YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለመግባት የሸንገን ቪዛ ፍቃድ ካገኙ 11 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ሆናለች፡፡

በህብረቱ ሸንገን ቪዛ ፍቃድ ከተሰጣቸው 54 የዓለም ሀገራት መካከል ከአፍሪካ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ግብፅ፣ ሞሪሺያስ፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያና ዛምቢያ ተካተዋል፡፡በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ድንበሮቻቸውን ዘግተው የቆዩት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት እ.ኤ.አ ከሀምሌ1/2020 ጀምሮ ድንበሮቻቸውን ሲከፍቱ እንዲገቡ ፍቃድ ከተሰጣቸው አገራት መካከል እንደ አሜሪካ እና ብራዚል ያሉ ወረርሽኙ ያገረሸባቸው አገራት አልተካተቱም። አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ጀማይካ እና ኩባ ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ፍቃድ ካገኙ 54 አገራት መካከል ናቸው። ሸንገን ቪዛ አብዛኛውን የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ውስጥ ተጓዦች ያለገደብ አንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የቪዛ አይነት ነው፡፡

ምንጭ፡- ገልፍ ኒውስ/ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ለሰፋፊ የእርሻ ልማት የዋለው መሬት ክልሉን ጎድቷል ተባለ!

በጋምቤላ ለሰፋፊ የእርሻ ልማት የዋለው መሬት በጥናት ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑ በክልሉ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዑሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ከ2000 ጀምሮ በክልሉ በሰፋፊ እርሻ ልማት ላይ እንዲሰማሩ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ባለሀብቶች በዘርፉ ያላቸው አቅምና ብቃት አልተፈተሸም። በክልሉ ለሰፋፊ እርሻ የሚውል 683 ሺህ ሔክታር መሬት ለ623 የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ተላልፏል። ለባለሀብቶቹ ከተላለፈው መሬት ውስጥ ልማት ላይ የዋለው 18 በመቶ ብቻ እንደሆነ በ2009 በተካሄደ ጥናት ተረጋግጧል።በመሆኑም ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት በማልማት ለወጣቶችም የሥራ ዕድል ባለመፍጠራቸው ክልሉ ማግኘት የሚገባውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሳያገኝ መቆየቱን ዑሞድ ገልጸዋል።

ከ10 ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል ለባለሀብቶች በሚሰጠው መሬት ላይ በፌዴራል መንግሥትና በክልሉ ባለሥልጣናት መካከል ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበርም አስታውሰዋል።የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት በስፋት ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ “በስልክ ትዕዛዝ ብቻ የእርሻ መሬት እንዲሰጥ ይደረግ ነበር” ብለዋል። በወቅቱ ክልሉ እስከ 500 ሔክታር መሬት ድረስ ለባለሀብቶች እንደሚያስተላልፍ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በፌዴራል መንግሥት በኩል ግን ከተባለው ሔክታር በላይ ነበር ብለዋል። በወቅቱ የነበረው አሰራር በተፅዕኖ ሥር የወደቀ ስለነበረ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት በኩል ለባለሀብቶቹ የሚሰጠው የመሬት ካርታ መደራረብ የታየበትና ለሙስና የተጋለጠ ነበርም ነው ያሉት።

በመሆኑም በካርታ አሰጣጥ ላይ የሙስና ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ተደርጓል ብለዋል። በክልሉ 284 ሺህ 796 ሔክታር መሬት ተመንጥሮ ሳይለማ እንደተቀመጠ የገለጹት ዑሞድ የክልሉ መንግሥት ባሳለፈው ውሳኔ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ተደርጓል ብለዋል። ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በክልሉ የሚከናወኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት ከፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት የፀዳ መሆኑንም ተናግረዋል።በጋምቤላ ክልል በሰፋፊ የእርሻ ልማት ለመሰማራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት 623 ባለሀብቶች መካከል የ360 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰርዟል፤ የወሰዱትም መሬት እንዲመለስ ተደርጓል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም ነገ ምክክር እንደሚደረግ ተገለጸ!

የትግራይ ክልል የራሱን የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችለው አዋጅ እንዲሁም የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ አዘጋጅቶ ለውይይት ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል።በአገሪቱ በዚህ ዓመት ማብቂያ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ ባለው የወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ምርጫው ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ቢወሰንም የትግራይ ክልል ግን ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ እንደወሰነ ማሳወቁ ይታወሳል።በዚህም በክልሉ ለማካሄድ ዕቅድ ከተያዘለት ክልላዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ሁለት የሕግ ረቂቅ ሰነዶች ተዘጋጅተው ነገ ማክሰኞ በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመወየያያት ቀጠሮ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ከሚደረግባቸው ረቂቅ ሰነዶች አንዱ የምርጫና የምርጫ ሥነምግባር ረቂቅ አዋጁ 130 አንቀጾችን የያዘ ነው ተብሏል።ሁለተኛው ሰነድ ደግሞ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም ለማደራጀት እንዲሁም ስልጣኑንና ተግባሩን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ 33 አንቀጾችን የያዘና 27 ገጾች ያሉት ሰነድ መሆኑን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ አንድ ሰው ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ልዩ ቦታው ማሞ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው ፡፡በግምት እድሜው 29 አመት የሆነው ወጣት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ ወዲያው እንዳለፈ ነው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገረው፡፡ይሁንና ወጣቱ ለምን ወደ ወንዙ ውስጥ እንደገባ እስካሁን አልታወቀም ተብሏል።ከዚሁ ጋር በተያያዘም ቅዳሜ እና እሁድ በከተማዋ ሁለት የእሳት አደጋዎች ተከስተው እንደነበረም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡የመጀመርያው የእሳት አደጋ የደረሰው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ሲሆን በአምስት መኖርያ ቤቶች የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡በዚህ አደጋ ምክንያት 240 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን 20 ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏል፡፡ሌላኛው አደጋ የደረሰው ደግሞ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አካባቢ በፎቶ ቤት የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን 3 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በየእለቱ 300 ሺህ ብር እያጣ ነው፡፡የ3 ወራት ኪሳራውም 27 ሚሊዮን ብር ደርሷል ተባለ፡፡

Via Sheger FM 102.1
@YeneTube @FikerAssefa
ወላጆች ከ9 ወር ጀምሮ ያሉ ህፃናትን የኩፍኝ ክትባት እንዲያስከትቡ ጥሪ ቀረበ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2/ 2012 ዓ.ም የኩፍኝ በሽታ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡ክትባቱ ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2/ 2012 ዓ.ም በሁሉም ጤና ተቋማት እና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ መግለጫውን የሰጡት የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ አስታውቀዋል።በክትባቱ ወቅት ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጂት የተደረገ መሆኑንም ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ኤርሚያስ አመልጋ የኢንቨስትመንት ባንክ እያቋቋሙ ነው!

የበርካታ የአዳዲስ ንግድ እንቅስቃሴዎችን በመጀመር የሚታወቁት ኤርሚያስ አመልጋ በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ ለመጀመር በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።ኤርሚያስ በአይነቱ ልዩ የሆነውን ባንክ ለመመስረት የተሠሩ ሥራዎች መኖራቸውን ለአዲስ ማለዳ ጠቅሰው፣ ይህም በቅርቡ አዲስ የንግድ እንቅስቃሴን ይዞ ብቅ እንደሚልም ተናግረዋል። አያይዘውም ኢንቨስትመንት ባንኩን ሥራ እምብዛም ባይገፉበትም በቅርቡ ግን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል።ከኢንቨስትመንት ባንኩም በተጨማሪ በርካታ የንግድ ዘርፎች ላይ በስፋት ለመሰማራት በሂደት ላይ መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ የተናገሩት ኤርሚያስ፣ በቅርቡም ‹ኤርሚያስ አመልጋ› የሚል ትልቅ ድረ ገጽ በመጀመር ወደ ሕዝቡ እንደሚደርሱና በተለይም የተለያዩ የንግድ ሐሳቦችን እና ተጨማሪ ሐሳቦችን በድረ ገጹ ላይ እንደሚገልጹም አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ምርጫ የሚያስፈጽም ተቋም እንዲመሠረት ለክልሉ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ እንደሚቀርብ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ይህ የሚሆንበት ምክንያትም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሠረታዊ የሉዓላዊነት መገለጫ መብት በመሆኑ ሊገሰስ ስለማይገባውና ክልሎችም በራሳቸው የአስተዳደር ወሰን ውስጥ በፌዴራል መንግሥት የማይገሰስ ሉዓላዊነት ያለቸው በመሆኑ እንደሆነ አመልክተዋል።

ጥቂት የማይባሉ የሕግና የሕገ መንግሥት ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኞች የትግራይ ክልል በራሱ መዋቅር ውስጥ የሚሆን የክልል ምርጫ አስፈጻሚ ለማቋቋምና ምርጫ ለማካሄድ እየተከተለው ያለውን ፖለቲካዊ መንገድ እየተቹ ሲሆን፣ የትችታቸው መሠረትም ሕገ መንግሥታዊ መብትን ለማስከበር ሕገ መንግሥቱን የመጣስ አካሄድ መከተል አይገባም የሚል ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትግራይ ክልል ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠውን ምላሽ አስመልክቶ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ላይ፣ የትግራይ ክልል በቀጣይ ሊይዝ የሚችለውን አቋም ወይም ሊወስድ የሚችለውን ዕርምጃ የተገነዘበ የሚመስል ምላሽ ተካቷል።

ይኸውም፣ ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠርና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተፅዕኖ ነፃና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማስፈጸም ሥልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን፣ አፈጻጸምንም ሆነ ተያያዥ ሁኔታን የሚወስነውም ቦርዱ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ውስጥ ስድስተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት፣ እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ሕጋዊ መሠረት የለውም፤›› የሚል ነው።

ምርጫ ቦርድ ለሰጠው ውሳኔ የሰጠውን አመክንዮ በተመለከተ አቶ ጌታቸው  ለሚዲያዎች በሰጡት አሰተያየት፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ በሆነ ምክንያት ምርጫ ማካሄድ አልፈለገም ተብሎ፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠ የክልሎች ወይም የብሔር ብሔረሰቦችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ይታጠፋል ማለት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ብቸኛ የምርጫ አስፈጻሚነት መብት የሚኖረው ምርጫ እንዲያስፈጽም ለቀረበለት ጥያቄ ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ ብቻ እንደሆነም አመልክተዋል።

‹‹የመምረጥ መብት ከምርጫ ቦርድ ህልውና በላይ ነው፤›› የሚሉት አቶ ጌታቸው፣ ‹‹ራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ከምርጫ ቦርድም ሆነ ከማንም በላይ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ምርጫ ቦርድ ለቀረበለት ጥያቄ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሎ የትግራይ ክልል ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተሽቀንጥሮ መጣል እንደሌለበትና እንደማይችልም ገልጸዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ ከ500 በላይ የሚሆኑ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች" ጣናን እንታደግ " በሚል መሪ መልዕክት ዛሬ ሰኔ 22/2012 ዓም በጧት በሊቦ ከምከም ወረዳ በሚገኘው የጣና ሃይቅ ተገኝተው የእንቦጭ አረም ማስወገድ ጀምረዋል።

Via Injibara Communication
@YeneTube @FikerAssefa
የኢራን መንግስት በዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል!

የኢራን መንግስት በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አልጀዚራ ሰበር ዜና ሲል ይዞ ወጥቷል። የእስር ማዘዣው በፕሬዝዳንቱ ላይ እንዲወጣ ምክንያቱ ከወራት በፊት የኢራኑ ጄኔራል ቃሴም ሶሌማኒ ኢራቅ ውስጥ በትራምፕ ትዕዛዝ በድሮን አማካኝነት በተፈፀመ ጥቃት መገደላቸው ነው ተብሏል፣ ዶናልድ ትራምፕንና በወቅቱ በጄኔራሉ ግድያ የተሳተፉ ከ30 የሚልቁ ሰዎችን አድኖ እንዲያቀርብላቸውም የኢራን ባለስልጣናት ኢንተርፖልን መጠየቃቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቱርክ አየር መንገድ በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ መብረር ሊጀምር ነው!

ኮሮና በርካታ አየር መንገዶችን እንቅስቃሴ ጎድቶ ከርሟል፡፡ አሁን አሁን ግን በተለይ የአውረጳ እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ እየተከፈተ መምጣቱ በረራዎችም እንዲጀመሩ እያስቻለ ይመስላል፡፡በግምባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ የአውሮፕላን አንቀሳቃሾ አንዱ የሆነው የቱርክ/ተርኪሽ አየር መንገድም ወደ አዲስ አበባ ያደርግ የነበረውን በረራ ከመጪው ሃምሌ 7/ ጁላይ 14 አንስቶ እንደሚጀምር ዛሬ ለካፒታል ጋዜጣ በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡አሁን ላይ የኮሮና ስጋት እየጨማረ የተጠቂዎች ቁጥርም 10 ሚሊዮን ያለፈ ቢሆንም በተለይ አብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ችግሩን መቆጣጠር በመቻላቸው ቀስ በቀስ ወደ እንቅስቃሴ እየገቡ ነው፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ጤና ቢሮ አካባቢ በቀን 08/03/2012 ዓ/ም ከምሽቱ 4፡00 አካባቢ ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ለመገላገል በገቡ ሰዎች ላይ በደረሰ ጉዳት የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት ይገኛል። ተጠርጣሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት የሚገኝ ሲሆን አጠቃላይ የድርጊቱን ሁኔታ በቀጣይ…
በ3 ሰዎች ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጣ!

ነዋሪነቱ በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 2 ቀጠና 4 ነዋሪ የሆነዉ የ29 ዓመት ወጣት ሙሉጌታ ሁሴን ሙሳ የተባለዉ ግለሰብ በዕለተ ሰኞ ህዳር 8 ቀን 2012 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ ፣ ልዩ ቦታዉ ጤና ቢሮ ሃያት መስጅድ በተባለ ቦታ ሆን ብሎ በሰዉ ህይወትና አካል ላይ ጉዳት ለማድረስ አስቀድሞ በማሰብና በመዘጋጀት በ3 ሰዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበትና በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት መሳሪያ ህይወታቸው እንዲልፍ ያደረገና በባለቤቱ ላይም አንገቷንና የቀኝ እጇን በመዉጋት የመግደል ሙከራ ያደረገባት በመሆኑ ተከሳሹ በፈጸመዉ ከባድ የሰዉ መግደል ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ እና አቃቢ ህግ የምርመራ መዝገቡን በሰዉና በህክምና ማስረጃ እንዲሁም በተያዘዉ ኤግዚቢት በማረጋገጥ ለሚመለከተዉ የፍትህ አካል/ ፍርድ ቤት/ የተላከ ሲሆን የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በቀን 17/10/2012 ዓ/ም በዋለዉ ግልጽ የወንጀል ችሎት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

መረጃዉ:- የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ነው
@YeneTube @FikerAssefa
የ10 ዓመት ህጻን ልጁን የደፈረው አባት በ9 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የካማሽ ከተማ አስ/ር ፖሊስ አስታወቀ።

የካማሽ ዞን ማረሚያ ቤት የሥራ ባልደረባ የሆነው ዋ/ሳጅን በላይ ታየ የገዛ ልጁን የ10 ዓመት ህጻን አስገድዶ የደፈራት መሆኑን የካማሽ ከተማ አስ/ር ፖሊስ መምሪያ አቤቱታ መቀበል መመርመር ዋና ስራ ሂደት ባለቤት ዋ/ኢ/ር ቃበታ መልካ ገልፀዋል፡፡ግለሰቡ ነዋሪነቱ ካማሽ ከተማ 02 ቀበሌ ዕለቱ ሰኞ ታህሳስ 08/04/2012 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የህጻኗ እናት ቤተሰብ ሞቶባት ለሃዘን በሄደችበት ወቅት ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሰክሮ በመምጣት የ10 ዓመቷን ህጻን ልጁን ከደበደባት በኋላ አስገድዶ የደፈራት መሆኑን ነው ዋ/ኢ/ር ቃበታ መልካ የገለጹት።

ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የሰውና የህክምና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለካማሽ ወረዳ ዐ/ህግ ያስተላለፈ ሲሆን ዐቃቢ ህጉም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ከተመለከተ በኃላ በወ/ል/መ/ቁ/ 122/12 ክስ በመመስረት ለካማሽ ወረዳ ፍ/ቤት አስተላልፏል፡፡የካማሽ ወረዳ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ክስ ሲመረምር ከቆየ በኃላ ግለሰቡ የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት መከላከል ባለመቻሉ የዐቃቢ ህግን ማስረጃ በመንተራስ ፍ/ቤቱ በ17/10/2012 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑ በመረጋገጡ በ9/ዘጠኝ/ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የካማሽ ከተማ አቤቱታ መቀበል መመርመር ዋና ስራ ሂደት ኃላፊ ዋ/ኢ/ር ቃበታ መልካ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ምንጭ: የክልሉ ፖሊስ ኮምሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 157 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ 5 ሰዎች ሁኔታ:

1.በህክምና ማዕከል የነበረ የ18 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

2.በአስከሬን ምርመራ የተገኘባቸው የ65 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)

3.በአስከሬን ምርመራ የተገኘበት የ10 አመት የትግራይ ክልል ነዋሪ

4.በአስከሬን ምርመራ የተገኘባቸው የ70 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ሴት)

5.በአስከሬን ምርመራ የተገኘበት የ34 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 157 ሰዎች ሲሆኑ ከአንድ ሰው በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(97) ሴት(60) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ7-83 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 298 ሰዎች (200 ከአዲስ አበባ፣ 87 ከሶማሊ ክልል፣ ከአማራ ክልል(9) 1 ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2430 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(132)፣ ከትግራይ ክልል(3)፣ ከኦሮሚያ ክልል(3)፣ከሶማሊ ክልል(3)፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል(1)፣ ከአማራ ክልል(5)፣ ከድሬዳዋ(5) እና ከአፋር ክልል(5)በድምር 157 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 35 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 103 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 132 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ የላቦራቶሪ ምርመራዎች አድራሻቸው አዲስ አበባ የሆኑ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3867 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማችን አዲስ አበባ የ 4 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 200 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን አዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-

👉አዲስ ከተማ 6
👉ቦሌ 17
👉ጉለሌ 12
👉ልደታ 21
👉ኮልፌ ቀራንዮ 7
👉ቂርቆስ 33
👉አራዳ 1
👉የካ 14
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 16
👉አቃቂ ቃሊቲ 5

@YeneTube @FikerAssefa
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ፡ ባሳለፍነው ሳምንት

👉 ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አበረታች ነው

👉 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ አይደለም ቢሆንም ግን

👉 አሁንም በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

👉 የማህበረሰብ ስርጭት እየጨመረ ነው

👉 በፅኑ የታመሙ እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ስለዚህ ስርጭቱን ለመቀነስና በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቀመጡትን ጥንቃቄዎች ሁሌም እንተግብር!

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እናድርግ!
አካላዊ ርቀታችንን እንጠብቅ!
የእጅ ንፅህና እንጠብቅ!
የግድ ካልሆነ በስተቀር ከቤት አንውጣ!

-ዶ/ር ሊያ ታደሰ
@YeneTube @FikerAssefa