YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የታማሚዎቹ ሁኔታ:

➡️ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፣ ዕድሜ 21

➡️የጀርመንና የቤልጅዬም የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ ፣ ዕድሜ 32

➡️ከስዊድን የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ፣ ዕድሜ 76

➡️ከስዊድን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ ፣ዕድሜ 34

➡️ከጃፓን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፣ ዕድሜ 39

➡️ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች፣ ዕድሜ 61

➡️የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ካላት እየተጣራ ይገኛል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
በናይጄሪያ አንድ የህክምና ባለሙያ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በናይጄሪያ በበኮሮናቫይረስ ምክንያት በህክምና ባለሙያ ላይ የደረሰው ህልፈት በአፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን፥ ለህልፈት የተዳረገው ዶክተር በግሉ ክሊኒክ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘውን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት በመያዙ ነው ተብሏል፡፡

ዶክተሩ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ሌጎስ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ለህክምና ገብቶ የነበረ ሲሆን፥ በወቅቱ ከባድ የህመም ምልክቶች ይታዩበት ነበር ተብሏል።

የናይጄሪያ የህክምና ማህበር ዶክተር ቹጎቦ ኢመካ አርብ እለት በኮሮና ቫረስ ለህልፈት የተዳረገን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት ለቫይረሱ መጋለጡን አስታውቋል።

በከጆሮና ቫይረስ ህይወቱ ያለፈው የ51 ዓመቱ ዶክተር የአስም በሽታ እንደነበረበት የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ የቫንጋርድ ጋዜጣ ማስነበቡ ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ
@Yenetube @Fikerassefa
ቦሪስ ትራምፕን ተከትለዋል!

ከኮሮና ህመም ያገገሙት የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንደ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁሉ ሃገራቸዉ ለዓለም የጤና ድርጅት የሚያደርገዉ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ድጋፍ እንዲሳብ ጠየቁ። የዓለም የጤና ድርጅት «WHO» የኮሮና ተስቦን በተመለከተ በሚገባዉ ጊዜ ተገቢ ርምጃን አላደረገም በሚል ነዉ ብሪታንያ ለ«WHO» የሚሰጠዉ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠረዉ ድጋፍ እንዲቆም የተጠየቀዉ ሲል «ኤክስፕሬስ» የተሰኘ የድረገፅን ጨምሮ የተለያዩ የብሪታንያ ድረገፆች የዘገቡት።

ትናንት ማክሰኞ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም የዜና ድርጅት የኮሮና ወረርሽኝ በተመለከተ ከቻይና የተላለፈዉን « የተዛባ መረጃ» በማሰራጨቱ ተኅዋሲዉም በዓለም ይህን ያህል ሊስፋፋ ችሏል ፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ነገር ባልተከሰተ ነበር ሲሉ ለድርጅቱ የሚሰጡትን ድጋፍ ያቋረጡበትን ዉሳኔ ተናግረዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ በመቀጠል ዓለም አቀፉን የጤና ድርጅት የምትደግፈዉ እንጊሊዝ ድጋፍዋ እንዲቋረጥ ተጠይቋል።

አንድ የእንጊሊዝ ባለስልጣን እንደተናገሩት ፤ « በዓለማችን ተዛምቶ የሚገኘዉ የኮሮና ተኅዋሲ ያደረሰዉ ከፍተኛ እልቂት ፤ የዓለም የጤና ድርጅት «WHO» ጥልቅ ታኅድሶ እንዲያደርግ የሚጠቁም ነዉ ብለዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን ገንዘብ በጊዜያዊነት እንድታቆም ለአስተዳደራቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን እንዳስታወቁ ፤ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን ገንዘብ ለጊዜው ለማቆም መወሰኗ እንዳሳዘናቸው መግለፃቸዉ ይታወቃል። ዶክተር ቴድሮስ አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅት የረዥም ጊዜ ለጋስ ወዳጅ ሆና ቆይታለች። ወዳጅነታችን እንደዚያው ይቀጥላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN)ሁለተኛዉ ቻናል ዛሬ የሙከራ ሥርጭት ጀምሯል፡፡ ይህ ቻናል OBN Horn Of Africa በሚል ስያሜ እንዲጠራ የክልሉ መንግስት ወስኗል፡፡ የቻናሉ ዋነኛ ዓላማ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን ማቀራረብ እና ወንድማማችነት ማጠናከር ነዉ፡፡ በተለይም የምስራቅ አፍሪካን ቀጠናዊ ትስስር እዉን ለማድረግ እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ እዉን ከማድረግ አኳያ የኦሮሞ ህዝብ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንዲወጣ ማስቻል ነዉ፡፡ በመሆኑም ቻናሉ በአፋን ኦሮሞ፣ ኢንግሊዘኛ፣ አረቢኛ፣ በሶማሊኛ፣ በትግርኛ፣ በሱዋሂሊ፣ በአፋርኛ አማርኛ፣ በሲዳሚኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ዜና፣ ፕሮግራሞች እና የመዝናኛ ዝግጅትቶችን የሚያሰራጭ ይሆናል!

ቻናሉን ለማግኘት:
Satellite:Eutelsat 8WB ku-band
Down link frequency:11137MHZ
POLARIZATION:HORIZONTAL
SYMBOL RATE:27500
FEC:5/6

Via Addisu Arega
@YeneTube @FikerAssefa
ዋፋ ሲናማ ( ሰይጣን ቤት) ለአረንጓዴ ፕሮጀክት ተብሎ ሊፈርስ ነው
 
የአራዳ መሬት ልማት ማኔጅምነት ቤሮ ከዛሬ 112 አመት በፊት በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ የተሰራውን በተለምዶ ስሙ ሜጋ አምፊ ቲያትር ወይንም ሰይጣን ቤት የተባለውን ሲኒማ ቤት ለአረንጓዴ ፕሮጀከት እንደሚያፈርሰው ለሲኒማ ቤቱ በድብዳቤ አሳውቋል።

በቅርስነት የተመዘገበው ቤት መፍረስ እንደማይችል የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ማስታወቁ ይታወቃል።

በቸርቸር ጉዳና አካባቢ የሚገኘወ ይሄ ሲኒማ ቤት የአማረኛ ፊልሞችን በማሳየት የሚታወቅ ሲሆን ቀድም ከአስርት አመታት በፊት ደግሞ የሙዚቃ ኮንሰርት ይካሄድበት ነበር።

Via:- www.fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
የቻይና የህክምና ባሉሙያዎች ኢትዮጵያ ገቡ!

ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን አዲስ አበባ ገብተዋል።በውስጡ 12 ልኡካንን የያዘው የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገቡት።የህክምና ባለሙያዎቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አቀባበል አድርገውላቸዋል።እነዚህ የህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቆይታቸው ልምዳቸውን የሚያጋሩ ሲሆን፥ በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ቴክኒካል ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ያካፍላሉ ተብሏል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በግንባታው ዘረፍ በአማካሪ ድርጅትነት የተሰማሩ ተቋማት /አማካሪ መሃንዲሶች/ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዝ 2 ሚሊየን 358ሺብር ድጋፍ አበረከቱ፡፡

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአማካሪ ድርጅቶቹ የድጋፍ አስተባባሪ ኢንጂነር ተስፍዬ ወርቅነህ ድርጅቶቹን በመወከል የብር ስጦታውን ለተቋቋመው የብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል እና ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ አስረክበዋል።

Via ERA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ኤርትራውያን የሚኖሩበትን ሕፃጽ መጠለያ ዘግታ ስደተኞቹን ሌላ ቦታ ልታሰፍር ነው። የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር እዮብ አወቀ "መዝጋት ልንጀምር ነው" ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባለፈው የካቲት መጠለያውን ለመዝጋት መዘጋጀታቸውን አስታውቀው የነበረ ቢሆንም እርምጃው በአገሪቱ ኮሮና በመገኘቱ መዘግየቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አስታውሷል።

በሕንፃጽ የሚኖሩ ወደ ሌላ ጣቢያ የመዘዋወር ወይም በኢትዮጵያ በቋሚነት የመኖርና የመስራት ምርጫ አላቸው።13,022 ስደተኞች የሚኖሩበት መጠለያ የሚዘጋው አንድም የተ.መ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የሚሰጠው ገንዘብ በመቀነሱ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ የሶስት ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ሰጠ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ ለጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞቹ የሶስት ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ መስጠቱን አስታወቀ።በዚህም ባንኩ ከደንበኞቹ መሰብሰብ የሚችለውን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ወደቀጣይ ጊዜ ማስተላለፉን ነው የገለጸው።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ባንኩ መንግስት ነዋሪዎችን የቤት ችግር ለመፍታት ያወጣውን ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ላለፉት ዓመታት ከ74 ቢሊዮን ብር በላይ በአዲስ አበባ ከተማና በክልል ከተሞች ለፕሮግራም ማስፈጸሚያ ብድር መስጠቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ነዋሪዎች ከባንኮች ጋር በመቆጠብ የቤት እድለኛ በሚሆኑበት ጊዜ የሚሰጠውን በረጅም ጊዜ የሚከፈል ውል ከ107 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማቅረቡንም ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
1
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢስቶንያ ፕሬዝደንት ጋር በኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያ በስልክ ተወያዩ!

የኢስቶንያ ፕሬዝደንት ከረስቲ ካልጁሌይድ ከፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባደረጉት የስልክ ጥሪ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡የበሽታውን ስርጭትም ሆነ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ለመቆጣጠር እንዲቻል የተቀናጀ አጋርነትን መፍጠር እንደሚገባ መሪዎቹ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ ባንድ ቀን 156 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን እንዳገኘች የሀገሪቱን ጤና ሚንስቴር ጠቅሶ ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ ኬንያ ደሞ 9 አዲስ በቫይረሱ ተያዙ ሰዎች እንዳገኘች እና በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችም 11 እንደደረሱ ሲትዝን ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ 168 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂና 13 በበሽታው የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2673 ሲደርስ 196 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።596 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

ምንጭ:Daily News Egypt
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ፖሊስ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን በሽብር ወንጀል ጠርጥሬዋለሁ በማለት በዛሬው እለት ችሎት እንዳቀረበው የጋዜጠኛው ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረመድህን ለአውሎ ሚዲያ ተናግረዋል።

እንደ ጠበቃው ከሆነ ፖሊስ ጋዜጠኛውን በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወጣቶችን በማደራጀት፤ በመንግስት ላይ አመፅ እንዲነሳ በማድረግ፤ የገንዘብ ዝውውር የሽብር ስራ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመፈፀምና ለወጣቶች በመስጠት ጠርጥሬዋለሁ ብሏል።

ፍርድ ቤቱ ለሰኞ ሚያዚያ 12 ቀጠሮ ሰጥቷል። ጋዜጠኛ ያየሰው በኮሮና ቫይረስ ላይ ባሰራጨው መረጃ በሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ተጠርጥሮ የታሰረው ከ3 ሳምንታት በፊት ሲሆን በትላንትናው እለት የአራዳ ምድብ ችሎት በ25 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ወስኖ ነበር።

Via:- አውሎ ሚዲያ / ElU
@Yenetube @Fikerassefa
በስልጤ ዞን በሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የቤት ለቤት የCOVID 19 በሽታ ተጠርጣሪዎች ልየታ ስራ ሊጀመር ነው ።

የስልጤ ዞን አዲስ አበባ እና ከአዳማ ከተሞች በቅርብ እርቀት ከመገኘት ባለፈ በተለያየ ማህበራዊ ትስስሮች የተገናኙ ከተሞች ናቸው፡፡ከነዚህ ከተሞች የሚመጡ መንገደኞችን 14 ቀናት Quarantine/በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ እና ምልክት ካላሳዩ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ይገኛል። ከዚሁ ጎን ለጎን የቤት ለቤት የቅኝት ስራችንን የጤና ኤክስቴንሽ ሰራተኞች አማካኝነተ ትኩሳት እና ሳል ያለባቸውን በቀበሌ ደረጃ በመለየት ለጤና ጣቢያ ሪፖርት በመድረግ በወረዳ ደረጃ የተቋቋሙት ምላሽ ሰጪ ኮሚቴዎች መረጃ በመስጠት በሀዋሳ በተቋቋመው የደቡብ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት የተጠርጣሪ ናሙና የመላክ ስራ እንደሚሰራ ተገልፆል፡፡

ምንጭ: ስልጤ ዞን ጤና መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የሱማልያ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ዝርዝር መረጃ⬆️
@Yenetube @Fikerassefa
የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃይር ቦልሴናሮ የሀገሪቱን የጤና ሚንስትር ከስልጣን አንስተዋል። ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው ለኮሮና ቫይረስ ወረርኝ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ሁለቱ ሰዎች የገቡበት ውዝግብ መሆኑን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል ።

@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ ቢያንስ 100 ኢትዮጵያውያን በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ተባለ!

በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ100 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን መሞታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ተናገሩ።አምባሳደር ፍጹም "ቁጥሩን በትክክል ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ከምናገኛቸው መረጃዎችን እስካሁን ከ100 ያላሱ ህይወታቸውን እንዳጡ እየሰማን ነው" ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ድሬደዋ : - ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተሠጠ ዉሳኔና መመሪያ
በሀገራችን ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁ ይታወቃል::

በመሆኑም ይህንኑ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከማስፈፀም አንፃር በአስተዳደሩ ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሠጣጥ ጋር ተያይዞ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል ::

በዉሳኔዉ መሰረት

1ኛ :-ገነገ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ሙሉና ጎዶሎ በሚል በፈረቃ ይሰጥ የነበረዉ አገልግሎት ቀርቶ ሁሉም አገልግሎት መስጠት ይችላል::
2:-ከተሽከርካሪዎች ሰዉ የመጫን መጠን ጋር በተያያዘ ማንኛም የሶስት እግር ተሽከርካሪ መጫን የሚችለዉ የተሳፋሪ ሰዉ ብዛት 1ሰዉ ብቻ እንዲሆን ተወስኗል::

3ኛ:-ከዚሂ ቀደም እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ብቻ እንዲሰጥ የተወሰነዉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሰአት ዉሳኔ እንደ ፀና የሚቆይ ይሆናል::

Via:- Dire Police
@Yenetube @Fikerassefa
ወልቂጤ ከተማ ላይ የጸረ-ተህዋሲያን የኬሚካል እርጭት በዋናው የአስፓልት መንገድ ላይ ዛሬ መካሄዱን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ተመልክተናል።

@YeneTube @Fikerassefa
የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ 189 ትራክተሮችን እና 2000 ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች አስረከቡ!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው ዕለት ሻሸመኔ በሚገኘው ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ የተገጣጠሙ 189 ትራክተሮችን እና 2000 ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች አስረክበዋል፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአርሶ አደሩን የአስተራርስ ዘይቤ በማዘመን ህይወቱን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ሓላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገልፀዋል፡፡ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ እስካሁን 427 ትራክተሮችን በመገጣጠም ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን አቶ አዲሱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa