YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለሁሉም ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስቸኳይ መልዕክት

ጉዳዩ፡- ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎችን ይመለከታል፡፡


መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ለሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመጋቢት 8/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ሳምንታት ቀጣይ አቅጣጫ እስከሚሰጥ ደረስ በክፍል ውስጥ የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎች እንዲቋረጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፤ ይህን መነሻ በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከተለውን ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ስጋት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሀገራችንም እስከ አሁን አምስት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ተረጋግጦ ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሆነና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመግታት መንግስት መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅትም በሽታው ወረርሽኝ መሆኑን ካወጀበት ጊዜ አንስቶ ለጥንቃቄ ይጠቅማሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መፍትሄዎች መካከል የሰዎች መሰባሰብን የሚሹ ጉዳዮችን ማስቀረት ይገኝበታል፡፡

ይህን መሰረት በማድረግ ለኮረና ቫይረሱ መስፋፋት ጥንቃቄ ሲባል የግል ከፍተኛ ትምህርት የመደበኛ፣ የማታ እንዲሁም የቅዳሜ እና እሁድ ትምህርትና ስልጠና ለሁለት ሳምንታት እንዲቋረጥ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

በመሆኑም የሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ አካዳሚክ እና የአስተዳራዊ ሰራተኞች በሙሉ ለ2 ሳምንታት በየቤታቸው እንዲቆዩ እየገለጽን በቆይታቸው ባሉበት ሆነው ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መመሪያዎችን ተከትለው ጥንቃቄ በማድረግ በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ ለ2 ሳምንታት የሚቆዩ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ፊት ለፊትና በክፍል የሚሰጡ ትምህርቶችን በማስቀረት ለተማሪዎች handout, reference books, online, soft copy materials ወ.ዘ.ተ በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግላቸዉ/ በቤታቸው ሆነዉ እንዲያነቡ ይደረግ፣ ለዚህም የግል ተቋማቱ ባለቤቶች፤ ኃላፊዎች እና መምህራን በኢሜይል፣ በቴሌግራም እና በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች የመማር ማስተማሩን ስራ ሊተኩ የሚችሉ ድጋፎችን እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም መልዕክቱ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በኩል ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በኢሜል አድራሻ የተላከ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የግል ዩንቨርስቲን በተመለከተ

የኮረና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ በሁሉም ግል እና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሁለት ሳምንት በክፍል ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት ስልጠና እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

@YeneTube @Fikerassefa
ስለ ኮሮና ቫይረስ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች

📌ነጭ ሽንኩርት ይከላከለዋል

📌በየ15 ደቂቃ ውሃ መጠጣት ይከላከለዋል

📌ሙቀትና ቅዝቃዜ ይከላከለዋል

እኚን የመሳሰሉ ያልተረጋገጡ ወሬዎች አምኖ እኚን ብቻ መጠቀም የባስ ለቫይረሱ ያጋልጣል።

#ኮሮና_ቫይረሱን ለመከላከል | እጅ መታጠብ | ሰላም አለመባበል | ባልታጠበ እጆህ አይን እና አፊንጫን መነካካት። እኚን በከተገበርን ቫይረሱን መከላከል እንችላለን።

@Yenetube @Fikerassefa
ማር፣ፌጦ፣ጤና አዳም፣ነጭ ሽንኩርት አንድ ላይ ፈጭታቹ አንድ ማንኪያ ዋጡ የሚል መልክት ሰዉን እያሸበረ ይገኛል።

መልክቱ ከአባቶች የተላከ ነው የሚሉት ነገር አለ። ነገር ግን የተኛቹ አባቶች እንደተላከ ግልፅ የወጣ ነገር የለም።

የተባለውን መተግበር ክፋት የለው
ለምን ? ከተባለ የተጠቀሱት ለሰውነታችን ገንቢ እንጂ ጎጂ አይደለም ነገር ግን እኚ መዳኒት ናቸው የተባሉት ንጥረ ነገሮች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

#አትሸወዱ #አትሸበሩ

ዛሬ የሀይማኖት አባቶች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በጥሞና ጤና ሚኒስትር የሚለውን ተከታተሉ ማለታቸው ይታወሳል ስለዚህም አባቶቻችን ያሉትን ጤና ሚንስትርን እንከታተል።

ሆኖም ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል #እጅን_መታጠብ አንደኛው እና #ዋነኛው_መንገድ ነው።


#እጃችሁን_ታጠቡ
#እጃችሁን_ታጠቡ
#እጃችሁን_ታጠቡ
@Yenetube @Fikerassefa
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ምክንያት የእጩ ተመራቂዎች ምርቃት አራዝሟል!!

@Yenetube @Fikerassefa
መአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ለኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ይሄንን ፈጭተችሁ በጥብጣችሁ ቀላቅላች ጠጡ ብለዋል የሚለው እንኳን ከገዳም ከገዳም ሰፈር አይወጣም ብሏል መዐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት።

@Yenetube @FikerAssefa
ኮሮናቫይረስ ንምክልኻሉ፥

#Share #Share
@Yenetube
ሚሽን ብራይት ኢትዮጵያ የሚመሰገን ተግባር ❗️
በመገናኛ አከባቢ የሚሽን ብራይት ኢትዮጵያን በጎ ፍቃደኞች እጅ በማሳታጠብ ላይ ናቸው።

እናመሰግናለን!!
@Yenetube @Fikerassefa
የተለያዩ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ትላንት የላከውን መግለጫ ያልተገበሩ ዩንቨርስቲዎች እንዳሉ መልክት እየደረሰን ይገኛል።

ዩንቨርስቲዎች የፊት ለፊት ትምህርት እንዲቀር ሳይንስና ከፈተኛ ትምህርት ሚኒስትር ስላሳሰበ እንድትተገብሩት እንመክራለን።

ይህ ለተማሪዉ ደንነት አስፈላጊ ነው!!
@Yenetube @Fikerassefa
በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል!

በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200 ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት እንደሚችል ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

Via Mayor Office of Addis Ababa
@Yenetube @Fikerassefa
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልክት አስተላልፏል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ኮሮና ካለበት ርቆ ለመገኘት ይህን ተግብሩ

1. አጭር ርቀት ጉዞዎችን በእግር መጏዝ

2. የተጨናነቁ ሰአታትን አሳልፎ መንቀሳቀስ

3. ማንኛውንም ስብሰባ ለጊዜው ብናቆም

4. ከሊፍት ይልቅ ደረጃን መጠቀም

5. የበር እጀታዎችንና የደረጃ ድጋፎችን በባዶ እጅ አለመተሻሸት

#ሼር_Share_
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮናን ለማሸነፍ-

1. የእጅና የእጅ ስልክ ንፅህናን መጠበቅ

2. ከሌሎች ጋር ካለን ቀጥተኛ ንክኪና የትንፋሽ ቅርርብ መቆጠብ

3. ለመከላከል ስለሚጠቅም ገለል ራቅ ብሎ መቆየት

4. ፍራቻን አለመንዛት: ከስግብግብነት መታቀብ

5. ለሌሎች ምሳሌ መሆን: በርቱ

@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አለመኖሩ ተገለፀ።

እንዲሁም አምስቱ ታማሚዎች ጥሩ ጤና ላይ እንደሚገኙ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው ከተባሉት 113 ግለሰቦች መካከል 74ቱ ነፃ መሆናቸውን ታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa