የደቡብ ጎንደር ዞን ከተሞች በሮቻቸውን ዘጉ!
እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ለመከላከል በደቡብ ጎንደር ዞን የህዝብ እንቅስቃሴ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የዞኑ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከል ኮማንድ ፖስት አስታወቋል፡፡
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

የወባ መድሃኒት ለወባ በሽታ መድሃኒትነት እንጂ ለ ኮሮና ቫይረስ ህክምና መድሃኒት መሆኑ ገና ባለመረጋገጡ ኢትዮፕያዊያን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ መንግስት አስታወቀ።የወባ መድሃኒት ለኮሮና በሽታ ህክምና ይውላል ወይንስ አይውልም ብሎ ለመፈረጅ የተለያዩ ምርመራዎች በመካሄድ ላይ በመሆኑ ህብረተሰቡ መድሃኒቱን ያለአግባብ መጠቀም እንደሌለበት የኢትዮጲያ ምግብ መድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራ ተጨማሪ 2 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች እንዳገኘች ከሻባይት ደረገጽ ዘግቧል፡፡ ጅቡቲ እና ሱማሊያ ደሞ ዛሬ የመጀመሪያዎቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሞተውባቸዋል፡፡ ኬንያ 5 በቫይረሱ ተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን ሲትዝን ቲቪ ዘግቧል፡፡
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ከአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመተባበር፤ ከ400 መቶ በላይ የሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ የኤልሻዳይ ማዕከል መውሰዱን አስታወቀ።
Via:- ELU
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- ELU
@Yenetube @Fikerassefa
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነት መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ጊዜያዊ ተገጣጣሚ ቤቶችን ሊገነባ ነው፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ጤና ዛሬ መጠነኛ መሻሻል ማሳየቱን ቃል አቀባያቸዉ አስታወቁ።
በኮቪድ 19 ክፉኛ የታመሙት ጆንሰን ካለፈዉ ዕሁድ ጀምሮ ፅኑ ሕሙማን በሚታከሙበት የሆስፒታል ክፍል በመታከም ላይ ናቸዉ።ቃል አቀባያቸዉ ዛሬ እንዳሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ሌሊቱን ሻል ብሏቸዉ ነዉ ያደሩት፤ መንፈሳቸዉም ጥሩ ነዉ።ይሁንና አሁንም ብርቱ ጥንቃቄ ከሚጠይቀዉ የሕክምና ክፍል አልወጡም።የ55 ዓመቱ ጎልማሳ በኮሮና ተሕዋሲ መለከፋቸዉ የተረጋገጠዉ ባለፈዉ የካቲት 27 ነበር።ጆንሰን በኮሮና ተሕዋሲ በመለከፍ የመጀመሪያዉ የሐያል ሐገር መሪ ናቸዉ።

#ሀዋሳ ውጤቱ አልተላከም ከአዲስ አበባ
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በትላንትናው ዕለት አንድ ግለሰብ የጤና እክል ገጥሟቸው የህክምና ዕርዳታ ለማግኘት ከአለታ ወንዶ ከተማ ወደ ሀዋሳ የሚገኝ አንድ አጠቃላይ ሆስፓታል በመምጣት ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የጤና ሁኔታቸው እየተባባሰ በመምጣቱ፣ የሚያስላቸው ፣ ፣የሰውነት የሙቀት መጠናቸው ከፍ ማለቱን ባለሙያዎች በማረጋገጣቸው ለክልሉ የኮረና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19)ሁኔታ ቅኝትና ክትትል ኮሚቴ ለማሳወቅ መደወላቸውን በመጥቀስ የኮረና ቅኝት ቡድን በፍጥነት ትናንት ደርሶ የታማሚውን ሁኔታ በማጣራት ምልክቱን በማግኘታቸው ናሙና በመውሰድ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ምርምር ተልኮ ከሌሊቱ 9 ሰዓት እንዲደርስ መደረጉ ተገልጾአል፡፡
ቢሮው አክሎ እንደገለጸው ታማሚው ለሌሎች በሽታዎች ምርመራ ማድረጋቸውና ቀድሞም ያሉባቸው ተጓዳኝ የጤና ችግሮች የልብና የኩላሊት እንዲሁም በድጋሚ ምርመራ የተረጋገጠው የሙቀት መጠናቸው ከፍ ማለትና የሚያስሉ መሆናቸው ከሚያሳዩአቸው ምልክቶች ታካሚው በኮሮና ቫይረስ (በኮቪድ-19) በሽታ ተጠርጥረው ናሙናቸው ለምርመራ ወደ ኢፒ ኤች አይ ተልኮ ታካሚው ለወረርሽኙ ተጠርጣሪ በመሆናቸው ውጤታቸው ባይገለጽም ሀዋሳ ከተማ ወደሚገኘው በተለምዶ ሳውዝ ስፕሪንግ የሚባለው ለይቶ ማቆያ በአምቡላንስ በመውሰድ ላይ እያሉ ኦክስጅኑን በገዛ እጃቸው ካቋረጡት ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
ተጠርጣሪው ግለሰብ ገና ምልክቱን በማሳየታቸው የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃው ደርሶት ናሙና በተወሰደ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ህክምና ሲያገኙበት ከነበረው ሀኪም ቤት ወደ ለይቶ ማቆያ በአምቡላንስ ኦክስጂን ተተክሎላቸው በመወሰድ ላይ እያሉ ህይወታቸው ያለፈ በመሆኑ ቢሮው የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ለከቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን በመመኘት እየገለጸ ግለሰቡ ህይወታቸው ያለፈው በኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ_19) መሆኑንና አለመሆኑን የምርመራው ውጤታቸው ሲደርስ የሚረጋገጥና የመገለጽ መሆኑ እንዲታወቅና ተረጋግጦ ለህብረተሰቡ ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ ማንኛውም አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ቢሮው ያሳስባል።
በደቡብ/ ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት ጤና ቢሮ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዋ ሰለባ የሆኑት የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት ህልፈታቸው ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ እስከ ቀብራቸው የነበሩትን ክስተቶች "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተከታትላለች፡፡ ለዝርዝር ዘገባ እና ፎቶዎች መስፈንጠሪያውን ይንኩ ⬇️
https://t.co/Mecrcpz9dI
https://t.co/Mecrcpz9dI
ዶናልድ ትራምፕ ለዶክተር ቴድሮስ ምላሽ ሰጡ!
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ላይ የከፈቱትን የቃላት ጦርነት ቀጥለውበታል።ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት "ጤናን ወደ ፖለቲካ አንጠምዝዘው" ማለታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ዋይት ሐውስ ውስጥ በሚካሄደው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዶክተር ቴድሮስ "ፖለቲካውን ትተን ወረርሽኙን ለማቆም ካልሰራን ሬሳ ሳጥን ማብዛት ነው" ስለማለታቸው ምላሽ የሰጡት ትራምፕ…"ምን ማለታቸው ነው ተጨማሪ ሬሳ ሳጥን ሲሉ…መጀመርያ እሱ (ዶ/ር ቴድሮስ) አገለግለዋለሁ ለሚለው ሕዝብ ኃላፊነቱን መወጣት ነበረበት።"
"ሁሉም ሥራው ቻይናን መሠረት ያደረገ ነው፤ ድንበር አትዝጉ፣ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም ሲል ነበረ፤ ድንበር አትዝጋ ቢለኝም እኔ ግን ዘግቻለሁ…(ከዓለም ጤና ድርጅት በተቃራኒው ስለሄድን ነው ሰው ማዳን የቻልነው)" ብለዋል ትራምፕ። ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያዋጡትን 400 ሚሊዮን ዶላር፣ ቻይና ከምትሰጠው 40 ሚሊዮን ዶላር ካወዳደሩ በኋላ ይህንን ፈንድ የመስጠቱን ጉዳይ እንደሚያጤኑት ተናግረዋል።በተመሳሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፖምፔዎ "ለዓለም ጤና ድርጅት የምንሰጠውን ገንዘብ እናጤነዋለን" ብለዋል ዛሬ፡፡
Via BBC

በአሜሪካ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 60,000 ብቻ ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት የአገሪቱ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ተናገሩ።
ዶ/ር ፋውቺ በወረርሽኙ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 200 ሺህ ድረስ እንደሚሆን ተንብየው ነበር።አሁን ይህንን ግምታቸውን ሊያስቀንሳቸው የቻለው በአሜሪካ ዜጎች አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት ማምጣቱን በመታየቱ ነው ብለዋል።
Via:- BBC / Getty Image

ማሳሰቢያ - ሀዋሳ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ የኮሮና ቫይረስን ታሳቢ በማድረግ ከግብይት ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ማሻሻያዎች ለማድረግ ተገዷል።
በዚህም መምሪያው በከተማዋ በሚገኘው አሮጌው ገበያ ያለውን የግብይት ስርዓትን አስመልክቶ ባደረገው ምልከታ በስፍራው ያለው ንግድ ቀድሞ ከነበረበት የሰዎች መሰብሰብ የተላቀቀ ሆኖ አልተገኘም።
ስለሆነም ካለብን የኮሮና ቫይረስ ስጋት አንፃር መምሪያው በገበያ ስፍራው ሊኖር ይገባል ያለውን አሰራር አስመልክቶ እንደሚከተለው እንዲደራጅ ተገዷል።
በዚህም መሰረት ላተወሰኑ ቀናት
1. አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም እሸት በቆሎ በአሮጌው አየር ማረፊያ እንዲገበያይ፣ በተጨማሪም ከሱቅ ውጪ የሚሸጡ አልባሳት በሙሉ በአሮጌው አየር ማረፊያ ለሽያጭ እንዲቀርቡ ተወስኗል፡፡
2. ከሰል፣ እንጨትና የእንጨት ውጤቶችን በሙሉ በኮረም ሜዳ እንዲገበያዩ፣
3.ጥራጥሬ፣ ቡና እና የሸክላ ውጤቶች በአሮጌው ገበያ /በቦታው ሆኖ/ ተበታትኖ እንዲገበያዩ ተወስኗል፡፡
መምሪያው የበሽታው አሳሳቢነትን እየቀነሰ ሲመጣ በአዲሱ የቦታ ለውጥ የሄዱ ነጋዴዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው መስራት እንደሚችሉ ይገልጻል።
ሆኖም የበሽታው ስጋት እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ሸቀጦችን ወደየህብረተሰቡ የሚያጓጉዝበትን ሁኔታ ከወዲሁ ማሰብ እንደሚጠበቅባቸው መምሪያው አሳስቧል።
ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም መምሪያው ገልጿል ።
ምንጭ:- ከተማ አስተዳደር
@Yenetube @FikerAssefa

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንትና የወቅት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የአለም አቀፉን ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር ዶከተር ቴድሮስ አድሃኖምን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም የኮሮናቫይረስ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ ማውገዛቸውን ተከትሎ ነው ራማፎሳ መግለጫውን የሰጡት።
በትናንትናው እለት ባወጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረትም ሆነ እሳቸው ከዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ጎን እንደሚቆሙና የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር አለም አቀፋዊ ህብረት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
Via:- BBC - Getty Images

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በ2ኛው ዙር ያመረተውን የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር ለጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ማስረከብን ከዩንቨርስቲው ገፅ ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ባለፈው ሳምንት አርብ ከ1 ሚሊዮን በታች ነበር፤ ትናንትና 1.5 ሚሊዮን ነበር፡፡ ዛሬ አርብ ቁጥሩ 1.6 ሚሊዮን ደርሷል፡፡
ይህም ማለት በሳምንት ብቻ 500ሺ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል ማለት ነው፡፡
እስካሁን በቫይረሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቻቸው የተያዙባቸው አገራት የሚከተሉት ናቸው፡፡
አሜሪካ (465ሺህ 329)፣ ስፔን (153ሺህ 222)፣ ጣሊያን (143ሺህ 626)፣ ፈረንሳይ (118ሺህ 235)፣ ጀርመን (118ሺህ 235)፣ ቻይና (82ሺህ 835)፣ ኢራን (66ሺህ 220)፣ ዩናይትድ ኪንግደም (65ሺህ 872) ቻይና ምንም እንኳ የቫይረሱ መነሻ ብትሆንም 77ሺ የሚልቅ ሕዝቧ አገግሟል፡፡
ይህ ቁጥር ሲታይ መዘንጋት የሌለበት ነገር ቢኖር ዜጎቻቸውን በብዙ ቁጥር የመመርመር አቅም የሌላቸው አገሮች በዚህ የአሐዝ ዝርዝር አለመካተታቸውን ነው፡፡
ይህ ከግምት ውስጥ ሲገባ በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ምናልባትም ከዚህ በብዙ ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ነው፡፡
Via:- BBC

ቻይና ውሻን እንደሚበላ ከብት ሳይሆን እንደቤት እንሰሳ የሚያይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅታለች
ዉሻ እንደከብት ታርዶ የሚበላባት ቻይና አዲስ ህግ እያረቀቀች ሲሆን ይሄም ህዝቦቿ ውሻን እንደቤት እንሰሳ እንዲያዩ እንጂ አርደው ለምግብነት እንዳያውሏቸው ያዛል ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
Via Tesfaye Getnet
@YeneTube @Fikerassefa
ዉሻ እንደከብት ታርዶ የሚበላባት ቻይና አዲስ ህግ እያረቀቀች ሲሆን ይሄም ህዝቦቿ ውሻን እንደቤት እንሰሳ እንዲያዩ እንጂ አርደው ለምግብነት እንዳያውሏቸው ያዛል ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
Via Tesfaye Getnet
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከሰትን ምክንያት በማድረግ እየተገነቡ ያሉ ህገወጥ ቤቶችን የማፍረሱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት መንግስት በሀገሪቱ የተፈጠረውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከል ላይ ትኩረት ማድረጉን እንደ ክፍተት በመጠቀም በቦሌ ክፍለ ከተማ በሌሊት ህገ ወጥ ግንባታ ያከናወኑ ግለሰቦች ቤት እንዲፈርስ ተደርጓል። በቀጣይም ለእንደዚህ አይነት ተግባሮች ከተማ አስተዳደሩም ሆነ ፖሊስ ኮሚሽኑ ምንም አይነት ምህረት አያደርግም። በዚህ ጉዳይም ከማንም ጋር ለድርድር አይቀርብም።
ቤቶቹ ዛሬ ባይሆንም ነገ ከነገ ወዲያ መፍረሳቸው አይቀርም ነበር ያሉት ኮማንደር ፋሲካ ከዚህ በኋላም አንዳንድ ችግሮች መከሰታቸውን አንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ህገ ወጥ ግንባታዎችን ለማስፋፋት የሚያስቡ ካሉ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል።
Via EPA