሊዮን ብር ይሰባሰባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ከባለድርሻ አካላት ይሆናል ብለዋል።
ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ መነሻ ሃብት ለማሰባሰብም የ10 ሚሊዮንና የአምስት ሚሊዮን ብር የሚከፈልበት የእራት ግብዣዎች የሚዘጋጅ ሲሆን ባለሃብቶች በገለሰብ ደረጃ፣ በኩባንያቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በሚያደንቋቸው ሰዎች ስም ትኬት መግዛት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
(ምንጭ፡- ኢፕድ)

አርቲስት ሓጎስ ገብረህይወት ከዚህ አለም በሞት ተለየ
አርቲስት ሓጎስ ገብረህይወት በትግራይ ብሔራዊ ክልል ከተማ ዓዲ ግራት የተወለደ ሲሆን በአደረበት ሕመም ምክንያት ለሁለት ቀናት በኮርያ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም አርፏል፡፡
አርቲስቱ ባለትዳር የሁለት ወንዶች እና የአንዲት ሴት ልጆች አባት ነበረ።
Via:- Fidel Post

የኦሞ ወንዝ ባስከተለው የውሃ መጥለቅለቅ 15 ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ
በደቡብ ክልል የሚገኘው የዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ውሃ በመጥለቀለቁ፤ 15 ሺህ ገደማ ሰዎች መፈናቀላቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ አስታወቀ። ወንዙ ባስከተለው ጎርፍ 15 ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሌሎች ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱንም ገልጿል።
የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ለማ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት የኦሞ ወንዝ ላስከተለው የውሃ መጥለቅለቅ መንስኤው #የግልገል_ጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከመጠን በላይ በመሙላቱ የተለቀቀ ውሃ ነው። በዚህም ምክንያት በዳሰነች ወረዳ ከሚገኙ 40 ቀበሌዎች ውስጥ ሃያ ስምንቱ በዚህ ሳምንት በወንዙ መጥለቅለቃቸውን አስረድተዋል።
Via:- ethiopiainsider

አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር በግብፅ ካይሮ ደረሱ
አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባሳለፍነው አርብ ካይሮ መድረሳቸውን በግብፅ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በፌስቡክ ገፁ ገለፀ። እንደዘገባው ከሆነ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ማርቆስ ተክሌ ባሳለፍነው አርብ ካይሮ ከተማ የገቡ ሲሆን ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ውስጥ በሚንስቴር ደኤታነት፣ በኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የውጪ አገልግሎት ስልጠና ተቋም ዳይሬክተርነት እንዲሁም በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደ እንደነበር ማስታወስ ይቻላል።
አምባሳደሩ በካይሮ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በአርብ እለት በደረሱበት ወቅት የተለያዩ የኢምባሲው ሰራተኞች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከተለያዩ ምንጮች መረዳት የተቻለ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ከአምባሳደር ማርቆስ ሹመት በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት ሁለት አምባሳደሮችን መሾሙን ከውጪ ጉዳይ ሚንስተር የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ። ይህም የአዲሱ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ብርሀኑ ፀጋዬና የአዲሷ በቤልጄም የኢትዮጵያ አምባሳደር ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ሹመት መሆኑን ከውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።
ፎቶ፡ በግብፅ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የፌስ ቡክ ገፅ
@Yenetube @FikerAssefa

የአፋር ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስኛ ዓመት የስራ ዘመን አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2013 ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ በጀትና የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ሃሰን የክልሉን የ2012 የስራ አፈጻጸምና ተያያዥ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ በጀቱ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። “በጀቱ ከ2012 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው” ብለዋል ።
Via:- Addis Maleda

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ170 ሺህ አለፈ
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ170 ሺህ አልፏል።
ትናንትናም ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው በ483 ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።
ከዚህ ውስጥ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ እና ሉዊዚያና ቀዳሚውን ቁጥር ይዘዋል ተብሏል።
በሀገሪቱ በዚህ ወቅት የሚጀምረው ጉንፋን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዳያባብሰው ስጋት አሳድሯል።
በሀገሪቱ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ይሕ ቁጥር በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
አሁን ላይም ከሃዋይ ፣ ከሳውዝ ዳኮታ እና ኢሊኖይ ግዛቶች በስተቀር የወረርሽኙ ስርጭት በመቀነስ ላይ መሆኑም ይነገራል።
ምንጭ፡-ሬውተርስ
@Yenetube @Fikerasaefa