ደቡብ አፍሪካ ከ47 ሺህ በላይ ሰዎችን ብትመረምርም የወረርሽኙን ሙሉ ምስል ለማወቅ የበለጠ ምርመራ ያስፈልጋል አለች!
በአገሪቱ ውስጥ እየተዛመተ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስትር አስታወቁ።ሚኒስትሩ ዝዌሊ ምክሂዜ እንደገለፁት ደቡብ አፍሪካ 47ሺ541 በኮሮና የተጠረጠሩ ሰዎችን የመረመረች ቢሆንም የወረርሽኙ መዛመት አለመዛመት ሙሉ ምስሉን ለማግኘት የበለጠ መሰራት አለበት ብለዋል።ደቡብ አፍሪካ ካሏት ቋሚ መመርመሪያዎች በተጨማሪ 67 ተንቀሳቃሽ መመርመሪያ ተሽከርካሪዎችንም መድባለች።ግለሰቦች ምልክቱ ታይቶባቸው ወይም ታመው ወደ ሆስፒታሎች ከመምጣታቸው በፊትም በየአካባቢያቸው በተመርመረው ያለውን ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

በእንጅባራ ከተማ የኮሮና በቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በንፁህ ውሃ አቅርቦት እጥረት ማህበረሰቡ ቅሬታውን እየገለጸ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ ውሃና አፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበያው አልማው እንደተናገሩት በከተማው ያለውን የውሃ እጥረቱን በተወሰነ ደረጃም ለማስታገስ በውሃ ቦቲ ከሱታና ምንጭ በመቅዳት በጣም የተቸገሩትን ከዋናው ውሃ በ11 ቀናት ወረፍ የማይደርስባቸውን፣ የውሃ መስመር የሌላቸውን፣ የሰው ቅርርብ የሚበዛባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እና መሰል የከፍ ችግር ያለባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ለከታታይ ቀናት አንደሚስራ ተናግረዎል። ዋናው የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በየ11 ቀናቱ ወረፍውን ጠብቆ በፍትሃዊ ለሁሉም መስመሮች ለማዳረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል።
Via Injibara communication

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የግጭቱ መንስኤ ትናንት አንድ ግለሰብ ባልታወቁ ሰዎች መደገሉን ተከትሎ በግልገል በለስ ከተማ ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ ወጣቶች መቀስቀሱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ ሕይወት ማለፉንም ጠቁመዋል፡፡ከ3፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደነበረም ነዋሪቹ አመልክተዋል፡፡ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የግልገል በለስ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ ቀስት የያዙ ወጣቶች ወደ ከተማው በመግባት በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው የከተማይቱ ነዋሪው እንሚሉትም ትናንት በግልገል በለስ አካባቢ 30 የሚደርሱ ከብቶች ተሰርቀው የነበረ ሲሆን ከብቶቹን ለመመለስም ነዋሪዎች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን 14 የሚሆኑትን መመለስ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሸህ የተባሉ ግለሰብ መገደላቸውን ጠቁመዋል፡፡የክልል ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሲተኩስ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
የመተከል ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፐክተር ጌታቸው ጅሬኛ በበኩላቸው በከተማው ዛሬ ጠዋት በተፈጠረው ግጭት አለመረጋጋት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የሰው ሕይወት ማለፉንም ያረጋገጡ ሲሆን፤ ዛሬ በነበረው ግጭት አንድ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ ላይም ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ የከተማ ፖሊስ ጣቢያ ጭምር በድንጋይ መደብደቡን እና አንድ የፖሊስ መኪናም በወጣቶች በተወረወሩ ድንጋይ መሰባበሩን አክለዋል፡፡
የመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማን ጨምሮ በስሩ በሚገኙ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት በሚቀሰቀሱ ግጭቶች በርካታ የሰው ሕይወት ማለፉን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ በዚሁ አካባቢ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ሥራ ከጀመረበት ሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ወዲህ ከአምስት ጊዜ በላይ በተቀሰቀሱ ግጭቶች ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡
Via DW

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከአሁን በፊት ይሰጥ የነበረውን ማንኛውም የውጭ አገልግሎትና የቅዳሜ ግማሽ ቀን አገልግሎት ከመጋቢት 25/2012ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ያቋረጠ መሆኑን ገልጿል።
-ኤጀንሲው
@YeneTube @FikerAssefa
-ኤጀንሲው
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
ምንጭ:የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ውስጥ ዛሬ የ6 አመት ልጅ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ መሞቱን ተከትሎ በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4 ደርሷል። በቫይረሱ የተጠቁት ደግሞ 122 መሆናቸውን የሀገሪቱን ጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ያሉትን ፈረንሳያዊ ዶክተሮች ድሮግባና ኤቶ አወገዙ!
ሁለት የፈረንሳይ ዶክተሮች በቴሌቪዥን ላይ በነበረ ውይይት የኮሮናቫይረስ የሙከራ ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገዱ ሲሆን፤ ታዋቂዎቹ አፍሪካውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ዲዲየር ድሮግባና ሳሙኤል ኤቶም የሰላ ትችታቸውን ሰንዝረዋል።
"አፍሪካ መሞከሪያ ላብራቶሪ አይደለችም፤ አፍሪካውያንም የላብራቶሪ አይጦች አይደለንም" በማለት ድሮግባ በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
የቀድሞው የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ በበኩሉ ዶክተሮቹን "ነፍሰ ገዳይ" ብሏቸዋል።
ከቀናት በፊት በፈረንሳዩ የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀረቡት ዶክተር ጂን ፖል ሚራና ዶክተር ካሚል ሎችት ውይይትንም ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው አጋርተውታል።
ዶክተሮቹ እንዳሉት ኤድስ ጥናቱ የተደረገው በአብዛኛው አፍሪካ ውስጥ ከመሆኑ አንፃር የኮቪድ-19 ክትባትም ሙከራ በአህጉሪቱ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
"ይህንን ሙከራ ማድረግ ያለብን አፍሪካ አይደለምን? የፊት ጭምብሎች በሌለበት፣ ህክምና በላደገበትና፣ መተንፈስ ቢያዳግት እንኳን ትንፋሽ መመለስ የሚያስችል መሳሪያ በሌለበት መሆን አይገባውም? ልክ እንደ ኤድስ በአፍሪካውያን የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች ጥናት እንደተሞከረባቸው።
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa

በኮሮና ስጋት የኬንያ መንግሥት ያስተላለፈውን እገዳ በማስፈጸም ላይ ያለው ፖሊስ አላስፈላጊ ሀይል እየተጠቀመ ነው መባሉ ተሰምቷል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ያስተላለፈውን የሰአት እላፊ እገዳ ተላልፈው በተገኙ ሰዎች ላይ የጸጥታ ሀይሎች ተገቢ ያሉትን እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
ፖሊስ ምንም አይነት ልዩነት ሳያደርግ መንገድ ላይ ያገኘውን ሁሉ ይደበድባል፤ ያንገላታል ያሉት በስፍራው የነበሩት የአይን እማኞች ናቸው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ የተላለፈውን ሰአት እላፊና ጥብቅ መመሪያ ለማስከበር ፖሊስ ወደ ላይ ይተኩሳል፤ አስለቃሽ ጋዝም ይጠቀማል ብለዋል፡፡

"ኮሮና ቢራ" በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርት አቁሚያለሁ አለ!
የሜክሲኮ ትልቁ ቢራ አምራች ኩባንያ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተወዳጁን “ኮሮና ቢራ” ማምረት ማቆሙን አስታወቀ።የአጋጣሚ ነገር ሆኖ ከኮቪድ-19 በሽታ ጋር ስሙ በመግጠሙ የዓለም መሳቂያ መሳለቂያ፤ የቀልድ ምንጭና ባለዝና መሆን የቻለው ኮሮና ቢራ ስሙ በማህበራዊ ሚዲያ ሲያነጋግር ቆይቷል።ታዲያ ብዙዎች እንደገመቱት ስሙ ከቫይረሱ ጋር በመግጠሙ የገበያ ድርቅ መትቶት አይደለም ምርት እያቆመ ያለው።አንዳንድ አሉባልተኞች ቢራው በስሙ ምክንያት በአሜሪካ የነበረው ገበያ አፈር ድሜ በልቷል ሲሉ ነበር፤ ኩባንያው ግን ምንም አይነት የገበያ እጦት አልገጠመኝም ሲል ሐሜቱን አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚያዝያ 01 - 03 2012 የቴክኖሎጂ አቅም ማስፋፊያ ስራ ስለሚሰራ ሁሉም ቅርንጫፎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቀ።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በድሬዳዋ በቀጣይ 2 ሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ ግለሰቦች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተባለ::
በድሬዳዋ የኮሮና ቫይረስን የተመለከተ መግለጫ ለጋዜጠኞች ዛሬ ተሰጥቷል::
በድሬዳዋ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መግለጫውን የሰጡት በዛሬው እለት ስራቸውን የጀመሩት አዲሷ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ናቸው::
ኃላፊዋ በመግለጫው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-
➡️ በድሬዳዋ አስተዳደር እስከዛሬ ድረስ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ከታየባቸው 9 ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል::
➡️ ከሁለቱም ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ እንዳላቸው የታወቀ 19 ግለሰቦች የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ወይም በተለምዶ ፈርንሳይ በሚባለው ሆስፒታል ተለይተው እንዲቆዩ ተደርጏል::
➡️ ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ተጨማሪ ግለሰቦችን በመለየት እና ወደ ለይቶ ማቆያ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል::
➡️ በተጨማሪም ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ ሊኖረኝ ይችላል ብለው የሚገምቱ ወይም የሚጠራጠሩ ግለሰቦች ለራሳቸውም ሆነ ለህብረተሰቡ ደህንነት ሲሉ ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ በመሆን ማህበረሰባዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል::
➡️ በድሬዳዋ አስተዳደር በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ በቫይረሱ የሚያዙ ግለሰቦች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ማሳያዎች አሉ::በመሆኑም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ በቀጣይ 2 ሳምንታት ከቤት ባለመውጣት እና እራሱን ከሰዎች ንክኪ በማራቅ እንዲሁም አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን በማድረግ በሽታውን መከላከል ይገባዋል::
Via Dire Mass Media

የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲምን የፍትህ እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾመ፡፡
የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በትላንትናው እለት ከክልሉ የፍትህና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊነታቸው ባነሳቸው አቶ አብዲ አድል ሀሰን ምትክ አዲስ ኃላፊ መሾሙ ታውቋል፡፡በዛሬው እለት ቢሮውን እንዲመሩ የተሾሙት ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም አሁን በእስር ላይ ከሚገኙት የቀድሞ የክልሉ ርእሰ መስተዳድድር አቶ አብዲ ኢሌ በፊት የነበሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱላሂ ሀሰን የልማት ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ከመስራታቸውም በላይ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች የሰሩም ናቸው ተብሏል፡፡ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም ዶክትሬታቸውን በፐብሊክ ፖሊሲ ካናዳ ከሚገኘው ካርተልን ዩኒቨርስቲ የያዙም መሆናቸው ታውቋል፡፡
Via Sheger Times Magazine

ምን አዲስ ደቡብ ክልል?
-#በሚቀጥለው ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ላይ ኮሮና ቫይረስ መመርመር የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱ የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዊት አስታውቋል።
- በቀጣይም በአርባምንጭ : በሚዛን አማን : በሆሳህና ምርመራ ማድረግ እንዲችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተገልፃል
- በክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ለይቶ ማቆያ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
- ሰፋፊ ቦታዎች ለምሳሌ ስታዲየምን የመሳሰሉ ቦታዎችን ወደ ህክምና ቦታዎች ለመቀየር ስራዎች እየተሰሩ ነው።
- በሃዋሳ ከተማ የሆቴል ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ያለ ምንም ደሞዝ መሰናበታቸን ጎዳና እንድንወጣ ሆነናል ሲሉ ለደቡብ ቴሌቭዥን ተናግረዋል።
- አርባምንጭ አየር ማረፊያ ተጓዦች ወደ ከተማ ከመግባታቸው በፊት የሙቀት መለኪያ እያተደረገ እንደሚገኝ ሰምተናል።
Via:- SRT
@Yenetube @Fikerassef

ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎች!
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሳይመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ሳያገኙ የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት በህገ ወጥ መልኩ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ (Hand sanitizers) ነው በማለት አምርተው ገበያ ላይ እያቀረቡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠየቀ።
ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት የምግብና መድኃኒት አስመጪዎች፣ አከፋፋዮችና አምራች ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እንደሚሰጥ ይታወቃል።በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በህጋዊ መንገድ በስፋት ተመርተው ገበያ ላይ እንዲቀርቡ ጊዜያዊ ፍቃድ በመስጠት ላይ ይገኛል።
ይሁን እንጅ በተደረገው የገበያ ጥናትና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሳይመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ሳያገኙ የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት በህገ ወጥ መልኩ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ (Hand sanitizers) አምርተው ገበያ ላይ እያቀረቡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያላገኙ እንዲሁም ጥራታቸውና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ በመሆናቸው ከገበያ እንዲሰበሰቡና ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል።
1.Mela Sanitizer
2.Narobi Sanitizer
3.Habesha Sanitizer
4.FOM Sanitizer
5.GST Sanitizer
6.Silva Sanitizer
7.Yero Hand Sanitizer
8.Adey Hand Sanitizer
9.Abyssinia Hand Sanitizer
10.TAFF አልኮል
መሆናቸውን በማሳወቅ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በማድረግ መሰል ምርቶች ሲያገኝ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅም ጠይቋል።
Via FBC

በሀዋሳ ከተማ የመግቢያና መውጫ በሮች ላይ የሙቀት ልኬት ምርመራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ። በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና በጤና ባለሙያዎች እማካኝነት እየተካሄደ የሚገኘው የሙቀት ልኬት ምርመራ ከበሽታው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምልክቶችን ለመለየት እንደሚያስችል ታምኖበታል። የከተማው አስተዳደር በበኩሉ ወረርሽኙን ለመከላከል ያስችላል ያለላቸውን ተጨማሪ ክልከላዎች መጣሉን አስታውቋል።
Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
የአዳማ ባለሃብቶች ለኮሮና መከላከል ስራ የሚውል 19 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!
የአዳማ ከተማ ባለሃብቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተጀመረውን ስራ ለማጠናከር ከ19 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማዋ ባለሀብቶች ከህዝብና ከሀገር በላይ ትርፍ የለም በማለት በወረርሽኙ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጉ ነው ።
Via ENA/OBN

#ፈረንሳይ
በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 1,120 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ከነዚህ መካከል 532 የሚሆኑት በ(Nursing Home) የነበሩ ፣ ከዚህ በፊት ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። እንዲሁም 5,233 ሰዎች በዛሬው ዕለት ብቻ በቫይረሱ ተይዘዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 1,120 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ከነዚህ መካከል 532 የሚሆኑት በ(Nursing Home) የነበሩ ፣ ከዚህ በፊት ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። እንዲሁም 5,233 ሰዎች በዛሬው ዕለት ብቻ በቫይረሱ ተይዘዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
Audio
በቸልተኝነት ምክኒያት እኔ ባመጣሁት ኮረናቫይረስ በኩላሊት እጥበት ሕክምና ላይ የነበረችውን ባለቤቴን ወሮ ሃና ገዛኢን ላሲዛት ችያለሁ ሲሉ አቶ ነጋሲ ክብሮም የተባሉ በጣሊያን ሚላን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። አቶ ክብሮም የሕንፃ እቃዎች መሸጫ ባለቤት በመሆናቸው ሱቃቸውን ከፍተው ሲሸጡ እንደነበር ገልፀው ቀን ከገበያተኛ የተላለፈባቸው ኮረናቫይረስ ማታ ቤት ሲገቡ ደግሞ ባለቤታቸውን ማስያዛቸውን ገልፀዋል።
Via:- VOA
@Yenetube @FikerAssefa
Via:- VOA
@Yenetube @FikerAssefa
በአሜሪካ በ24 አሰት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ 1,300 ሰዎች ሲሞቱ 30,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
በኮሮና ቫይረስ ሰርጭት ትልቅ ስጋት የገባችው አሜሪካ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 1,300ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተውባታል ። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 7,152ደርሷል።
በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 277,953 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 30,000 ሰዎች ኬዝ የተመዘገበው በ24 ሰዓት ነው።
Via:- Tesfay Getenet

በኢኳዶር በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ሬሳ ቀባሪ በማጣት በመንገድ ላይ እየተከመሩ መሆኑ ተነገረ
በደቡብ አሜሪካዊቷ ኢኳዶር በተለይም ጓያኩዊል በተባለችው የወደብ ከተማዋ በኮሮና ቫይረስ ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ሬሳ ተቀብሎ የሚቀብርላቸው አካል እያጡ መሆኑን ገልፀው በዚህ ምክንያት ሬሳ መንገድ ላይ እየተከማቸ መሆኑን ገልፀዋል።
አንድ የሟች ስምና አድራሻ የገለፀ ሰው እንዲህ በማለት በቲዊተር ገፁ ፅፏል "በእግዚአብሔር ስም እርዱኝ ።ሬሳው እዚህ ሰነበተ ። ምን ላርግ? ማንም ወስዶ ሚቀብረው አልተገኝም ።እባካቹ ልለምናቹ ወስደን እንቅበረው።
ሌላ ሰው ደግሞ እንዲህ ብሎ ፅፏል " እዚህ በቫይረሱ የሞተ የሶስት ቀን እሬሳ አለ ።እባካቹ አድራሻዬ ይኸው ኑ እና እንቅበረው በማለት ፅፏል።
ኢኳዶር በቫይረሱ 145 ሰው መሞቱን 3,330 ሰው ደግሞ መያዙን ብትገልፅም ቁጥሩ ተቀባይነት የለውም ከእዚ ይበልጣል በማለት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሌኒን ሞርኖ መናገራቸው ይታወሳል።
Via:- Tesfay Getnet