YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶችን ልካለች።

የህክምና ቁሳቁሶች ዛሬ አዲስ አበባ የደረሱ ሲሆን፥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መሆናቸውን ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የህክምና ቁሳቁሶቹ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ክፍል ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ አማካኝነት የተገዙ ናቸው።

የተደረገው ድጋፍ የህክምና ማስክ፣ የቀዶ ጥገና ጋዎኖች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ሙሉ አካልን የሚሸፍኑ የህክምና አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የትንሳኤን በዓል ስናከብር ርቀታችንን ጠብቀንና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን አለበት... ዶክተር ሊያ ታደሰ

የትንሳኤ በዓልን ስናከብር እንደተለመደው በመሰባሰብ ሳይሆን ርቀታችንን ጠብቀንና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን እንዳለበት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ። ዶክተር ሊያ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።በዓሉን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመታገል ለሚያሳልፉ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት መስጫ ሰራተኞችም ከወዲሁ ምስጋና አቅርበዋል።

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እለት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ቀደም ይህንን በዓል በአብሮነትና በመሰባሰብ ያሳልፋሉ ብለዋል።ሆኖም አሁን ካለንበት ፈታኝ ወቅት አንጻር በዓሉን በመሰባሰብና በአብሮነት ማክበር እጅግ አደገኛ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።በመሆኑም በዓሉን ስናከብር እራሳችንና ቤተሰባችንን ከኮሮናቫይረስ በመከላከል መሆን እንዳለበት መክረዋል።በምግብ ዝግጅት ወቅት ያለምንም መዘናጋት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ምግቦችን አብስሎ መመገብ ይገባልም ብለዋል።"አንዳችን ለሌላችን በማሰብ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ማለፍ አለብን" ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
#96
በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 96 ደረሰ።

- ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረጉ 842 ምርመራዎች አራት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቀዋል። በአጠቃላይ 6231 ምርመራዎች ተደርገዋል

@YeneTube @FikerAssefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ:
አራቱም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ

1.ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ዕድሜ 22

2.በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ እድሜ 52

3.በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው የባህር ዳር ነዋሪ ፣ ዕድሜ 52

4.የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ካላት እየተጣራ ያለ የአዲስ ቅድም ነዋሪ፣ዕድሜ 23

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ ሊንቀሳቀሱ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) በፈረቃ ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገለጸ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ኮሚቴ የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ ላይ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 የሆኑ የቤት ተሽከርካሪዎች በሌዳ ቁጥራቸው ሙሉና ጎዶሎነት በፈረቃ እንደሚንቀሳቀሱ ተገልጿል።በዚህም የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ዓርብ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፥ የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ነገ ቅዳሜ ይንቀሳቀሳሉ ተብሏል።

ክልሎችም እንደራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ መመሪያ አውጥተው እንደሚተገብሩት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በመግለጫው ላይ የከተማ ታክሲ አገልግሎት በሚሰጡም ሆነ በሃገር አቋራጭ አውቶብሶች ላይ የወጣው መመሪያ በአግባቡ እንደሚተገበር ተነስቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዋፋ ሲናማ ( ሰይጣን ቤት) ለአረንጓዴ ፕሮጀክት ተብሎ ሊፈርስ ነው   የአራዳ መሬት ልማት ማኔጅምነት ቤሮ ከዛሬ 112 አመት በፊት በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ የተሰራውን በተለምዶ ስሙ ሜጋ አምፊ ቲያትር ወይንም ሰይጣን ቤት የተባለውን ሲኒማ ቤት ለአረንጓዴ ፕሮጀከት እንደሚያፈርሰው ለሲኒማ ቤቱ በድብዳቤ አሳውቋል። በቅርስነት የተመዘገበው ቤት መፍረስ እንደማይችል የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ማስታወቁ ይታወቃል።…
#ሰይጣን ቤት በአሁኑ ወቅት ዋፋ ሲኒማ ተብሎ የሚጠራው ቦታ እንደማይፈርስ አዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር አረጋገጠ።

ቦታው በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ታሪካዊ እንደመሆኑ ታሪካዊ ይዞታውን በጠበቀ መልኩ የመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚገነባው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት አካል ሆኖ በአዲስ መልክ የሚገነባ ይሆናል ተብሏል።

ቦታው አሁን ላይ ያለበት ይዞታ ቦታውን በማይመጥን መልኩ በእቃ ማስቀመጫነት እያገለገለ እንደሚገኝ የከቲባ ፀ/ቤተ ተናግሯል ።

ቦታዉ ታሪካዊ ይዞታውን እንደጠበቀ በዘመናዊ መልኩ ተመልሶ ለአገልግሎት እንዲውል ይሰራል ተብሏል ።

#ሰሞኑንን_ሰይጣን ቤት ሊፈርስ እንደሆነ በሰፊው ሲነገር ቆይቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
#News_Alert ጎረቤት ሀገር ጅቡቲ በ24 ሰዐት ውስጥ 141 ኬዝ ሪፓርት ተደርጓል። እስከዛሬ 732 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን ተነግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአፍሪካ በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ 10 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊጠቁ እንደሚችሉ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ የስርጭት መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በቀጣዮቹ 3 እና 6 ወራት 10 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል ሲሉ አንድ የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡ በአፍሪካ የአለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክንውን ሀላፊ ሚካኤል ያኦ እንዳሉት ቫይረሱ በአፍሪካ ያለውን ስርጭት መጠን በረጅም ጊዜ ለመገመት አስቸጋሪ ነው ብለዋል።

አሁን ባለው የስርጭት ሂደት በቀጣዮቹ 3 እና 6 ወራት የተጠቂ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል አልጀዚራ ዘግቧል።አክለውም ምናልባትም በጤና ባለሙያዎችን ምክር እና መንግስታት የሚጥሉትን ገደቦች በትክክል የሚተገበሩ እንደሆነ ከግምቱ በብዙ እጥፍ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ተናግረዋል።

ሚካኤል ያኦ አክለውም ትንበያው ሊለወጥ አለያም ሊቀየር የሚችል መሆኑን የገለፁ ሲሆን ኢቦላን በተመለከተ እንጅግ የከፋ ትንበያዎች ሰዎች በወቅቱ ባህሪያቸውን በመለወጣቸው በተሰጡ መላምቶች ልክ ጉዳት አላመጣም ብለዋል፡፡

በአለም እጅግ ደሀ በሆነችው አህጉር አፍሪካ እስካሁን ከ 17 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ሲረጋገጥ 900 ገደማ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ሞተዋል፡፡ይህ ቁጥር በቀጣዮቹ 6 ወራት በከፍተኛ መጠን ሊያሻቅብ እንደሚችል ነው ድርጅቱ ያስታወቀው

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በዓሉ እንቅስቃሴያችንን ገድበን የምናከብረው መሆን አለበት

- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

ሰዎች የፋሲካ በዓልን እንቅስቃሴያቸውን በመገደብ ሊያከብሩ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

የጤና ሚኒስትሯ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “በዓሉ እርስ በእርስ ማዕድ የምንቋደስበት፣ፍቅርን እና መተሳሰብን የምንገልፅበት ቢሆንም አሁን እንቀድሞ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ ተጠራርቶ የሚከበረው ሳይሆን አብረን ከምንኖራቸው የቤተሰብ አባላቶች ጋር ብቻ ሆነን የምናከብረው መሆን ይኖርበታል” ብለዋል።

ፍቅራችንንም አንዱ ለአንዱ በመጠንቀቅ የምንገልፅበት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ወደ መገበያያ ስፍራዎችም ሲኬድ አካላዊ ርቀትን ጠብቀን እና የአፍ መሸፈኛዎችን በመጠቀም መሆን እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት።

የእንሰሳት እርድ በሚካሄድበት ጊዜም በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል ያሉት ዶ/ር ሊያ፥ ምግብንም አብስሎ መመገብ ይገባል ነው ያሉት።

እራሳችንን መገደባችን፣ መታግሳችን እና ዛሬ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ለወደፊት በጥሩ ሁኔታ ማክበር እንድንችል ወሳኝ እርምጃዎች መሆናቸውንም አንስተዋል።

በመጨረሻም ይህንን በዓል ወረርሽኙን ለመከላከል በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ የሚያሳልፉ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎችም እያበረከቱ ላሉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በመተከል ዞን እና አዋሳኝ በሆነው አዊ ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ሁከት በዘላቂነት መፍትሄ ለመስጠት በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና አስታውቀዋል።

ከአሁን በፊት ታውጆ በፖለቲካ አመራሩ ሲመራ የነበረው ኮማንድ ፖስት አጥጋቢ ውጤት ባለማምጣቱ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲመራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።በቀጠናው በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ግጭቶችን እልባት በመስጠት እስከ ግንቦት 30/2012 ዓ/ም ድረስ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት ቀየ ለማስመለስ ኮማንድ ፖስቱ እንደተቋቋመ ብርጋዴር ጄኔራሉ ጨምረው ተናግረዋል።

በሁለቱም ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ህገ ወጥ የጦር እና ድምፅ አልባ መሳሪዎችን ቁጥጥር በማድረግ የህብረተሰቡን የአብሮነት ዕሴት ለመመለስ ኮማንድ ፖስቱ በትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል።በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ይህ ኮማንድ ፖስት ከአሁን በፊት የተዘረፉ ንብረቶችን በማስመለስ እና ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ሁከት በሚፈጥር አካል ላይ የሀይል እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቁሟል።

ምንጭ: የመተከል ዞን ኮምኒኬሽን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
ጀርመን በዛሬው ሪፖርቷ 3,380 አዲስ የኮቪድ-19 ተጠቂዎችና 299 ሞት አሳውቃለች።በሀገሪቱ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 133,830 ሲደርስ የሟቾች ቁጥር 3,968 መድረሱን CGTN ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
#News_alert በጣልያን በ24 ሰዐት ውስጥ 3,493 አዲስ ኬዝ እና 575 ሞት ተመዝግቧል።

በጣልያን 172,434 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሲኖሩ 22,745 ህይወታቸውን አተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በትግራይ የኮሮና ቫይይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ዳሰሳ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቤቶችን ማዳረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ!

በትግራይ ክልል ኮሮና ቫይይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ዳሰሳ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቤቶች በማየት ውጤታማ ስራ ማከናወኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠረጠሩ 33 ሰዎች ተለይተው የደም ናሙናቸው ለምርመራ እየተወሰደ መሆኑ ተመልክቷል።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ዛሬ ጥዋት በሰጡት መግለጫ “ቫይረሱን ለመከላከል ባለፉት አራት ቀናት በመላው የክልሉ ከተሞችና ወረዳዎች የተደረገው የዳሰሳ ስራ ውጤታማ ነበር” ብለዋል።በዳሰሳ ስራውም በእያንዳንዱ ቤተሰብ አባላት የኮሮና ቫይረስ ግንዛቤን፣ያሉት የመከላከያ ግብአት፣በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችና በቅርብ ጊዜ አዳዲስ ወደ ክልሉ የገቡ ሰዎችን መለየት መቻሉን ዶክተር ሓጎስ ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን" የጦር ሰራዊት " ቀኗን በወታደር ሳይሆን በህክምና መሳሪያዎች ትዕይንት አክብራለች።

ዛሬ በኢራን" የጦር ሰራዊት " ቀን ላይ ወታደሮች ፣የጦር መሳርያና ጀቶች በአደባባይ አልታዩም።ይልቁንስ በኮሮናቫይስ የሞቱ ፣የታመሙ እና ቫይረሱ ከገባ ቀን ጀምሮ ለተዋደቁ ዜጎቿን ለማሰብ ወታደሮች የህክምና ጋዎን በማድረግ በተንቀሳቃሽ ክሊኒክ የሆስፒታል እቃዎችን አንዲሁም መድሀኒቶችን ወደ መንገድ በማውጣት ምንም ታዳሚ በሌለበት መንገድ በመኪና በማዘዋወር ቀኑን አስባለች።

" ለጤናችን ስንል ትዕይንቱን ሰው አንዲታደመው አላደረግንም ።አሁን ሀገራችንን የገጠመው ጠላትን እየተዋጉልን ያሉት ዶክተሮችና ነርሶች ናቸው ።ትልቅ ክብር ይገባቸዋል " ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ ተናግረዋል።

Via:- Tesfay genet
@Yenetube @Fikerassefa
ቻይና የኮሮና ወረርሽኝን ስፋት ደብቃለች፤ ከዓለም ጤና ድርጅት የተለየ ግንኙነት አላት በሚል ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን የቀረበባትን ወቀሳ አስተባበለች።

ወረርሽኙ በተቀሰቀሰባት የውኻን ከተማ በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቀድሞ የቻይና መንግሥት ካሳወቀው 50 በመቶ ጨምሯል።

የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን መንግሥታቸው ለዓለም ጤና ድርጅት፣ የሚመለከታቸው አገሮች እና ቀጠናዎች የወረርሽኙን ኹኔታ በግልፅነት እና በኃላፊነት ያሳውቅ እንደነበር በዛሬው ዕለት ተናግረዋል። ቻይና ከዓለም ጤና ድርጅት እጅግ የቀረበ ግንኙነት አላት በሚል ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች የሚቀርበውን ወቀሳም "ስም የማጥፋት ዘመቻ" ሲሉ ቃል-አቀባዩ አጣጥለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የወሰደቻቸው እርምጃዎች እና ስለወረርሽኙ የምታቀርባቸውን መረጃዎች በተደጋጋሚ ሲያጣጥሉ ሰንብተዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ እና የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዶሚኒክ ራብ በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።
አስራ አንድ ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት የውኻን ከተማ በኮሮና ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቀደም ሲል ቻይና ይፋ ካደረገችው በላይ ሆኖ መገኘቱ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጭሯል።

የከተማው ባለሥልጣናት በወረርሽኙ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,869 መሆኑን ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ይኸ ከቀደመው በ1,290 ሰዎች ሞት ከፍ ያለ ነው። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን ግን አገራቸው ምንም የደበቀችው ነገር የለም ሲሉ ማስተባበያ ሰጥተዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን "ወረርሽኙ በአቅም ማነስ ምክንያት አንዳንድ ሆስፒታሎች ከበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ የመረጃ ሥርዓት ጋር በሰዓቱ መገናኘት አልቻሉም ነበር።

ሆስፒታሎች ተጨናንቀው፤ የሕክምና ባለሙያዎች ሕሙማንን በመርዳት ተወጥረው ነበር። ዘግይተው የቀረቡ፤ ጭርሱን ያልቀረቡ እንዲሁም ሐሰተኛ ሪፖርቶች ነበሩ። ይሁንና ምንም መሸፋፈን አልነበረም። እንደዚያ እንዲደረግም አንፈቅድም" ሲሉ ተናግረዋል።

ቃል-አቀባዩ የቻይናን ስም ያጠፋሉ ያሏቸውን አገሮች በስም አልጠቀሱም። አገራቸው በሑባይ ግዛት ውኻን ከተማ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ወረርሽኝ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣል የተቆጣጠረችው ከግዛቷ ተሻግሮ ዓለምን ካዳረሰ በኋላ ነበር። በቻይና መንግሥት መረጃ መሠረት 4,632 ሰዎች በኮሮና ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
#አዲስ_አበባ_ዛሬ

#በአከባቢያችሁ_ያለውን የቀንድ ከብት ገበያ ፎቶ አጋሩን ጥንቃቄ የጎደለው ወይንም ጥንቃቄ የተሞላበት ከሆነም እናጋራለን።

አላማው አንዱ ከሌላው እንንዲማር ነው።
ሠመራ ዩንቨርሲቲ Covid-19 ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ሳንታይዘር እና ከእጅ ኒኪኪ ነፃ የሆነ የእግር መርገጫ ያለው የውሃ መታጠቢያ እና ሣሙና ማድረጊያ machine ሠርቶ ፤ገዝተው መጠቀም የማይችሉትን የማህበረሰብ ክፍል በመለየት፤ ለማከፋፈል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ዝግጅቱን መጨረሱን የዩንቨርስቲ የሚዲያ አካላት አሳውቀውናል።

@YeneTube @Fikerassefa