YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ስለ ኮሮና ቫይረስ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች

📌ነጭ ሽንኩርት ይከላከለዋል

📌በየ15 ደቂቃ ውሃ መጠጣት ይከላከለዋል

📌ሙቀትና ቅዝቃዜ ይከላከለዋል

እኚን የመሳሰሉ ያልተረጋገጡ ወሬዎች አምኖ እኚን ብቻ መጠቀም የባስ ለቫይረሱ ያጋልጣል።

#ኮሮና_ቫይረሱን ለመከላከል | እጅ መታጠብ | ሰላም አለመባበል | ባልታጠበ እጆህ አይን እና አፊንጫን መነካካት። እኚን በከተገበርን ቫይረሱን መከላከል እንችላለን።

@Yenetube @Fikerassefa
ማር፣ፌጦ፣ጤና አዳም፣ነጭ ሽንኩርት አንድ ላይ ፈጭታቹ አንድ ማንኪያ ዋጡ የሚል መልክት ሰዉን እያሸበረ ይገኛል።

መልክቱ ከአባቶች የተላከ ነው የሚሉት ነገር አለ። ነገር ግን የተኛቹ አባቶች እንደተላከ ግልፅ የወጣ ነገር የለም።

የተባለውን መተግበር ክፋት የለው
ለምን ? ከተባለ የተጠቀሱት ለሰውነታችን ገንቢ እንጂ ጎጂ አይደለም ነገር ግን እኚ መዳኒት ናቸው የተባሉት ንጥረ ነገሮች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

#አትሸወዱ #አትሸበሩ

ዛሬ የሀይማኖት አባቶች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በጥሞና ጤና ሚኒስትር የሚለውን ተከታተሉ ማለታቸው ይታወሳል ስለዚህም አባቶቻችን ያሉትን ጤና ሚንስትርን እንከታተል።

ሆኖም ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል #እጅን_መታጠብ አንደኛው እና #ዋነኛው_መንገድ ነው።


#እጃችሁን_ታጠቡ
#እጃችሁን_ታጠቡ
#እጃችሁን_ታጠቡ
@Yenetube @Fikerassefa
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ምክንያት የእጩ ተመራቂዎች ምርቃት አራዝሟል!!

@Yenetube @Fikerassefa
መአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ለኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ይሄንን ፈጭተችሁ በጥብጣችሁ ቀላቅላች ጠጡ ብለዋል የሚለው እንኳን ከገዳም ከገዳም ሰፈር አይወጣም ብሏል መዐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት።

@Yenetube @FikerAssefa
ኮሮናቫይረስ ንምክልኻሉ፥

#Share #Share
@Yenetube
ሚሽን ብራይት ኢትዮጵያ የሚመሰገን ተግባር ❗️
በመገናኛ አከባቢ የሚሽን ብራይት ኢትዮጵያን በጎ ፍቃደኞች እጅ በማሳታጠብ ላይ ናቸው።

እናመሰግናለን!!
@Yenetube @Fikerassefa
የተለያዩ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ትላንት የላከውን መግለጫ ያልተገበሩ ዩንቨርስቲዎች እንዳሉ መልክት እየደረሰን ይገኛል።

ዩንቨርስቲዎች የፊት ለፊት ትምህርት እንዲቀር ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ስላሳሰበ እንድትተገብሩት እንመክራለን።

ይህ ለተማሪዉ ደንነት አስፈላጊ ነው!!
@Yenetube @Fikerassefa
በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል!

በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200 ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት እንደሚችል ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

Via Mayor Office of Addis Ababa
@Yenetube @Fikerassefa
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልክት አስተላልፏል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ኮሮና ካለበት ርቆ ለመገኘት ይህን ተግብሩ

1. አጭር ርቀት ጉዞዎችን በእግር መጏዝ

2. የተጨናነቁ ሰአታትን አሳልፎ መንቀሳቀስ

3. ማንኛውንም ስብሰባ ለጊዜው ብናቆም

4. ከሊፍት ይልቅ ደረጃን መጠቀም

5. የበር እጀታዎችንና የደረጃ ድጋፎችን በባዶ እጅ አለመተሻሸት

#ሼር_Share_
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮናን ለማሸነፍ-

1. የእጅና የእጅ ስልክ ንፅህናን መጠበቅ

2. ከሌሎች ጋር ካለን ቀጥተኛ ንክኪና የትንፋሽ ቅርርብ መቆጠብ

3. ለመከላከል ስለሚጠቅም ገለል ራቅ ብሎ መቆየት

4. ፍራቻን አለመንዛት: ከስግብግብነት መታቀብ

5. ለሌሎች ምሳሌ መሆን: በርቱ

@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አለመኖሩ ተገለፀ።

እንዲሁም አምስቱ ታማሚዎች ጥሩ ጤና ላይ እንደሚገኙ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው ከተባሉት 113 ግለሰቦች መካከል 74ቱ ነፃ መሆናቸውን ታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተባለ

ቴአትርና ሲኒማ ቤቶቹ እንዲዘጉ ትዕዛዝ የተላለፈው ትናንት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ሁሉም ትያትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች ዝግ መሆናቸው ይታወቃል። በትናንትናው እለት ሴንቸሪ ሲኒማ ለተጠቃሚዎቹ በቴሌግራም ገፁ ላይ ባስተላለፈው መልዕክትም ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ለቀጣይ 15 ቀናት ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።

- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም መናሃሪያዎች የውሃ ማጠራቀሚያዎችን እያሰራጨ መሆኑን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ በሚገኙ ሁሉም መናሃሪያ ላይ የውሃ ማጠራቀሚያ ማጠራቀሚያ ታንከር እና የአልኮል ቁሳቁሶች ተደራሽ ለማድግ እየተሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

ቃሊቲን ጨምሮ በመዲናዋ ባሉት መናሃሪያዎች የሚከፋፈሉ አስር ሮቶዎች ተገዝተው የማከፋፈል ስራ በዛሬው እለት መጀመሩን ሰምተናል፡፡

ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የሚጓዙ ሃገር አቋራጭ ተሸከራካሪዎች ላይ ባይረሱን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶች በየመናሃኒያ ጣቢያው ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ሮቶዎቹን የመግዛት ስራ ተጠናቆ ወደ መናሃሪያዎቹ የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን ሰምተናል፡፡

በትራንስፖርት ባስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለጣቢያችን እንደነገሩን ከሁሉም በላይ በሽታውን ለመከላከል በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የተለያዩ የመከላከያ ስራዎች በመሰራት ላይ እንገኛለን ብለውናል፡፡

አገር አቋራጭ ተሸከርካራች ላይ ህዝቡ ለመሳፈር ወደየመናሃሪያው ሲመጣ እጁን ታጥቦ እንዲሳፈር በማሰብ የተለያዩ የጥንቃቄ ቁሳቁሶች ወደ ስፍራው እየተላኩ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ተቋሙ በምክትል ዋና ዳሬክተር የሚመራና ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቋሞ ወደ ስራ እንደተገባና በቀጣይም በትራንስፖርቱ ላይ ተግባዊ የሚደረጉ የመከላከያ ስራዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ሰምተናል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa