YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የአዲስ አበባ ጉብኝት "ከሱዳን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እውቅና ውጪ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ምክር የተከናወነ ነው" በሚል የተሰራጨን መረጃ የሱዳን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት "ሐሰት" ሲል አጣጣለ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💻ከNat mobile & Computers
ማንኛውንም አይነት Laptop በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛለን

በተጨማሪም
🔴#ጥራት   ያላቸውንና   ምርጫዎን  የጠበቁ  ላፕቶፖች እና ታብሌቶች  ሳይለፉ   ሳይደክሙ  ከኛ ይሸምቱ ከሙሉ ዋስትና ጋር  

Dell i5 7th 17500br
HP i5 14500br

ስልክ
+251911522626
+251953120011

Inbox @Natyendex

🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች በዋስትና

A01 2019 /16 GB/ 5,500 ብር
A10S 2019 /32 GB/ 6,699 ብር
A20S 2019 /32 GB/ 8,499 ብር
A30S 2019 /64 GB/ 10,499 ብር
A30S 2019 /128 GB/ 10,999 ብር

A50S 2019 /128 GB/ 4GB 13,499
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 13,999
A31 2020 /128 GB/ 4GB 12,499
A51 2020 /128 GB/ 6GB 14,499 ብር

A60 2019 /64 GB/ 6GB 12,999 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 15,999 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 19,499 ብር
A71 2020 /128 GB/ 8GB 19,999 ብር

M30S 2019 /64 GB/ 4GB 11,499
M30S 2019 /128 GB/ 4GB 12,499
📌M31 2020 /128 GB/ 6GB 14,499

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii

@HEYOnlinemarket
#ስለምታስበው_አስብ
#ሁለተኛው_ዕትም_በገበያ_ላይ

በቀን ከ12 ሺ እስከ 60 ሺ ሀሳቦች በአእምሯችን እንደሚመላለሱና ከ80 እስከ 95 ፐርሰንት የሚሆኑት ሀሳቦች አሉታዊና የተደጋገሙ እንደሆኑ ያውቃሉ?

#ስለምታስበው_አስብ የተሰኘው መጽሐፍ አላስፈላጊ ሀሳቦቻችንን ተቆጣጥረን እንዴት ጥርት ባለ ሁኔታ ማሰብ እንዳለብን የሚያሳይ፣ አሉታዊና ትርኪምርኪ የሆኑ ሀሳቦቻችንን ለማጽዳት የሚረዳ መጽሐፍ ነው!

“አዕምሯችን እንዴት እንደሚሰራ እንደ ርችት ፍንትው ባለ ህብረቀለም የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ ትንሽም ቢሆን የአስተሳሰብ እክል አለብኝ ብለው ካሰቡ ይሄ አስገራሚ መጽሐፍ #እንደ_መድሃኒት_ቢታዘዝልዎት_አይከፋም፡፡
ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ

#የምናስብ_ከሆነ_ይህ_መጽሐፍ_የግድ_ያስፈልገናል!!!

#በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች_እጅ_ያገኙታል
http://tttttt.me/teklutilahun
በጥፊ እየመታ የሚያስተምረው መፅሐፍ 3ተኛ ዕትም!!!

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ!!!

‹‹በጥበብ የመኖር ዕሴት››

ቁጥር 1 ዓለም አቀፍ ሽያጭ የተቀዳጀው THE SUBTLE ART OF NOT GIVING A ... መፅሐፍ ‹‹በጥበብ የመኖር ዕሴት›› በሚል ርዕስ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በድጋሜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

መፅሐፉ በጥበብ የመኖር ዕሴቶችን ሲዘረዝርልዎ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህን ጥበቦች ሳያውቁ በመቆየትዎ ይቆጫሉ፡፡
ግን አይዞዎት አሁንም አልረፈደም! መቼም ቢሆን ደግሞ አይረፍድም!!

ከዚህ በፊት ሲያነቡት እንደነበሩት የሳይኮሎጂ መፅሐፍት አይነት ሳይሆን በልዩ ሁኔታ የሚያሰለጥንዎ ለየት ያለ መፅሐፍ ነው፡፡

ርያን ሆሊደይ የተባለ የከፍተኛ ሽያጭ መፅሐፍት ደራሲ ስለዚህ መፅሀፍ እንዲህ ነው ያለው ‹‹የተሻለ ህይወት መኖር መጀመር ከፈለጉ ይሄንን መፅሐፍ ያንብቡ! መፅሐፉ ፊትዎ ላይ አስፈላጊ ጥፊ እያሳረፈ የሚያስተምርዎ መፅሐፍ ነው!!››

ሶስተኛው ዕትም በገበያ ላይ ስለዋለ በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
Forwarded from YeneTube
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።


የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo

ነው።
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ህይወታቸውን ላጡ የቀድሞ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የፀጥታ አካላት መታሰቢያ የሰማእታት ሀውልት ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሰረት ድንጋዩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎችም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው የተቀመጠው ።

የደም ልገሳና ችግኝ ተከላም የሰኔ 15 ሰማእታት ዝክር ስነስርአት አካል ነው ሆኖ እየተተገበረ ነው።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በትላንትናው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ183 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ!

በትላንትናው ዕለት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን ባልታየ መልኩ ዕለታዊ ጭማሪ መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተመዘገበው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ቁጥር ዕለታዊ ሪከርድ ሆኗል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት፣ ለዚህም የሰሜን እና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ ገልጿል።በዕለቱ ከ183 ሺህ በላይ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን መመዝገባቸውን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

ከእነዚህ ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ የተመዘገበው ብራዚል ውስጥ ሲሆን፣ አሜሪካ እና ሕንድ በተከታታይ ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ ሀገራት መሆናቸውን ጠቁሟል።ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡ በከፊል በዓለም ዙሪያ እየተደረገ ያለው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያደገ መምጣቱን የሚያንፀባርቅ ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።በሌላ በኩል እስካሁን በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ9 ሚሊዮን 51 ሺህ በላይ መድረሱን ከወርልዶሜትርስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።ከእነዚህ መካከል ከ4 ሚሊዮን 842 ሺህ በላይ ሲያገግሙ ወደ 471 ሺህ ገደማ ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በድምፃዊነት በዜማና ግጥም ስራው ትልቅ አሻራ ያኖረውና እርሱም በማቀንቀን የሚታወቀው ሱራፌል አበበ ዛሬ ከዚህ አለም መለየቱን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምተናል።የኔቲዩብ ለሟች ቤተሰብ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፎቶ: መገናኛ አካባቢ ዮናስ በርሄና አንዷለም ሞገስ የተባሉ የ"ያ ስቱዲዮ" አርቲስቶች ከከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ፈቃድ አግኝተው እየሳሉት የሚገኘው የግድግዳ ላይ ስዕል(Graffiti)፣

በምስሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ፣ የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ያሉበት ሲሆን፣ "ሁሉም ጥሩ ይሆናል" የሚል መልዕክት ተፅፎበታል።

ምንጭ:ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄደ፡፡

የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት በዛው እለት ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄዷል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤የአዲስ አበባ ከንቲባ ም/ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እንዲሁም የጀነራሉ ቤተሰቦችና የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል።

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄደ፡፡ የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት በዛው እለት ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄዷል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤የአዲስ አበባ ከንቲባ ም/ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤የአዲስ…
በተያያዘ ዜና ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰየሟል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም መሰየሙ ተገልጿል፡፡በቀጣይም በጀነራሉ ስም ሃውልት እንደሚቆምላቸው እና በስማቸውም ፓርክ እንደሚሰራ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
ሰኔ 15 ቀን የሚከበረው የትግራይ የሰማዕታት ቀን ዘንድሮም ለ32ኛ ጊዜ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ በተለያዩ መርኃ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት ጧፍ የማብራት መርኃ ግብር የተካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የትግራይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ፣ የሰማዕታት ቤተ ሰቦችና፣ ነባር ታጋዮችና የተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች በተገኙነት በሰማዕታት ሐውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

Via Dimtsi Weyane
@YeneTube @FikerAssefa
የወላይታ ዞን ም/ቤት ራሱን ችሎ በክልልነት ለመደራጀት ባቀረበው ጥያቄ ላይ ለመወያየት የጠራው 4ኛ ዙር ፣ 7ኛ አመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ በጉተራ አዳራሽ ተጀምሯል። ስብሰባው በOMN ቴሌቪዥን በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ሎተሪ በየ አስራ አምስት ቀኑ ያወጣ የነበረውን የመደበኛ ሎተሪ እጣ አቋረጠ፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር 600 ሺህ ብር ደርሶ የነበረው የመደበኛ ሎተሪ እጣ አስተዳደሩ በደረሰበት ኪሳራ ምክንያት እጣው እንዲቋረጥ መወሰኑን ገልጿል።የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የመደበኛ ሎተሪ የሎተሪ ሺያጭ በ30 በመቶ እንደቀነሰበትም ነው አስተዳደሩ የተናገረው፡፡የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ ንዋይ እንደተናገሩት ባጭር ጊዜ ሎተሪው ተሸጦ ካላለቀ ከፍተኛ ኪሳራ ነው የሚያጋጥመው ያ ደግሞ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲታይ የማይፈቻል ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና አስተዳድር ባለፉት 11 ወራት ከሎተሪ ሽያጭ 702 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡አስተዳደሩ አስራ አምስት አይነት የሎተሪ አይነቶችን ለገበያ አቅርቦ ነው ይህንን ብር የሰበሰበው፡፡ይህም የእቅዱን 83 ከመቶ ጠቅላላ የገበያ አፈጻጸም እንደሆነም ነው ያስታወቀው፡፡አስተዳደሩ በበጀት አመቱ በጠቅላለው 143 ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን 278 ሚሊየን ብር ለባለ እድለኞች እንዲሁም 111 ሚሊየን ብር ደግሞ ለሎተሪ አዟሪዎች ኮሚሽን እንደከፈለም ገልጿል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የእምቦጭ አረም በጣና ሀይቅ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ጎበኙ።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል። ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል።

አንቲቦዲ ማለት ሰውነታችን ለበሽታ በሚጋለጠበት ወቅት ለበሽታው ከተጋለጠ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በሽታውን ለመከላከል ሰውነታችን የሚያመርታቸው የበሽታ ተከላካዩች ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቦዲ መመረት በእድሜ፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የምንጠቀማቸው መድሁኒቶች፣ የበሽታው ከባድነት እና ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል። ምርመራው ከሰውነታችን ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ሲሆን የበሽታው ተከላካዮች (አንቲቦዲ) እንደየበሽታው ዓይነት የሚለያዩ ሲሆን ምርመራው ኮቪድ-19 ለመካላከል እና ለ መቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ነገር ግን የአንቲቦዲ ምርመራ ውጤትን ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም።

ይህ የቅኝት ዳሰሳ በሀገራችን ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለማወቅ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል። በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።

-የኢትዮጲያ ህብረተሰቡ ጤና ኢኒስትቲዩት
@YeneTube @FikerAssefa
የዘንድሮዉ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በኢንተርኔት (ኦን ላይን) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አብደልሙኒየም አደም እንዳስታወቁት በተያዘዉ የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሄራዊ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት በትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈዉ መመሪያ መሰረት አስፈላጊ ጥናትና ዝግጅቶች እየተደረጉበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢቋረጥም በቴሌግራምና በቴሌቪዥን አዉታሮች ትምህርቶች ሲተላለፉ መቆየታቸዉን ያስታወሱት ኃላፊዉ የፈተና ጊዜ በዉል ባይገለጽም ተማሪዎች ዝግጅት እንያደርጉ መልዕክቶች ሲተላለፉ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈዉ መመሪያ መሰረት ወረርሽኙ ባለመቆሙ የዘንድሮዉ ብሄራዊ ፈተና በኦንላይን እንዲሰጥ በመወሰኑ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያለዉ ሁኔታ ተጠንቶ ለፈተና የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታዉቀዋል፡፡ቀደም ሲል የፈተና አሰጣጥን በተመለከተ ግልፅ መረጃ እንዳልተሰጠና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ ሲደረግ ቆይቶ አሁን ላይ ፈተናዉ እንደሚሰጥ የተገለጸ በመሆኑ ተማሪዎች ሳይዘናጉ ባላቸዉ ጊዜ ሁሉ አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ተፈታኞች ራሳቸዉን እንዲመዝኑና እንዲዘጋጁ ለማድረግ በትምህርት ቢሮዉ የቴሌግራም ቻናል ሞዴል ፈተናዎች እየተለቀቁ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ አብደልሙኒየም ወላጆችም ለልጆቻቸዉ ጊዜ ሰጥተዉ እንዲደግፏቸዉ ጠይቀዋል፡፡በሌላ በኩል ክልላዊ ፈተናን በተመለከተ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በመግለፅ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜና ሁኔታ በተመለከተም በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጥን አቅጣጫ እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via BGMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 131 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3238 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 131 ሰዎች ሲሆኑ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(94) ሴት(37) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ2-80 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 84 ሰዎች(79 ከአዲስ አበባ፣ 2 ከኦሮሚያ፣ 2 ከትግራይ እና 1 ከደቡብ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(98)፣ ከኦሮሚያ ክልል(16)፣ከአማራ ክልል(1) ፣ ከትግራይ ክልል(1)፣ከሶማሊ ክልል(4)፣ ከአፋር ክልል(3)፣ ከድሬዳዋ(3)፣ ከደቡብ ክልል(3) እና ከጋምቤላ ክልል(2) በድምር 131 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 38 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa